በቀን 21/06/2015 እና 22/06/2015 ዓ.ም ስለ አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ስለሚያወሳው አዋጅ ቁጥር 1183/2012 እና ስለ በሰዎች መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ጽንሰ ሀሳብ እና ገዢ ህጎቹ ዙርያ ለቦሌ ክ/ከተማ የምክር ቤት አባላት የተሰጠ ስልጠና የሚያሳይ ምስል። በነበረው ስልጠናም ብዙ ሀሳቦች ከተሰብሳቢው ተነስቷል። በተለይ ስለ አስተዳደራዊ ውሳኔ አሠጣጥ ላይ በተሰጠው ስልጠና መሠረት ብዛት ያላቸው ሀሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን በዚህ ዙሪያም ከምክር ቤት አባላቱ ምን እንደሚጠበቅ አትኩሮት በመሥጠት ምላሽ ከአሰልጣኝ ተሠጥቷል።
145.2015 የመኖሪያ ቤት-.pdf
793.9 KB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀው የቤት ኪራይ ክፍያ ላይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ሲል ለ 90 ቀናት ማራዘሙ ይታወቃል። ይህንም መሠረት በማድረግ ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 145/2015 ከየካቲት 19/2015 ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ያጸደቀውን ለግንዛቤ እንዲውል እነሆ ብለናል። መልካም ቀን።
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
የፌደራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_የሰበር_ሥነ_ሥርዓት_መመሪያ_ቁጥር_17_2015.pdf
ከሚያዝያ 19 ቀን 2015 ኣ.ም ጀምሮ በስራ ላይ የዋለ!
የዋስትና መብት
የዋስትና መብት ማለት በወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ የሚያዝ ሰዉ ከእስር የሚፈታበት ስነ-ስርዓት ነዉ። ማንም ሰዉ ከህጉ ዉጪ መታሰር የለበትም የሚለዉን የህገ መንግስቱ ድንጋጌ የሚረዳ መብት ነዉ። ዋስትናም ፍርድ ቤት ከመቅረብ በፊት ወይም በኋላ ለሰጥ ይችላል። በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ አንቀጽ 28 መሰረት ጽኑ እስራት የማያስቀጣ ወንጀል፣ወንጀል ስለመፈጸሙ ጥርጣሬ ካለ እና ተጠርጣሪዉ ወንጀሉን እንደፈጸመ አጥራጣሪ ከሆነ ፍርድ ቤት መቅረብ ሳያስፈልግ ፖሊስ በዋስትና መልቀቅ እንደሚችል ይደነግጋለ። በዚሁ ህግ አንቀጽ 63 ስር ደግሞ ፍርድ ቤት ሞት ቅጣት ወይም 15 አመት እና ከዛ በላይ ጽኑ እስራት የማያስቅጣ ወንጀል ከሆነ እና ተጎጂዉ ካልሞተ ዋስትና አስፈርሞ መልቀቅ እንደሚችል ያስቀምልጣ።
ዋስትና የሚከለከልባቸዉ ሁኔታዎች
በወ/መ/ስ/ስ/ህግ መሰረት ተጠርጣሪዉ
-ግዴታዉን እንደማይወጣ ከታወቀ
- ቢለቀቅ ሌላ ወንጀል ይፈጽማል ተብሎ ሲገመት
-ማስረጃ ያጣፋል ወይም ያሸሻል ተብሎ ከታመነ
- በዚህ ህግ አንቀጽ 63 እና 28 ላይ የተገለጸዉ በተቃራኒ ተሙዋለቶ ከተገኘ
ከልዩ ህጎች ለምሳሌ የጸረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007 መሰረት
-ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ ወንጀል ከሆነ
-ከ4 አመት በላይ እና ክ10 አመት በታች የሚያስቀጡ ወንጀሎች በተደራራቢነት ተፈጽመዉ ድምራቸዉ ክ10 አመት በላይ ካስቀጣ ዋስትና አይፈቀድም።
ከዚህም በተጨማሪ በሌሎች ልዩ ህጎች በተቀመጡ ምክንያቶች ዋስትና ሊከለከል ይችላል።
ስለ ዋስትና ህግ የሚደነግጉ ህጎች
1. ህገ-መንግስት (አንቀጽ 19)
2. የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ (አንቀጽ 28፣ ከ 63-79)
3. የጸረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007
4. የሰበር ዉሳኔዎች ለምሳሌ ያህል ቅጽ 19 መ/ቁጥር 112725
እና የመሳሰሉት ናቸዉ።
የዋስትና መብት በምን ሊቁዋረጥ ይችላል?
1. ክስ ሲቁዋረጥ
2. በመደበኛ ክርክር ዋስትና ሲያዝ የጊዜ ቀጠሮ
3. ከወንጀል ነጻ መባል
4. ጥፋተኝንት ዉሳኔ ተሰጥቶ ተከሳሹ ቅጣቱን እየፈጸመ ፍ/ቤቱ ዋስትና ይመለስ ሲል
5. የዋስትና ይዉረድልኝ ተብሎ ዋሱ ተከሳሹን በችሎት ሲያቀርብ
6. ዋሱ ሲሞት
7. የዋስትና ግዴታ ሳይፈጸም ሲቀር
8. በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 74 መሰረት አዲስ ማስረጃ /ጉዳይ/ሲገኝ እና የመሳሰሉት ናቸዉ።
የዋስትና መያዣ መጠን በምን ይወሰናል?
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 69 መሰረት
1. የወንጀሉ ክብደት
2. ተጠርጣሪዉ መለቀቁ ለህዝብ አስጊ ከሆነ
3. ተጠርጣሪዉ በተፈለገ ጊዜ የማይቀርብ መሆኑ
4. የተከሳሹ እና የዋሶቹ ሀብት ከግምት ይገባሉ።
የዋሶች ግዴታ
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 70፦ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ተከሳሹ ፍ/ቤት እንዲቀርብ ማድረግ።
ለዋስትና መያዣነት ምን ሊጠየቅ ይችላል?
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 69 ስር የተጠቀሰዉ ከግምት ገብቶ
1.ጥሬ ብር
2. የማይንቀሳቀሱ ወይም ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች
3. የስራ ዋስ።
የአካሌ ነጻ ይዉጣልኝ ክስ የት ይቀርባል?
ፖሊስ ማንኛዉንም ተጠርጣሪ 48 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በአቅራቢያዉ ወዳለ ፍ/ቤት ማቅረብ እንዳለበት ህጉ ያስቀምጣል። ይህንም ሳያረግ ከቀረ ተጠርጣሪዉ ሆነ ሌላ ሰዉ ወክሎት አካሌ ነጻ ይዉጣልኝ ማቅረብ እንደሚችሉ የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ አንቀጽ 177 ጀምሮ ያለዉ ይደነግጋል። ይህን መሰሉንም ክስ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መቅረብ እንዳለበት የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በአንቀጽ 11(3) ላይ ያስቀምጣል።
የቦሌ/ክ/ከ/የህ/ስ/ህ/ማ/ዳይሬክቶሬት
ዐ/ህግ ዉብአለም መስፍን

❤1👍1
የቦሌ ክ/ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ በመfeጠር በሊዝ ህጎች ላይ ሰልጠና እንድንሰጥለት ለክፍላችን ባቀረበዉ ጥያቄ መሰረት በዛሬዉ ቀን ለሰላም ሰራዊቱ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናዉም ከአገሪቷና ከከተማ የመሬት ፖሊሲ በመነሳት ስለሊዝ ጽንሰ ሀሳብ በሰፊዉ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡ የስልጠናዉም ዋነ አላማ የሰላም ሰራዊቱ ስለ ሊዝ ጠቅላላ እዉቅና ኖሮት ከዛም በመቀጠል ከህገ ወጥ የመሬት ወረራ ጋር በተገናኘ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ምን አይነት ቅጣቶች እንዳሉት አዉቆ እራሱም ከእንደዚህ አይነት ወንጀሎች እንዲቆጠብ በተጨማሪም ሌሎች ሲፈጽሙ ባለዉ ስልጣን ሁሉ ህጉን እንዲያስፈጽም ነዉ፡፡
👏1
የቦሌ ክፍለ ከተማ የህግ ስርፀት እና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ከክ/ከተማው የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ዙሪያ በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል እና መቆጣጠር የትብብር ጥምረት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ዐ/ህግ ከሆኑ አቶ ነብዩ ጋር በመሆን 700 ለሚሆኑ ተጎጂ የህብረተሠብ ክፍሎች ስልጠና ተሰጥቷል።
Forwarded from Ethiopia Check
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopiaCheck Video Explainer
የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተብሎ በወጣው አዋጅ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን አጭር ቪድዮ እንመልከት።
@EthiopiaCheck
የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተብሎ በወጣው አዋጅ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን አጭር ቪድዮ እንመልከት።
@EthiopiaCheck