የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ ስም የነበረን የግል ንብረት በጋብቻ ወቅት በንብረቱ ላይ መሰረታዊ መሻሻል ቢደረግበትና ይሄው መሻሻል የተደረገው የባለንብረቱ የግል ገንዘብ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ህጉ ንብረቱ የተጋቢዎች የጋራ ነው የሚል
ግምት የሚወስድ ስለመሆኑ፣ ሰበር ቅፅ (17) መዝገብ ቁጥር 94952
Forwarded from አለ ሕግ
በአከራይ ተከራይ መመሪያ 7/2016 ዙሪያ አንቀፅ 22 ስለአስተዳደራዊ እርምጃ እና ቅጣት ለግንዛቤ የተወሰደ

አስተዳደራዊ ቅጣት 👇

ማንኛውም አከራይ ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ የመኖሪያ ቤት ያለ አገልግሎት እንዲቀመጥ ያደረገ እንደሆነ:-

ሀ/ ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት 5%፤
ለ/ከሁለት በላይ እስከ ሶስት ዓመት 10%፤
ሐ/ከሶስት በላይ እስከ አራት ዓመት 15%፤
መ/ከአራት እስከ አምስት ዓመት 20%፤
ሠ/ ከአምስት አመት በላይ 25%፤

በንብረት ግብር ክፍያ ላይ ተጨማሪ እንደ ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
በከተማችን አዲስ አበባ ከአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ጋር በተያያዘ ለሚገጥሞት ማንኛውም ችግር ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ያውቁ ኖሯል?

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም አከራይ ከመጋቢት 24/2016 ዓ.ም ጀምሮ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘ የቤት ኪራይ ጭማሪ አልያም ቤቱን ይልቀቁልኝ የሚል ግፊት ከደረሰብዎ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ጥቆማ መስጠት እና መብትዎን ማስከበር ይችላሉ።

የጥቆማ ስልክ ቁጥሮች 👇👇👇

+251118722917

+251118553820
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
የውል ይርጋ
---------------
1)የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810(2) ላይ የተመለከተው የይርጋ ገደብ ተፈፃሚ የሚሆነው ውል በፈቃድ ጉድለት ወይም በችሎታ ማጣት የተነሳ እንዲፈርስ ጥያቄ የቀረበ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህቁ 1810 የሰ/መ/ቁ 48012 ቅፅ 12
2)በውል ግንኑነት ውስጥ የራስን ግዴታ ሳይወጡ ሌላው ወገን ግዴታውን አልተወጣም በሚል የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1757 በሰ/መ/ቁ 39568 በቅፅ 12
3)የማይንቀሳቀስ ንብረት ሻጭ በዉሉ መሠረት የመፈፀም ፍላጎት የሌለው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ለገዢ ያላሳወቀ እንደሆነ ገዥ ውሉ እንዲፈፀምለት የመጠየቅ መብቱ በ10  ዓመት ይርጋ የሚታገድበት ስለመሆኑ 1845;1789:1731:1732 የሰ/መ/ቁ 38935 ቅፅ 12
4)የፍትሐብሄር ጉዳዮች የ ይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1846 የሰ/መ/ቁ 36756 ቅፅ 12
5)የፀና የውል ግዴታ የገባ ሰው ውሉ በፍርድ እንዲሰረዝ ለመጠየቅ የሚችለው ሌላኛው ተዋዋይ ወገን ግዴታውን በአግባቡ ያልፈፀመ(ያልተወጣ) እንደሆነ ወይም የፈፀመው ፍፁም ባልሆነ አኳኃን ከሆነ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1784;1785(2).(1)"የሰ/መ/ቁ 66935 ቅፅ 13 ላይ ሰፍሯል።
https://t.me/ethiolawtips
👍1
የቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ሰኔ 12 ቀን 2016 ዐ.ም በፌደራሉ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ዙሪያ የአደባባይ ግንዛቤ ፈጠራ ስራ ሰራ!!! በዝግጅቱም ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ምንነት፣ ዘመን፣ መታደስ፣ መቋረጥ እንዲሁም በአዋጁ ስለሚቋቋሙ ተቋማት ስልጣንና ሃላፊነት ግንዛቤ ተፈጥሯል። እነሆ ከዝግጅቱ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎች!!!!!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
በስርአተ_ትምህርት_ጥሰትና_ስታንዳርድ_ባለማሟላት_የተዘጉ_ተቋማት_ዝርዝር.pdf
901.1 KB
#AddisAbaba : በስርዓተ ትምህርት ጥሰት እና ስታንዳርድ ባለለመሟላት የተዘጉ ትምህርት ቤቶች ዝርዝር።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን አይቀጥሉም የተባሉ ናቸው።

ፍኖተ ሎዛን በተመለከተ ግን ይህን ያንብቡ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88408?single

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
በራሳቸው የዘጉ ተቋማት ዝርዝር.pdf
1015.4 KB
#AddisAbaba

በራሳቸው የዘጉ ትምህርት ቤቶች ዝርዝርን ይመለከቱ።

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የቅድመ_አንደኛ_ተቋማት.pdf
10.8 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የአንደኛና_መካከለኛ_ደረጃ.pdf
6.1 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የአንደኛ እና መካከለኛ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የአጠቃላይ_2ኛ_ደረጃ.pdf
1.8 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
Forwarded from ስለ-ሕግ ⚖ 𝐀𝐁𝐎𝐔𝐓-𝐋𝐀𝐖 (Ashenafi F. Sendeku)
የሰበር መ/ቁ 227978
ሕዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም

የፋይናንስ ተቋማት ለሰጡት ብድር አከፋፈል በመያዣነት የያዙት ተሽከርካሪ የጦር መሣሪያ ጭኖ በመገኘቱ የተነሳ በጉምሩክ ኮሚሽን ሲወረስ የተሽከርካሪው ባለቤት (ተበዳሪው) የውርስ ውሳኔውን ሕጋዊነት በመቃወም ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ጣልቃ በመግባት የክርክሩ ተካፋይ መሆን ይችላሉ ወይስ አይችሉም?

የፋይናንስ ተቋማት ለሰጡት ብድር በመያዣነት የያዟቸው ተሽከርካሪዎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ለማዘዋወር ድርጊት መፈጸሚያነት ውለው ሲገኙ በጉምሩክ ኮሚሽን አስተዳደራዊ ውሳኔ ውርስ የሚደረጉ ሲሆን የፋይናንስ ተቋማቱም የውርስ ውሳኔው በተሽከርካሪዎቹ ላይ ያላቸውን የቀደምትነት መብት ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው የሚል ክርክር ያቀርባሉ።

በጉምሩክ አዋጅ ቁ. 859/06 አንቀጽ 153 መሠረት የጉምሩክ ጉዳዮች አቤቱታ አጣሪ የሥራ ክፍል የውርስ ውሳኔውን በማጽናት በሰጠው ውሳኔ ላይ የተሽከርካሪው ባለቤት ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው ይግባኝ ላይ አበዳሪው ባንክ በታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ የአሰራር መመሪያ ቁ. 02/11 አንቀጽ 16(1)(ሀ) መሠረት የጣልቃ ገብ አቤቱታ በማቅረብ የክርክሩ ተካፋይ መሆን ይችላል? ወይስ ጉዳዩ በቀጥታ ለመደበኛ ፍ/ቤቶች የሚቀርብ ነው? በሚለው ጉዳይ ላይ ግልጽነት ባለመኖሩ ለክርክር በር ሲከፍት ቆይቷል።

የታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ የፋይናንስ ተቋማቱ የሚያቀርቡትን የጣልቃ ገብ አቤቱታ ተቀብሎ የማየት ሥልጣን በሕግ ያልተሰጠው መሆኑን በመጥቀስ አቤቱታውን ውድቅ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ጉዳዩን በይግባኝ የሚመለከቱ መደበኛ ፍ/ቤቶች ደግሞ የጉምሩክ ጥፋት መፈጸሙን ተከትሎ የሚጣሉ አስተዳደራዊ ቅጣቶችንና የውርስ ውሳኔዎችን ሕጋዊነት በመቃወም የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ የማየትና መርምሮ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የመስጠት የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ ነገር ሥልጣን ለጉምሩክ ኮሚሽን አቤቱታ አጣሪ የሥራ ክፍሎች የተሰጠ በመሆኑና በጉምሩክ አዋጁ የተዘረጋው የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት በጉዳዩ ላይ ያገባናል የሚሉ ሦስተኛ ወገኖች ወደ ክርክሩ በመግባት መብትና ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚችሉበትን አሠራር ያልዘረጋ በመሆኑ ተበዳሪው (የተሽከርካሪው ባለቤት) ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ የፋይናንስ ተቋሙ የክርክሩ ተካፋይ ሊሆን ይገባል የሚል አቋም ያንጸባርቃሉ።

ይህንን በሚመለከት የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 227978 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። ሰ/ሰ/ችሎቱ
- በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚካሄዱ ክርክሮች የሚያከራክረው ጉዳይ ተሽከርካሪው የጦር መሣሪያ ጭኗል? አልጫነም..ሊወረስ ይገባል? አይገባም የሚል ክርክር በመሆኑና የፋይናንስ ተቋማቱም የቀዳሚነት መብት ያላቸው ስለመሆኑ ከማንሳት በስተቀር ተሽከርካሪው የጦር መሣሪያ ጭኗል ወይስ አልጫነም በሚለው የክርክር ፍሬ ጉዳይ ላይ የሚያቀርቡት ክርክር አለመኖሩን፤ በመሆኑም ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ፍሬ ጉዳይ ላይ መብት ወይም ጥቅም የሌላቸው መሆኑን...

- የቀዳሚ መብት ጥያቄ የሚነሳው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3059(1) መሠረት በመያዣ የተያዘው ንብረት በሌሎች ገንዘብ ጠያቂዎች ተይዞ ንብረቱ በሀራጅ ከተሸጠ በኋላ የተገኘው ገንዘብ የሁሉንም ዕዳ መሸፈን በማይችል ጊዜ መሆኑንና የቅድሚያ መብት አቤቱታ በዚህ ደረጃ የሚነሳ አለመሆኑን፤ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ክርክሩ እንዲገቡ በሚል በሥር ፍ/ቤቶች የሚሰጥ ውሳኔ በባንኩና በተበዳሪው መካከል ያለውን የብድር/መያዣ ውል መሰረት ያደረገ አለመሆኑን በማንሳት ....ባንኩ የብድር ውሉን መሠረት በማድረግ የሚያቀርበውን የመብት ጥያቄ ግን በመጠበቅ ውሳኔ ሰጥቷል።

በመሆኑም የፋይናንስ ተቋማት በመያዣነት የያዙት ተሽከርካሪ የውርስ ውሳኔ ሲተላለፍበት የመያዣ ውሉን መሠረት አድርገው በመደበኛ ፍ/ቤቶች ክስ ከሚመሰርቱ በስተቀር የውርስ ውሳኔውን ሕጋዊነት ብቻ በሚመለከተው በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በተሽከርካሪው ባለቤትና በጉምሩክ ኮሚሽን መካከል በሚካሄድ ክርክር ጣልቃ ገብተው ለመከራከር አይችሉም።


Tsegazeab Zerihun Gebeyehu, an Attorney for FDRE Customs Commission.

JOIN ስለ-ህግ ABOUT-LAW
Telegram- https://telegram.me/ethiolawblog
Facebook- https://m.facebook.com/aboutlawlegalservice
LinkedIn- https://www.linkedin.com/company/aboutethiopian-law
👍1
የቤት ሠራተኞች ሕጋዊ የሰነድ ውል እንዲኖራቸው የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሊዘጋጅ ነው
***
የአገር ውስጥ የቤት ሠራተኞች ከአሠሪዎቻቸው ጋር ሕጋዊ የሰነድ ውል እንዲኖራቸው ጥናት በማድረግ፣ የሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው ለዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመ ክርስቲያናዊ ድርጅት የቤት ሠራተኞች የሥራ ላይ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታን አስመልክቶ፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ የሥራ ሁኔታቸውን በሕግ የሚደነግግ ደንብ እስኪወጣ ድረስ፣ በመንግሥት ደረጃ ተቀባይነት ያለው የሥራ ቅጥር ውል ለመንደፍ የሚያስችል ውይይት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲያካሂድ ነው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የሦስትዮሽ ግንኙነት ማስተግበሪያ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳልክ ተክለ ሃዋሪያት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የቤት ሠራተኞች ከአሠሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ጤናማ እንዲሆንና መብቶቻቸው እንዲጠበቁ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡
የቤት ሠራተኞች መብቶቻቸውንና ግዴታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲለዩ እንዲህ ዓይነት አሠራር መከተል አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት ገልጸው፣ ማናቸውም የቤት ሠራተኞች ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ አገር የሥራ ሥምሪት በበቂ ሁኔታ እንዲሠለጥኑ ሚኒስቴሩ የተሻለ አሠራርን ዘርግቶ ወደ ሥራ መግባቱን አክለዋል፡፡
በቅርቡም ጥናት ተደርጎበት ወደ ሥራ የሚገባበት ይህ አሠራር ለውጭ አገር የሥራ ሥምሪት መነሻነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የገለጹት ኃላፊው፣ ጥናቱንም ከዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመ ክርስቲያናዊ ድርጅትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የሚሠራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
ለዓለም አቀፍ በጎ አገልግሎት የቆመው ክርስቲያናዊ ድርጅት ሠራተኞች በተለያዩ ክልሎች ላይ የሠሩትን ጥናት እንደ መነሻነት በመጠቀም፣ የቤት ሠራተኞችና አሠሪዎች መብትና ግዴታቸው ምንድነው የሚለውን ጉዳይ ከተጠቃሚዎቹ በማወቅ የሕግ ማዕቀፍ የሚዘጋጅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት በተመለከተ ማንኛውም ዜጋ ወደ ውጭ ሥራውን ከጀመረበት ጀምሮ አገልግሎት እስከሚያገኝበት ድረስ፣ የራሱ የሆነ አሠራር እንዳለውና መመርያም ጭምር እንደተዘጋጀለት ጠቁመዋል፡፡
የቤት ሠራተኞች የሥራ ሁኔታቸው በሕግ ጥበቃ ባለመደረጉ እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰትና ልዩ ልዩ አካላዊ እንዲሁም ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማስቀረት በአሠሪና በሠራተኛ አዋጅ የተቀመጠውን ደንብ እንዲወጣ መንግሥትን እየወተወተ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡
በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ደንብ እስኪወጣ የሠራተኞቹን መብትና ግዴታ፣ እንዲሁም የአሠሪዎቹን ኃላፊነት የሚያሳይ የሥራ ውል ተነድፎ ሥራ ላይ እንዲውል መደረግ እንዳለበት ኢሠማኮ ያምናል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት እንዲቻል ደንብና መመርያዎች እንዲወጡ በአዋጁ ቢደነገግም፣ በተፈለገው መጠን ተሠርቶ ባለመታየቱ እንደ ማንኛውም ሠራተኛ በጋራ በመሆን የጋራ ችግሮቻቸውን የሚመክሩበት፣ የመደራጀት መብት እንዲኖራቸው ያልተቋረጠ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አብራርተዋል፡፡
የቤት ውስጥ ሠራተኞች በአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ ተካተው ተገቢውንና ወጥ የሆነ አደረጃጀት እንዲኖራቸው ለማስቻል፣ የዓለም ሥራ ድርጅት ድንጋጌ ቁጥር 189 የኢትዮጵያ የሕግ አካል እንዲሆን ሁሉም ለባለድርሻ አካል የግሉን ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
ኮንቬሽኑን ኢትዮጵያ እንድታፀድቅና የሕጎቿ አካል እንዲሆን ለማስቻል በሕጉ ላይ በቂ ዕውቀት ባላቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች አካላት በሚገኙ ባለሙያዎችን ጭምር በመጠቀም የሕግ አካላት፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የሠራተኞችና የአሠሪዎች አደረጃጀቶች፣ የፌዴራልና የክልል አስፈጻሚ አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የጋራ ውይይቶች አድርገው የተጎዱና የተረሱ ወገኖች ሰብዓዊና የሥራ ላይ መብቶቻቸው መጠበቅ እንዳለበት በማመን የጋራ ስምምነት ተደርሷል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
👍2
Forwarded from abyssinialaw.com⚡️ (Attorney Liku Worku)
የማታለል ወንጀል ከእምንት ማጉደል ወንጀል በምን ይለያል? በድንጋጌዎቹ የወንጀል ክስ ለማቅረብ በመሠረታዊነት መሟላት ያለባቸው የማስረጃ ዓይነቶችስ ምንድናቸው?

በ፡-ሲሳይ ጎኣ

ይህ ጽሑፍ ከማታለልና ከእምነት ማጉደል ጋር በተያያዙ እየተነሱ ያሉ ችግሮችን በወፍ በረር ቅኝት ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡ በጽሑፉም የሚከተሉትን ዋና ጉዳዮች ያገኛሉ፡፡

- በንብረት ላይ የሚፈፀም ወንጀል በጠቅላላው
- አታላይነት
- እምነት ማጉደል
- እምነት ማጉደል ከማታለል የሚለይበት መሰረታዊ ነገር
- የእምነት ማጉደል ወንጀል በመሰረታዊነት ለማቋቋም በወንጀል
ህጉ አንቀፅ 675 ላይ የተመለከተው መስፈርት
- አንቀፁን ከመተግበር አንፃር በተግባር የሚያጋጥሙ ችግሮች

ጽሑፉን በማንበብና ለሌሎች በማካፈል የኢትዮጵያ የሕግ አቋምን ይደግፉ!

https://www.abyssinialaw.com/blog/yematale-wenije-ke-i-niti-magude-wenije-be-ni-yileya-bedinigagewocu-yewenije-kisi-lemaqirebi-bemeseretawi-ti-memwalati-yalebace-yemasireja-eyi-tocisi-nidinace-1
👍1
#ተራዘሟል

በአዲስ አበባ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ  እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ።

ምዝገባው ሰኔ 30 ያበቃል መባሉ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል ምዝገባ ተከናውኗል።

አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ ይገኛል ብሏል።

ነገር ግን ፦
- በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ
- ቀሪ ያልተመዘገበው የተከራይ አከራይ ውል እስከ ሰኔ 30/2016 መዝግቦ ለማጠናቀቅ አዳጋች ስለሚሆን
- ቀኑ እንዲራዘምም ከህብረተሰብ በቀረበ ጥያቄ  የምዝገባ ጊዜው እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ/ም መራዘሙን ቢሮው ገልጿል።

ነዋሪዎች ጊዜው ተራዘመ ብለው ሳይዘናጉ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ፣ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ሳይጨናነቁ ምዝገባ እንዲያካሂዱ ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministration
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ባልና ሚስት በጋብቻ መካከል የሚያደርጉት የስጦታ ውል ተቀባይነት አለው?

በጋብቻ መካከል በየትኛውም ንብረት ላይ ባልና ሚስት እርስ በራስ የሚያደርጉት የስጦታ ውል ፍ/ቤት ቀርቦ ካልፀደቀ በቀር  በህግ ፊት ተቀባይነት የለውም።ሲል የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ.መ.ቁ. 158292 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
@lawyerhenoktaye

+251911954039
Telegram 🔥👇
https://t.me/ethiolawtips
Business law tips
@henoktayelawoffice
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ከህግ ውጪ የተቋረጠ የስራ ውል ለሰራተኛው የሚያስገኛቸው ጥቅማጥቅሞች

1 የስራ ስንብት ክፍያ
የስራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ሰራተኛ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 39(1) እና 40(1) መሰረት እንደ ነገሩ ሁኔታ የአንድ አመት ደሞዙን የሚደርስ የስራ ስንብት ክፍያ ያገኛል፡፡

2. የካሳ ክፍያ
የስራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ከስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 43(4)(ለ) መሰረት የካሳ ክፍያ ያገኛል፡፡ሆኖም ካሳው የሰራተኛውን ማዕከላዊ የቀን ደሞዝ ደመወዙ በ180 ተባዝቶ ከሚያገኘው ውጤት መብለጥ የለበትም፡፡
3. ያልተጠቀሙበት የአመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ የሚከፈል ክፍያ
የስራ ውሉ አለአግባብ የተቋረጠበት ሰራተኛ ከስራ ስንብት ክፍያ እና ከካሳ ክፍያ በተጨማሪ ያልተጠቀመበት የአመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ በአዋጅ 1156/11 አንቀፅ 77(4) መሰረት ይከፈለዋል፡፡
4. ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ
ሰራተኛው የሚለግበትን የአሰሪ ንብረት መልሶ ክሊራንስ ከጨረሰ በኋላ ሊከፈሉት የሚገቡ ክፍያዎች በ7 ቀን ውስጥ ካልተከፈሉት በአዋጁ አንቀፅ 38 መሰረት እስከ 3 ወር ደመወዝ ሊከፈለው ይችላል፡፡
5.ያልተከፈለው የወር ደመወዝ ካለ ይከፈለዋል፡፡
6. ለተጨማሪ ስራ ክፍያ
ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጪ በበአል ቀናት የተሰራ ስራ፤በእረፍት ቀናት የተሰራ ስራ ካለ ለእነኝህ ስራዎች በአዋጅ አንቀፅ 66 እና 68 መሰረት ሰራተኛው ክፍያ ያገኛል፡፡
7. የስራ የምስክር ወረቀት
በአዋጁ አንቀፅ 12(8) መሰረት ሰራተኛው የስራ ልምድ ማስረጃ ያገኛል አንድ የግል ድርጅት ሰራተኛ የስራ ውሉ የህግ ውጪ ሲቋረጥ የሚያገኛቸው ህጋዊ ጥቅማ ጥቅሞች እነዚህ ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ  :- ይህ ተግባራዊ የሚሆነው ለግል ሰራተኞች ብቻ ነው፡፡
#Join 👇
https://t.me/ethiolawtip
የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral Damage)
የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral Damage) ምንነት
የህሊና ጉዳት ካሳ (Moral damage) በአንድ ሰው ድርጊት ምክንያት ለደረሰ የስሜትና የመንፈስ ጉዳት በፍርድ ቤቶች የሚወሰን የካሳ ዓይነት ነው፡፡ የህሊና ጉዳት በተጎጂው ላይ የደረሰውን የስሜት መጎዳት፣ የሥነ-ልቦና ጉዳት፣ ሐዘን፣ ሀፍረት፣ ውርደት፣ አእምሮአዊ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ መጥፎ ስም፣ የቆሰሉ ስሜቶች፣ የሞራል ድንጋጤ፣ ማህበራዊ ውርደት፣ በአካላዊ ስቃይ ምክንያት የተከሰተ የሞራል ጉዳት እና ተመሳሳይ ጉዳቶች ያካትታል። ከፍትሐብሔር ግንኙነት በተጨማሪ በወንጀል ጉዳይ ተጎጂው በተከሳሹ የወንጀል ድርጊት ምክንያት የደረሰበትን የሞራል ስቃይ ለመካስ ያገለግላል።
የህሊና ጉዳት ካሳ ፅንሰ-ሀሳብ በባህሪው ተጎጂው የደረሰበት ጉዳት ለማካካስ የሚሰላ ነው፡፡ እንዲሁም ተጎጂው በገንዘብ ረገድ ለደረሰበት ጉዳት ሳይሆን በህሊናው ላይ ለደረሰበት ጉዳት የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡ ስለሆነም የሞራል ጉዳት ወይም የህሊና ጉዳት ካሳ ቁሳዊ ላልሆኑ ጉዳቶች እንደ ማከሚያ የተሰጡ የጉዳት ክፍያዎች ናቸው፡፡
የህሊና ጉዳት ካሳ የሚያስከፍሉ ጉዳቶች በፍትሐብሔር ህግ
የህሊና ጉዳት ካሳ በመሰረቱ ለደረሰው ጉዳት ካሣ ለመክፈል ተመዛዛኝ በሆነ አድራጎት ሊፈፀም በሚቻልበት ጊዜ ሁሉ ጥፋተኛው በደሉ ለሚያስከትለው የሕሊና ጉዳት ካሳን መክፈል እንደሚገባ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2105(1) ስር ተደንጓል፡፡
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2105(2) የህሊና ጉዳት በሕጉ በግልፅ ካልተመለከተ በቀር የገንዘብ ካሳ የማያስከፍል መሆኑ ተቀምጧል። በሌሎች ህጎች ስለ ሞራል ካሳ የተደነገጉ ድንጋጌዎች እንዳሉ ሆነው በፍትሐብሔር ሕጉ ከውል ውጪ ስለሚደርስ ሃላፊነት ሥር የገንዘብ ካሳ የሚያስገኙ የህሊና ጉዳት ዓይነቶች በፍትሐ ብሔር ሕጉ ከቁጥር 2106 እስከ ቁጥር 2115 ድረስ ያሉት ብቻ ናቸው።
በፍትሐብሄር ህጉ የህሊና ጉዳት ካሳ የሚያስከፍሉ ጥፋቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ታስቦ የተደረገ ጥፋት (በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2106)፡- በከሳሹ ላይ ታስቦ የህሊና ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ ዳኞች በዚሁ በደል ካሳ ስም ተከሳሹ ለከሳሹ በርትዕ ካሳ እንዲከፍል ወይም ከሳሹ ላመለከተው በጎ አድራጎት ድርጅት እንዲከፈል ለመፍረድ ይችላሉ።
በተበዳዩ ሰውነት ላይ ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2107)፡- ተከሳሹ በከሳሹ ላይ አስቀያሚ ወይም የሚያስጠላ መጥፎ መንካት በሚያደርግበት ወቅት ለተበዳይ ካሳ ይከፈለዋል።
ያለአግባብ ሰውን በመያዝና በማገድ የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2108)፡- ተከሳሹ ህግን ተቃራኒ በሆነ አኳኋን የከሳሹን ነፃነት አግዶ በተገኘ ጊዜ የሚከፈል የህሊና ጉዳት ካሳ ነው፡፡
በስም ማጥፋ ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2109)፡- ከሳሹ ተሰድቦ ወይም ስሙ ጠፍቶ ሲገኝ
• ከሳሹ በወንጀል ህግ የሚያስቀጣ ወንጀል ሰርቷል በማለት ስሙን በማጠፋት የበደለው እንደሆነ፣
• የስም ማጥፋት ሥራዎች ከሳሹን በሞያ ሥራ ችሎታ የሌለው ወይም እውነተኛነት የሌለው መሆኑን ለማሳመን የተደረገ እንሆነ፣
• ነጋዴ ሆኖ ዕዳውን ለመክፈል አይችልም በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሆነ እንደሆነ፣
• ተላላፊ በሽታ አድሮበታል በማለት ለማሳመን የሚጥር እንደሆነ፣
• አስነዋሪ የሆነ ጠባይ አለው በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሚጥር እንደሆነ የህሊና ጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ይሆናል።
የባልና ሚስትን መብት በመድፈር የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2110)፡- ተከሳሹ የባልነት ወይም የሚስትነትን መብቶች ነክቶ የተገኘ እንደሆነ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡
ልጅን ነጥቆ በመውሰድ የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2111)፡- የልጁ ጠባቂነት የከሳሹ ሆኖ ተከሳሹ ልጁን ነጥቆ በመውሰዱ ጥፋተኛ ሆኖ በወንጀል በሚቀጣበት ወቅት የሚከፈል ክፍያ ነው።
ንብረቶችን በመድፈር የሚደርስ ጥፋት (በፍ/ሕ/ቁ 2112)፡- ከሳሹ እንዳይደርስበት በግልፅ ያስታወቀውን በመቃወም ተከሳሹ በደንብ በእጁ ወይም በይዞታው የሚገኘውን ንብረት የወሰደበት እንደሆነ ወይም በርስቱና በቤቱ የገባበት እንደሆነ በከሳሹ ላይ ስለ ደረሰው ጉዳት ለዚህ በደል ካሳ ሊወሰን ይችላል።
በአካል ጉዳት ወይም በሞት የሚደርስ ጉዳት(በፍ/ሕ/ቁ 2113)፡- አካሉ በመጉደሉ ለተበደለው ሰው ወይም ሰውየው የሞተ እንደሆነ ለዘመዱ የጉዳት ካሳ በአስተያየት ተገቢ ኪሳራ ዳኞች ሊቆርጡ ይችላሉ፡፡
የንፁህ ህሊናን ክብር በመድፈር የሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2114)፡- ማንኛውም ሰው በመድፈር ሥራ ወይም ለክብረ ንፅህና ተቃራኒ በሆነ ተግባር በወንጀል የተቀጣ እንደሆነ ዳኞቹ ለተደፈረችው ሴት በህሊና በደል ካሳ ስም ተከሳሹ የሚሰጠውን በርትዕ የሚገባ ካሳ ሊቆርጡ ይችላሉ። እንዲሁም ለሴቲቱ ባል ወይም ቤተ ዘመዶች ካሳ ሊቆረጥ ይችላል።
በሚስት ላይ ስለሚደርስ ጉዳት (በፍ/ሕ/ቁ 2115)፡- ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ሚስት ላይ የአካል ጉዳት በማድረሱ በትዳር በኩል ለባሏ የምትሰጠው ጥቅም ወይም ደስታ እንዲቀንስ ያደረገ እንደሆነ ስለበደል ካሳ ዳኞች በበዳዩ ላይ ለባለቤቷ በርትዕ ተገቢ የሆነ ኪሳራ ሊቆርጡለት ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት በሚስት ላይ ለደረሰው ጉዳት ባል የሚያቀርበው ክስ ሚስቱ ለደረሰባት ጉዳት ስለካሳ ጥቅም ከምታቀርበው ክስ ተጨማሪና የተለየ ነው፡፡ የህሊና ጉዳት ካሳ ክፍያ መጠን
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2116 ስር እንደተደነገገው የካሳ ልክ ምን ያህል መሆኑን በርትዕ በአስተያየት ለመወሰንና የቤተ ዘመዱ እንደራሴ ሆኖ ለመነጋገር የሚችል ማን እንደሆነ ለማወቅ ዳኞች የአገር ልማድን መሰረት በማድረግ የሚወስኑ ሲሆን የጉዳት ካሳውም በማናቸውም ምክንያት ከ1000 የኢትዮጵያ ብር የበለጠ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የገንዘብ መጠን ሕጉ በወጣበት ዘመን ከፍተኛ ነው ሊባል ቢችልም በአሁኑ ጊዜ ግን በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በመሆኑም በዛ በኋላ በወጡ ልዩ ህጎች የህሊና ጉዳት ካሳ መጠን ላይ መሻሻሎች ታይተዋል፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ ሕግጋት ሲሻሻሉ ሕግ አውጪው የሞራል ካሳውን መጠን በገንዘብ መጠን ሳይወስን ዳኞች እንደጉዳዩ እንዲወስኑ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡ የደቡብ ክልል የቤተሰብ ሕግ ግን በባልና ሚስት መካከል ያለው የመከባበር፣ የመተጋገዝና የመተማመን ግዴታ ከተጣሰ እስከ ብር 10,000 ድረስ ካሳ ዳኞች ሊወስኑ እንደሚችሉ በሕጉ መቀመጡ የተሻለ ሕግ አድርጎታል፡፡ እንዲሁም በቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ቁጥር 410/1996 አንቀፅ 34(4) መሰረት የሕሊና ጉደት ካሳ 100,000 ብር የማያንስ መሆኑ ይደነግጋል፡፡ በሌላ በኩል የመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀፅ 84(2) ለስም ማጥፋት ወንጀል የሚወሰነው የሞራል ካሳ መጠን ከብር 300,000 እንደማይበልጥ ይደነግጋል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የህሊና ጉዳት በህጉ በዝርዝር ለተቀመጡ ጥፋቶች ብቻ የሚከፈል ሲሆን የካሳው አላማም የገንዘብ ጥቅምን ለማስገኘት ሳይሆን ለደረሰ የስሜት ጉዳት እና ስብራት ማካካሻ ለመስጠት ነው፡፡ በመሆኑም የሞራል ጉዳት ደርሶብኛ የሚል ሰው የህሊና ጉዳት ካሳ ማግኘት እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል።
👎1