የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል፣ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 መሠረት በወንጀል ሕግ የተካተቱ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ በዚህ አዋጅ መሠረት የተደነገጉ የመብት እገዳዎችን፣እርምጃዎችን፣የተሰጠ መመሪያ ወይም ትእዛዝን የጣሰ ማንኛውም ሰው እስከ ሶስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺህ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።

ሰናይ ምሽት!
በዛሬው ዕለት(በ21/08/2012 ዓ.ም) በቦሌ ክ/ከተማ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በየሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ስር ባሉ ሁለት ዐቃቤ ሕጎች(ህድአት ጌታቸው እና ኦምኒኤል ከበደ) በአስተዳደሩ መግቢያ በር ጋር በሞንታርቦ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈፀሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ዙሪያ በተደረገው ግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ ደንቡ ላይ የተካተቱ ትርጓሜዎችን፣የተከለከሉ ተግባራትን እና የተጣሉብን ግዴታዎች ምን ምን እንደሆኑ ሙያዊ ትንተና የተሰጠ ሲሆን ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ ስለ ኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች፣ስለ ተከለከሉ ተግባራት፣ስለ ተጣሉብን ግዴታዎች እንዲሁም በአዋጁ መሠረት የተካተቱትን የተከለከሉ ተግባራትንም ሆነ የተጣሉብንን ግዴታዎች መጣስ የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያመጣ ግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ ቢሆንም ሁላችንም መጠንቀቅ ያለብንን ያህል እየተጠነቀቅን አይደለም።በተለይም ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች ሁለት የአዋቂ እርምጃ መራራቅ እንዳለብን እየዘነጋን ይመስላል
በተቻለን መጠን ጥንቃቄ አይለየን!