Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Ethio Construction Engineering
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-             የቀጠለ.. .) 2.የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Contract security/ Performance  የውል ማስከበሪያ ዋስትና (contract security) ወይም የመልካም ሼል አፈጻጸም ዋስትና (performance bond) የሚባለው አንድም ግራ ቀኙ ለገቡት ውል መልካም አፈጻጸም ሲባል በአንድ ሦስተኛ ወገን የሚሰጥ ዋስትና ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም…
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-

                    
                               የቀጠለ.. .)

3.የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee)

የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሲባል ሥራ ተቋራጩ ጨረታውን አሸንፎ ውል ተፈርሞ ወደ ሥራው ሊገባ ሲል የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሥራ ተቋራጩ የተወሰነ የቅድሚያ ገንዘብ በመስጠቱ ምክንያት ሥራ ተቋራጩ በአንጻሩ ለወሰደው ገንዝብ የሚያቀርበው ዋስትና ነው፡፡

በመሰረቱ በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ጅማሮ የቅድሚያ ክፍያ መኖር በአንድ በኩል ሥራ ተቋራጩ ያለምንም የገንዘብ ችግር ለሥራው የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች መግዣ ይሆነዋል፡፡ ወይም ደግሞ ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ከፍሎ ለንዑስ ተቋራጮች በሚሰጥበት ጊዜ እንደ ሥራ ማስጀመሪያ (mobilization commission) ይሆናቸዋል፡፡

ስለ ቅድሚያ ክፍያ አስፈላጊነት ታዋቂው የኮንስትራክሽን ክሌም ጸሀፊ ጆን ስካይስ እ.ኤ.አ 1999 በወጣው መጽሀፋቸው እንዳብራሩት ቅድሚያ ክፍያ መኖር ለሥራ ተቋራጮች ከመጥቀሙ ባሻገር የጨረታ ወጥ መለኪያ (tender standardization) ተድርጎ ስለሚወሰድ ጭምር ነው፡፡
የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና መኖረን አስመልክቶ የመንግስት ግዥ አዋጅ ቁ.649/2001 በአንቀጽ 48 እንደተመለከተው የቅድመ ክፍያ ሊፈጸም የሚችለው ሥራ ተቋራጩ በቅድሚያ ክፍያ መልክ ከሚወስደው ገንዘብ መጠን ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቀርብ እንደሆነ ይናገራል፡፡

የመንግስት የኮንስትራክሽን ውሎችን የቅድሚያ ክፍያ መጠንን በተመለከተ እኤአ በ2010 የወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ የግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.26 ላይ የቅድመ ክፍያ መጠን የውሉን 30(ሰላሣ) ፐርሰንት መብለጥ የለበትም፡፡ ሆኖም ግን በአገር በቀል የሥራ ተቋራጮች የሚሰራ የመንገድ ግንባታ ሲሆን ግን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ እስከ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት ይደርሳል፡፡
ዝርዝር ሁኔታው በእያንዳንዱ ጨረታ ይገለጻል፡፡

በሥራ ተቋራጩ የሚቀርበው የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው መጠን የተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡ የዋትናው አቀራረብም በቼክ፣ ያል ቅደመ ሁኔታ የሚቀርብ የባንክ ዋስትና ወይም በቅድመ ሁኔታ የሚዘጋጅ የመድን ዋስትና ሊሆን ይችላል፡፡

ሌላው የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ለምን ዓላማ መዋል እንደለበትና በምን አግባብ ሊሰጥ እንደሚችል መመሪያው በአንቀጽ 16.26.7 ተመልክቶታል፡፡ በተለይም የመንገድ እና ህንጻ ግንባታ የሚሰሩ ሥራ ተቋራጮች በቅድሚያ ክፍያው ገንዘብ ስለሚገዙት የማሽነሪ ዝርዝር በመመሪያው መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡


4.የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
                          ይቀጥላል.. .)

@etconp
🙏19👍14❤1
Ethio Construction Engineering
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-                                                     የቀጠለ.. .) 3.የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee) የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሲባል ሼል ተቋራጩ ጨረታውን አሸንፎ ውል ተፈርሞ ወደ ሥራው ሊገባ ሲል የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሼል ተቋራጩ የተወሰነ የቅድሚያ ገንዘብ በመስጠቱ ምክንያት ሼል ተቋራጩ በአንጻሩ…
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-

                    
                               የቀጠለ.. .)

4.የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)

የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡ በተለይም ከላይ ስለዋና ገንዘብ መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡ በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡

የጥገና እና ብልሽጽ አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡ በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡-በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ዐ.ነገር ይነበባል፡-

"ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡ ”


በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
ሆኖም~ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የለውም::

@etconp
👍14👌1
Statement 1: A slump cone measures 100 mm (top diameter), 200 mm (bottom diameter) and 350 mm height.
Statement 2: Slump test helps in qualitatively understanding the setting time of concrete
Anonymous Quiz
20%
Both statements are false
41%
Statement 1 is true and statement 2 is false
22%
Both statements are true
17%
Statement 1 is false and statement 2 is true
👍7❤3👏1
The self-compaction concrete has ______ slump value
Anonymous Quiz
44%
250 mm
16%
500 mm
27%
100mm
13%
650 mm
😢9🙏3❤2🏆1
Quantity of cement required (in terms of 50 kg. bags) to cast a 5 m × 4 m slabs (RCC 1 ∶ 2 ∶ 4) of thickness 10 cm is approximately:
Anonymous Quiz
39%
8 bags
18%
11 bags
24%
13 bags
19%
14 bags
👍16❤10🙏2
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍6❤1
በ እግረመንገዳችን የታዘብነውን እናካፍላችሁ!

ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ወደ 22 ተብሎ በሚጠራው መንገድ ላይ ነው፡፡

ይህን የምትመለከትቱት ... በዚህ መንገድ ይታይ የነበረው ትንንሽ የመንገድ መበላሸቶችና ጉድጓዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ሰፋ መለስተኛ ባህር በመለወጥ ላይ ናቸው፡፡

በተለይ አደይ አባባ ስታዲየም እስክትጨርሱ ያለው የጎርፍና የመንገድ ብልሽት መኪና የሚያበላሽና ለ እግረኞች እዳ ሆንዋል፡፡

በጅምር ላይ ያለው አደይ አበባ ስታዲየም አጥሩን እያጠበበ ሲሆን ለመንገዱ የውስጥ ቱቦዎች እየገቡ መሆኑ ይታያል፡፡

ይህ መንገድ እንደሌሎቹ መንገዶች በፍጥነት ሊሰራ ከሚገባው ውስጥ ይመስለናል፡፡

መንገዱ መቼ ይሆን ቀን የሚወጣለት ያስብላል?

@etconp
❤8👍5
ከመገናኛ ሲኤምሲ የተዘረጋውን የባቡር መስመር ለማንሳት ሲካሄድ የቆየ ጥናት መጠናቀቁ ተሰማ


በ2008 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት፣ ሥራውን ሲጀምር 41 ባቡሮችን በመያዝ ነበር፡፡ ባቡሮቹ አገልግሎት መስጠት በጀመሩ በጥቂት ጊዜያት ብልሽት ሲያጋጥማቸውና አገልግሎት መስጠት ሲያቆሙ መመልከት የተለመደ ነበር።

ከ475 ሚሊዮን ዶላር በላይ የወጣበት የከተማዋ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት፣ የታሰበውን ትርፍ በማግኘት ዕዳውን መክፈል ቀርቶ፣ ለመለዋወጫ ዕቃዎች ግዥና ለሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎች ድጎማ እየተደረገለት ቆይቷል። 

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ገብቶ በነበረው ውል መሠረት፣ ዋናውን ብድርና ወለዱን በዓመት ሁለት ጊዜ እየከፈለ በአሥር ዓመታት ውስጥ የተገነባበትን ወጪ እንዲከፍል መስማማቱን፣ ከዚህ በፊት ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለሪፖርተር መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ ነገር ግን ከ2008 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 2013 ዓ.ም. ድረስ 16 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ማስመዝገቡን ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

Via ሪፖርተር

@etconp
👍8❤1
👉የኢትዮጵያ የህንጻ ኮዶችን የሚያሻሽልና አዲሶችን የሚያካትት ፕሮጀክት ስምምነት ተካሄደ

🚧የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን  ነባር የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የሚያሻሽልና አዳዲዲስ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የሚያካትት ፕሮጀክት ስምምነት ከአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር ተፈራርሟል።

🏷ነሀሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የስምምነት ፊርማ ስነስርአት ላይ እንደተመለከተው 20 ነባርና በስራ ላይ የሚገኙ የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የማሻሻልና የማዘመን እንዲሁም 10 አዳዲስና አስገዳጅ ኮድና ስታንዳርዶችን የማዘጋጀት ፕሮጀክት ነው።

⏺ለፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በኩል 57 ሚሊዮን ብር የተበጀተ ሲሆን የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ11 ወር አገባዶ ያስረክባል።

▶️ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ  እና የኢንስቲትዩቱ ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ልብሰወርቅ ነጋሽ ተፈራርመዋል።

▶️በስነስርአቱ ላይ á‹¨áˆáˆˆá‰ą ተቋማት የስራ ሀላፊዎች በሰነዶቹ ዝግጅት ላይ መካተት ያሉባቸውና ትኩረት በሚሰጣቸው ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

🚧የ ኢትዮጵያ ህንጻ ኮዶች  ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ሶስት ጊዜ ክለሳና ማሻሻያ የተካሄደባቸው ሲሆን የኮንስትራክሽን ዘርፉ ፍላጎት ውስብስብ መሆን፣ እንደሀገርም በዘርፉ ከፍተኛ ለውጥ  በመኖሩ እና አዳዲስ ግብአቶችና አሰራሮች  እያደጉ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህን ነባራዊ ሁኔታዎች ያገናዘበ የኮድና ስታንዳርድ ማሻሻያና አዳዲስ ሰነዶች ዝግጅት እንደሚደረግ ተሰምሮበታል።

💫በቀጣይም የዘርፉን ውጤታማነት ከፍ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን  ለማከናወን ሁለቱ ተቋማት ግንኙነታቸው እንደሚጠናከር በስምምነት ስነስርአቱ ላይ ተመልክቷል።

@etconp
👍17👏4
@etconp EBCS 1-8.rar
122.5 MB
📚ETHIOPIAN BUILDING CODE STANDARD
.
it is compressed by zip file you should use wrinrar to extract the file.

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
@ETCONp ASTM MNL 41 .PDF
9 MB
Fracture and Fatigue Control in Structures - Applications of Fracture Mechanics


Author(s): Barsom, John M.; Rolfe, Stanley T.

Series: MNL 41

Publisher: ASTM International,

Year: 1999

https://t.me/ETCONpWORK
👍12🙏4❤1👌1
የካንቲቲ ሰርቨየሮች ሚና?🚧


💫የግንባታ ፕሮጄክቶችን የፋይናንስ እና ህጋዊ ጉዳዮችን በመምራት የቁጥር ቀያሾች በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

🚧ዋና ኃላፊነታቸው የሚያጠቃልሉት፡-

1. የወጪ ግምት፡- የቁሳቁስ፣የጉልበት፣የመሳሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን በግንባታ ፕሮጀክት
ውስጥ ያሉ ወጪዎችን በትክክል የመገመት የቁጥር ቀያሾች ሃላፊነት
አለባቸው።

የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያደርጉ የሚያግዙ ትክክለኛ ግምቶችን ለማቅረብ ያላቸውን እውቀት እና የግንባታ ወጪ እውቀታቸውን ይጠቀማሉ።


2. የዋጋ ቁጥጥር፡- የፕሮጀክት ወጪን በቅርበት በመከታተል የፕሮጀክት ወጪን በመቆጣጠር ፕሮጀክቱ በበጀት ውስጥ መቆየቱን ያረጋግጣል።

ሊከሰቱ የሚችሉ ወጪዎችን በመለየት ከፕሮጀክት ቡድኖች ጋር በጥራት ላይ ጉዳት ሳያስከትሉ ወጪዎችን ለመቀነስ መንገዶችን ይፈልጋሉ።


3. ግዥ፡ የቁጥር ቀያሾች በግዥ ሂደቱ ላይ የጨረታ ሰነዶችን በማዘጋጀት እና በመገምገም፣ ከአቅራቢዎችና ከንዑስ ተቋራጮች ጋር ውል በመደራደር እና ከአቅራቢዎች ጋር ያለውን ግንኙነት በመምራት ቁሳቁስና አገልገሎት በበጀት ውስጥ እንዲደርሱ ያግዛሉ።


4. እሴት ኢንጂነሪንግ(Value Engineering)፡- የቁጥር ቀያሾች ወጪን ለመቀነስ እና የግንባታ ፕሮጀክቶችን በእሴት ምህንድስና ለማሻሻል እድሎችን ይለያሉ።

የፕሮጀክት ወጪዎችን ለማመቻቸት የሚያግዙ አማራጭ ቁሳቁሶችን፣ የግንባታ ዘዴዎችን እና የንድፍ መፍትሄዎችን ለመመርመር ከአርክቴክቶች፣ መሐንዲሶች እና ተቋራጮች ጋር በመተባበር ይሰራሉ።


5. የስጋት አስተዳደር፡- የቁጥር ቀያሾች ከግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዘው ሊከሰቱ የሚችሉትን የፋይናንስ፣ ህጋዊ እና ቴክኒካል ተግዳሮቶች
አስቀድመው በመለየት ከግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዘው የሚመጡትን
ስጋቶች ይገመግማሉ።

ለአደጋ ቅነሳ ስልቶች ምክሮችን ይሰጣሉ እና ያልተጠበቁ ጉዳዮችን ተፅእኖ እንዴት መቀነስ እንደሚችሉ የፕሮጀክት
ቡድኖችን ይመክራሉ።


6. የኮንትራት አስተዳደር፡- የግንባታ ኮንትራቶችን በማስተዳደር ረገድ የቁጥር ቀያሾች ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ፣ የኮንትራት ውሎችን እና ሁኔታዎችን መገምገም፣ የክፍያ ማረጋገጫዎችን ማዘጋጀት እና በፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል አለመግባባቶችን በመፍታት።
ሁሉም ተዋዋይ ወገኖች የውሉን ውል መከበራቸውን እና ክፍያዎች
በትክክል እና በሰዓቱ መፈጸሙን ያረጋግጣሉ

በአጠቃላይ

ብዛት ቀያሾች በፕሮጀክቱ የሕይወት ዑደት ውስጥ ወጪዎችን፣ ውሎችን እና አደጋዎችን በብቃት በመምራት የግንባታ ፕሮጀክቶችን የፋይናንስ ስኬት ለማረጋገጥ
ይረዳሉ።

እውቀታቸው እና ትኩረታቸው በግንባታ ፕሮጀክት አሰጣጥ ላይ ተጠያቂነትን፣ ግልፅነትን እና ቅልጥፍናን ያነሳል።

ቴሌግራም መልዕክት መስጫ ቦት
t.me/ETCONpBOT • ••☜|]


@etconp
 
👍14👌1