Forwarded from ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️ (Daniel Fikadu)
ከስምና ከክብር ላይ የሚፈጸም ጥፋት ከኢትዮጲያ ህግ አንጻር ሲፈተሽ
***
ይህ ድርጊት በፍትሐብሔርም በወንጀል ሕግም ጥፋት ነው የወንጀል ሕግ ቁጥር 613ን ተመልከቱ እነዚህ ቁጥሮች በኘሬስና ሀሳብን በነፃ የመግለፅ ሕገ መንግስታዊ መብት ላይ የተደረጉ ገደቦች ናቸው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የኢፊዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 39 /3/ ስር የኘሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነፃነት መረጋገጡን ደንግጉ አንቀፅ 29/6/ ስር የሰውን ክብርና መለካም ስም ለመጠበቅ ሲባል ሕጋዊ ገደቦች በእነዚህ መብቶች ላይ ሊደነገጉ ይችላሉ ይላል፡፡ ስለሆነም በዚህ ገደብ አማካኝነት ጥበቃ የተደረገላቸው መልካም ስምና ክብር ናቸው፡፡
ይህን ያህል ለመግቢያ ካልን አንዳንድ ነጥቦችን አንስተን እንወያይ የስም ማጥፋት ድርጊት የሚፈፀምበት ሰው በሕይወት ያለ መሆን አለበት ይህም የሰም ማጥፋት የሚደረገው ስሙ የጠፋው ሰው እንዲጠላ ወይም እንዲዋረድ ወይም እንዲሳቅበትና ብሎም ስሙ በጠፋው ሰው ላይ ሌላው እምነት እንዳይኖረው ለማድረግ ወይም መልካም ዝናው ወይም የወደፊት ዕድሉ እንዲበላሽ ለማድረግ ነው፡፡ ይህን ያደረገ ጥፋተኛ ነው፡፡
አንዳንድ ምሳሌዎችን እንውሰድ፡፡ አንድ ሰው በወንጀል ሕግ የሚያስቀጣ ወንጀል ሳይፈፀም ሰርቷል ወይም አንድን የሕክምና ዶክተር ችሎታ እያለው ችሎታ የለውም ማለት አንድን ነጋዴ ሳይከስር ዕዳውን ለመክፈል አይችልም ማለት ተላላፊ በሽታ ሳይኖርበት እንዳለበት አድርጐ ማውራት ለስም ማጥፋት እንደምሳሌ ልንወስዳቸው እንችላለን፡፡ እንዲሁም ነገሩ እውነት ሆኖም ሰውዬውን ለመጉዳት ብለን ካደረግነው ድርጊታችን ጥፋት ይሆናል፡፡ /የወ.ሕግ 613/
አንድ ቃል ወይም አረፍተ ነገር ስም ማጥፋት ነው እንዲባል ቃሉ ወይም ዐረፍተ ነገሩ ለሶስተኛ ሰው ሊነገር ይገባል፡፡ ለሶስተኛ ሰው ሳይሆን ለራሱ ለተበዳዩ ቀጥታ የተነገረ እንደሆነ ስም ማጥፋት ሳይሆን ስድብ /insult/ ነው የሚሆነው፡፡
ስም የማጥፋት ድርጊት በቃል ሊሆን ይችላል፡፡ በፅሁፍና እንዲሁም በሌላ ዘዴ /ለምሳሌ ሌላ የኪነ ጥበብ ውጤት / ሊሆን ይችላል፡፡ ስም ማጥፋት አለ ለማለት የግድ የመጉዳት ሃሳብ መኖር የለበትም፡፡ 2045 /1/ እንዲሁም ቁጥር 2ዐ45/2/ ስር እንደተደነገገው በብድን ስም /group defamation/ የለም፡፡ ስለሆነም አንድ ሰው ስም አጠፋ ለማለት በንግግሩ ወይም በፅሁፍ የማንንም ሰው በተለይ ካልገለፀ በቀር ስም እንዳጠፋ አይቆጠርም፡፡ ሆኖም ግን ይህ አድራጉቱ ሌላ ሰው እንዲጉዳ አስቀድሞ ለመረዳት መቻሎ ከተረጋገጠ አላፊ ሊሆን እንደሚችል ቁጥር 2ዐ41/3/ ይደነግጋል፡፡
ቀጥለን መከላከያዎችን እንመለከታለን፡፡ የመጀመሪያው መከላከያ ቁጥር 2ዐ46 ስር የተደነገገው የሕዝብን ጥቅም በሚነኩ ጉዳዩች ላይ አሳብን መግለፅ ነው፡፡ ይህ የተገለፀው ሃሳብ ሌላውን ሰው በሕዝብ ዘንድ የሚያስወቅስ እንኳን ቢሆን እንደስም ማጥፋት አይቆጠርም ሆኖም ስም አጠፋ የተባለው ሰው ጠፋ የተባለው ሰው ላይ የሰጠው አስተያየት ሃሰት መሆኑን በእርግጠኝነት ካወቀ ጥፋተኛ ይሆናል፡፡
ሁለተኛው መከላከያ ደግሞ የተነገረው ነገር እውነት መሆኑ ነው፡፡ ይህንንም በማስረጃ ማረጋገጥ አለበት ሆኖም ግን የተባለው ነገር እውነት ቢሆንም ስሙ ጠፋ የተባለውን ሰው ሆን ብሎ ለመጉዳት ቃሉን ወይም ዓረፍተ ነገሩን የተናገረው ተከሣሽ ጥፋተኛ ይሆናል፡፡ /በቁጥር 2ዐ47/
ሶስተኛ መከላከያ ደግሞ የማይደፈር መብት በእንግሊዝኛው /immunity/ የሚባለው ነው፡፡ ይህ መብት ለተወሰኑ ሰዎች የተሰጠ ነው ለፖርላማ አባላትና በፍርድ ቤት ፊት ለሚከራከሩ ወገኖች፡፡ አንድ የፖርላማ አባል በፖርላማ ውስጥ በሚደረግ ውይይት ሀሳቡን ሲገልፅ ግለሰብን አንስቶ ሊናገር ይችላል፡፡ ይህ ግን የፖርላማ አባሉን በስም ማጥፋት ተጠያቂ ሊያደርግው አይችልም፡፡
በፍርድ ሂደት ክርክርም የሰዎች ስም ሊነሳ ይችላል ለፍትህ አሰጣጥ የግድ ከሆነ ግለሰብ ሊነሳ ይችላል፡፡ ይህን ያነሳ ተከራካሪ በስም ማጥፋት ጥፋተኛ አይባልም፡፡
በተጨማሪም ቁጥር 2ዐ45/2/ ስር እንደተደነገገው በምክር ቤት ወይም በፍርድ ቤት የተደረገን ንግግርና ክርክር እንዳለ /እንደወረደ እንደሚባለው/ የገለጠ ሰውም በአላፊነት ሊጠየቅ የሚችለው ስሙ በውይይቱ ወይም በክርክሩ የተነሳውን ሰውዬ ለመጐዳት ብቻ አስቦ ከሆነ ብቻ ይሆናል፡፡
በመጨረሻም የስም ማጥፋት ተግባር በጋዜጣ ላይ ሊደረግ ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ስም አጠፋ የተባለው ሰው ፋጥተኛ የሚሆነው፣
አንድን ሰው ለመጉዳት ብሎ አስቦ ከሆነ
ይህንንም የፈፀመው በከፍተኛ ቸልተኝነት ከሆነ
ወዲያውኑ መልሶ ይቅርታ ካልጠየቀ ነው፡፡
በሌላ አባባል ስም ማጥፋቱን የፈፀመ አንድን ሰው ለመጉዳት ሆን ብሎ አስቦ ሳይሆንና በቸልተኝነት ካልሆነ ይህንንም ካደረገ በኃላ ወዲያውኑ መልሶ ይቅርታ ከጠየቀ ጥፋተኛ አይሆንም፡፡ 2ዐ49/1/
ቁጥር 2ዐ49 /2/ እና /3/ የይቅርታው አጠያየቅ ጊዜ እና በምን ላይ መሆን አለበት የሚለውን ይመልሳሉ፡፡ በንዑስ ቁጥር ሁለት መሠረት ስም ማጥፋት ድርጊቱ የተደረገው ከአንድ ሳምንት በበለጠ ጊዜ በሚወጣ ጋዜጣ ላይ ከሆነ ይቅርታው የግድ የሚቀጥለው ጋዜጣ እስኪወጣ መጠበቅ የለበትም ይህ ከሆነ ተበዳዩ ይጉዳል፡፡ የጠፋውንም ስምና ጉዳቱንም ማስተካከል የማይቻልበት ደረጃ ላይ ሊደረስ ይችላል፡፡ ስለዚህ ይቅርታው ተበዳዩ በሚመርጠው ጋዜጣ ላይ መውጣት አለበት፡፡ ይህ ጋዜጣ የበዳዩም ሊሆን ይችላል፡፡ የሌላ ሰወ ጋዜጣም ሊሆን ይችላል፡፡ ተበዳዩ ጋዜጣ ካልመረጠ በንዑስ ቁጥር ሶስት መሠረት የስም ማጥፋቱ ነገርና የይቅርታው መጠየቁ የሚታተመው ስምን ማጥፋቱ በወጣበት ተከታይ ዕትም ላይ ይሆናል፡፡
#በአብዱል መሊክ አቡበከር

👍1
Forwarded from Abrham Yohanes Law Corner (Abrham Yohanes)
185837_የሰበር_አጣሪ_ችሎት_አሰያየምና_ከዳኞች_አሰያየም_አንጻር_የጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_ፕሬዝዳንት_ሥልጣን.pdf
325.4 KB
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ
የውክልና አይነቶች ከሕግ አንፃር
=================================
በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ::
1ኛ.ጠቅላላ ውከልና
ይህ ውክልና በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ነው፡፡ ጠቅላላ ውክልና ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው የውክልና አይነት ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 2204 የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት ምን ምን አይነት ስራዎች እንደ ሆኑ በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም፡-
• የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ፣ መጠበቅ
• ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት
• በብድር የተሰጠውን ሀብት መሰብሰብ
• ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ ማስቀመጥ
• ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ መስጠት
• ሰብሎችን መሸጥ
• ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሽጥ የአስተዳደር ስራዎች ናቸው፡፡
2ኛ ልዩ ውክልና
ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ውጪ ተወካይ የተለየ ተግባር እንዲፈፅምለት በመግለፅ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው፡-
• የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ
• አስይዞ መበደር
• ካፒታሎችን ኢንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በማሕበር የመግባት
• ስጦታን ማድረግ
• በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈፀም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡
የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች
የፍትሐብሔር ህጉ በቁጥር 2208 እና ተከታዮቹ መሰረት ተወካይ በርካታ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት ተወካይ ለወካይ በሚሰራበት ወቅት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እና በውክልና በተሰጠው አደራ ላይ ልክ አንድ የቤተሰብ አባት እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መከወን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም ተወካዩ በሚሰራበት ወቅት ለወካዩ ጥቅም ማሰብ እና ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን የሚጠበቅበት ሲሆን ወካዩ ሳያውቅ በወኪልነቱ ምክንያት ከሚሰራው ስራ አንዳችም ጥቅም መውሰድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ ሁሉ የስራውን አካሄድ፣ መግለጫ እና ሂሳብ በየጊዜው ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በውክልናው ምክንያት የሚያገኛቸውን መረጃዎችም የወካዩን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ መጠቀም የለበትም፡፡
በሌላ በኩል ወካዩም ግዴታዎች እንዳሉበት ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2219 እና ተከታዮቹ መረዳት ይቻላል፡፡ በዋናነትም ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ ለመክፈል ውል ገብቶ ከሆነ ወይም ተወካዩ በውክልና የፈፀመው በሙያ ውስጥ በተመለከተ የግል ሥራው ከሆነ ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ የውክልናው ሥራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈን የሚጠበቅበት ሲሆን ተወካዩ ለወካዩ ጥቅምና ለውክልና ስራው መልካም አካሄድ ሲል በወኪልነቱ ከሚገባው የውል ግዴታ ነፃ ሊያወጣው ይገባል፡፡
የውክልና ጥቅም
ውክልና ለወካይ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ የሚያስፈልገው ስራ በወኪሉ በኩል ማከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸውም እንደ ተፈጥሯዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆናቸው በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ምክንያት ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም እድሜቸው ለአካለመጠን ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ የሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስቻል ውክልና ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ የሚካተት ነው፡፡
ስለውክልና መቅረት
ውክልና ከተሰጠ በኋላ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል ማለት ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ሊሆንባቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎች በህጉ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ሁኔታዎች መካከል ውክልናን መሻር፣ የውክልና ስልጣንን መተው፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት ስልጣንን ቀሪ ከሚያረጉ ሁኔታዎች መካካል ናቸው፡፡
ውክልናን መሻር
ወካይ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን መሻር እና ለተወካይ የሰጠውን የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካለት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል አላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ትክክለኛ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በመላ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም፡፡
የወኪል የውክልና ስልጣኑን መተው
ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን ለመተው የሚችል ሲሆን የውክልና ሥራውን መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልና ስራውን መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍፁም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠለት ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡ በሌላ በኩል ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ እና ከመካከላቸው አንድኛው የውክልና ስራውን ለመቀጠል በአንድ ምክንያት ያልቻለ እንደሆነና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎቹንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃልይ ውክልና ጊዜን፣ ገንዘብን እና አቅምን በመቆጣብ በዋናነት ወካዩን የሚጠቅም በመሆኑ የታለመለትን አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ወገኖች የውክልና ስምምነት በህጉ ላይ የተቀመጡለትን መስፈርቶች እና ሁኔታዎችን ማወቅ እና ማሟላት አለባቸው፡፡
ንቃተ ሕግ
https://t.me/Ethiopialegalinfo
@Ethiopialegalinfo

Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
የፍትሐብሔር ክስ አዘገጃጀት እና በክሱ ላይ መገለጽ የሚገባቸው ነገሮች ከፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 222-225
==============================
በአንድ ክርክር የሚዘጋጀው ክስ የአንድን ሰው መብት ማስገኘትም ማሳጣትም ይችላል። የከሳሽ ሀሳብ ግልጽ ካልሆነ ለፍርድ ቤት የተጠየቀውን ዳኝነት በአግባቡ የማይገልጽ ከሆነ ማግኘት የሚገባውን መብት ያሳጣል። አንድ ክርክር ስኬታማ እንዲሆን የሚዘጋጀው ክስ ወሳኝነት አለው። በመሆኑም ከዚህ ቀጥሎ ያሉት አንድ ክስ ስዘጋጅ መያዝ የሚገባቸው ነገሮች ናቸው:-
1. #በክስ ጽሑፍ ላይ ስለሚሰፍሩ ነገሮች
⨳ማናቸውም የክስ ጽሑፍ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱን ነገሮች የያዘ መሆን አለበት፡፡
⨳ክሱ የሚቀርብለት ፍርድ ቤት የሚያስችልበትን ቦታና ስሙን፡፡
⨳የክሱን አርዕስት፡፡
⨳የከሳሹንና የተከሳሹን ሥም ልዩ መግለጫውን የሚኖርበት ⨳ቦታና መጠሪያው የሚሰጥበትን አድራሻ፡፡
⨳ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በሕግ ችሎታ የለውም የተባለ ሲሆን ይህንኑ መግለጽ፡፡
⨳ከሳሹ ክስ የሚያቀርበው በጠበቃነት በነገር ፈጅነት ወይም በወኪልነት እንደሆነ ክሱን ለማቅረብ ያለውን ሥልጣን መግለጽ፡፡
⨳ለክሱ ምከንያት የሆትን ነገሮችና እነዚሁም የተፈጠሩበት ጊዜና ስፍራ፡፡
⨳ፍርድ ቤቱ ነገሩን ለመቀበል ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ የሚያስረዳውን ሁኔታ፡፡
⨳ተከሳሹ ለክሱ ምክንያት በሆነው ነገር ውስጥ አግባብ እንዳለው ወይም ተጠሪ የሚሆንበትን ምክንያት ወይም ለሚቀረበው ክርክር በአላፊነት የሚጠየቅበትን ሁኔታ፡፡
⨳አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ነገር ግምት፡፡
⨳መንግስት የሚከስበት ወይም የሚከሰስበት ጉዳይ ሲሆን ከዚህ በላይ እንደተነገረው ዝርዝር ነገር መስጠት አስፈላጊ አይሆንም ነገር ግን የከሳሹን ወይም የተከሳሹ መስሪያ ቤትና የባለስልጣኑ ስም ብቻ መግለጽ በቂ ነው፡፡
2.#ከክስ ማመልከቻ ጋር ተያይዘው ስለሚቀርቡ ጽሑፎችና መግለጫዎች
⨳ከሳሹ ከሚያቀርበው የክስ ማመልከቻ ጋር ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ነገሮች አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
⨳ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜ ምስክር ይሆኑኛል የሚላቸውን ሰዎች የስም ዝርዝር ከነ አድራሻው፤የሚጠሩበትን ምክንያት እንዲሁም ማስረጃ ይሆኑኛል የሚላቸውን ጽሑፎች ጽሑፎቹም በእጁ የማይገኘ ሲሆኑ የሚገኙበትን ስፈራና በማን እጅ እንደሚገኙ በመግለጽ አያይዞ ካቀረበው ዝርዝር በቀር ሌላ አስረጅ ወይም ማስረጃ የሌለው መሆኑን አረጋግጦ በማስታወቅ፡፡
⨳ለክሱ መነሻ ወይም መሠረት የሆነውን ሰነድ ዋናውን ወይም ትክክል ግልባጩን፤
⨳የሚያቀርበው ምሰስክር ወይም የጽሑፍ ሰነድ የሌለው ስሆን ይህንኑ ገልጾ ማረጋገጥ፡፡
⨳በክሱ ማመልከቻ ላይ ለተጠቀሱት ተከሳሾች ሁሉ በቂ የሆነ የክስ አቤቱታ ግልባጭ ከዚህ ጋር ተያይዘው የቀረቡትን የጽሑፎችና ሌሎችም ማስረጃወች የምስክሮች ስም ዝርዝር ማናቸውም ለፍርድ ቤቱ የደረሱትን መግለጫዎች ትክክል ግልባጫቸው እንዲደርሳቸው ማድረግ፤
⨳ከዚህ በላይ ባለው ንዑስ ቁጥር የተነገረው ድንጋጌ እንደተበቀ ቢሆንም እንኳ ፍርድ ቤቱ የፈቀደ እንደሆነ ለክሱ መሰረት የሆነውን ሰነድ ትክክል ግልባጭ ለተከሳሹ እንዲደርሰው ከማድረግ ይልቅ ዋናው በፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት እንዲቀመጥና ተከሳሹ መጥቶ እንዲያየው ለማዘዝ ይችላል፡፡
3. #የሚጠየቀውን ዳኝነት በዝርዝር ስለ መግለጽ
⨳ከሳሽ በሚያቀርበው የክስ ማመልከቻ ላይ በተለየ ወይም በምትክ ወይም በተለዋዋጭ የሚጠይቀውን ዳኝነት መግለጽ አለበት ነገር ግን ከሳሹ በክሱ ላይ እንዲሰጠው የሚጠይቀው ዳኝነት ጠቅላላ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የክሱን ጭብጥና የማስረጃውን አካባቢ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ትክክለኛ መስሎ የታየውን ፍርድ ሊሰጠው ይችላል፡፡
⨳ከሳሹ ክሱን የመሰረተው በብዙ ጉዳዮች ወይም በተለያዩ ነገሮች ላይ የሆነ እንደሆነ በተለይ በየአንዳንዱ ጉዳይ እንዲታይለት የሚጠይቀውን ዳኝነት መግለጽ አለበት፡፡
4. #ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ነገር ለይቶ ስለ መግለጽ
⨳ለክርክሩ መሠረት ወይም መነሻ የሆነው ጉዳይ የተወሰነ ወይም የተለየ ነገር ስሆን በማመልከቻው ላይ ነገሩን አብራርቶ በመለየት መግለጽ አለበት፡፡
⨳ክሱ የሚመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሆነ እንደሆነ በክሱ ማመልከቻ ላይ ንብረቱን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችሉት ምልክቶች መገለጽ ይኖረባቸዋል፡፡ ይኸውም ንብረት የሚለው በአካባቢው ወሰን ወይም በርስት መመዝገቢያ ላይ በተሰጠው ተራ ቁጥር በሆነ ጊዜ የወሰኑ ምልክት ወይም በመዝገብ ላይ የተሰጠው ቁጥር መገለጽ ይገባዋል፡፡
5. #ገንዘብን ለመጠየቅ በሚቀርብ ክስ ላይ ስለሚቀርቡ ዝርዝር መግለጫዎች
⨳ክስ የሚቀርበው በገንዘብ የሆነ እንደሆነ ከሳሹ የሚጠይቀውን ገንዘብ በማመልከቻው ላይ በትክክለኛ ሁኔታ ገልጾ ማስታወቅ አለበት፡፡
⨳ከሳሹ የሚጠይቀው ገንዘብ ልኩ ሊታወቅ የሚችለው በርሱና በተከሳሹ መካከል የሂሳብ ማጣራት ተግባረ ከተፈጸመ በኋላ የሆነ እንደሆነ በሚያቀርበው የክስ ማመልከቻ ላይ ሊጠይቅ የሚገባውን ገንዘብ በግምት ለመግለጸ ይችላል፡፡
⨳ክሱ የቀረበው ተለይቶ የታወቀ ዕቃ ወይም ሌላ ነገር ለማስመለስ የሆነ እንደሆነ ለክሱ መሠርት የሆነውን ነገር ትክክለኛ ዋጋ በማመልከቻው ላይ መገለጽ አለበት፡፡
⨳የቀረበው ክስ የሚያልቅ ወይም የሚበላሽ ወይም እለታዊ አገልግሎት ያለው ነገር የሚመለከት ስሆን በማመልከቻው ላይ የዚሁኑ የዕለት ዋጋ መግለጽ ያስፈልጋል፡፡

Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (Assefa Mebrate)
አዋጅ_ቁጥር_1320_2016_የመኖሪያ_ቤት_ኪራይ_ቁጥጥር_እና_አስተዳደር_አዋጅ_docx_1.docx
52.6 KB
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016
Forwarded from Tibebu S.
የዲስፕሊን ኮሚቴ ስልጠና.pptx
96.3 KB
Forwarded from አለ ሕግ
#👉⚖️ በሀገራችን የወንጀል ሕግ ሥርዓት መሠረት ያለአግባብ ለተከሰሱ፣ ለተቀጡም ሆነ ፍርዳቸውን ለተቀበሉ ሰዎች ካሳ የሚከፈልበት ሥርዓት የለም፤ ነገር ግን ንፁሐን ለደረሰባቸው በደል መነሻ የሆኑት የግል አቤቱታ አቃራቢዎችና ሐሰተኛ ምስክሮች ሚጠየቁበት ሥርዓት አለ።
#በወንጀል ጉዳይ ክስ የቀረበበት ሰው ከቀረበበት ክስ ነፃ መሆንን በሁለት መንገድ መመልከት ይቻላል።
🚨1ኛ. ዓቃቤ ሕግ ክሱን ባለማስረዳቱ ነፃ መሆን
#👉⚖️ በመርህ ደረጃ በወንጀል ጉዳይ ከሳሽ የሚሆነው ዓቃቤ ሕግ ነው። ዓቃቤ ሕግ የሚያቀርበውን ክስ ተከሳሽ የፈጸመው ስለመሆኑ የማስረዳት ግዴታ አለበት። ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ግለሰቡ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ከጥርጣሬ በፀዳ ሁኔታ Beyound reasonabl doubt ማስረዳት ይጠበቅበታል።
#👉⚖️ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ ይህንን ግዴታውን ካልተወጣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር1️⃣4️⃣1️⃣መሠረት ግለሰቡን ተከላከል ማለት ሳያስፈልገው በነፃ ሊያሰናብተው ይችላል።
🚨2ኛ. ተከሳሽ ወንጀሉን አለመፈጸሙን በመከላከሉ ነፃ መሆን
#👉⚖️ በወንጀል የተከሰሰ ሰው ክስ የቀረበበትን ጉዳይ በበቂ ሁኔታ ከተከላከለ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር1️⃣4️⃣9️⃣መሠረት ከክሱ ነፃ ይሆናል።
🚨የወንጀል ኃላፊነት
#👉⚖️ በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 447 ላይ እንደተመለከተው ሰውን በሐሰት ወንጀል ወይም መክሰስ ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እሥራትና በመቀጮ ያስቀጣል። ነገር ግን በሐሰት የቀረበው ክስ ግለሰቡን ከዚህ በላይ የሆነ ቅጣትን አስከትሎ እንደሆነ በንፁህ ሰው ላክ በተወሰነው ቅጣት ልክ ይቀጣል።
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube
https://youtube.com/@Ale_Hig

የወራሾች ክስ ማስቀጠል ሂደትና የይርጋ ጊዜ
⚖️ክስ ያቀረበ ከሳሽ ሲሞት የወራሾች በክርክር ውስጥ መግባት
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49(1) ድንጋጌ መሰረት ክሱን ለመቀጠል መብት አለኝ የሚሉ ወገኖች ዋናው ከሳሽ ወይንም ከሳሾች በሞቱ በአንድ አመት ውስጥ ክሱን ለመቀጠል እንዲፈቀድላቸው ሳያመለክቱ የቀሩ እንደሆነ የተጀመረው ክርክር ውድቅ እንደሚሆን የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 49(2) ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል፡፡ ይህ ድንጋጌ ክሱን ለመቀጠል መብት አለኝ የሚል ወገን ክሱን ለመቀጠል እንዲፈቀድለት ማመልከቻውን የሚያቀርብበትን የጊዜ ገደብ የሚመለከት ሲሆን ከሳሽ ወይም ከሳሾች በሞቱ በአንድ አመት ውስጥ ክሱን ለመቀጠል ሳያመለክቱ መቅረታቸው ከተረጋገጠ የተጀመረው ክርክር ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ የሚደነገግ ሲሆን ከዚህ ጊዜ በኋላም ጥያቄው ሲቀርብ ተቀባይነት የሚያገኝበት አግባብ መኖሩን የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 55(2) ድንጋጌ ያሳያል፡፡
⚖️በዚህም መሰረት ከሳሹ ራሱ ወይም ከሳሽ የነበረው የሟቹ ንብረት አስተዳዳሪ ነኝ የሚል ባለአደራ ወይም የከሰረው ከሳሽ ንብረት አስተዳዳሪ የሆነ ሰው ወይም የዋናው ከሳሽ መብት ተላልፍልኛል የሚል ሰው ክሱ ቀሪ በሆነ ወይም በተሰረዘ በስድስት ወር ውስጥ የቀረበው ክስ እንዲቀጥል ወይም መሰረዙ እንዲነሳለት ለማመልከት የሚችል ስለመሆኑ የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ክሱ ቀሪ የሆነው ወይም የተሰረዘው በከሳሹ ጉድለት ያለመሆኑን የተረዳው እንደሆነ ይህ ምክንያት ስለደረሰው ኪሳራ ተገቢ መስሎ የታየውን ወስኖ የቀረው ወይም የተሰረዘው ክስ እንዲቀጥል ለማዘዝ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 55(3) ድንጋጌ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ይህ ድንጋጌ አቤቱታው ክሱ ቀሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ በሚቆጠር ስድስት ወራት ውስጥ መቅረብ እንዳለበትና በበቂ ምክንያት መደገፍ እንዳለበት የሚደነግግ ሲሆን በቂ ምክንያት የሚለውን ሐረግ ግን መመዘኛው ምን እንደሆነ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ በቂ ምክንያት አለ ወይስ የለም? የሚለው ጥያቄ አመልካቹ በተገቢው ጊዜ አስፈላጊውን ስርዓት ያልፈፀመበት ምክንያት ተገቢ የሆነ ምክንያት ስለነበረው ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን በመመልከት በፍርድ ቤቱ አዎንታዊ ምላሽ ከአገኘ በቂ ምክንያት አለ ብሎ ለመደምደም የሚችልበትን አግባብ የሚያሳይ ነው፡፡
⚖️በመሆኑም የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 49 እና 55(2) እንዲሁም 55(3) ድንጋጌዎች ሲታዩ ክርክሩን ለመቀጠል የአንድ አመት ጊዜ ከአለፈ ጥያቄው ተቀባይነት የሌለው መሆኑንና ይህ የጊዜ ገደብ በማለፍ መዝገቡ ከተዘጋ ወይም ክሱ ቀሪ ከሆነ በኋላ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ክርክሩ እንዲቀጥል ወይም ቀሪ የሆነ ክስ እንዲንቀሳቀስ በቂ ምክንያት ያለው መሆኑን አቤቱታ አቅራቢው ከገለፀ እና ፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅራቢው አስፈላጊውን ስርዓት ያልፈፀመበት ምክንያት ተገቢ በሆነ ምክንያት መሆኑን ከተረዳው ክርክሩ እንዱቀጥል ማድረግ የግድ የሚል መሆኑን የሚያስገነዝቡን ናቸው፡፡
⚖️ከዚህ አንፃር ሲታይ ከሳሽ በመሞቱ ምክንያት የተዘጋ መዝገብን ለማንቀሳቀስ ፍጹም የሆነ ይርጋ የአንድ አመት ስድስት ወራት ጊዜ ነው ቢባል እንኳ ፍርድ ቤት መዝገቡ ተዘግቶ የቆየበትን ጊዜ በማስላት ብቻ ጊዜውን መቁጠር ያለበት ሳይሆን በጊዜ ገደቡ ውስጥ ጥያቄውን ያቀረበው አቤቱታ አቅራቢ የቆየበትን ሁኔታ ሁሉ አግባብነት ካላቸው ሌሎች የመሰረታዊ ህግ ድንጋጌዎችና አንድ ሰው ከሳሽ ለመሆን መሟላት ያለባቸውን የስነ ሥርዓት ሕግ መስፈርቶች ማየትን የግድ የሚል ነው፡፡
⚖️የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 49 እና 55(3) ሥነ-ሥርዓታዊ ድንጋጌዎች እንደመሆናቸው መጠንም የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው መቼ ነው? ከሚለው ጥያቄ አንጻር ጉዳዩ መታየት ያለበት ነው፡፡ ይህንኑ ጥያቄ ለመመለስ ደግሞ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1846 እና የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 48 ድንጋጌዎችን ይዘት መመልከት ተገቢ ይሆናል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1846 ድንጋጌ መሰረት የይርጋ ጊዜ መነሻው በመብት መስራት የሚቻልበት ጊዜ ነው፡፡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 48 ድንጋጌ መሰረት ደግሞ ክርክሩ እንዲቀጥል የሚያስችለው መብት የማይቋረጥ ከሆነ የከሳሽ ወይም የተከሳሽ መሞት ክርክሩን እንዲቆም አያደርገውም በሚል ተቀምጧል፡፡ ከዚህ የስነ ስርዓት ድንጋጌ ውስጥ "ክርክሩ እንዲቀጥል የሚያስችለው መብት የማይቋረጥ ከሆነ" የሚለው ሐረግ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 826(2) እና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1986 ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ የሚታይ ነው፡፡
በዚህም መሰረት በዚህ መብት አንድ ሰው ሊሰራ ይችላል ተብሎ የሚታሰበው ተገቢውን የወራሽነት ማስረጃ ከያዘ በኋላ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 62452 ቅጽ 13፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 48፣ 49(1)፣ 55(2)፣ 55(3) ፍ/ህ/ቁ. 826(2)፣ 1846፣ 1986
Join 👇👇
https://t.me/ethiolawtips

Forwarded from ይግባኝ ምክረ ሕግ ⚖️
የግንቦት_ወር_2016_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ_1.PDF
1.8 MB
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ቀለብ አወሳሰን መመሪያ.pdf
1005.5 KB
ቀለብ አወሳሰን መመሪያ.pdf
-------------------------------
የቀለብ አወሳሰን መመሪያ መርሆች
💥የልጅ ቀለብ በዋናነት የህፃናት ጥቅምን ቀዳሚ ማድረግ አለበት።ቀለብ ሰጪዋች ወላጆች በሚሆኑበት ጊዜ አቅማቸው በፈቀደ መጠን ልጆቻቸውን የማሳደግና የመንከባከብ ሕጋዊ ሐላፊነታቸውን እንደገቢያቸው መጠን የሚጋሩት ይሆናል።
💥የልጅ ቀለብ በሚወሰንበት ሂደት ወላጆች ለመኖር የሚያስፈልጓቸውን መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ታሳቢ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም በየትኛውም ሁኔታ ግን ለልጅ ቀለብ የመስጠት ግዴታን የሚያግድ መሆን የለበትም።
💥የልጅ ቀለብ አወሳሰን የልጅን መሠረታዊ ፍላጎቶችን ልዩ ወጪዎች ታሳቢ ማድረግ ያለበት ሲሆን ከወላጆች አንዱ የተሻለ ገቢ ያለው ከሆነ ልጁ የዚህ ገቢ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል።ከዚህ በተጨማሪም ልዩ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸውን ሕፃናት ከግምት ያስገባ መሆን ይኖርበታል።

Forwarded from Legal Insight Ethiopia
ብርበራ
ብርበራ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችን ፣ በወንጀል ድርጊት ምክንያት የተገኙ ቁሳቁሶችን ፣ ምርመራ ለሚደረግበት ጉዳይ ጠቀሜታ ያላቸውን ሌሎች ማናቸውም ማስረጃዎች ለመፈለግ እና ለመያዝ በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ወይም የተጠቀሱት ነገሮች ተደብቀውባቸዋል በሚባሉ በሌሎች ሰዎች ቤቶች ውስጥ የሚከናወን የወንጀል ምርመራ ተግባር ነው፡፡ ብርበራ ለማድረግና በሚደረግበት ወቅት የሚከተሉትን መርሆች መከተል አስፈላጊ ነው።
✔ ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር የሰዎችን ቤት መበርበር አይችልም።
✔ ብርበራ የሚደረገው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው። በፍርድ ቤት የተለየ ትእዛዝ ሲሰጥ ብቻ ከዚ ሰአት ውጭ ሊካሄድ ይችላል።
✔ ማንኛውም የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውን እና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት ያለበት ሲሆን መርማሪው ፖሊስ ወይም አብሮት ያለ የፖሊስ አባል በማዘዣው ላይ ከተመለከተው ውጭ ሌላው ዕቃ መያዝ አይችልም።
✔ መርማሪው ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በማዘዣ ትዕዛዙ የተመለከተውን ዕቃ በሚይዝበት ጊዜ የተያዘውን ዕቃ ዝርዝር መዝግቦ መያዝ ያለበት ሲሆን ከተቻለ ገለልተኛ የሆነ ሰው ሊስቱ ላይ እንዲፈርምበት ይደረጋል።
✔ ብርበራ የሚያደርገው ብርበራ ከሚደረግበት ሰው ጋር ተመሳሳይ ፆታ ባለው ሰው ነው።
✔ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ፖሊስ አስፈላጊውን ሀይል ብቻ ይጠቀማል።

#1. በወንጀል ጉዳይ ለተጠረጠረ ግለሰብ ጠበቃ ለማቆም ምንም ዓይነት ውክልና አያስፈልዎትም።
#2. በወንጀል ጉዳይ ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ለተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮም ይሁን ለዋናው ክስ በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነትዎን ከመናገር ባለፈ ስለተጠረጠሩበት ጉዳይ የሕግ ባለሙያ እንዳማክር በቂ ጊዜ ይሰጠኝ ብለው የመጠየቅና የማግኘት መብት አለዎት።
#3. የተጠረጠሩበት ወንጅል ቅጣት እጅግ ከባድ ከሆነ እና ጠበቃ ለመቅጠር አቅም የሌለዎት እንደሆነ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተከላከይ ጠበቃ እንዲመደብልዎት ይጠይቁ።
#4. ሚገጥምዎትን ነገር አያውቁትምና ስለእርስዎ በመሆን ጉዳይዎትን ያከናውንልዎ ዘንድ እጅጉን ቅርቤ ለሚሉት የቤተሰብዎ አባል ሙሉ ውክልና ይስጡ።
#5. አሁን ላይ ሕጋዊ ውክልና ለመስጠት ብሔራዊ መታወቂያ /National ID/ ግድ እየሆነ ነውና በጊዜ መታወቂያውን በእጅዎት ያድርጉ።
#6. የትኛውን ለፍርድ ቤት የሚቀርብ አቤቱታ ከማቅረብዎ በፊት የሕግ ባለሙያ ያማክሩ፤ ምንም ቢሆን ለሕግ ምክር አገልግሎት የሚጠየቁት ክፍያ ከሚያጡት መብትዎ አንጻር ወጪ አስወጣኝ የሚሉበት አይሆንም።
#7. የትኛውንም አቤቱታ ለፍርድ ቤት ሲያቀርቡ የእያንዳንዱን ቀሪ በአግባቡ ማስቀመጥ እንዳለብዎት አይዘንጉ።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
ከችሎት ሰዓት ውጪ ባሉ
በማንኛውም የሥራ ሰዓት በስልክ
የሕግ ነክ ጉዳዮችን ለማማከር
☎️ 09 10 61 69 50 ይጠቀሙ።
በውስጥ መስመር ጥያቄዎችን ለመጠየቅና የሕግ ምክር አገልግሎት ለማግኘት
@laws2016 ይጠቀሙ።

Forwarded from Awlachew.B.Gebru
=====በፍርድ አፈፃፀም የማይወስዱ እና የማይታገዱ ንብረቶች=======
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
✅ የቤተሰቡ ህልውና ለመጠበቅ ለለት አገልግሎት የሚውሉ የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶች ፤ የመኝታ አልጋ እና ልብሶች
✅ለእለት የሙያ ስራወች አግልግሎት ለንግድ ስራ ማከናወኛ የሚውሉ ተገቢ የሆኑ እቃኸች
✅የፍርድ ባለእዳው አርሶ አደር ከሆነ ለእርሻ ስራው አስፈላጊ የሆኑ በሬወች፤ የዘር እህሎች
✅ለራሱ እና ለቤተሰቡ ህልውና ለመጠበቅ የሚሆን የሶስት ወር መተዳደሪያ የሚበቃ ገንዘብ እና ለእለት ምግብ አስፈላጊ የሚሆን ስንቅ
✅ ለጡረታ እና ለወር ቀለብ የሚከፈል ገንዘብ......
✅ እንዳይሸጥ እንዳይከበር እና ለእዳ መክፈያ እንዳይሆን በሌላ ህግ የተወሰነ ማንኛውም ንብረት።
source : ፍብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 404
BY ©#Awlachew.B
Via #ንቃተ #ህግ

Forwarded from ስለፍትሕ (Talk To Lawyer)
#ፍርድ ቤቶች ሚቀበሏቸው ሕጋዊ የቅጣት ገደብ ምክንያቶችን
#መሠረቱ
👉አንድ ቅጣት የሚገደበው ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ጥፋተኛ በተባለበት ውሳኔ በእስር ላይ ሳይደረግ ለጊዜው ቅጣቱ እንዳይፈጸምበት በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል ወደ መደኛ ማኅበራዊ ሕይወቱ ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን ፍርድ ቤት ሲያምንበት ነው።
👉ገደብ ከተሰጠ በኋላ የታሰበውን ውጤት ያላስገኘ እንደሆነ በማንኛውም ጊዜ ሊሻር ይችላል።
#ቅጣት የሚገደበው
1️⃣ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ከሆነ፤
2️⃣ጠባዩ አደገኝነት እንደሌለው ከታመነ፤
3️⃣ጥፋቱ በመቀጮ ወይም በግዴታ ሥራ ወይም ከሦስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት የሚያስቀጣ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው የሚወስንበትን ቅጣት ሳይፈጽም ለተወሰኑ ጊዜያት ጠባዩ ቢፈተሽ የሚታረም መሆኑን እምነት የጣለበት እንደሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቅጣቱ ሳይወሰን የተወሰነ የፈተና ጊዜ ይሰጠዋል።
4️⃣ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈጸሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት እንደማያደርግ ፍርድ ቤቱ ካመነ ቅጣቱን ሊገድብለት ይችላል።
#ቅጣት የማይገደበው
1️⃣ጥፋተኛው ከዚህ በፊት በጽኑ እሥራት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ እሥራት ቅጣት ተፈርዶበት ከነበረ እና አሁንም በተከሰሰበት ጉዳይ እነዚህ ቅጣቶች የሚፈጸሙበት ከሆነ፤
2️⃣ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ የፅኑ አሥራት የሚፈረድበት ከሆነ፤
3️⃣ቅጣቱ ታግዶለት ለፈተኛ በተለቀቀበት ጊዜ ውስጥ አስቦ አንድ ወንጀል ከፈጸመ፤
4️⃣ቅጣቱ ቢገደብለት የሚታሰበውን ዓይነት መልካም ውጤት እንደማይገኝ ፍርድ ቤቱ ያመነ እንደሆነ።
ፍርድ ቤት ቅጣቱን ከመገደቡ በፊት ስለተከሳሹ የቀድሞ ታሪክ፣ የነበረው ጠባይ፣ የአኗኗሩና የሥራው ሁኔታ ምን እንደነበረ ምርመራ ተደርጎ ማስረጃ እንዲቀርብ ሊጠይቅ ይችላል።
👉የሚወሰነው የቅጣት ገደብ ከ2 ዓመት ሊያንስ ከ5 ዓመት ሊበልጥ አይችልም።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
#laws2016
https://t.me/NegereFej
#ነገረ_ፈጅ

Forwarded from የሕግ ዜና
#በውርስ ክርክር ላይ ከሚገጥሙ እንግዳ ጉዳዮች መካከል ሟች ኑዛዜ አድርጎልኛል ወይም አድርጎልናል የሚሉ ተከራካሪዎች መቅረባቸው ነው።
#ልዩ የሚያደርግ ይህ አለ የሚባለው ኑዛዜ በውልና ማስረጃ ተደርጎ እንዲሁ በፍርድ ቤት ጸድቆ እንደማስረጃነት የሚቀርብ መሆኑ ነው።
በሌለ መብት ኑዛዜ ማድረግና ውጤቱ
#ሟች ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው በሕግ ባለውና በተጠበቀለት መብት እና ድርሻ ልክ ብቻ ነው። ባልና ሚስት በትዳር እየኖሩ ባለበት ሁኔታ ባል ወይም ሚስት የአንዳቸውን ድርሻ ጠቅልለው ኑዛዜ ቢያደርጉበት በሌላቸው መብትና ድርሻ ላይ የተደረገ በመሆኑ የተናዘዙት ኑዛዜ ከድርሻቸውና ከመጠናቸው ያለፈውን ያህል ልክ ብቻ ፈራሽ ይሆናል።
#እንደዚህ ያለ ማስረጃ እንደመከራከሪያ ማስረጃ ሆኖ ሲቀርብ ሊሰጥ ከሚገባው ምላሽ ውስጥ ቀዳሚው መሆን ያለበት ሟች ፈጸመ የተባለው ኑዛዜ ከድርሻው በማለፍ በመሆኑ የሕግ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም መባል አለበት።
#በዚህ ረገድ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 8 በመዝገብ ቁጥር 32817 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ "ተናዛዡ ከራሱ ንብረት ጋር የሌላ ሰውን ንብረትም ጨምሮ በመዘርዝር ኑዛዜ አድርጎ ይህ ኑዛዜ በፍርድ ቤህ ቢጸድቅም እንኳን የሌላ ሰው የሆነውን ንብረት በተመለከተ የተደረገው ኑዛዜ ዋጋ ሊሰጠው አይገባም። በራሱ ንብረቶች ላይ የተናዘዘው ግን ተለይቶ ዋጋ ሊሰጠው ይገባል።" በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/NegereFej
#ልዩ የሚያደርግ ይህ አለ የሚባለው ኑዛዜ በውልና ማስረጃ ተደርጎ እንዲሁ በፍርድ ቤት ጸድቆ እንደማስረጃነት የሚቀርብ መሆኑ ነው።
በሌለ መብት ኑዛዜ ማድረግና ውጤቱ
#ሟች ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው በሕግ ባለውና በተጠበቀለት መብት እና ድርሻ ልክ ብቻ ነው። ባልና ሚስት በትዳር እየኖሩ ባለበት ሁኔታ ባል ወይም ሚስት የአንዳቸውን ድርሻ ጠቅልለው ኑዛዜ ቢያደርጉበት በሌላቸው መብትና ድርሻ ላይ የተደረገ በመሆኑ የተናዘዙት ኑዛዜ ከድርሻቸውና ከመጠናቸው ያለፈውን ያህል ልክ ብቻ ፈራሽ ይሆናል።
#እንደዚህ ያለ ማስረጃ እንደመከራከሪያ ማስረጃ ሆኖ ሲቀርብ ሊሰጥ ከሚገባው ምላሽ ውስጥ ቀዳሚው መሆን ያለበት ሟች ፈጸመ የተባለው ኑዛዜ ከድርሻው በማለፍ በመሆኑ የሕግ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም መባል አለበት።
#በዚህ ረገድ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 8 በመዝገብ ቁጥር 32817 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ "ተናዛዡ ከራሱ ንብረት ጋር የሌላ ሰውን ንብረትም ጨምሮ በመዘርዝር ኑዛዜ አድርጎ ይህ ኑዛዜ በፍርድ ቤህ ቢጸድቅም እንኳን የሌላ ሰው የሆነውን ንብረት በተመለከተ የተደረገው ኑዛዜ ዋጋ ሊሰጠው አይገባም። በራሱ ንብረቶች ላይ የተናዘዘው ግን ተለይቶ ዋጋ ሊሰጠው ይገባል።" በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/NegereFej
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
Forwarded from Law forum (marye kasse)
የኮምፒውተር ወንጀል የሚያስከትለው ተጠያቂነት
መግቢያ
በአለማችን ቴክኖሎጂ እየረቀቀ እና ሥራዎችን እያቀላጠፈ ይገኛል፡፡ የኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአት ከነዚህ ቴክኖሎጂዎች በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ቴክኖሎጂ ለአለማችን አጋዥ ቢሆንም ለጥቃት ተጋላጭ ከመሆኑ አንፃር የራሱ ውስንነቶች ያሉት እና የጥንቃቄ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ የኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአትን እንዲሁም የኮምፒውተር ወንጀልን ምንነት አና የሚስከትለውን ተጠያቂነት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
ኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአት ምንነት
በኮምፒውተር አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀፅ 2(3) መሰረት ኮምፒውተር ወይም የኮምፒውተር ሥርአት ማለት በሶፍትዌር እና ማይክሮቺፕ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የዳታ ፕሮሰሲን፣ ክምችት፣ ትንተና፣ ሥርጭት፣ ግንኙነት ወይም ሌሎች ሂሳባዊ ወይም አመክንዮአዊ ተግባራትን የሚያከናውን ማንኛውም መሳሪያ እና የመሳሪያውን ተገጣሚ አካል የሚጨምር እንደሆነ ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡፡
የኮምፒውተር ወንጀል ምንነት
በአዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀፅ 2(1) መሰረት የኮምፒዩተር ወንጀል ማለት በኮምፒዩተር፣ በኮምፒውተር ሥርአት እና በኮምፒዩተር ዳታ (ኔትዎርክ) ላይ የሚፈፀምን ወንጀል፣ እነዚህኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም የሚፈፀምን መደበኛ ወንጀል እንዲሁም ይህንኑ በመጠቀም ህገወጥ የኮምፒውተር ዳታ ማሰራጨትን የሚያከትት ነው፡፡ የወንጀሉ ዋነኛ ማጠንጠኛም በኮምፒዩተሩ ዳታ ላይ ያተኮረ ሆኖ በኔትወርክ አማካይነት ዳታውን ከመደበኛ አሰራሩ ውጭ ማበላሸት ወይም ማዛባትና ማሰራጨት ለዚህም አላማ ያለባለቤቱ ፍቃድ ኮምፕዩተሩን ማግኘት የሚመለከት ነው፡፡
የሳይበር ጥቃት መከላከል በአለምአቀፍ ደረጃ
የሳይበር ጥቃት የኮምፒውተር ሥርአት ወይም ኔትዎረክን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማግኘት ሲሆን አላማውም ጉዳት ማድረስ ነው፡፡ የሚያደርሰውም ጉዳት ብልሽት፣ ማዛባት፣ ማስወገድ ወይም የኮምፒውተሩን ሥርአት በመለወጥ ማጥፋት፣ በሥርአት ውስጥ ያለ መረጃን ማዛባት ወይም መስረቅን ይጨምራል፡፡ ይህ ጥቃት የማጥቃት እስትራቴጂ ባለው በማንኛውም ሰው ወይም ቡድን ከየትኛውም ቦታ ሊሰነዘር ይችላል፡፡ ጥቃቱን የሚፈፅሙ ሰዎች የሳይበር ወንጀለኞች ወይም በተለምዶ ሀከሮች ተብለው ይታወቃሉ፡፡
የሳይበር ጥቃት አለማቀፍ ወንጀል መሆኑን መግባባት ያለ ቢሆንም ይህንኑ ድርጊት የሚያወግዝ ወጥ የሆነ አለማቀፍ ህግ ግን እስካሁን የለም፡፡ ይሁንና በጉዳዩ ላይ አህጉራዊ ስምምነቶች ያሉ ሲሆን ለአብነት ያክል በአፍሪካ ደረጃ በ2008 የወጣው የአፍሪካ ህብረት የሳይበር ደህንነት እና ግላዊ ዳታ ለመጠበቅ የወጣውን ስምምነት (African Union Convention on Cyber Security and Personal Data Protection) መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአውሮፓ ህብረት ደረጃ የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል እ.አ.አ በ2001 በሀንጋሪ የወጣው ስምምነት Convention on Cybercrime (በተለምዶ የቡዳፔስት ስምምነት እየተባለ የሚጠቀሰው) ተጠቃሽ ስምምንት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ሀገራት በግዛታቸው የሚፈፀሙ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል ህግ በማውጣት ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የሳይበር ክልልን መቆጣጠር እና ማስተዳደር ከመንግስት ተቋማት በተጨማሪ የሌሎች አካላትን ተሳትፎ ይፈልጋል፡፡ ይኸውም ለኢንተርኔት መፈጠር እና መስፋፋት መሪ ሚና የተጫወቱ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማለትም እንደ ጉግል፣ ፌስቡክ፣ የኢንተርኔት እስታንዳርድ እና ፕሮቶኮል አዘጋጆች፣ ሲቪል ማህበራት እና የመሳሰሉት የዘርፉ ቁልፍ ተዋናይ አካላት ዘርፉን በማስተዳደር እና የሳይበር ጥቃትን ከመከላከል አኳያ ከመንግስታት በተጨማሪነት ጉልህ ሚና አላቸው፡፡
የኮምፒዩተር ወንጀል በኢትዮጵያ
መረጃ የማግኘት እና የማሰራጨት መብት በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ስር ጥበቃ የሚደረግለት መብት ቢሆንም የሀገር ደህንነት እና የህዝብን ሰላም እና ጤና ለመጠበቅ ሲባል በህግ ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል ከህገመንግስቱ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል። በዚሁ መሰረት በአገራችን የህግ ሥርአት በኮምፒዩተር ሥርአት አማካይነት የሚፈፀሙ ህገወጥ የመረጃ ተደራሽነት፣ ማዛባት፣ ጠለፋ እና ማጥፋት ተግባራት የተከለከሉ እና በወንጀልነት የተፈረጁ የሚያስቀጡ ድርጊቶች ጭምር ናቸው፡፡
የሳይበር ጥቃት የሀገራትን ሉአላዊነት የሚጥስ እና ከአንድ የአለማችን ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ በቀላሉ የሚፈፀም እና የአለምን ሰላምና ደህንነት የሚነሳ አደገኛ አለማቀፍ ወንጀል ነው፡፡ ይህ የሳይበር ጥቃት በህጋችን የኮምፒዩተር ወንጀል ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተደነገገውም በ1996 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ህግ ከአንቀጽ 706 እስከ 711 ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ ድንጋጌዎች ብቻቸውን በየግዜው እየተወሳሰበ የመጣውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የወንጀል ተጋላጭነት በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር ባለመቻሉ በአዲስ መልክ እራሱን ችሎ በአዋጅ እንዲሸፈን ለማድረግ በማሰብ በኮምፒዩተር ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 958/2008 በዝርዝር ተደንግጎ ወጥቷል፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው ይሄው ህግ ሲሆን ቀጥለን ዋና ዋና የወንጀሉን ድንጋጌዎች ባጭሩ የምንቃኝ ይሆናል፡፡
• ህገወጥ ደራሽነት (አንቀጽ 3) ይኸውም ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ሥርዓት፣ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ኔትዎርክ ደራሽነት በከፊልም ሆነ በሙሉ ማግኘት ነው፡፡
• ህገወጥ ጠለፋ (አንቀጽ 4)- ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ ይፋዊ ያልሆነን የኮምፒዩተር ዳታ ወይም የዳታ ፕሮሰሲንግ አገልግሎት መጥለፍ ነው፡፡
• በኮምፒዩተር ሥርዓት ላይ ጣልቃ መግባት (አንቀጽ-5) -ያለ ፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ዳታን በማስገባት፣ በማሰራጨት፣ በማጥፋት ወይም በመለወጥ የኮምፒዩተር ሥርዓትን ወይም ኔትወርክን መደበኛ ተግባር በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ማደናቀፍ፣ ማወከ፣ ማውደም ወይም እንዲቋረጥ ማድረግ ነው፡፡
• በኮምፒዩተር ዳታ ላይ ጉዳት ማድረስ (አንቀት 6)- ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ዳታን መለወጥ፣ ማጥፋት፣ ማፈን፣ ትርጉም እንዳይኖረው ወይም ጥቅም እንዳይሰጥ ወይም ለሕጋዊ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው፡፡
• ከኮምፒዩተር መሣሪያና ዳታ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ወንጀሎች (አንቀጽ 7)- በኮምፒዩተር ሥርዓት በኮምፒዩተር ዳታ ወይም በኔትዎርክ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ እየታወቀ ለዚህ ዓላማ ተብለው የተመረቱ ወይም የተሻሻሉ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞችን ሆነ ብሎ በኮምፒዩተር ሥርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ነው፡፡
• የኮምፒዩተር ዳታን ወደ ሐሰት መለወጥ (አንቀጽ 9)- የሌላን ሰው ጥቅም ለመጉዳት ወይም ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ያልተገባ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ሕጋዊ ውጤት ያለውን ወይም ሊኖረው የሚችለውን የኮምፒዩተር ዳታ ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም ሐሰተኛ የኮምፒዩተር ዳታ ማዘጋጀት ወይም በዚሁ መገልገል ነው፡፡
• በኮምፒዩተር አማካኝነት የሚፈፀም የማታለል ወንጀል (አንቀጽ 10)- አሳሳች የኮምፒዩተር ዳታዎችን በማሰራጨት፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት በመጠቀም፣ ሌላውን ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን ማንኛውም ጥቅም የሚጎዳ ድርጊት እንዲፈፅም ማድረግ ነው፡፡

• የኤሌክትሮኒክ ማንነት ስርቆት (አንቀጽ 11)- የማታለል ወንጀል ለመፈፀም ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት የሌላን ሰው የኤሌክትሮኒክ ማንነት የሚያረጋግጥ ዳታ ያለባለቤቱ ፈቃድ በኮምፒዩተር ሥርዓት አማካኝነት ማምረት፣ ማግኘት፣ መሸጥ፣ ይዞ መገኘት ወይም ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡
እነዚህን የወንጀል ድርጊቶች መፈፀም በህጉ ለየወንጀል አይነቶቹ የተደነገገውን በመደበኛ አፈፃፀም እስከ 5 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና በገንዘብ ቅጣት የሚያስቀጣ ሲሆን በከባድ ሁኔታ የተፈፀመ ሲሆን ማለትም ወንጀሎቹ የተፈፀሙት ፡-
• ለወታደራዊ ጥቅም ወይም ለዓለም አቀፍ ግንኙነት ሲባል በሚመለከተው አካል ጥብቅ ምስጢር ተብሎ በተሰየመ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ዳታው በሚገኝበት የኮምፒዩተር ሥርዓት ወይም ኔትዎርክ ላይ ከሆነ ወይም
• አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ወይም ሀገሪቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ በምትገኝበት ወቅት ከሆነ
• በቁልፍ መሠረተ ልማት ላይ ከሆነ
• በሕግ የሰውነት መብት ለተሰጠው ተቋም አገልግሎት ብቻ በሚውል የኮምፒዩተር ሥርዓት ላይ ከሆነ እና
በመሰል ሁኔታዎች በመፈፀሙ ወንጀሉ ከባድ በሆነበት ጊዜ ቅጣቱ እንደ ወንጀል አይነቶቹ ከብዶ እንዳደረስው ጉዳት እና አፈፃፀሙ እየታየ እስከ 25 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሚደርስ መቀጮ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡
ማጠቃለያ
በጥቅሉ የኮምፒዩተር ወንጀል በአገር ሰላም እና ደህንነት ብሎም ምጣኔ ሀብታዊ እና ማህበራዊ አድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ወንጀል ስለሆነ ሁሉም ሰው ይሄን አውቆ ከዚህ ወንጀል እራሱን ማራቅ እና ተፈፅሞም ሲገኝ ከህግ አካላት ጋር በመተባበር ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀርቡ እና ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ