የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንደ አስገዳጅ ህግ እንደሚቆጠር ግልፅ ነው። ነገር ግን በቅድሚያ የሚደረገው የውል ስምምነት ከህግና ከሞራል የሚፃረር መሆን የለበትም። በዚሁ መሰረት ከውል ጋር በተያያዘ ተዋዋይ የሆነ ወገን ውሉን የፈፀምኩት ተገድጄና ከፍላጐቴ ውጭ ነው በሚል የሚያደርገውን ክርክር ዳኞች (ፍ/ቤቶች) የዚህን ተዋዋይ ወገን እድሜ፣ ጾታ፣ የተዋዋይ ወገኖችን ልዩ ግንኙነት እና አጠቃላይ ተያያዥነት ያላቸው አኳኋኖች ጭምር መሰረት በማድረግ መወሰን ያለባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1706/1/,1678/ሀ/,1809 ድንጋጌዎች መሠረት በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 12 ላይ አስገዳጅ ወሳኔ ሰጥቶበታል።
https://t.me/ethiolawtips
❤1
የሞት ፍርድ በኢትዮጵያ እንዴት ይፈጸማል? ምን ያህልስ ተቀባይነት አለው?
***
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሞት ቅጣት እየጨመረ መሆኑን ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ እአአ በ2023 ብቻ 1153 የሞት ቅጣት መመዝገቡን አስታውቋል።
ይህ አሃዝ በ2022 ከነበረው 883 የሞት ፍርድ አንጻር የ31 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተገለጸው። አምነስቲ በ2015 ብቻ 1634 ከመዘገበ በኋላ 2023 ከፍተኛው የሞት ቅጣት የተላለፈበት ዓመት ሆኗል።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት በኢትዮጵያ ያለውን የሞት ቅጣት ቁጥር በይፋ አላስቀመጠም። ሆኖም አለፍ ገደም እያለ በአገሪቱ በተለያዩ ወቅቶች የሞት ቅጣት መተላለፉ ተዘግቧል።
በኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ በምትገኘው ሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከወራት በፊት ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው የእንጀራ እናት ሞት ተፈረዶባታል። ጥፋተኛ ሆና በተገኘችው ግለሰብ ላይ ውሳኔውን ያስተላለፈው የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትነው- ቢቢሲ።
ከሰሞኑ ከአባቱ ጋር በተፈጠረ የጥቅም ግጭት በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ አባቱን፣ እናቱን፣ አጎቱ እና የ9 ዓመት ታናሽ ወንድሙን የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል። ውሳኔውን ያሳለፈው የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው - ፋና።
በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ደከ ኦዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እናቱን በቢላዋ በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ውሳኔውን ያሳፈው የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው- ፋና።
በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሕግ ክፍል መምህር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር መሐሪ ረዳኢ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሞት ቅጣት የሚጣልባቸው ጉዳዮች “በጣም ውስን” መሆናቸውን ይገልጻሉ።
ጭካኔ እና ነውረኝነት በተሞላበት መንገድ ሆን ተብሎ የሚደረግ ግድያ እና ከአገር ክህደት ጋር በተያያዙ የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ የሞት ቅጣቱ እንደሚወሰን ሕጉን ጠቅሰው ለቢቢሲ አስረድተዋል።
“በተቻለ መጠን አጥብቦ ነው [የሞት ፍርድ ቅጣት] ሕጉ የሚተቀረጸው” የሚሉት የሕግ መምህሩ፣ በዚህ ምክንያትም ተፈጸማኒቱ አነስተኛ ነው።
ሕጉ አጥብቦ ከመቀረጹም በላይ ዳኞችም የሞት ቅጣት ሲያስተላልፉ ተከሳሽ የፍርድ ማቅለያ ምክንያቶችን ማቅረብ በማይችልበት ሁኔታ ነው። የወንጀለኛው ዕድሜም ከ18 ዓመት በላይ መሆን ይጠበቅበታል። “ከዚያ በታች ወንጀል በሚፈጸሙ ላይ [ቅጣቱ] አይጣልም።”
ብዙ ጊዜ የሞት ፍርድ ተላለፈ ተብሎ በመገናኛ ብዙኃን ይነገራል። ጉዳዩ እዚህ ጋር ያበቃ፤ የሞት ፍርዱ የሚፈጸም ቢመስልም ተጨማሪ ሂደቶች ይኖራሉ። ተከሳሽ ይግባኝ በማለት የተለየ ፍርድ ሊያገኝ ይችላል።
ይግባኙ ተቀባይነት አጥቶ ፍርድ ቤቱ የሞት ቅጣቱን ካጸና በኋላም በቀጥታ ወደ ማስፈጸም አይገባም። የሞት ቅጣቱ እንዲፈጸም በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር መጽደቅ ይኖርበታል።
በቁጥር ብዙ ባይሆኑም በዚህ ሂደት ውስጥ አልፈው የሞት ቅጣት ተፈጻሚ የሆኑባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸውን ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ያስታውሳሉ።

ሆኖም ባለፉት 25 እና 30 ዓመታት ውስጥ የሚታወቁ የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው ጥቂት መሆናቸውን አንስተዋል። በቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ የመግደል ሙከራ አድርገው በተያዙት ከሱዳን የመጡ ናቸው በተባሉ አሸባሪዎች ላይ የሞት ቅጣት እንደተፈረደባቸው አስታውሰዋል።
“ጄኔራል ሃየሎም አርአያን የገደለው ሰው የሞት ፍርድ ተፈርዶበት እንደተፈጸመበት አስታውሳለሁ። በተመሳሳይም ክንፈ ገብረመድኅንን [የቀድሞው የደኅንነት ኃላፊ ነበሩትን] የገደለው ሰው የሞት ፈርድ ተወስኖበነት እንደተፈጸመበት፣ የአልሻባብ ታጣቂዎችም ይመስለኛል ድሬዳዋ ወይም ጅግጅጋ በፈጸሙት ጥቃት ተይዘው እንደተፈጸመባቸው አስታውሳለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
በሞት ቅጣቱ ላይ ርዕሰ ብሔሮች ውሳኔ እንዲሰጡበት መደረጉ “የፖለቲካ ጉዳይ ነው” ይላሉ ተባባሪ ፕሮፌሰር መሐሪ።
የሰው ሕይወት ጉዳይ ስለሆነ “ድንጋጌዎችን ብቻ አይቶ ከተወሰነ እና ከተፈጸመ ከባድ ሊሆን ይችላል። . . . ለፍርድ ቤት ብቻ ሊተው አይገባም። ርዕሰ ብሔር የአገር ተወካይ ስለሆኑ እዚያ ድረስ ጸድቆ ነው መወሰን ያለበት ከሚል የመነጨ ይመስለኛል” ብለዋል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ርዕሰ ብሔሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጋቸው የራሱ የሆነ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል። በሞት ቅጣት አላምንም የሚል ርዕሰ ብሔር ከመጣ የሞት ቅጣት የተላለፈበት ግለሰብ ውሳኔው ተግባራዊ ሳይደረግበት ሊቀመጥ የሚችልበት ዕድል ይፈጠራል።
“ርዕሰ ብሔሮች በማጽደቁ ላይ እግር የመጎተት ነገር ስላለ አፈጻጸሙ አነስተኛ ነው” የሚሉት የሕግ ምሑሩ፣ “ለምሳሌ ፕሬዝዳንት ግርማ በነበሩበት ጊዜ የራሳቸው ፍልስፍና ስለነበራቸው ብዙም ሲያጸድቁ አልታየም። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅም ያጸደቁበትን [ጊዜ] አላስታወስም። ስለዚህ የፍርድ ቤት ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የርዕሰ ብሔር ውሳኔም ስላለበት . . . ቅጣቱ እየተፈጸመ አይመስለኝም።”
ፍርድ ቤት አንድ ተከሳሽ ሞት ይገባዋል ብሎ ወስኖ ይህን ውሳኔ ሲያሳልፍ ፍርዱን እንዲያጸድቅ ኃላፊነት የተሰጠው አካል [ርዕሰ ብሔር] በተለያየ ምክንያት አላጸድቅም ካለ ፍርደኛው የተጣለበት ቅጣት ተግባራዊ ሳይሆን እንዲቆይ ምክንያት ይሆናል።
“ሥርዓቱ እርስ በርስ የሚጠባበቅበት መንገድ አበጅቷል ተብሎ ነው የሚወሰደው። የሞት ቅጣት ያስፈልጋል የሚል ርዕሰ ብሔር ካለ ከፍርድ ቤት የሚመጣለትን እያጸደቀ እርምጃ ሊያስወስድ ይችላል። ተገቢ አይደለም የሚል ሲመጣ ደግሞ በተቀራኒው መሆኑ አይቀርም” ብለዋል።
ርዕሰ ብሔሩ የሞት ፍርዱ እንዲተገበር በፊርማቸው ካላረጋገጡ ወንጀለኛው ፍርደኛ ሆኖ ይቀመጣል። አንድ ሰው የተፈረደበትን የእስር ጊዜ 2/3ኛውን በማረሚያ ቤት ካሳለፈ በኋላ በሚያሳየው የባህሪ መሻሻል አመክሮ እንዲያገኝ የሚያስችለው የሕግ አግባብ አለ። ባህሪው ለውጥ ከሌለው ግን ሙሉውን የእስራት ጊዜ በማረሚያ ቤት እንዲያሳልፍ ይገደዳል።
ይህ ግን የሞት ቅጣት ለተላለፈበት ሰው አይተገበርም። ፍርደኛው በሞት እንዲቀጣ ርዕሰ ብሔሩ ባይፈርሙ እንኳ ቀሪውን ሕይወቱን በእስር አሳልፎ “አስከሬኑ ከማረሚያ ቤት ይወጣል ማለት ነው።” #BBC Amharic
👍2
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ ስም የነበረን የግል ንብረት በጋብቻ ወቅት በንብረቱ ላይ መሰረታዊ መሻሻል ቢደረግበትና ይሄው መሻሻል የተደረገው የባለንብረቱ የግል ገንዘብ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ህጉ ንብረቱ የተጋቢዎች የጋራ ነው የሚል
ግምት የሚወስድ ስለመሆኑ፣ ሰበር ቅፅ (17) መዝገብ ቁጥር 94952
Forwarded from አለ ሕግ
በአከራይ ተከራይ መመሪያ 7/2016 ዙሪያ አንቀፅ 22 ስለአስተዳደራዊ እርምጃ እና ቅጣት ለግንዛቤ የተወሰደ

አስተዳደራዊ ቅጣት 👇

ማንኛውም አከራይ ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ የመኖሪያ ቤት ያለ አገልግሎት እንዲቀመጥ ያደረገ እንደሆነ:-

ሀ/ ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት 5%፤
ለ/ከሁለት በላይ እስከ ሶስት ዓመት 10%፤
ሐ/ከሶስት በላይ እስከ አራት ዓመት 15%፤
መ/ከአራት እስከ አምስት ዓመት 20%፤
ሠ/ ከአምስት አመት በላይ 25%፤

በንብረት ግብር ክፍያ ላይ ተጨማሪ እንደ ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
በከተማችን አዲስ አበባ ከአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ጋር በተያያዘ ለሚገጥሞት ማንኛውም ችግር ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ያውቁ ኖሯል?

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም አከራይ ከመጋቢት 24/2016 ዓ.ም ጀምሮ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘ የቤት ኪራይ ጭማሪ አልያም ቤቱን ይልቀቁልኝ የሚል ግፊት ከደረሰብዎ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ጥቆማ መስጠት እና መብትዎን ማስከበር ይችላሉ።

የጥቆማ ስልክ ቁጥሮች 👇👇👇

+251118722917

+251118553820
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
የውል ይርጋ
---------------
1)የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810(2) ላይ የተመለከተው የይርጋ ገደብ ተፈፃሚ የሚሆነው ውል በፈቃድ ጉድለት ወይም በችሎታ ማጣት የተነሳ እንዲፈርስ ጥያቄ የቀረበ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህቁ 1810 የሰ/መ/ቁ 48012 ቅፅ 12
2)በውል ግንኑነት ውስጥ የራስን ግዴታ ሳይወጡ ሌላው ወገን ግዴታውን አልተወጣም በሚል የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1757 በሰ/መ/ቁ 39568 በቅፅ 12
3)የማይንቀሳቀስ ንብረት ሻጭ በዉሉ መሠረት የመፈፀም ፍላጎት የሌለው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ለገዢ ያላሳወቀ እንደሆነ ገዥ ውሉ እንዲፈፀምለት የመጠየቅ መብቱ በ10  ዓመት ይርጋ የሚታገድበት ስለመሆኑ 1845;1789:1731:1732 የሰ/መ/ቁ 38935 ቅፅ 12
4)የፍትሐብሄር ጉዳዮች የ ይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1846 የሰ/መ/ቁ 36756 ቅፅ 12
5)የፀና የውል ግዴታ የገባ ሰው ውሉ በፍርድ እንዲሰረዝ ለመጠየቅ የሚችለው ሌላኛው ተዋዋይ ወገን ግዴታውን በአግባቡ ያልፈፀመ(ያልተወጣ) እንደሆነ ወይም የፈፀመው ፍፁም ባልሆነ አኳኃን ከሆነ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1784;1785(2).(1)"የሰ/መ/ቁ 66935 ቅፅ 13 ላይ ሰፍሯል።
https://t.me/ethiolawtips
👍1
የቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ሰኔ 12 ቀን 2016 ዐ.ም በፌደራሉ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ዙሪያ የአደባባይ ግንዛቤ ፈጠራ ስራ ሰራ!!! በዝግጅቱም ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ምንነት፣ ዘመን፣ መታደስ፣ መቋረጥ እንዲሁም በአዋጁ ስለሚቋቋሙ ተቋማት ስልጣንና ሃላፊነት ግንዛቤ ተፈጥሯል። እነሆ ከዝግጅቱ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎች!!!!!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
በስርአተ_ትምህርት_ጥሰትና_ስታንዳርድ_ባለማሟላት_የተዘጉ_ተቋማት_ዝርዝር.pdf
901.1 KB
#AddisAbaba : በስርዓተ ትምህርት ጥሰት እና ስታንዳርድ ባለለመሟላት የተዘጉ ትምህርት ቤቶች ዝርዝር።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን አይቀጥሉም የተባሉ ናቸው።

ፍኖተ ሎዛን በተመለከተ ግን ይህን ያንብቡ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88408?single

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
በራሳቸው የዘጉ ተቋማት ዝርዝር.pdf
1015.4 KB
#AddisAbaba

በራሳቸው የዘጉ ትምህርት ቤቶች ዝርዝርን ይመለከቱ።

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የቅድመ_አንደኛ_ተቋማት.pdf
10.8 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የአንደኛና_መካከለኛ_ደረጃ.pdf
6.1 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የአንደኛ እና መካከለኛ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የአጠቃላይ_2ኛ_ደረጃ.pdf
1.8 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
Forwarded from ስለ-ሕግ ⚖ 𝐀𝐁𝐎𝐔𝐓-𝐋𝐀𝐖 (Ashenafi F. Sendeku)
የሰበር መ/ቁ 227978
ሕዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም

የፋይናንስ ተቋማት ለሰጡት ብድር አከፋፈል በመያዣነት የያዙት ተሽከርካሪ የጦር መሣሪያ ጭኖ በመገኘቱ የተነሳ በጉምሩክ ኮሚሽን ሲወረስ የተሽከርካሪው ባለቤት (ተበዳሪው) የውርስ ውሳኔውን ሕጋዊነት በመቃወም ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ጣልቃ በመግባት የክርክሩ ተካፋይ መሆን ይችላሉ ወይስ አይችሉም?

የፋይናንስ ተቋማት ለሰጡት ብድር በመያዣነት የያዟቸው ተሽከርካሪዎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ለማዘዋወር ድርጊት መፈጸሚያነት ውለው ሲገኙ በጉምሩክ ኮሚሽን አስተዳደራዊ ውሳኔ ውርስ የሚደረጉ ሲሆን የፋይናንስ ተቋማቱም የውርስ ውሳኔው በተሽከርካሪዎቹ ላይ ያላቸውን የቀደምትነት መብት ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው የሚል ክርክር ያቀርባሉ።

በጉምሩክ አዋጅ ቁ. 859/06 አንቀጽ 153 መሠረት የጉምሩክ ጉዳዮች አቤቱታ አጣሪ የሥራ ክፍል የውርስ ውሳኔውን በማጽናት በሰጠው ውሳኔ ላይ የተሽከርካሪው ባለቤት ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው ይግባኝ ላይ አበዳሪው ባንክ በታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ የአሰራር መመሪያ ቁ. 02/11 አንቀጽ 16(1)(ሀ) መሠረት የጣልቃ ገብ አቤቱታ በማቅረብ የክርክሩ ተካፋይ መሆን ይችላል? ወይስ ጉዳዩ በቀጥታ ለመደበኛ ፍ/ቤቶች የሚቀርብ ነው? በሚለው ጉዳይ ላይ ግልጽነት ባለመኖሩ ለክርክር በር ሲከፍት ቆይቷል።

የታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ የፋይናንስ ተቋማቱ የሚያቀርቡትን የጣልቃ ገብ አቤቱታ ተቀብሎ የማየት ሥልጣን በሕግ ያልተሰጠው መሆኑን በመጥቀስ አቤቱታውን ውድቅ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ጉዳዩን በይግባኝ የሚመለከቱ መደበኛ ፍ/ቤቶች ደግሞ የጉምሩክ ጥፋት መፈጸሙን ተከትሎ የሚጣሉ አስተዳደራዊ ቅጣቶችንና የውርስ ውሳኔዎችን ሕጋዊነት በመቃወም የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ የማየትና መርምሮ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የመስጠት የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ ነገር ሥልጣን ለጉምሩክ ኮሚሽን አቤቱታ አጣሪ የሥራ ክፍሎች የተሰጠ በመሆኑና በጉምሩክ አዋጁ የተዘረጋው የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት በጉዳዩ ላይ ያገባናል የሚሉ ሦስተኛ ወገኖች ወደ ክርክሩ በመግባት መብትና ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚችሉበትን አሠራር ያልዘረጋ በመሆኑ ተበዳሪው (የተሽከርካሪው ባለቤት) ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ የፋይናንስ ተቋሙ የክርክሩ ተካፋይ ሊሆን ይገባል የሚል አቋም ያንጸባርቃሉ።

ይህንን በሚመለከት የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 227978 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። ሰ/ሰ/ችሎቱ
- በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚካሄዱ ክርክሮች የሚያከራክረው ጉዳይ ተሽከርካሪው የጦር መሣሪያ ጭኗል? አልጫነም..ሊወረስ ይገባል? አይገባም የሚል ክርክር በመሆኑና የፋይናንስ ተቋማቱም የቀዳሚነት መብት ያላቸው ስለመሆኑ ከማንሳት በስተቀር ተሽከርካሪው የጦር መሣሪያ ጭኗል ወይስ አልጫነም በሚለው የክርክር ፍሬ ጉዳይ ላይ የሚያቀርቡት ክርክር አለመኖሩን፤ በመሆኑም ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ፍሬ ጉዳይ ላይ መብት ወይም ጥቅም የሌላቸው መሆኑን...

- የቀዳሚ መብት ጥያቄ የሚነሳው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3059(1) መሠረት በመያዣ የተያዘው ንብረት በሌሎች ገንዘብ ጠያቂዎች ተይዞ ንብረቱ በሀራጅ ከተሸጠ በኋላ የተገኘው ገንዘብ የሁሉንም ዕዳ መሸፈን በማይችል ጊዜ መሆኑንና የቅድሚያ መብት አቤቱታ በዚህ ደረጃ የሚነሳ አለመሆኑን፤ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ክርክሩ እንዲገቡ በሚል በሥር ፍ/ቤቶች የሚሰጥ ውሳኔ በባንኩና በተበዳሪው መካከል ያለውን የብድር/መያዣ ውል መሰረት ያደረገ አለመሆኑን በማንሳት ....ባንኩ የብድር ውሉን መሠረት በማድረግ የሚያቀርበውን የመብት ጥያቄ ግን በመጠበቅ ውሳኔ ሰጥቷል።

በመሆኑም የፋይናንስ ተቋማት በመያዣነት የያዙት ተሽከርካሪ የውርስ ውሳኔ ሲተላለፍበት የመያዣ ውሉን መሠረት አድርገው በመደበኛ ፍ/ቤቶች ክስ ከሚመሰርቱ በስተቀር የውርስ ውሳኔውን ሕጋዊነት ብቻ በሚመለከተው በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በተሽከርካሪው ባለቤትና በጉምሩክ ኮሚሽን መካከል በሚካሄድ ክርክር ጣልቃ ገብተው ለመከራከር አይችሉም።


Tsegazeab Zerihun Gebeyehu, an Attorney for FDRE Customs Commission.

JOIN ስለ-ህግ ABOUT-LAW
Telegram- https://telegram.me/ethiolawblog
Facebook- https://m.facebook.com/aboutlawlegalservice
LinkedIn- https://www.linkedin.com/company/aboutethiopian-law
👍1
የቤት ሠራተኞች ሕጋዊ የሰነድ ውል እንዲኖራቸው የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሊዘጋጅ ነው
***
የአገር ውስጥ የቤት ሠራተኞች ከአሠሪዎቻቸው ጋር ሕጋዊ የሰነድ ውል እንዲኖራቸው ጥናት በማድረግ፣ የሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው ለዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመ ክርስቲያናዊ ድርጅት የቤት ሠራተኞች የሥራ ላይ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታን አስመልክቶ፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ የሥራ ሁኔታቸውን በሕግ የሚደነግግ ደንብ እስኪወጣ ድረስ፣ በመንግሥት ደረጃ ተቀባይነት ያለው የሥራ ቅጥር ውል ለመንደፍ የሚያስችል ውይይት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲያካሂድ ነው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የሦስትዮሽ ግንኙነት ማስተግበሪያ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳልክ ተክለ ሃዋሪያት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የቤት ሠራተኞች ከአሠሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ጤናማ እንዲሆንና መብቶቻቸው እንዲጠበቁ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡
የቤት ሠራተኞች መብቶቻቸውንና ግዴታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲለዩ እንዲህ ዓይነት አሠራር መከተል አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት ገልጸው፣ ማናቸውም የቤት ሠራተኞች ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ አገር የሥራ ሥምሪት በበቂ ሁኔታ እንዲሠለጥኑ ሚኒስቴሩ የተሻለ አሠራርን ዘርግቶ ወደ ሥራ መግባቱን አክለዋል፡፡
በቅርቡም ጥናት ተደርጎበት ወደ ሥራ የሚገባበት ይህ አሠራር ለውጭ አገር የሥራ ሥምሪት መነሻነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የገለጹት ኃላፊው፣ ጥናቱንም ከዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመ ክርስቲያናዊ ድርጅትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የሚሠራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
ለዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመው ክርስቲያናዊ ድርጅት ሠራተኞች በተለያዩ ክልሎች ላይ የሠሩትን ጥናት እንደ መነሻነት በመጠቀም፣ የቤት ሠራተኞችና አሠሪዎች መብትና ግዴታቸው ምንድነው የሚለውን ጉዳይ ከተጠቃሚዎቹ በማወቅ የሕግ ማዕቀፍ የሚዘጋጅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት በተመለከተ ማንኛውም ዜጋ ወደ ውጭ ሥራውን ከጀመረበት ጀምሮ አገልግሎት እስከሚያገኝበት ድረስ፣ የራሱ የሆነ አሠራር እንዳለውና መመርያም ጭምር እንደተዘጋጀለት ጠቁመዋል፡፡
የቤት ሠራተኞች የሥራ ሁኔታቸው በሕግ ጥበቃ ባለመደረጉ እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰትና ልዩ ልዩ አካላዊ እንዲሁም ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማስቀረት በአሠሪና በሠራተኛ አዋጅ የተቀመጠውን ደንብ እንዲወጣ መንግሥትን እየወተወተ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡
በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ደንብ እስኪወጣ የሠራተኞቹን መብትና ግዴታ፣ እንዲሁም የአሠሪዎቹን ኃላፊነት የሚያሳይ የሥራ ውል ተነድፎ ሥራ ላይ እንዲውል መደረግ እንዳለበት ኢሠማኮ ያምናል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት እንዲቻል ደንብና መመርያዎች እንዲወጡ በአዋጁ ቢደነገግም፣ በተፈለገው መጠን ተሠርቶ ባለመታየቱ እንደ ማንኛውም ሠራተኛ በጋራ በመሆን የጋራ ችግሮቻቸውን የሚመክሩበት፣ የመደራጀት መብት እንዲኖራቸው ያልተቋረጠ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አብራርተዋል፡፡
የቤት ውስጥ ሠራተኞች በአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ ተካተው ተገቢውንና ወጥ የሆነ አደረጃጀት እንዲኖራቸው ለማስቻል፣ የዓለም ሥራ ድርጅት ድንጋጌ ቁጥር 189 የኢትዮጵያ የሕግ አካል እንዲሆን ሁሉም ለባለድርሻ አካል የግሉን ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
ኮንቬሽኑን ኢትዮጵያ እንድታፀድቅና የሕጎቿ አካል እንዲሆን ለማስቻል በሕጉ ላይ በቂ ዕውቀት ባላቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች አካላት በሚገኙ ባለሙያዎችን ጭምር በመጠቀም የሕግ አካላት፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የሠራተኞችና የአሠሪዎች አደረጃጀቶች፣ የፌዴራልና የክልል አስፈጻሚ አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የጋራ ውይይቶች አድርገው የተጎዱና የተረሱ ወገኖች ሰብዓዊና የሥራ ላይ መብቶቻቸው መጠበቅ እንዳለበት በማመን የጋራ ስምምነት ተደርሷል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
👍2
Forwarded from abyssinialaw.com⚡️ (Attorney Liku Worku)
የማታለል ወንጀል ከእምንት ማጉደል ወንጀል በምን ይለያል? በድንጋጌዎቹ የወንጀል ክስ ለማቅረብ በመሠረታዊነት መሟላት ያለባቸው የማስረጃ ዓይነቶችስ ምንድናቸው?

በ፡-ሲሳይ ጎኣ

ይህ ጽሑፍ ከማታለልና ከእምነት ማጉደል ጋር በተያያዙ እየተነሱ ያሉ ችግሮችን በወፍ በረር ቅኝት ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡ በጽሑፉም የሚከተሉትን ዋና ጉዳዮች ያገኛሉ፡፡

- በንብረት ላይ የሚፈፀም ወንጀል በጠቅላላው
- አታላይነት
- እምነት ማጉደል
- እምነት ማጉደል ከማታለል የሚለይበት መሰረታዊ ነገር
- የእምነት ማጉደል ወንጀል በመሰረታዊነት ለማቋቋም በወንጀል
ህጉ አንቀፅ 675 ላይ የተመለከተው መስፈርት
- አንቀፁን ከመተግበር አንፃር በተግባር የሚያጋጥሙ ችግሮች

ጽሑፉን በማንበብና ለሌሎች በማካፈል የኢትዮጵያ የሕግ አቋምን ይደግፉ!

https://www.abyssinialaw.com/blog/yematale-wenije-ke-i-niti-magude-wenije-be-ni-yileya-bedinigagewocu-yewenije-kisi-lemaqirebi-bemeseretawi-ti-memwalati-yalebace-yemasireja-eyi-tocisi-nidinace-1
👍1
#ተራዘሟል

በአዲስ አበባ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ  እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ።

ምዝገባው ሰኔ 30 ያበቃል መባሉ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል ምዝገባ ተከናውኗል።

አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ ይገኛል ብሏል።

ነገር ግን ፦
- በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ
- ቀሪ ያልተመዘገበው የተከራይ አከራይ ውል እስከ ሰኔ 30/2016 መዝግቦ ለማጠናቀቅ አዳጋች ስለሚሆን
- ቀኑ እንዲራዘምም ከህብረተሰብ በቀረበ ጥያቄ  የምዝገባ ጊዜው እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ/ም መራዘሙን ቢሮው ገልጿል።

ነዋሪዎች ጊዜው ተራዘመ ብለው ሳይዘናጉ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ፣ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ሳይጨናነቁ ምዝገባ እንዲያካሂዱ ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministration