የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016
Forwarded from አለ ሕግ
#👉⚖️ በሀገራችን የወንጀል ሕግ ሥርዓት መሠረት ያለአግባብ ለተከሰሱ፣ ለተቀጡም ሆነ ፍርዳቸውን ለተቀበሉ ሰዎች ካሳ የሚከፈልበት ሥርዓት የለም፤ ነገር ግን ንፁሐን ለደረሰባቸው በደል መነሻ የሆኑት የግል አቤቱታ አቃራቢዎችና ሐሰተኛ ምስክሮች ሚጠየቁበት ሥርዓት አለ።
#በወንጀል ጉዳይ ክስ የቀረበበት ሰው ከቀረበበት ክስ ነፃ መሆንን በሁለት መንገድ መመልከት ይቻላል።
🚨1ኛ. ዓቃቤ ሕግ ክሱን ባለማስረዳቱ ነፃ መሆን
#👉⚖️ በመርህ ደረጃ በወንጀል ጉዳይ ከሳሽ የሚሆነው ዓቃቤ ሕግ ነው። ዓቃቤ ሕግ የሚያቀርበውን ክስ ተከሳሽ የፈጸመው ስለመሆኑ የማስረዳት ግዴታ አለበት። ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ግለሰቡ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ከጥርጣሬ በፀዳ ሁኔታ Beyound reasonabl doubt ማስረዳት ይጠበቅበታል።
#👉⚖️ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ ይህንን ግዴታውን ካልተወጣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር1️⃣4️⃣1️⃣መሠረት ግለሰቡን ተከላከል ማለት ሳያስፈልገው በነፃ ሊያሰናብተው ይችላል።
🚨2ኛ. ተከሳሽ ወንጀሉን አለመፈጸሙን በመከላከሉ ነፃ መሆን
#👉⚖️ በወንጀል የተከሰሰ ሰው ክስ የቀረበበትን ጉዳይ በበቂ ሁኔታ ከተከላከለ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር1️⃣4️⃣9️⃣መሠረት ከክሱ ነፃ ይሆናል።
🚨የወንጀል ኃላፊነት
#👉⚖️ በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 447 ላይ እንደተመለከተው ሰውን በሐሰት ወንጀል ወይም መክሰስ ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እሥራትና በመቀጮ ያስቀጣል። ነገር ግን በሐሰት የቀረበው ክስ ግለሰቡን ከዚህ በላይ የሆነ ቅጣትን አስከትሎ እንደሆነ በንፁህ ሰው ላክ በተወሰነው ቅጣት ልክ ይቀጣል።

https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube
https://youtube.com/@Ale_Hig
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
የወራሾች ክስ ማስቀጠል ሂደትና የይርጋ ጊዜ
⚖️ክስ ያቀረበ ከሳሽ ሲሞት የወራሾች በክርክር ውስጥ መግባት
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 49(1) ድንጋጌ መሰረት ክሱን ለመቀጠል መብት አለኝ የሚሉ ወገኖች ዋናው ከሳሽ ወይንም ከሳሾች በሞቱ በአንድ አመት ውስጥ ክሱን ለመቀጠል እንዲፈቀድላቸው ሳያመለክቱ የቀሩ እንደሆነ የተጀመረው ክርክር ውድቅ እንደሚሆን የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 49(2) ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል፡፡ ይህ ድንጋጌ ክሱን ለመቀጠል መብት አለኝ የሚል ወገን ክሱን ለመቀጠል እንዲፈቀድለት ማመልከቻውን የሚያቀርብበትን የጊዜ ገደብ የሚመለከት ሲሆን ከሳሽ ወይም ከሳሾች በሞቱ በአንድ አመት ውስጥ ክሱን ለመቀጠል ሳያመለክቱ መቅረታቸው ከተረጋገጠ የተጀመረው ክርክር ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ የሚደነገግ ሲሆን ከዚህ ጊዜ በኋላም ጥያቄው ሲቀርብ ተቀባይነት የሚያገኝበት አግባብ መኖሩን የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 55(2) ድንጋጌ ያሳያል፡፡
⚖️በዚህም መሰረት ከሳሹ ራሱ ወይም ከሳሽ የነበረው የሟቹ ንብረት አስተዳዳሪ ነኝ የሚል ባለአደራ ወይም የከሰረው ከሳሽ ንብረት አስተዳዳሪ የሆነ ሰው ወይም የዋናው ከሳሽ መብት ተላልፍልኛል የሚል ሰው ክሱ ቀሪ በሆነ ወይም በተሰረዘ በስድስት ወር ውስጥ የቀረበው ክስ እንዲቀጥል ወይም መሰረዙ እንዲነሳለት ለማመልከት የሚችል ስለመሆኑ የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ክሱ ቀሪ የሆነው ወይም የተሰረዘው በከሳሹ ጉድለት ያለመሆኑን የተረዳው እንደሆነ ይህ ምክንያት ስለደረሰው ኪሳራ ተገቢ መስሎ የታየውን ወስኖ የቀረው ወይም የተሰረዘው ክስ እንዲቀጥል ለማዘዝ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 55(3) ድንጋጌ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ይህ ድንጋጌ አቤቱታው ክሱ ቀሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ በሚቆጠር ስድስት ወራት ውስጥ መቅረብ እንዳለበትና በበቂ ምክንያት መደገፍ እንዳለበት የሚደነግግ ሲሆን በቂ ምክንያት የሚለውን ሐረግ ግን መመዘኛው ምን እንደሆነ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ በቂ ምክንያት አለ ወይስ የለም? የሚለው ጥያቄ አመልካቹ በተገቢው ጊዜ አስፈላጊውን ስርዓት ያልፈፀመበት ምክንያት ተገቢ የሆነ ምክንያት ስለነበረው ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን በመመልከት በፍርድ ቤቱ አዎንታዊ ምላሽ ከአገኘ በቂ ምክንያት አለ ብሎ ለመደምደም የሚችልበትን አግባብ የሚያሳይ ነው፡፡
⚖️በመሆኑም የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 49 እና 55(2) እንዲሁም 55(3) ድንጋጌዎች ሲታዩ ክርክሩን ለመቀጠል የአንድ አመት ጊዜ ከአለፈ ጥያቄው ተቀባይነት የሌለው መሆኑንና ይህ የጊዜ ገደብ በማለፍ መዝገቡ ከተዘጋ ወይም ክሱ ቀሪ ከሆነ በኋላ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ክርክሩ እንዲቀጥል ወይም ቀሪ የሆነ ክስ እንዲንቀሳቀስ በቂ ምክንያት ያለው መሆኑን አቤቱታ አቅራቢው ከገለፀ እና ፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅራቢው አስፈላጊውን ስርዓት ያልፈፀመበት ምክንያት ተገቢ በሆነ ምክንያት መሆኑን ከተረዳው ክርክሩ እንዱቀጥል ማድረግ የግድ የሚል መሆኑን የሚያስገነዝቡን ናቸው፡፡
⚖️ከዚህ አንፃር ሲታይ ከሳሽ በመሞቱ ምክንያት የተዘጋ መዝገብን ለማንቀሳቀስ ፍጹም የሆነ ይርጋ የአንድ አመት ስድስት ወራት ጊዜ ነው ቢባል እንኳ ፍርድ ቤት መዝገቡ ተዘግቶ የቆየበትን ጊዜ በማስላት ብቻ ጊዜውን መቁጠር ያለበት ሳይሆን በጊዜ ገደቡ ውስጥ ጥያቄውን ያቀረበው አቤቱታ አቅራቢ የቆየበትን ሁኔታ ሁሉ አግባብነት ካላቸው ሌሎች የመሰረታዊ ህግ ድንጋጌዎችና አንድ ሰው ከሳሽ ለመሆን መሟላት ያለባቸውን የስነ ሥርዓት ሕግ መስፈርቶች ማየትን የግድ የሚል ነው፡፡
⚖️የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 49 እና 55(3) ሥነ-ሥርዓታዊ ድንጋጌዎች እንደመሆናቸው መጠንም የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው መቼ ነው? ከሚለው ጥያቄ አንጻር ጉዳዩ መታየት ያለበት ነው፡፡ ይህንኑ ጥያቄ ለመመለስ ደግሞ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1846 እና የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 48 ድንጋጌዎችን ይዘት መመልከት ተገቢ ይሆናል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1846 ድንጋጌ መሰረት የይርጋ ጊዜ መነሻው በመብት መስራት የሚቻልበት ጊዜ ነው፡፡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 48 ድንጋጌ መሰረት ደግሞ ክርክሩ እንዲቀጥል የሚያስችለው መብት የማይቋረጥ ከሆነ የከሳሽ ወይም የተከሳሽ መሞት ክርክሩን እንዲቆም አያደርገውም በሚል ተቀምጧል፡፡ ከዚህ የስነ ስርዓት ድንጋጌ ውስጥ "ክርክሩ እንዲቀጥል የሚያስችለው መብት የማይቋረጥ ከሆነ" የሚለው ሐረግ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 826(2) እና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1986 ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ የሚታይ ነው፡፡
በዚህም መሰረት በዚህ መብት አንድ ሰው ሊሰራ ይችላል ተብሎ የሚታሰበው ተገቢውን የወራሽነት ማስረጃ ከያዘ በኋላ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 62452 ቅጽ 13፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 48፣ 49(1)፣ 55(2)፣ 55(3) ፍ/ህ/ቁ. 826(2)፣ 1846፣ 1986
Join 👇👇
https://t.me/ethiolawtips
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ቀለብ አወሳሰን መመሪያ.pdf
1005.5 KB
ቀለብ አወሳሰን መመሪያ.pdf
-------------------------------
የቀለብ አወሳሰን መመሪያ መርሆች
💥የልጅ ቀለብ በዋናነት የህፃናት ጥቅምን ቀዳሚ ማድረግ አለበት።ቀለብ ሰጪዋች ወላጆች በሚሆኑበት ጊዜ አቅማቸው በፈቀደ መጠን ልጆቻቸውን የማሳደግና የመንከባከብ ሕጋዊ ሐላፊነታቸውን እንደገቢያቸው መጠን የሚጋሩት ይሆናል።
💥የልጅ ቀለብ በሚወሰንበት ሂደት ወላጆች ለመኖር የሚያስፈልጓቸውን መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ታሳቢ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም በየትኛውም ሁኔታ ግን ለልጅ ቀለብ የመስጠት ግዴታን የሚያግድ መሆን የለበትም።
💥የልጅ ቀለብ አወሳሰን የልጅን መሠረታዊ ፍላጎቶችን ልዩ ወጪዎች ታሳቢ ማድረግ ያለበት ሲሆን ከወላጆች አንዱ የተሻለ ገቢ ያለው ከሆነ ልጁ የዚህ ገቢ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል።ከዚህ በተጨማሪም ልዩ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸውን ሕፃናት ከግምት ያስገባ መሆን ይኖርበታል።
https://t.me/ethiolawtips
Forwarded from Legal Insight Ethiopia
ብርበራ

ብርበራ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችን ፣ በወንጀል ድርጊት ምክንያት የተገኙ ቁሳቁሶችን ፣ ምርመራ ለሚደረግበት ጉዳይ ጠቀሜታ ያላቸውን ሌሎች ማናቸውም ማስረጃዎች ለመፈለግ እና ለመያዝ በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ወይም የተጠቀሱት ነገሮች ተደብቀውባቸዋል በሚባሉ በሌሎች ሰዎች ቤቶች ውስጥ የሚከናወን የወንጀል ምርመራ ተግባር ነው፡፡ ብርበራ ለማድረግና በሚደረግበት ወቅት የሚከተሉትን መርሆች መከተል አስፈላጊ ነው።

✔ ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም  የፖሊስ አባል በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር የሰዎችን ቤት መበርበር አይችልም።

✔ ብርበራ የሚደረገው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው። በፍርድ ቤት የተለየ  ትእዛዝ ሲሰጥ ብቻ ከዚ ሰአት ውጭ ሊካሄድ ይችላል።

✔ ማንኛውም የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውን  እና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት ያለበት ሲሆን መርማሪው ፖሊስ ወይም አብሮት ያለ የፖሊስ አባል በማዘዣው ላይ ከተመለከተው ውጭ ሌላው ዕቃ መያዝ አይችልም።

✔ መርማሪው ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በማዘዣ ትዕዛዙ የተመለከተውን ዕቃ በሚይዝበት ጊዜ የተያዘውን ዕቃ ዝርዝር መዝግቦ መያዝ ያለበት ሲሆን ከተቻለ ገለልተኛ የሆነ ሰው ሊስቱ ላይ እንዲፈርምበት ይደረጋል።

✔ ብርበራ የሚያደርገው ብርበራ ከሚደረግበት ሰው ጋር ተመሳሳይ ፆታ ባለው ሰው ነው።

✔ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ፖሊስ አስፈላጊውን ሀይል ብቻ ይጠቀማል።
#1. በወንጀል ጉዳይ ለተጠረጠረ ግለሰብ ጠበቃ ለማቆም ምንም ዓይነት ውክልና አያስፈልዎትም።
#2. በወንጀል ጉዳይ ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ለተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮም ይሁን ለዋናው ክስ በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነትዎን ከመናገር ባለፈ ስለተጠረጠሩበት ጉዳይ የሕግ ባለሙያ እንዳማክር በቂ ጊዜ ይሰጠኝ ብለው የመጠየቅና የማግኘት መብት አለዎት።
#3. የተጠረጠሩበት ወንጅል ቅጣት እጅግ ከባድ ከሆነ እና ጠበቃ ለመቅጠር አቅም የሌለዎት እንደሆነ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተከላከይ ጠበቃ እንዲመደብልዎት ይጠይቁ።
#4. ሚገጥምዎትን ነገር አያውቁትምና ስለእርስዎ በመሆን ጉዳይዎትን ያከናውንልዎ ዘንድ እጅጉን ቅርቤ ለሚሉት የቤተሰብዎ አባል ሙሉ ውክልና ይስጡ።
#5. አሁን ላይ ሕጋዊ ውክልና ለመስጠት ብሔራዊ መታወቂያ /National ID/ ግድ እየሆነ ነውና በጊዜ መታወቂያውን በእጅዎት ያድርጉ።
#6. የትኛውን ለፍርድ ቤት የሚቀርብ አቤቱታ ከማቅረብዎ በፊት የሕግ ባለሙያ ያማክሩ፤ ምንም ቢሆን ለሕግ ምክር አገልግሎት የሚጠየቁት ክፍያ ከሚያጡት መብትዎ አንጻር ወጪ አስወጣኝ የሚሉበት አይሆንም።
#7. የትኛውንም አቤቱታ ለፍርድ ቤት ሲያቀርቡ የእያንዳንዱን ቀሪ በአግባቡ ማስቀመጥ እንዳለብዎት አይዘንጉ።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
ከችሎት ሰዓት ውጪ ባሉ
በማንኛውም የሥራ ሰዓት በስልክ
የሕግ ነክ ጉዳዮችን ለማማከር
☎️ 09 10 61 69 50 ይጠቀሙ።
በውስጥ መስመር ጥያቄዎችን ለመጠየቅና የሕግ ምክር አገልግሎት ለማግኘት
@laws2016 ይጠቀሙ።
Forwarded from Awlachew.B.Gebru
=====በፍርድ አፈፃፀም የማይወስዱ እና የማይታገዱ ንብረቶች=======
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
✅ የቤተሰቡ ህልውና ለመጠበቅ ለለት አገልግሎት የሚውሉ የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶች ፤ የመኝታ አልጋ እና ልብሶች
✅ለእለት የሙያ ስራወች አግልግሎት ለንግድ ስራ ማከናወኛ የሚውሉ ተገቢ የሆኑ እቃኸች
✅የፍርድ ባለእዳው አርሶ አደር ከሆነ ለእርሻ ስራው አስፈላጊ የሆኑ በሬወች፤ የዘር እህሎች
✅ለራሱ እና ለቤተሰቡ ህልውና ለመጠበቅ የሚሆን የሶስት ወር መተዳደሪያ የሚበቃ ገንዘብ እና ለእለት ምግብ አስፈላጊ የሚሆን ስንቅ
✅ ለጡረታ እና ለወር ቀለብ የሚከፈል ገንዘብ......
✅ እንዳይሸጥ እንዳይከበር እና ለእዳ መክፈያ እንዳይሆን በሌላ ህግ የተወሰነ ማንኛውም ንብረት።
source : ፍብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 404

BY ©#Awlachew.B
Via #ንቃተ #ህግ
Forwarded from ስለፍትሕ (Talk To Lawyer)
#ፍርድ ቤቶች ሚቀበሏቸው ሕጋዊ የቅጣት ገደብ ምክንያቶችን
#መሠረቱ
👉አንድ ቅጣት የሚገደበው ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ጥፋተኛ በተባለበት ውሳኔ በእስር ላይ ሳይደረግ ለጊዜው ቅጣቱ እንዳይፈጸምበት በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል ወደ መደኛ ማኅበራዊ ሕይወቱ ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን ፍርድ ቤት ሲያምንበት ነው።
👉ገደብ ከተሰጠ በኋላ የታሰበውን ውጤት ያላስገኘ እንደሆነ በማንኛውም ጊዜ ሊሻር ይችላል።
#ቅጣት የሚገደበው
1️⃣ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ከሆነ፤
2️⃣ጠባዩ አደገኝነት እንደሌለው ከታመነ፤
3️⃣ጥፋቱ በመቀጮ ወይም በግዴታ ሥራ ወይም ከሦስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት የሚያስቀጣ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው የሚወስንበትን ቅጣት ሳይፈጽም ለተወሰኑ ጊዜያት ጠባዩ ቢፈተሽ የሚታረም መሆኑን እምነት የጣለበት እንደሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቅጣቱ ሳይወሰን የተወሰነ የፈተና ጊዜ ይሰጠዋል።
4️⃣ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈጸሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት እንደማያደርግ ፍርድ ቤቱ ካመነ ቅጣቱን ሊገድብለት ይችላል።
#ቅጣት የማይገደበው
1️⃣ጥፋተኛው ከዚህ በፊት በጽኑ እሥራት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ እሥራት ቅጣት ተፈርዶበት ከነበረ እና አሁንም በተከሰሰበት ጉዳይ እነዚህ ቅጣቶች የሚፈጸሙበት ከሆነ፤
2️⃣ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ የፅኑ አሥራት የሚፈረድበት ከሆነ፤
3️⃣ቅጣቱ ታግዶለት ለፈተኛ በተለቀቀበት ጊዜ ውስጥ አስቦ አንድ ወንጀል ከፈጸመ፤
4️⃣ቅጣቱ ቢገደብለት የሚታሰበውን ዓይነት መልካም ውጤት እንደማይገኝ ፍርድ ቤቱ ያመነ እንደሆነ።
ፍርድ ቤት ቅጣቱን ከመገደቡ በፊት ስለተከሳሹ የቀድሞ ታሪክ፣ የነበረው ጠባይ፣ የአኗኗሩና የሥራው ሁኔታ ምን እንደነበረ ምርመራ ተደርጎ ማስረጃ እንዲቀርብ ሊጠይቅ ይችላል።
👉የሚወሰነው የቅጣት ገደብ ከ2 ዓመት ሊያንስ ከ5 ዓመት ሊበልጥ አይችልም።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
#laws2016

https://t.me/NegereFej
#ነገረ_ፈጅ
Forwarded from የሕግ ዜና
#በውርስ ክርክር ላይ ከሚገጥሙ እንግዳ ጉዳዮች መካከል ሟች ኑዛዜ አድርጎልኛል ወይም አድርጎልናል የሚሉ ተከራካሪዎች መቅረባቸው ነው።
#ልዩ የሚያደርግ ይህ አለ የሚባለው ኑዛዜ በውልና ማስረጃ ተደርጎ እንዲሁ በፍርድ ቤት ጸድቆ እንደማስረጃነት የሚቀርብ መሆኑ ነው።
በሌለ መብት ኑዛዜ ማድረግና ውጤቱ
#ሟች ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው በሕግ ባለውና በተጠበቀለት መብት እና ድርሻ ልክ ብቻ ነው። ባልና ሚስት በትዳር እየኖሩ ባለበት ሁኔታ ባል ወይም ሚስት የአንዳቸውን ድርሻ ጠቅልለው ኑዛዜ ቢያደርጉበት በሌላቸው መብትና ድርሻ ላይ የተደረገ በመሆኑ የተናዘዙት ኑዛዜ ከድርሻቸውና ከመጠናቸው ያለፈውን ያህል ልክ ብቻ ፈራሽ ይሆናል።
#እንደዚህ ያለ ማስረጃ እንደመከራከሪያ ማስረጃ ሆኖ ሲቀርብ ሊሰጥ ከሚገባው ምላሽ ውስጥ ቀዳሚው መሆን ያለበት ሟች ፈጸመ የተባለው ኑዛዜ ከድርሻው በማለፍ በመሆኑ የሕግ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም መባል አለበት።
#በዚህ ረገድ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 8 በመዝገብ ቁጥር 32817 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ "ተናዛዡ ከራሱ ንብረት ጋር የሌላ ሰውን ንብረትም ጨምሮ በመዘርዝር ኑዛዜ አድርጎ ይህ ኑዛዜ በፍርድ ቤህ ቢጸድቅም እንኳን የሌላ ሰው የሆነውን ንብረት በተመለከተ የተደረገው ኑዛዜ ዋጋ ሊሰጠው አይገባም። በራሱ ንብረቶች ላይ የተናዘዘው ግን ተለይቶ ዋጋ ሊሰጠው ይገባል።" በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ

https://t.me/NegereFej
Forwarded from Law forum (marye kasse)
የኮምፒውተር ወንጀል የሚያስከትለው ተጠያቂነት
መግቢያ

በአለማችን ቴክኖሎጂ እየረቀቀ እና ሥራዎችን እያቀላጠፈ ይገኛል፡፡ የኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአት ከነዚህ ቴክኖሎጂዎች በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ቴክኖሎጂ ለአለማችን አጋዥ ቢሆንም ለጥቃት ተጋላጭ ከመሆኑ አንፃር የራሱ ውስንነቶች ያሉት እና የጥንቃቄ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ የኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአትን እንዲሁም የኮምፒውተር ወንጀልን ምንነት አና የሚስከትለውን ተጠያቂነት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

ኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአት ምንነት

በኮምፒውተር አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀፅ 2(3) መሰረት ኮምፒውተር ወይም የኮምፒውተር ሥርአት ማለት በሶፍትዌር እና ማይክሮቺፕ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የዳታ ፕሮሰሲን፣ ክምችት፣ ትንተና፣ ሥርጭት፣ ግንኙነት ወይም ሌሎች ሂሳባዊ ወይም አመክንዮአዊ ተግባራትን የሚያከናውን ማንኛውም መሳሪያ እና የመሳሪያውን ተገጣሚ አካል የሚጨምር እንደሆነ ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡፡

የኮምፒውተር ወንጀል ምንነት

በአዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀፅ 2(1) መሰረት የኮምፒዩተር ወንጀል ማለት በኮምፒዩተር፣ በኮምፒውተር ሥርአት እና በኮምፒዩተር ዳታ (ኔትዎርክ) ላይ የሚፈፀምን ወንጀል፣ እነዚህኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም የሚፈፀምን መደበኛ ወንጀል እንዲሁም ይህንኑ በመጠቀም ህገወጥ የኮምፒውተር ዳታ ማሰራጨትን የሚያከትት ነው፡፡ የወንጀሉ ዋነኛ ማጠንጠኛም በኮምፒዩተሩ ዳታ ላይ ያተኮረ ሆኖ በኔትወርክ አማካይነት ዳታውን ከመደበኛ አሰራሩ ውጭ ማበላሸት ወይም ማዛባትና ማሰራጨት ለዚህም አላማ ያለባለቤቱ ፍቃድ ኮምፕዩተሩን ማግኘት የሚመለከት ነው፡፡

የሳይበር ጥቃት መከላከል በአለምአቀፍ ደረጃ
የሳይበር ጥቃት የኮምፒውተር ሥርአት ወይም ኔትዎረክን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማግኘት ሲሆን አላማውም ጉዳት ማድረስ ነው፡፡ የሚያደርሰውም ጉዳት ብልሽት፣ ማዛባት፣ ማስወገድ ወይም የኮምፒውተሩን ሥርአት በመለወጥ ማጥፋት፣ በሥርአት ውስጥ ያለ መረጃን ማዛባት ወይም መስረቅን ይጨምራል፡፡ ይህ ጥቃት የማጥቃት እስትራቴጂ ባለው በማንኛውም ሰው ወይም ቡድን ከየትኛውም ቦታ ሊሰነዘር ይችላል፡፡ ጥቃቱን የሚፈፅሙ ሰዎች የሳይበር ወንጀለኞች ወይም በተለምዶ ሀከሮች ተብለው ይታወቃሉ፡፡

የሳይበር ጥቃት አለማቀፍ ወንጀል መሆኑን መግባባት ያለ ቢሆንም ይህንኑ ድርጊት የሚያወግዝ ወጥ የሆነ አለማቀፍ ህግ ግን እስካሁን የለም፡፡ ይሁንና በጉዳዩ ላይ አህጉራዊ ስምምነቶች ያሉ ሲሆን ለአብነት ያክል በአፍሪካ ደረጃ በ2008 የወጣው የአፍሪካ ህብረት የሳይበር ደህንነት እና ግላዊ ዳታ ለመጠበቅ የወጣውን ስምምነት (African Union Convention on Cyber Security and Personal Data Protection) መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአውሮፓ ህብረት ደረጃ የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል እ.አ.አ በ2001 በሀንጋሪ የወጣው ስምምነት Convention on Cybercrime (በተለምዶ የቡዳፔስት ስምምነት እየተባለ የሚጠቀሰው) ተጠቃሽ ስምምንት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ሀገራት በግዛታቸው የሚፈፀሙ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል ህግ በማውጣት ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

የሳይበር ክልልን መቆጣጠር እና ማስተዳደር ከመንግስት ተቋማት በተጨማሪ የሌሎች አካላትን ተሳትፎ ይፈልጋል፡፡ ይኸውም ለኢንተርኔት መፈጠር እና መስፋፋት መሪ ሚና የተጫወቱ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማለትም እንደ ጉግል፣ ፌስቡክ፣ የኢንተርኔት እስታንዳርድ እና ፕሮቶኮል አዘጋጆች፣ ሲቪል ማህበራት እና የመሳሰሉት የዘርፉ ቁልፍ ተዋናይ አካላት ዘርፉን በማስተዳደር እና የሳይበር ጥቃትን ከመከላከል አኳያ ከመንግስታት በተጨማሪነት ጉልህ ሚና አላቸው፡፡

የኮምፒዩተር ወንጀል በኢትዮጵያ

መረጃ የማግኘት እና የማሰራጨት መብት በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ስር ጥበቃ የሚደረግለት መብት ቢሆንም የሀገር ደህንነት እና የህዝብን ሰላም እና ጤና ለመጠበቅ ሲባል በህግ ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል ከህገመንግስቱ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል። በዚሁ መሰረት በአገራችን የህግ ሥርአት በኮምፒዩተር ሥርአት አማካይነት የሚፈፀሙ ህገወጥ የመረጃ ተደራሽነት፣ ማዛባት፣ ጠለፋ እና ማጥፋት ተግባራት የተከለከሉ እና በወንጀልነት የተፈረጁ የሚያስቀጡ ድርጊቶች ጭምር ናቸው፡፡

የሳይበር ጥቃት የሀገራትን ሉአላዊነት የሚጥስ እና ከአንድ የአለማችን ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ በቀላሉ የሚፈፀም እና የአለምን ሰላምና ደህንነት የሚነሳ አደገኛ አለማቀፍ ወንጀል ነው፡፡ ይህ የሳይበር ጥቃት በህጋችን የኮምፒዩተር ወንጀል ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተደነገገውም በ1996 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ህግ ከአንቀጽ 706 እስከ 711 ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ ድንጋጌዎች ብቻቸውን በየግዜው እየተወሳሰበ የመጣውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የወንጀል ተጋላጭነት በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር ባለመቻሉ በአዲስ መልክ እራሱን ችሎ በአዋጅ እንዲሸፈን ለማድረግ በማሰብ በኮምፒዩተር ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 958/2008 በዝርዝር ተደንግጎ ወጥቷል፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው ይሄው ህግ ሲሆን ቀጥለን ዋና ዋና የወንጀሉን ድንጋጌዎች ባጭሩ የምንቃኝ ይሆናል፡፡

• ህገወጥ ደራሽነት (አንቀጽ 3) ይኸውም ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ሥርዓት፣ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ኔትዎርክ ደራሽነት በከፊልም ሆነ በሙሉ ማግኘት ነው፡፡
• ህገወጥ ጠለፋ (አንቀጽ 4)- ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ ይፋዊ ያልሆነን የኮምፒዩተር ዳታ ወይም የዳታ ፕሮሰሲንግ አገልግሎት መጥለፍ ነው፡፡

• በኮምፒዩተር ሥርዓት ላይ ጣልቃ መግባት (አንቀጽ-5) -ያለ ፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ዳታን በማስገባት፣ በማሰራጨት፣ በማጥፋት ወይም በመለወጥ የኮምፒዩተር ሥርዓትን ወይም ኔትወርክን መደበኛ ተግባር በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ማደናቀፍ፣ ማወከ፣ ማውደም ወይም እንዲቋረጥ ማድረግ ነው፡፡

• በኮምፒዩተር ዳታ ላይ ጉዳት ማድረስ (አንቀት 6)- ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ዳታን መለወጥ፣ ማጥፋት፣ ማፈን፣ ትርጉም እንዳይኖረው ወይም ጥቅም እንዳይሰጥ ወይም ለሕጋዊ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው፡፡

• ከኮምፒዩተር መሣሪያና ዳታ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ወንጀሎች (አንቀጽ 7)- በኮምፒዩተር ሥርዓት በኮምፒዩተር ዳታ ወይም በኔትዎርክ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ እየታወቀ ለዚህ ዓላማ ተብለው የተመረቱ ወይም የተሻሻሉ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞችን ሆነ ብሎ በኮምፒዩተር ሥርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ነው፡፡

• የኮምፒዩተር ዳታን ወደ ሐሰት መለወጥ (አንቀጽ 9)- የሌላን ሰው ጥቅም ለመጉዳት ወይም ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ያልተገባ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ሕጋዊ ውጤት ያለውን ወይም ሊኖረው የሚችለውን የኮምፒዩተር ዳታ ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም ሐሰተኛ የኮምፒዩተር ዳታ ማዘጋጀት ወይም በዚሁ መገልገል ነው፡፡

• በኮምፒዩተር አማካኝነት የሚፈፀም የማታለል ወንጀል (አንቀጽ 10)- አሳሳች የኮምፒዩተር ዳታዎችን በማሰራጨት፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት በመጠቀም፣ ሌላውን ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን ማንኛውም ጥቅም የሚጎዳ ድርጊት እንዲፈፅም ማድረግ ነው፡፡
Forwarded from Law forum (marye kasse)
• የኤሌክትሮኒክ ማንነት ስርቆት (አንቀጽ 11)- የማታለል ወንጀል ለመፈፀም ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት የሌላን ሰው የኤሌክትሮኒክ ማንነት የሚያረጋግጥ ዳታ ያለባለቤቱ ፈቃድ በኮምፒዩተር ሥርዓት አማካኝነት ማምረት፣ ማግኘት፣ መሸጥ፣ ይዞ መገኘት ወይም ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡
እነዚህን የወንጀል ድርጊቶች መፈፀም በህጉ ለየወንጀል አይነቶቹ የተደነገገውን በመደበኛ አፈፃፀም እስከ 5 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና በገንዘብ ቅጣት የሚያስቀጣ ሲሆን በከባድ ሁኔታ የተፈፀመ ሲሆን ማለትም ወንጀሎቹ የተፈፀሙት ፡-
• ለወታደራዊ ጥቅም ወይም ለዓለም አቀፍ ግንኙነት ሲባል በሚመለከተው አካል ጥብቅ ምስጢር ተብሎ በተሰየመ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ዳታው በሚገኝበት የኮምፒዩተር ሥርዓት ወይም ኔትዎርክ ላይ ከሆነ ወይም
• አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ወይም ሀገሪቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ በምትገኝበት ወቅት ከሆነ
• በቁልፍ መሠረተ ልማት ላይ ከሆነ
• በሕግ የሰውነት መብት ለተሰጠው ተቋም አገልግሎት ብቻ በሚውል የኮምፒዩተር ሥርዓት ላይ ከሆነ እና
በመሰል ሁኔታዎች በመፈፀሙ ወንጀሉ ከባድ በሆነበት ጊዜ ቅጣቱ እንደ ወንጀል አይነቶቹ ከብዶ እንዳደረስው ጉዳት እና አፈፃፀሙ እየታየ እስከ 25 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሚደርስ መቀጮ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡

ማጠቃለያ
በጥቅሉ የኮምፒዩተር ወንጀል በአገር ሰላም እና ደህንነት ብሎም ምጣኔ ሀብታዊ እና ማህበራዊ አድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ወንጀል ስለሆነ ሁሉም ሰው ይሄን አውቆ ከዚህ ወንጀል እራሱን ማራቅ እና ተፈፅሞም ሲገኝ ከህግ አካላት ጋር በመተባበር ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀርቡ እና ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (fasika aggena)
የቦሌ ክ/ከተማ የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ፣ ምርመራ፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና የተጠያቂነት ስርአትን ለመዘርጋት በወጣው ደንብ ቁጥር 143/2015 ዙሪያ በቀን 20/09/2016 ዐ.ም ስልጠና ሰጠ!!! በመድረኩም ከተለያዩ የሲቪክ ማህበራት፣ ማለትም፣ ከሴቶች፣ ከአካል ጉዳተኞች፣ ከወጣቶችና ከአረጋውያን አደረጃጀቶች፣ የተወጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የደንቡን አላማና አስፈላጊነት፣ የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ፣ ምርመራ፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና የተጠያቂነት ስርአትን እንዲሁም በደንቡ የተቋቋመውን የስራ ክፍል አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ተሳታፊዎችም ስልጠናው ጠቃሚ መሆኑ ገልጸው በቀጣይ መሰል ስልጠናዎች በስፋት እንዲሰጡ ሃሳብ ሰጥተዋል። እነሆ ከመድረኩ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎች!!!!