የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል፣ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 መሠረት በወንጀል ሕግ የተካተቱ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ በዚህ አዋጅ መሠረት የተደነገጉ የመብት እገዳዎችን፣እርምጃዎችን፣የተሰጠ መመሪያ ወይም ትእዛዝን የጣሰ ማንኛውም ሰው እስከ ሶስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺህ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።

ሰናይ ምሽት!