የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
ሰላም! እንዴት ከርማችኋል!
ምንም አይነት እውቀት፣ ክህሎት፣ የስራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም እንኳን የመንግስት ሰራተኞች መሆን የማይችሉ ሰዎች እንዳሉ ያውቃሉ?
እንግዲያውስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም በአንቀጽ 14 የመንግሥት ሠራተኛ ሆነው ሊቀጠሩ ስለማይችሉ ሰዎች የደነገገውን ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፤
ሀ) ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ሰው፤
ለ) ቅጣቱ ከተፈጸመ፣ በይርጋ ከታገደ ወይም በይቅርታ ከተሠረዘ በኋላ 5 ዓመት ያለፈው ካልሆነ በስተቀር የሙስና፣ የእምነት ማጉደል፣ የስርቆት፣ የማጭበርበር ወይም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈረደበት ማንኛውም ሰው፤
ሐ) የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ የሌለው ሰው፤
መ) በሕግ በተደነገገው መሠረት ቃለ-መሀላ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው፤
ሠ( ከሥራ ከተሰናበተ ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመት ካልሞላው በስተቀር ከማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በዲስፕሊን ጉድለት ምክንያት ከሥራ የተሰናበተ ሰው፤
የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ሊቀጠር አይችልም።
በመሆኑም ማንኛውም ሰው በመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ ለማገልገል ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ፥
ሀ) ከኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ምርመራ በስተቀር የጤንነት ማረጋገጫ የሕክምና ምርመራ እና
ለ) ከሙስና፣ ከእምነት ማጉደል፣ ከስርቆት፣ ከማጭበርበር ወይም ከአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከፖሊስ የተሰጠ ማስረጃ
የማቅረብ ግዴታ አለበት።

ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም
ፋሲካ አጌና (የህ/ስ/ም/መ/ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቃቤ-ሕግ)
👍1
በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ጽንሰ ሀሳብ እና ገዢ ህጎቹ
ለሰዉ ልጆች በህግ እዉቅና ካገኙ ሰብአዊ መብቶች አንዱ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት ነዉ።ይህም መብት በተለያዩ ምክንያቶች ሊገደብ ይችላል። አንዱ ምክንያት ሊሆን የሚችለዉም የሌላን ሀገር ሉአላዊነት ከመጠበቅ አንጻር ነዉ። አንድ ሀገር ምንም ነገር ወደ ሀገሯ እንዲገባም ሆነ እንዳይገባ የምታወጣቸዉ ህጎች ይኖራሉ። አንዱም ህግ ሊሆን የሚችለዉ አንድ ሰዉ ወደ ሀገሯ ለመግባት በቅድሚያ ሊያሙዋላ የሚገባዉ ቀድመ ሁኔታ ነዉ። ይህንም ቅድመ ሁኔታ ሳያሙዋላ ወደዛ ሀገር የገባ እንደሆነ ህገወጥ እንቅስቃሴ እንዳደረገ ይወሰዳል። በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ዓ.ም አንቀጽ 8 ላይ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ሲተነተን “ማንኛዉም ሰዉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገንዘብ ወይም ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት በማሰብ ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዲገባ፣ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጣ፣ በኢትዮጵያ ግዛት እንዲተላለፍ ያደረገ ወይም ሰዉን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት ዝግጅት ያደረገ፣በሂደት ላይ የተገኘ፣ ያገዘ ወይም የተቀበለ” በማለት ያስቀምጠዋል፡፡ ስለዚህ ይህን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሌላ ሰዉ እንዲፈጽመው እነዚህ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች የፈጸመም ማንኛዉም ሰዉ በወንጀል ሀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል።
በሌላ በኩል ደግሞ ይሀዉ ተመሳሳይ አዋጅ አንቀጽ 3 ላይ በሰው የመነገድ ወንጀልን ሲያብራራ ``ማንኛዉም ሰዉ ሌላዉን ሰዉ በባርነት ወይም በባርነት መሰል ተግባር ፣በአገልጋይነት ወይም እዳ መያዣነት የያዘዉ ፣አካሉን በማዉጣት ወይም በዝሙት አዳሪነት ወይም መሰል የወሲብ ተግባር ብዝበዛ የፈጸመበት፣በግዳጅ ስራ ወይም አገልግሎት፣በልመና፣ በወንጀል ተግባር ፣በግዳጅ ጋብቻ፣ ወይም በማህጸን ኪራይ ያሰማራ ወይም ህጻናትን በጉልበት ስራ የበዘበዘ ወይም እነዚህን መሰል የብዝበዛ ተግባራት የፈጸመ “ ሲል ያስቀምጣል። ከነዚህ ትርጓሜዎች የምንረዳዉ በሰዉ የመነገድ ወንጀል ተጎጂዉን በቀጥታ በመጠቀም የሚፈጸም ወንጀል ሲሆን ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ደግሞ ተጎጂዉን በማጓጓዝ ድንበር በማሻገር የሚፈጸም ወንጀል ነዉ። በሌላም በኩል በሰዉ መነገድ ወንጀል በአብዛኛው ከተጎጂዉ ፍቃድ ውጪ በሆነ መንገድ የሚፈጸም ወንጀል ሲሆን ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል የተጎጂዉ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህም ወንጀሎች ሲፈጸሙ በተለያየ መንገድ እገዛ ያደረገ ማንኛዉም ሰዉ የራሱ የሆን ቅጣት እንደሚጠብቀዉ ከዚሁ አዋጅ መረዳት ይቻላል።
በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል የሚገዛበትን ህጎች ስንመለከትም
1. በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ዓ.ም
2. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ የወጣዉ የወንጀል ህግ አዋጅ ቁጥር 414/2016 ዓ.ም ከአንቀጽ 596-አንቀጽ 598 ያሉት
3. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ያሳለፈዉ ዉሳኔ ቁጥር 55/25 በአገራችን አዋጅ ቁጥሮች 736/2004 እና 737/2004 እንደጸደቀዉ የመሳሰሉት ያሉ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩልም እነዚህን ህጎች በስራ ላይ ለማዋል ያወጣቸዉ ደንብና መመሪያዎች አሉ።
1. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰዎች መነገድ እና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ተጎጂዎች የቅብብሎሽ ሥርዓት መመሪያ፣
2. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል እና መቆጣጠር የትብብር ጥምረትአባላት፡የስራ ቡድኖችን አደረጃጀት እና አሰራር ለመወሰን የወጣ መመሪያ
3. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰዎች የመነገድ እና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን መከላከል እና መቆጣጠር ምክር ቤት እና የትብብር ጥምረት ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 126 /2014 ናቸው።
በዚህም መሰረት በቦሌ ክፍለ ከተማ በክፍለ ከተማዉና በስሩ ባሉ ወረዳዎች የጥምር ቡድኑ ተመስርቶ ወደ ሰራ የገባበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። የጥምር ቡድኑም ፦
1. የግንዛቤ ፈጠራ፤የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት የስራ ቡድን
2. የተጎጂዎች መልሶ ማቋቋም የስራ ቡድን
3. የወንጀል መከላከል እና የህግ ማስከበር የስራ ቡድን
4. አለም አቀፍ እና ውጪ ግንኙነት ጉዳይ የስራ ቡድን
5. በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል መረጃና አስተዳደር የሥራ ቡድን
6. የጥናትና ምርምር የስራ ቡድን፣
7. እንዲሁም ወደፊት እንደየሁኔታዉ ሊጨመሩ የሚችሉ ቡድኖች ታሳቢ ተደርጎ በመመሪያዉ ተካቱዋል።
በቦ/ክ/ከ/አ/ፍ/ጽ/ቤት/የሕ/ስር/ምክ/መ/ዳይሬክቶት
ዐ/ህግ ዉብአለም መስፍን
ታህሳስ ወር,2015 ዓ.ም
Administrative procedure proclamation(1).pdf
1.2 MB
እንዴት ዋላችሁ
የአስተዳደር ተቋማት በሰዎች መብቶችና ጥቅሞች ላይ የሚያስከትሉትን ጣልቃ ገብነት በሕግ የሚመራና ለሕግ
የሚገዛ መሆኑን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤
የአስተዳደር ተቋማት የውሳኔ አሰጣጥና የመመሪያ አወጣጥ መርሆዎችና ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም በአስተዳደራዊ
ውሳኔዎችና መመሪያዎች ቅር የተሰኘ ሰዉ የውሳኔዎቹንና የመመሪያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት
ሥርዓት በመደንገግ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን አስፈላጊ
በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግስት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፹፫/፪ሺ፲፪(1183/2012)
የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓትን
ለመደንገግ ወጥቷል::
የቦ/ክ/ከ/የህ/ስ/ህ/ም/ዳ ዐ/ህግ ውብአለም መስፍን
የፍትህሐብሔር ስነ-ስርዓት ሕግ
በአገራችን የሰዎችን መብትና ግዴታዎች ዘርዝረዉ የሚያቀርቡ እና ሌላዉ ደግሞ መብቶችና ግዴታዎች እንዴት ወደ ስራ እንደሚገቡ ስነ-ስርዓቱን የሚደነግጉ ሕጎች አሉ። እንደ የፍትሐብሔር ሕግ(በዉስጡ የዉርስ፣የንብረት፣የዉል፣የዉክልና የምሳስሉትን ሕጎች የያዘ ነዉ)፣የቤተሰብ ሕግ፣የወንጀል ህግ ያሉት  የሰዎችን መብትና ግዴታዎች ዘርዝረዉ የሚያስቀምጡ ሲሆኑ እንደ የፍትህሐብሔር ስነ-ስርዓት ሕግ፣ የወንጀል ስነ-ስርዓት ሕግ እና የመሳሰሉት ደግሞ የስነስርዓት ህጎች ናቸዉ። እነዚህ የስነ-ስርዓት ህጎች አንድ ሰዉ በህጉ ያገኛቸዉን መብትና ጥቅሞች ማስከበር ሲፈልግ የሚከተላቸዉን መንገዶች ዘርዝሮ የሚያስቀምጥ ነዉ። 
ከስነ-ስርዓት ህጎች አንዱ የሆነዉም የፍትህሐብሔር ስነ-ስርዓት ሕግ ሲሆን በዉስጡም የፍትሐብሔር ክርክር ማንሳት የሚፈልግ ሰዉ (ተፈጥሮአዊ ሆነ በህግ ሰዉነት የተሰጠዉ)  ከክስ አመሰራረት አንስቶ ፍርድ ቤት ዉስጥ የሚካሄዱ ሰነስርዓቶችን፣ የፍርድ ቤት ስልጣን፣ የይግባኝ አቀራረብ፣ እግድ አሰጣጥ፣ የተከራካሪ ወገኖች መብት ማለፊያ መንገዶች እያሉ የሚቀጥሉ አካሄዶችን እንዴት መከተል እንዳለበት የሚያሳይ ህጋችን ነዉ። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዳኞች የፍትሐብሔር ክርክሮችን እንዴት መምራት እንዳልባቸው እና ትእዛዝ፣ብይን እና ፍርድ ምን አይነት ስርአት ተከትለዉ እንዴት መስጠት እንዳለባቸዉ የሚያሳዩ አንቀጻት የያዘ ነዉ። 
በመሆኑም ክርክር ማቅረብ የሚፈልግ ሰዉ በመጀመሪያ ማስረጃዎቹን ካሰባሰበ በኋላ በፍትህሐብሔር ስነ-ስርዓት ሕግ (የፍ/ስ/ስ/ህ/) አንቀጽ 222 እና 223 መሰረት ክሱን አዘጋጅቶ ለፍርድ ቤት በማቅረብ ቀጠሮ በማስያዝ ለተከሳሽ መጥሪያ በአግባቡ ማድረስ ይጠበቅበታል። በአግባቡ መጥሪያ ደርሶት ችሎት ቀርቦ ክርክሩን ያላሰማም ተከሳሽ ጉዳዩ በሌለበት እንዲቀጠል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ይሰጣል። ተከሳሹ መጥሪያ ደርሶት ከቀረበም በጽሁፍ መልሱን እንዲያቀርብ ይደረጋል ነገር ግን ማስገደድ አይቻልም። ቀጣዩ ሂደትም የሚሆነዉ ክስ መስማት ነዉ። ክስ ለመስማት በተቀጠረበትም ቀን ተከሳሽ ካልቀረበ ክርክሩ በሌለበት እንዲሰማ የሚደረግ ሲሆን ከሳሽ ካልቀረበ ደግሞ መዝገቡ ይዘጋል። ከሳሽ ባይቀርብም እንኳን ተከሳሽ ከቀረበበት ክስ ያመነዉ ካለ ፍርድ ቤቱ በታመነዉ ልክ ዉሳኔ መስጠት እንዳለበት የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 73 ይደነግጋል። ግራቀኝ ቀርበዉ ክርክራቸዉን ካሰሙ ግን ፍርድ ቤቱ ለጉዳዩ አግባብነት ያለዉን ጭብጥ መስርቶ እነዚህን ጭብጦች ሊያስረዱ የሚችሉ ማስረጃዎች የሰነድም ይሁን የሰዉ እንዲቀርቡ ያደርጋል። በመጨረሻም አግባብነት ያለዉ ዉሳኔ ወይም ብይን ይሰጣል። 
የችሎቱ አመራር በአጭሩ ከላይ የተቀመጠዉ ሲሆን ስለ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የተወሰነ ልበላችሁ። የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ፍርድ ቤቱ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር መግባት ሳያስፈልገዉ መዝገቡን መዝጋት የሚያስችለው የስነስርዓት ሂደት ነዉ። ይህም መቃወሚያ በራሱ በፍርድ ቤቱ ተነሳሽነት ወይም በተከሳሽ በኩል ሊነሳ ይችላል።  የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244 ላይም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሆነው ሊቅርቡ የሚችሉትን ዘርዝሮ አስቀጧምል። እነዚህ መቃወሚያዎች ፍርድ ቤትም ሆነ ተከራካሪ ወገኖች ግዜያቸዉንም ሆነ ጉልበታቸዉን ያላግባብ ሳያባክኑ ጉዳዩ በአጭሩ የሚያልቅበትን መንገድ የሚፈጥሩ በመሆናቸዉ ጥቅማቸዉ ቀላል የሚባል አይደለም። በመቃወሚያነት ሊቀርቡ ከሚችሉ ነጥቦች መካከልም ይርጋ፣ከዚህ በፊት በሌላ መዝገብ ክርክር ተደርጎበት ዉሳኔ ያረፈበት ከሆነ ወይም በሌላ መዝገብ በመታየት ላይ ከሆነ፣ በእርቅ ያለቀ ጉዳይ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ከሌለዉ የመሳሰሉት ናቸዉ።
የፍትህሐብሔር ስነ-ስርዓት ሕግ እንዲህ በአጭር ጽሁፍ ቀርቶ በመድብል እንኳን ቢጽፉት ሁሌም አዲስ ጉዳይ የማይጠፋዉ ሰፊ እና ሳቢ የሆነ ክፍል በመሆኑ ከብዙ በትንሹ አልኳችሁ።
የቦሌ/ክ/ከ/ህ/ስ/የህ/ም ዳይሬክቶሬት
ዐ/ህግ ዉብአለም መስፍን 
👍1