Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🖐ቴሌግራም ላይ የ Star Gift በ Reaction መልክ መስጠት ተጀምሮዋል!

🏷ምንቀርብላቹ ኮንተንቶች ከተመቻቹ Star Gift በመስጠት ይበልጥ እንድንሰራ አበርቱን🙏
❤6
#ADVERTISEMENTS

🌟Training (With Discount)

🌟Online Class (With Certificate)

1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. Structural Design in ProtaStructure Software
8. Autocad Price = 2500birr
9. Sap2000 Price = 2500birr
10. Autodesk Revit Architecture
11. WatrGems


🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount

🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken

🫵For Registration - 0948552002 Or 0933575753 or @AbelMuluken

🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution

🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
🏆6👍3
👉የአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት “በከተማዋ መግቢያ” ቦታዎች ሊከናወን ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እንደ ኮዬ አደባባይ፣ ጎሮ እና ሰሚት ባሉ “የከተማዋ መግቢያ” እና “ማስፋፊያ ላይ በሚገኙ” አካባቢዎች ሊያከናውን ነው።

43 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ፤ ከሸገር ከተማ የኮሪደር ልማት ጋር “በማስተሳሰር” እንዲከናወን ታቅዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የኮሪደር ልማት” ሲል የጠራውን ዋና ዋና መንገዶችን የማስዋብ፣ የእግረኛ መንገድን የማስፋት፣ መዝናኛ ቦታዎችን የመገንባት እንዲሁም የመንገድ ዳር መብራት እና ቴሌኮሚዩኒኬሽን መስመሮችን በዘመናዊ መንገድ የመዘርጋት ሥራ የጀመረው በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ ነበር።

የከተማዋን ታዋቂ እና ነባር አካባቢዎችን የሸፈነው የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት፤ አምስት መስመሮችን የያዘ ነው። በመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፣ ቦሌ፣ መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ሲኤምሲ ይገኙበታል።

የኮሪደር ልማቱ ሲከናወን ተለይም በፒያሳ አካባቢ ጥንታዊ ኪነ ሕንጻዎችን ጨምሮ በርካታ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን፣ በዚሁ ግንባታ ምክንያት 11 ሺህ ገደማ ነዋሪዎች ከአካባቢው መነሳታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታውቀው ነበር።

የከተማ አስተዳደሩ፤ በድምሩ 48 ኪሎ ሜትር ለሚሸፍነው ለመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት፤ 33 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንም መግለጻቸውም ይታወሳል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግምገማ እየተደረገበት የተካሄደው ይህ የኮሪደር ልማት፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነችን ጨምሮ ከፍተኛ የከተማዋ ኃላፊዎች ግንባታ የሚከናወንባቸውን መስመሮች ተከፋፍለው ሥራውን መርተውታል።

ከኮሪደር ልማቱ መስመሮች ውስጥ ቀድሞ የተመረቀው በከንቲባዋ ክትትል ስር የነበረው ከአራት ኪሎ ፒያሳ የሚደርሰው መንድ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የተመረቀውን ከመገናኛ ሲኤምሲ የተዘረጋውን ልማት ጨምሮ ሌሎቹ መስመሮች በተለያዩ ጊዜያት ክፍት ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ የገነባቸውን እነዚህን “መሃል ከተማ” የሚገኙ መስመሮች፤ “የከተማዋ መግቢያ ተብለው ከተለዩ ቦታዎች እና በማስፋፊያ [ላይ] ከሚገኙ አካባቢዎች ጋር ለማስተሳሰር” ማቀዱን ቢቢሲ ከከተማ አስተዳደሩ ጥናት ተመልክቷል።

በምዕራፍ ሁለት የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ላይ የተደረገው ይህ ጥናት በከተማዋ የፕላን እና ልማት ቢሮ የተዘጋጀ ነው። በአጠቃላይ 43 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚኖረው የምዕራፍ ሁለት የኮሪደር ልማት፤ ቦሌ፣ ለሚ ኩራ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞችን እንደሚያካትት የጥናት ሰነዱ ያሳያል።

ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በአምስት መስመሮች ላይ የሚከናወን ነው። ከእነዚህ መስመሮች ውስጥ ከፍተኛ ዝርመት ያለው “ከአንበሳ ጋራዥ - መብራት ኃይል - ጎሮ - ኮዬ አደባባይ” የሚደርሰው መንገድ ነው። ይህ መስመር 14.8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።

“ከቦሌ ካርጎ - ቡልቡላ - ኮዬ አደባባይ” የሚደርሰው ሁለተኛው ረጅም መስመር ደግሞ 12.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ውስጥ የተካተተው ሌላኛው መስመር “ከቦሌ ድልድይ” ተነስቶ “በቦሌ ሆምስ - በአየር መንገድ ቪአይፒ መግቢያ” አድርጎ መዳረሻው “ጎሮ” አካባቢ ነው።

“ከጎሮ አደባባይ” የሚነሳው አራተኛው መስመር አምስት ኪሎ ሜትር ርዝመት እንደሚኖረው በጥናት ሰነዱ ላይ ሰፍሯል። ይህ መስመር “ከጎሮ አደባባይ - በሰባ ሁለት አካባቢ - ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ አካባቢ - ፍየል ቤት - ሲ ኤም ሲ አደባባይ” አካባቢዎችን ይሸፍናል።

“ከፍየል ቤት - ፊጋ - ሰሃሊተ ምህረት አደባባይ - ጃክሮስ” የሚደርሰው አምስተኛው መስመር ደግሞ 5.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው።

በከተማዋ የአስተዳደር ወሰን ማብቂያ አካባቢ የሚገኙ አካባቢዎችን ያካተተው ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ፤ “በትግበራ ላይ ከሚገኙ የሸገር [ከተማ] የልማት ኮሪደሮች ጋር በማስተሳሰር የሚከናወን” እንደሆነ የጥናት ሰነዱ ያመለክታል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አምስት ከተሞችን በአንድ የከተማ አስተዳደር ስር በማድረግ ባለፈው ዓመት የተመሠረተው የሸገር ከተማ፤ ሰኔ ወር ላይ “ዘጠኝ የልማት ኮሪደሮችን” በመለየት ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቆ ነበር።

የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን እና ልማት ቢሮ ያዘጋጀው የጥናት ሰነድ፤ ከኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ጋር በሚዋሰኑ አካባቢዎች የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከአጎራባቹ ከተማ ጋር “ወጥ የሆነ ዲዛይን ተዘጋጅቶላቸው በጋራ የሚለሙበትን ማዕቀፍ መፍጠር” እንደሚያስፈልግ አስፍሯል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ውስጥ በተካተቱት አካባቢዎች ላይ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት እንደ መጀመሪያው ምዕራፍ ሁሉ የእግረኛ መንገድን የማስፋት ውጥን ያለው ነው። በዋና መንገድ (አስፓልት) ጠርዝ የሚገኙ አካባቢዎች የአስር ሜትር ስፋት እንዲኖራቸው እንደታሰበ በጥናቱ ላይ ተጠቅሷል።

አምስት ሜትሩ የሚውለው ለእግረኛ መንገድ ሲሆን፤ የሳይክል መስመር ደግሞ ሦስት ሜትር ስፋት ይኖረዋል። በአስፓልቱ በኩል የሚኖረው ቀሪው ሁለት ሜትር ለአረንጓዴ ልማት ቦታ እንደሚውል ጥናቱ ያስረዳል።

በአምስቱ መስመሮች የሚገነባው የኮሪደር ልማት በሌሎች አካባቢዎች እንደተሠራው ሁሉ፤ የታክሲ ማቆሚያ ቦታዎችን፣ የሕዝብ መፀዳጃ፣ የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሁም በከተማ፣ ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ደረጃ የሚገነቡ ፓርኮችን እንደሚያካትት ጥናቱ ገልጿል።

የመኖሪያ ቤቶች ግንባታም የዕቅዱ አካል እንደሆነ የሚያመለክተው ጥናቱ፤ “ከቦሌ ሆምስ - አንበሳ ጋራዥ -አይሲቲ ፓርክ” ባለው አካባቢ ውስጥ “የማስፈሪያ ቦታ” (relocation site) እንደሚኖር ያስረዳል። በዚህ ስፍራ ላይ “ቅይጥ የመኖሪያ ቤቶች” (mixed residence) ይገነባሉ ተብሏል።

በኮሪደር ልማቱ ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የሚነሱ” ቦታዎች ጉዳይ በሰነዱ ላይ “ውሳኔ” እንዲሰጥባቸው ከተዘረዘሩ ነጥቦች መካከል ነው። ነባር ግንባታዎች “በልማቱ ውስጥ የሚካተቱበት መንገድ” መፈጠር እንዳለበት የሚያስገነዝበው ሰነዱ፤ የኮሪደር ልማቱ በሚከናወንባቸው መስመሮች ላይ ለሚገኙ ሕንጻዎች ሁለት አማራጮችን አስቀምጧል።

“ከሁለት ወለል በላይ” ላላቸው ሕንጻዎቸ የተቀመጠው አማራጭ “ታዛ (Arcade) እንዲያካትቱ ማድረግ” የሚል ነው። ይህ ዓይነቱ አማራጭ የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት በተካሄደባቸው አካባቢዎች በሚገኙ ሕንጻዎች ላይም የተተገበረ ሲሆን፣ የህንጻዎቹ የምድር ወለል የፊት ለፊት ገጽታ ፈርሶ ቦታው ለእግረኛ ክፍት እንዲሆን ተደርጓል።

ከሁለት ወለል በታች ላሉ ግንባታዎች የተቀመጠው አማራጭ፤ “በጥናቱ መሠረት ወደ ልማት ውስጥ ማስገባት” የሚል ነው። በምዕራፍ ሁለት በተካተቱ ቦታዎች ለሚገኙ “ይዞታዎችን የመለየት፣ የመተንተን፣ ግምት እና የምትክ አገልግሎቶችን የመለየት ሥራ” እየተከናወነ መሆኑን ጥናቱ ይጠቅሳል።

በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ውስጥ ከተካተቱት መስመሮች መካከል በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙት ሦስት ግንባታዎች “በቅርቡ” እንደተጀመሩ የክፍለ ከተማው የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለቢቢሲ አረጋግጧል።

@etconp
👍25❤4
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍5👏1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
❤1
👉HOW MANY TYPES OF BEAM IN CONSTRUCTION ENGINEERING?

🔰Introduction

✳️A beam is a horizontal structural element that travels horizontally and is designed to bear vertical loads that are applied to the building frame.

The load is distributed to the ends of the beam and then transferred to the column, wall, and posts on both sides of the beam. It can only bear weights applied laterally to the beam's axis.

🚧Different types of beams in construction are classified based on the following conditions.

❇️Based on Construction Materials
❇️Based on Loads & Supports
❇️Based on Shape of Cross Section
❇️Based on Equilibrium Conditions
❇️Based on Geometry
❇️Based on Construction Methods

📌Types of Beams In Construction

✅Beams can be simply supported, which means they are supported on both ends but can rotate freely.

☄Fixed: Both ends are supported and fixed to prevent spinning.

⏺Overhanging: one or both ends of the supports are overhanging.

⏺Continuous means that it spans more than two supports.

⏺Cantilevered means just one end is supported.

🔥They can be statically determinate (i.e., their reactions can be solved with equilibrium conditions) or statically indeterminate (i.e., they can't be solved using equilibrium conditions).

🔥Beams were traditionally made of wood, although they can now be made of steel, concrete, or composite materials.

❇️There are many different cross-section shapes to choose from, such as square, rectangular, circular, I-shaped, T-shaped, H-shaped, C-shaped, tubular, and so on.

⏺Straight, curved, or tapered beams are also available.

📌Common Types Of Beams In Construction Engineering

✳️Universal Beam:-A universal beam (UB) has an 'I' or 'H'-shaped cross-section and is available in several standard diameters. In the plane of the web, it is a very effective form for handling bending and shear stresses. Using initials to denote the kind of section is the conventional approach for describing the dimensions of a typical hot-rolled steel section. 'UB 203 x 133 x 25', for example, is a universal beam with nominal dimensions of 203 mm deep, 133 mm broad, and a weight of 25 kg/m.

✳️Beam With Trusses:-The addition of cables or rods to make a truss strengthens trussed beams.

✳️Hip Beam:-Hip beams are ubiquitous in roofs, where they support additional load-bearing beams (or rafters) that branch away from them on either side and slope down to the eaves, forming the roof's tilted, inclined hip.

☄Beam Made Of Composite Materials

⏺It's a structural component built from two different materials that are linked together to form a single unit.Composite beams include downstand beams, flitch beams, and shallow flooring.

☄Open Web Beam:-For structures with lengthy spans and light-to-moderate loads, open web beams are widely employed.

🔰Beam With Latticework
Lattice beams are a type of open web beam that can span up to 15 meters and have a high depth-to-weight ratio. Plate girder lattice beams and tubular lattice beams are two types of lattice beams.

☄Bridge Made Of Beams

✅Beam bridges are simple bridges with a beam-like deck supported by abutments or piers on both ends.

✅Chilled Beam

⏺Chilled beams are used to give cooling to buildings' interior regions. Chilled beams are often placed evenly over space's ceiling. Chilled water is pushed via copper cooling coils linked to aluminium fins, which convectively cool the air.

✅Tying Beam

👍A horizontal beam in a roof or roof truss that connects two rafters.'

@etconp
👍12❤8😢1
👉በሀገራችን ኢትዮጵያ በግንባታው ዘርፍ የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች:-

🚧በኮንስትራክሽንፈ ኢንዱስትሪ የማጭበርበር አመለካከትና ተግባር የሚስተዋልበት ነባራዊ ሁኔታ መኖሩ

🚧በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰለጠነና የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ኃይል እጥረት ያለ መሆኑ

🚧የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ስራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተሳለጠ ያለመሆኑ

🚧በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሠማሩ አማካሪዎችና ተቋራጮች መካከል ተወዳዳሪነት በሚፈለገው ደረጃ ማድረስ ያልተቻለ መሆኑ

🚧ለኮንስትክሽን ኢንዱስትሪ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ሠንሠለት ያልተዘረጋ መሆኑ

🌟ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መስፋፋትና መጠናከር የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጥር የፋይናንስና የማሽነሪ አቅርቦት ሥርዓት የተጠናከረ ያለመሆን

🌟የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዋና ዋና ባለሚናዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ለዘርፉ የተፋጠነ ዕድገት በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ ያለመፈጠሩ

🌟የህንፃ ግንባታና መጠቀሚያ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አገልግሎት የተጠናከረ ያለመሆን

🌟ፈርጀ ብዙ ሥራዎች ከኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሥራዎች ጋር ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገበሩበት ሥርዓት ያለመዘርጋቱ

🌟የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም ወይም ፓኬጅ አዘጋጅቶ በተሟላና በቀጣይነት ያለመተግበር

🌟ለባለሞያዎችና ስራተቋራጮች የሚደረግ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እጅግ አናሳ መሆን

@etconp
👍9👌3
👉NEW VACANCY

⭐️Construction Project Manager

#atta_trading_plc

#Addis_Ababa

💫Bachelor’s Degree in Civil Engineering, Construction Management, or a related field with relevant work experience in project management within the construction industry. A Master’s degree or PMP certification is a plus.

🏷Duties & Responsibilities:

- Develop detailed project plans, including timelines, budgets, and resource allocation, ensuring alignment with project objectives.
- Lead and manage multidisciplinary teams, including engineers, foremen, and construction workers, to ensure project goals are met.

⏺Quanitity Required: 10

🚧Minimum Years Of Experience: #3_years
🚧Maximum Years Of Experience: #10_years

📌Deadline: September 22, 2024

📩How To Apply: Submit your CV along with your educational background, work experience, and cover letter via email: attatradingplc@gmail.com

🌟For More Construction Vacancy Visit The Link Below👇

https://t.me/ETCONpWORK
👍4🙏3❤1🕊1
👉የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የፖርኪንግ እና ፕላዛ  ግንባታ ሼል በጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ የመኪና ፖርኪንግ ግንባታ እና የህዝብ አደባባይ (public plaza) ግንባታ ሥራዎች  በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የምህንድስና ዘርፍ ምክትል ዋና ሼል አስኪያጅ መለሾ አለቃ (ዶ/ር) በከተማዋ  ከሚሰሩ  የኮሪደር ልማት ሥራዎች መካከል የፖርኪንግ እና ፕላዛ  ግንባታ ሥራዎች  ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቅሰው ስራዎቹ ከተጀመሩ ሶስት እና አራት ወራትን ያስቆጠሩ እና በአፈፃፀም ደረጃ 40 % እና 50 በመቶ ደርሰዋል ብለዋል፡፡ 

ግንባታዎቹ እየተከናወኑ የሚገኙት ሜክሲኮ፣ አራት ኪሎ፣ ፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይ ፊት ለፊት፣ ደጎል አደባባይ፣ ባሻ ወልዴ ፣ ቴውድሮስ አደባባይ፣ መገናኛ አከባቢ እና ሌሎች አከባቢዎች እየተሰራ ሲሆን  ከወቅታዊ የዝናብ ሁኔታ እንዲሁመ በአንዳንድ አከባቢ ካለው አስቸጋሪ የመሬት የቁፋሮ ሾል አንፃር የግንባታ ፕሮጀክቶቹ በጥሩ አፈፃፀም ሂደት ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ምክትል ዋና ሼል አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራው  ቅንጅታዊ አሰራር ከማጎልበት ባሻገር  ለበርካታ ዜጎችን ቋሚና ጊዚያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፤ ግንባታዎቹ ሲጠናቀቁ ደግሞ የህዝብ አደባባይና መናፈሻ ስፍራዎችን ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባለፈ ፤በከተማው የትራፊክ ፍሰት ላይ ጉልህ አበርክቶ ይኖራቸዋል፡፡

@etconp
❤8👍3
#ADVERTISEMENTS

🌟Training (With Discount)

🌟Online Class (With Certificate)

1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. Structural Design in ProtaStructure Software
8. Autocad Price = 2500birr
9. Sap2000 Price = 2500birr
10. Autodesk Revit Architecture
11. WatrGems


🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount

🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken

🫵For Registration - 0948552002 Or 0933575753 or @AbelMuluken

🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution

🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
❤3👍1🔥1
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/

🌟የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት/contract agreement በአሰሪ/client እና በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

🚧እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው መቸ ነው? የሚለው ማለትም የውል አቀራረብ/offer እና አቀባበል/acceptance በሚመለከት በፍትሀብሄር ህጉ 1681 እና ተከታዮቹ የተደነገገው እና የውል ፎርም ጉዳይ ከግምት ውስጥ መግባት ጭምር አለበት፡፡ ETCONp

🚧የግል የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮችን በሚመለከተው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ አሰሪና ተቋራጭ ስለሚሰራው ስራ እና ስለዋጋው ካልተስማሙ በስተቀር የተቋራጭነት ውል አለ እንደማይባል ተደንግጓል፡፡

🌟ሌላው ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎችን በሚመለከት ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው ጭምር ተፈጸሚነት እንዳለው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3131(1) ይደነግጋል፡፡ ETCONp

🚧የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጽሁፍ መደረግ እንዳለባቸው በፍትሀብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1724 ላይ ተደንግጓል፡፡

🚧የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2005(1) ላይ እንደተደነገገው ደግሞ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ የተጻፈውን ቀን በሚመለከት በተፈራራሚዎች መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ነው ይላል፡፡

🌟እንግዲህ ውል የተደረገበት ቀን በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የውል ግንኙነት መቋቋሙን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡

🚧ውል ደግሞ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋዮች መካከል እንደህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731(1) ይደነግጋል፡፡

🌟ሆኖም ግን ውሉ የተደረገበት ቀን የውሉ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም፡፡

@etconp
👍11❤8
Living The Urban Periphery .pdf
51.4 MB
👉አዲስ መጽሀፍ

💫በአፍሪካ ከተሞች ዳርቻ መሰረተ ልማት እና የነዋሪ ህይወት ላይ ያጠነጠነ በበይነመረብ በነጻ የተለቀቀ መጽሀፍ

🏷Living the urban periphery

❇️Infrastructure, everyday life and economic change in African city-regions

🚧Authors: Paula Meth, Sarah Charlton, Tom Goodfellow, and Alison Todes

⏺የአፍሪካ የከተማ ዳርቻ ቦታዎች ብዙ ምርምር  ያልተደረገባቸው ስፍራዎች  ናቸው።

🌟መጽሀፉ ምሳሌ  የሚሆኑ የከተማ ዳርቻዎችን  ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኢትዮጵያና ከናይጄርያ የወሰደ ሲሆን በነዚህ ቦታዎች ላይ የሚከሰቱትን ኢኮኖሚያዊ፣ መሰረተ ልማታዊ፣ ስፍራዊ ማህበራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ክስተቶችን ይተነትናል።


⏹በመጽሀፉ ውስጥ ያሉ ምዕራፎችን በመጻፍ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል።

Via Architecture and Urbanism

@etconp
👍7❤2
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍3
Ethio Construction Engineering
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ 🌟የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት/contract agreement በአሰሪ/client እና በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ 🚧እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው…
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ እና በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/

በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡

*በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/

በመርህ ደረጃ የውል የግንባታ ስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ የውሉ የግንባታ ጊዜ ተብሎ የሚጠቀሰውን ቀን ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ስህተት ነው፡፡ ETCONp

ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ መካከል ከተፈረመ በኋላ የግንባታው ተጨባጭ ስራ በተለያየ ምክንያት ሊዘገይ ይችላል፡፡ለምሳሌ ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ የይገባኛል ጭቅጭቅ ቢነሳበት ጭቅጭቁ እስኪፈታ ድረስ አሰሪው የግንባታውን ሳይት ለተቋራጩ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ግንባታው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ ሳይጀመር መቆየቱ የማይቀር ይሆናል፡፡

*ለተቋራጩ የሳይት ርክክብ/site handover/

ለግንባታ የተወሰነው ቦታ ከጥያቄ ነጻ ከሆነና አሰሪው ሙሉ ባለይዞታ ለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ፤ ውል ላዋዋለው ሥራ ተቋራጭ የሥራ ቦታውን ያስረክባል ወይም የሳይት ርክክብ ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡ ETCONp

ይህ ከሆነ በኋላ አሰሪው ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራውን የሚጀምርበትን ቀን
- በርክክብ ወቅት በቃለ ጉባዔ ይወስናል፡፡
- ወይም አስቀድሞ በውሉ ልዩ ሁኔታዎች(Special condition of contract) ላይ በተቀመጠው ቀን እንደሆነ ታውቆ በተባለው ቀን ሥራ ይጀመራለረ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ሥራ ተቋራጩ ሳይት ሳይረከብ የግንባታው ጅማሬ ቀን ሊቆጠር አይችልም ማለት ነው፡፡
ሳይት ርክክብ ከተደረገ በኋላ እንደፕሮጀክቱ ዓይነት ወይም መጠን ስፋት የሞቢላይዜሽን ቀን ተጨምሮ ዋና የግንባታ ሥራ ማስጀመሪያው ቀን ይወሰናል፡፡ ስለዚህ ተቋራጩ የግንባታ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ሞቢላይዝ እስከሚያደርግበት ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ የስራ መጀመሪያ ቀን ሊጀምርበት አይገባም፡፡

በዚህ ረገድ በተግባር አልፎ አልፎ ስህተት ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ይሄውም አሰሪዎች አንዳንዴ የግንባታውን ጊዜ ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምረው በመቁጠር እና ተቋራጩን በቂ ምክንያት ካለህ የጊዜ ማራዘሚያ/Time extension/ ጠይቅ የሚሉበት የተሳሳተ ሁኔታና አጋጣሚ አለ፡፡

በዚህ ረገድ በሀገራችን እና በአለም ሀገራት እየተሰራባቸው ያሉ የዳበሩ የፊዲክ ጀኔራል ኮንዲሽኖች እና በሀገራችን ተጣጥመው የተቀረጹ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ምን ይዘት አላቸው የሚለውን እና የፍትሀብሄር ህግ ድንጋጌዎችን ደግሞ ቀጥለን እንዳስሳለን፡፡

1. FIDIC RED BOOK 1999

በፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ክሎስ 8.1 ላይ ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ስራ እንዲጀምር ማስታወቅ እንዳለበት እና ከ7 ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንደሚገባው ይጠቅሳል፡፡ ETCONp

እንደዚሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር የስራ መጀመሪያው ቀን/ Commencement date/ ተቋራጩ በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ42 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡

በተጨማሪም ተቋራጩ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ወዲያውኑ እና ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡ተቋራጩ/contractor/ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ምክንያት ሳይኖረው ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት በክሎስ ላይ የተቀመጠውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ ደግሞ አሰሪው/client/ውሉን ለማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 15.2(c) ላይ ተቀምጧል ETCONp

2. FIDIC 1987

በኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ፎር ወርክስ ኦፍ ሲቪል ኢንጅነረንግ ኮንስትራክሽን ፊዲክ 1987 ቨርሽን ክሎስ 41.1 ላይ ስለ ኮመንስመንት ዴት/የስራ መጀመሪያ ቀን ተቀምጧል፡፡ይዘቱም መሀንዲሱ የስራ መጀመሪያውን ቀን በጨረታ ሰነዱ አፔንዴክስ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት የሚገልጽ ነው፡፡ተቋራጩም የስራ መጀመሪያው ቀን በመሀንዲሱ ከተገለጸለት በኋላ ያለመዘግየት እና በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ስራውን መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡

የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቆጠር የሚጀምረውም ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ስለመሆኑ ክሎስ 43.1 ላይ ተቀምጧል፡፡

እንግዲህ ተቋራጩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በክሎስ 41.1 ላይ በተመለከተው አግባብ የግንባታ ስራውን ሳይጀምር የቀረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለማቋረጥ እና ተቋራጩን ከሳይት ለማስወጣት መብት/expel right/ እንዳለው ክሎስ 63.1 ያስቀምጣል፡፡

3. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር  አቋም/MoWUD 1994

ይህ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1994 ስራ ላይ አውሎት የነበረው የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/MoWUD 1994 በተለይ ከፊዲክ/FIDIC 1987 ቨርሽን የተወሰደ ሲሆን ስለኮመንስመንት ዴት በሁለቱም ጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡
ስለዚህ ማብራሪያውን መድገም አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡

4. የመንግስት ግዢዎች ኤጀንሲ/PPA 2011

በፒፒኤ 2011 ቨርሽን ክሎስ 71 ላይ የስራ መጀመሪያ ቀን በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ወይም ደግሞ በአስተዳደራዊ መንገድ በኢንጅኒየሩ በሚሰጥ ትእዛዝ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡ ETCONp

እንዲሁም በሌላ ሁኔታ በውሉ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር ለተቋራጩ የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ ታስቦ ከ120 ቀናት ለማለፍ አይችልም፡፡

5-የፍትሀብሄር ህግ

የስራ ማከናወኛ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610 - 2637) በሚመለከት በውሉ ላይ የጊዜ ጉዳይ በግልጽ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ተቋራጩ ወዲያውኑ ሾል መጀመር እንደሚኖርበት በአንቀጽ 2619 ላይ ተደንግጓል፡፡የግንባታ ጊዜ በተገለጸባቸው ውሎች ደግሞ ሾል ተቋራጩ ስራውን ወዲያው ያልጀመረ እንደሆነ እና በጊዜ ገደቡ የግንባታ ስራውን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ አሰሪው ለተቋራጩ ስራውን የሚጀምርበትን ጊዜ ሊወስንለት እንደሚችል በአንቀጽ 2618 ላይ ተቀምጧል፡፡  ETCONp

ሌላው እነዚህ ደንቦች ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ስራ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3019-3040) በሚመለከተው የግል የስራ ተቋራጭነት ውል ላይ ጭምር ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው ከአንቀጽ 3019(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡

የአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውል ማለትም የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3244 እና ተከታዮቹ) በሚመለከት እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን ግዴታዎቹን በውሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ደግሞ ግዴታው በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ መፈጸም እንደሚኖርበት በአንቀጽ 3174 ላይ ተቀምጧል፡፡

ይህ ድንጋጌ ስለአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጠቅላላው የተደነገገ ሲሆን የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውልን በሚመለከተው ልዩ ክፍል ላይም በግልጽ ስለስራ ጊዜ ተደንግጓል፡፡

@etconp
👍19❤2
This media is not supported in the widget
VIEW IN TELEGRAM
😢7👍5❤3🏆1
👉ለአርባምንጭ ሁለገብ ስታዲየም ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

🚧ለአርባምንጭ ሁለገብ ስታዲየም ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀምጧል፡፡

🏷የመሠረት ድንጋዩን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ አስቀምጠዋል።

⭐️ስታዲየሙበአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ደረጃ የሚሰራ ሲሆን÷የመጀመሪያው የግንባታ ሒደት 17 ሺህ ሰው የሚይዝና 16 ሜትር ከፍታ እንደሚኖው ተገልጿል፡፡

Via FBC

@etconp
👍7❤2
#GERD

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ በትናንትናው ዕለት 3ኛው እና 4ኛው ተርባይኖች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታወቁ።

ሌሎቹ ዩኒቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ነው የጠቀሱት።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፈው በጀት ዓመት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የኃይል አቅርቦት 17 በመቶ የሚሆነውን አስተዋፅኦ ማድረጉን ማስታወቁ ይታወሳል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀደም ብለው ሥራ የጀመሩት 2 ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት መቻላቸው የተበሰረው ከሁለት ዓመት በፊት በ2014 በዚሁ በያዝነው ወር ውስጥ ነው።

@etconp
👍15❤4👏1🙏1