የመዲናዋ ታላላቅ ፕሮጀክቶች አቅዶ የመፈጸም አቅም የፈጠሩ ናቸው
የአዲስ አበባ ከተማ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት በመዲናዋ እስካሁን ያከናወናቸው የግንባታ ሥራዎች በጥራት የመገንባትና በወቅቱ የመፈጸም መልካም ተሞክሮ የተገኘበት መሆኑ ተገለጸ::
የግንባታ ሥራዎቹም 90 በመቶ ያህል በእቅዱ መሠረት የተፈጸሙ መሆናቸውን አስታወቀ::
የጽህፈት ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምሬሳ ልኪሳ የፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ጽህፈት ቤቱ እያከናወናቸው ያሉ የግንባታ ሥራዎች ውል በታሰረላቸው የጊዜና የገንዘብ መጠን በእቅዳቸው መሠረት የተከናወኑ መሆናቸውንና 90 በመቶ ያህሉም በእቅድ መሠረት የተፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል:: በእስካሁኑ ሥራዎቹም አቅዶ የመፈጸም አቅም መፍጠር መቻሉን አስታውቀዋል::
እንደ ኢንጂነር ምሬሳ ገለጻ፤ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ በእቅዱ መሠረት ካከናወናቸው የግንባታ ሥራዎችም የታላቁ ቤተመንግሥት የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) እና ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ህንፃ (የህንፃ ኮምፕሌክስ)፣ አብርኆት ቤተ መፃሕፍት፣ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት፣ በኮልፌና አያት አካባቢዎች የተከናወኑት የገበያ ማዕከላት ግንባታዎች እንዲሁም የኢንዱስትሪ ክላስተር ለአብነት ይጠቀሳሉ::
በተለይም የኢንዱስትሪ ክላስተሩ ሁለት ክፍሎች እንዳሉትና በአንደኛው ክላስተር 35 ለመገንባት ታቅዶ 45 በመፈጸም ከእቅድ በላይ መከናወኑን እንዲሁም በሁለተኛው ክፍል 20 ለመገንባት ታቅዶ 18 መፈጸሙን ኢንጂነር ምሬሳ ጠቅሰዋል::
ይሄን ውጤት ማስመዝገብ የተቻለው ለሥራው ጊዜ በመስጠት፣ ጥራት ላይም እንዲሁ ትኩረት በማድረግ በአጠቃላይ ቁርጠኛ በመሆን እንደሆነም አክለው ተናግረዋል::
በዚህ ወቅት የግንባታ ዕቃና የሲሚንቶ ዋጋ መናር ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሆነና የክረምት ወቅትም ለግንባታ ሥራ ምቹ እንዳልሆነ የጠቀሱት ኃላፊው፤ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ እነዚህን ሁሉ ታሳቢ አድርጎ ኃላፊነቱን በስኬት ለመወጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል::
በዚህ ፕሮጀክት የተገኙ ልምዶችና የተወሰዱ ትምህርቶች የቴክኖሎጂ ሽግግር ከመገኘቱ በተጨማሪ ሥራን በአግባቡ ካለመወጣት ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን በማስቀረትና የተሻለ የሥራ ባህልን በማዳበር ከፍተኛ ትምህርት እንደተገኘበት ኢንጂነር ምሬሳ ጠቁመዋል::
በፕሮጀክቱ በጥራት የመገንባትና በወቅቱ የመፈጸምን አቅም ጭምር ገንብተንበታል ሲሉ ገልጸዋል:: ፕሮጀክቱ ላይ የተገኙት መልካም ተሞክሮዎች ተቀምረው ለወደፊትም ሥራ ላይ ማዋል የሚቻል እንደሆነ ጠቁመዋል::
ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር በኩልም ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ በሚያከናውናቸው የግንባታ ሥራዎች ከከፍተኛ እስከ አነስተኛ የሥራ ዘርፎች ዜጎችን ያሳተፈ መሆኑንና እስካሁን ለ10 ሺህ 540 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰዋል::
ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ እያከናወናቸው ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እርስ በርስ የተናበቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል::
ኢንጂነር ምሬሳ በመልእክታቸውም በፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ ተሰርተው ለአገልግሎት እየበቁ ያሉ ሥራዎች ለትውልድ የሚሸጋገሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የመዲናዋ ነዋሪም በዚህ እሳቤ እየተገለገለበት ጠብቆና ተንከባክቦ ለተተኪው ትውልድ ማሸጋገር እንዳለበት አሳስበዋል::
Via አዲስ ዘመን
@etconp

👍6👏1🏆1
👉ውድ ቤተሰቦቻችን ለ ዛሬ የ RCC አሪፍ ኖት ከነ የተሰሩ ምሳሌዎች ጋር ልናጋራቹ ወደናል።
🌟እናንተም ለወዳጆቻቹ በማጋራት ኣግዙን።
⚡️Best Notes and worked Exampls Of Roller Compacted Concrete Course 👇👇👇

👍6
❤3