Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (Wubalem Mesfin)
የቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በየአመቱ ታህሳስ 5 የሚከበረውን አለም አቀፍ የስደተኞች ቀን በማስመልከት ከየካ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር መገናኛ በሚገኘው ዲያስፖራ አደባባይ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር በድምቀት አከበረ!
በመርሃ-ግብሩም ላይ በአዲስ አበባ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በሰዉ መነገድ እና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤተ ሃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳን ጨምሮ የክ/ከተሞቹ የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዐቃብያነ-ህግ ተገኝተውበታል። ፕሮግግራሙን የቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ አቶ ሙሉቀን አዲሱ በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት ሲሆን በመቀጠልም የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ በወንጀሉ አስከፊነት ዙሪያ መልክታቸዉን አስተላልፈዋል።
በግንዛቤ ፈጠራዉ ላይ ካስማ እና ብሩህ የተባሉ የበጎ አድራጊ ድርጅቶች ተሳታፊ የሆኑበት ሲሆን የነዚህ ድርጅቶች አባል የሆኑ የስደት ተመላሾች በግንዛቤ ፈጠራዉ ላይ የራሳቸዉን የስደት ልምድ ለህብረተሰቡ አካፍለዋል። በዚህም ስደት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ከተቻለ በአገር ሰርቶ ለመለወጥ ካልሆነም ስደት ምርጫዉ የሆነ ሰዉ ህጋዊ መንገድ እንዲጠቀም አመክረዉ መልክታቸዉን አስተላልፈዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የወንጀሉን አስከፊነት እና በሰው የመነገድ ሆነ በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ማለት ምን ማለት እንደሆነ ወንጀሉንም ፈጽሞ የተገኘ የሚጠብቀዉን የእስርም ሆነ የገንዘብ ቅጣት ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል እንዲሁም ወንጀሉም ሲፈጸም ያየ ወይም የሰማ በነጻ የስልክ መስመር 6370 ላይ ጥቆማ መስጥ እንደሚችል የሚያስረዳ መልእክት ለህብረተሰቡ በበራሪ ጽሁፍና በድምጽ ማስተላልፍ ተችሏል።