Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የግንባታ ዲዛይን ለተቋራጭ ይሰጣልን?

🌟አንድ ግንባታ ዲዛይን በአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች ከተሰራ በኋላ ሙሉ የዲዛይን ሰነዱ በወረቀት ቅጅ (hard copy) እና በሶፍት ቅጅ (soft copy) ለባለቤቱ ይሰጣል።

🚧ነገር ግን በ’ ከተማ ልማት እና ሥራዎች ሚኒስቴር አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1 (Ministry Of Works And Urban Development Standard Conditions Of Contract Clause 6

⏺(1) ‘Custody of Drawings’) መሰረት፣ የግንባታ ዲዛይኑ የግንባታ ክትትል ለሚያከናውነው ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (supervision engineer) በሶፍት ቅጅ (soft copy) ሊሰጥ የሚችል ቢሆንም ለግንባታ ተቋራጩ (contractor) መሰጠት ያለበት ሁለት

⏺(2) የወረቀት ቅጂዎችን ሲሆን  ያለምንም ክፍያ በባለቤቱ ወጪ መዘጋጀትና ለተቋራጩ መሰጠት አለባቸው።

▶️የግንባታ ተቋራጩ የሚፈልገው ተጨማሪ ቅጂዎች ካሉ በራሱ ወጪ እንዲባዙለትና እንዲሰጡት ማድረግ ይችላል፣ ነገር ግን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማባዛትና ለሦስተኛ (ሌላ) ወገን አሳልፎ መስጠት ተቋራጩን ያስጠይቀዋል። ግንባታው ሲጠናቀቅ ተቋራጩ በውሉ መሠረት በቅጂ የቀረቡትንና የተረከባቸውን ሁሉንም ዲዛይኖች ለመሐንዲሱ (Engineer) እንዲመልስ በሕግ ግዴታ አለበት።

#ConstructionLaw

@etconp
👍15❤2🙏2
👉ማስታወቅያ

🫵ለተከበራችሁ የማኅበራችን አባላት በሙሉ!

መንግሥት በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ አጋርነት (Public Private Partnership) የመኖሪያ ቤት ልማት ፕሮጀክቶችን መከናወን እንደሚፈልግና በዚህ ረገድም እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ሲነገር መቆየቱ ይታወቃል፡፡

አሁንም በዚህ የአጋርነት የልማት ማዕቀፍ ሊሳተፉ የሚችሉ ሥራ ተቋራጮችን በስፋት እንዲሳተፉ ማስፈልጉን በመጥቀስ በነገው ዕለት ማለትም ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በጉዳዩ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

የውይይቱን የሚካሄድበት ቦታ እና ሰዓት እንደተገለፀልን የምናሳውቅ መሆኑን እየገለፅን በዚህ ዓይነቱ የልማት መርኃ-ግብር ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱ ያላችሁ የማኅበራችን አባላት ግን ፍላጎታችሁን ከወዲሁ በዚሁ ገፅ ላይ ለማኅበራችን ፅ/ቤት እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር

@etconp
🙏10👍5❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉ይህ በዚህ ቪድዮ የምታዪት ግንብ የተገነባው ጃፓንን ከሱናሚ አደጋ ለመታደግ ታስቦ ነው።

🚧The great wall of Japan to protect Japan against tsunamis.

@etconp
❤7👍4👌2😢1
@ETCONp Building Cost Rate.xls
1 MB
👉አብዛኞቻችሁ በጠየቃችሁን መሰረት

🚧BUILDING COST RATE ANALYSIS SAMPLE ከዚህ ፅሁፍ አያይዘንላቹሀል።


@etconp
🙏10❤5👍5
👉በ2024 ሊጎበኙ የሚገባቸው ምርጥ ከተሞች የትኞቹ ናቸው?

🌟በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ቱሪስቶች ሊጎበኟቸው የሚገቡ የዓለማችን 10 ምርጥ ከተሞችን የብሪታንያው ታይም አውት ኩባንያ ይፋ አድርጓል፡፡

🚧በዚሁ መሠረት÷ ኒውዮርክ፣ ኬፕታውን፣ በርሊን፣ ለንደን፣ ሊቨርፑል፣ ማድሪድ፣ ሜክሲኮ፣ ቶኪዮ፣ ሮም እና ፖርቶ በቅደም ተከተላቸው መሠረት በ2024 ሊጎበኙ የሚገባቸው ምርጥ ከተሞች ተብለው ተመርጠዋል፡፡

🖱የምርጥ ከተሞችን ምርጫ ለማከናወንም በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች የሚኖሩ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎችን እና ዓለም አቀፍ ፀሐፍትን አነጋግሬያለሁ ብሏል አውት ኩባንያ፡፡

☄የዓለም ምርጥ ከተሞች ምርጫ የተከናወነበት ዋና ዓላማም ቱሪስቶች ከተሞችን አንዲጎኙ ለማነሳሳት ነው ተብሏል፡፡

✨ኩባንያው ይፋ ባደረገው መሰረት ኒውዮርክን ቀዳሚ ከተማ አድርጓታል

✨በተጨማሪም በከተማዋ የሚዘወተሩ ልዩ ልዩ ምግቦች፣ ዕድሜ ጠገብ ሕንጻዎች፣ ታሪካዊ ቦታዎች፣ ዕድሜ ጠገብ ሙዚዬሞች፣ ቴአትር ቤቶች እና ባሕላዊ ትዕይንቶች መኖር ለኒው ዮርክ በግንባር ቀደም ተመራጭነት የራሳቸውን ሚና አበርክተዋል፡፡

🖱በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ልትጎበኝ የሚገባት ከተማ ተብላ በሁለተኛነት ለተመረጠችው ኬፕታውንም÷ በባሕር መከበቧ፣ ተራራማ አካባቢ ላይ መገኘቷ እና ማራኪ የተፈጥሮ ገፅታ መላበሷ ውበት ሆነውላታል፡፡

🚧የኬፕታውን ባሕላዊ ጨዋታዎች፣ አለባበሶች፣ የምሽት ቴአትር ቤቶች፣ ሬስቶራንቶች፣ የወይን እርሻዎችም ለከተማዋ መመረጥ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡

🚧በሌላ በኩል የበርሊን ግንብ፣ የሪችስታግ ሕንጻ፣ የብራንደንበርግ በሮች፣ የአይሁዶች ሙዚዬም እና ሌሎች ታሪካዊ ሥፍራዎች ውበት ያላበሷት የጀርመኗ በርሊን ልትጎበኝ የሚገባት ምርጥ ከተማ ተብላ በሦስተኛ ደረጃ ላይ እንድመረጥ አድርገዋታል፡፡

@etconp
👍10😁1
✋ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ እስቲ ይቺ ከታች ያለችው ጥያቄ እንወያይባት

👉አንዳንድ የግንባታ ስራ ውሎች ላይ የፕሮጀክት የመዘግየት የጉዳት ካሳ (Liquidated Damage) ለማስላት 0.1% x የቀሪ ሰራዎችን (Remaining Works) የሚል ነገር ይካተታል።

🚧ለእንደነዚህ አይነት ውሎች የውል ጊዜያቸው ካለቀ በኋላ Interim payment ቢጠየቅ Liquidated Damage እንዴት ሊሰላ ይችላል?

🚧የውል ጊዜው ካለቀ በኋላ የተስሩ እና በክፍያ ሰነዱ ላይ በተካተቱት ስራዎች ላይ ብቻ ነው ወይስ አጠቃላይ የውል ጊዜው ካለቀ በኋላ በተሰሩትና ባልተሰሩትም (ወደፊት በሚሰሩት) ስራዎች ጭምር በማካተት?

#ConstructionLaw

📩ሀሳብ አስተያየትዎ ከታች ባለው ሊንክ ፃፉልን እና እንወያይበት
.
http://t.me/COTMp
❤6🕊2
👉ስኬል/Scale/

➡️ዛሬ ለ አንድ የህንፃ ፕላን ለማንበብ ከሚጠቅሙን አንዱ የሆነውን ስኬልን እናያለን።

▶️አርክቲክቱ የህንፃው ፕላን ዲዛይን ሲያደርግ ከሚገነበው ቤት እኩል መጠን ያለው አድርጎ መስራት አይችልም።

▶️በዚህም የተነሳ በስኬል አሳንሶ ሶፍትዌር(AutoCAD) ላይ ዲዛይን ያደርገውን በወረቀት ፕሪንት ተደርጎ በተቀመጠው ስኬል መሰረት ህንፃው ይገነባል።

➡️ለተለያየ አላማ የተለያዩ የስኬል አይነቶችን ሊጠቀም ቢችልም ለ ህንፃ እና መንገድ ግንባታ በብዛት የሚጠቅሙ የ ስኬል አይነቶች የሚከተሉት ናቸው:-

🚧1. 1:200 ሲነበብ አንድ ለሁለት መቶ ሲሆን ትርጉሙም 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 200 ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።

🚧2. 1:100 ሲነበብ አንድ ለአንድ መቶ ሲሆን ትርጉሙም 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 100ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።

🚧3. 1:50 (አንድ ለ ሃምሳ) ትርጉሙ 1 ሚ.ሜ ፕላን ላይ 50 ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።

🚧4. 1:20 (አንድ ለ ሃያ) ትርጉሙ 1ሚ.ሜ ፕላን ላይ 20ሚ.ሜ መሬት ላይ ይወክላል ማለት ነው።

#Architecture

@etconp
👍23❤2
Demolition

Building demolition is the process of dismantling structures along with the materials used in the construction of the property. A building is demolished for various reasons such as: it’s past its span of serviceability, the structural integrity is compromised, parts of the establishment will need to be refurbished to improve its quality and value.


Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=OGQ5ZDc2ODk2ZA==

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp?mibextid=LQQJ4d

@etconp
👍13
👉ኦቪድ ቤቶች ባንክ ወደ ስራ ሊገባ ነው ተባለ

ኦቪድ ቤቶች ባንክ አክሲዮን ማህበር ወደስራ ሊያስገባው የሚያስችለውን የአክሲዮን ሽያጭ በስካይላይት ሆቴል ባካሄደው መርሃ ግብር አስጀምሯል።

ባንኩ 20 ቢሊዮን ብር ካፒታል ለማሰባሰብ የሚረዳውን የ20 ሚሊዮን የአክሲዮን ሽያጭ ያቀረበ ሲሆን የአክሲዮን ሽያጩ ሥራ እንዲጀምር የሚያስፈልገውን ካፒታል ለማሰባሰብ የሚረዳው መሆኑ ተገልጿል።

ከአክስዮን ሽያጭ የሚሰበሰበው ገንዘብ ባንኩ በመላው ኢትዮጵያ የቤትና የቤት ብድር አቅርቦትን የማስፋፋት ተልዕኮውን እንዲወጣ ያስችለዋል ተብሏል።

የባንኩ ዝቅተኛ የግለሰብ አክሲዮን ግዥ 200,000 ብር ፣ ከፍተኛው 1 ቢሊዮን ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሥራ ለመጀመር 5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የሚያስፈልገው እንደሆነ ተገልጿል።

ኦቪድ ኮንስትራክሽን በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ 60,000 ቤቶችን ለማልማት ያቀደ ሲሆን ባንኩ እቅዱን ለማሳካት ትልቅ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

የቤቶቹ ግንባታ 450 ቢሊዮን ብር ይፈጃል የተባለ ሲሆን በኦቪድ ኮንስትራክሽንና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ70፡30 የሽርክና ስምምነት መሰረት የሚገነባ መሆኑ ተጠቁሟል።

የከተማ አስተዳደሩ በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለልማት የሚውል 460 ሄክታር የሚጠጋ መሬት ማዘጋጀቱም ነው የተገለፀው።

@etconp
👍16❤2
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706 ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👍7❤1
👉የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor)

🚧የግንባታ ዋጋ በሚወጣበት ጊዜ የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor) የሚባል ጽንሰ ሀሳብ አለ።

🌟የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor) ማለት “አንድ ሰው ወይም ማሽን በተመሳሳይ ሰዓት ስንት ሥራዎች ላይ ሊሳተፍ ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ መሰረት አድርጎ የሚሰላ የዋጋ ማባዣ መረጃ ሲሆን ብዙ ጊዜ በሰው ኃይል ላይ የሚተገበር ነው።

🖱ለምሳሌ፦ አንድ ፎርማን በአንድ ፕሮጀክት ላይ የሚሰሩ የቁፋሮ፣ የድንጋይ ግንባታ፣ የአፈር ሙሌት፣ የፌሮ ሥራዎችን ሊቆጣጠር ይችላል።

⏺በዚያ ሰዓት ፎርማኑ አራት ሥራዎችን እየተቆጣጠረ ስለሆነ የጠቃሚነት ተሳትፎው (Utilization Factor) ለአራት ሥራዎች ነው ማለት ነው።

▶️ይህ ማለት ለቁፋሮ፣ ለአፈር ሙሌት፣ ለፌሮ ሥራ፣ ለድንጋይ ግንባታ ሥራዎች የፎርማን አስተዋጽኦ ለእያንዳንዳቸው ያላቸው 25%፣ 25%፣ 25%፣ 25% ነው ማለት ነው። በዚህ አግባብ ለአንዱ ሥራ ዋጋ በሚወጣበት ጊዜ የፎርማን አስተዋጽኦ በ25% ይባዛል ማለት ነው።

🖱ለምሳሌ፦ አንድ ፎርማን በሰዓት 75 ብር የሚከፈለው ቢሆን እና የቁፋሮ ሥራን ዋጋ እያሰላን ቢሆን በቁፋሮ ሥራ የዋጋ ስሌት ውስጥ የፎርማኑ በሰዐት ይከፈለው የነበረው 75ብር በ25% (0.25) ይባዛል ማለት ነው።

⏺ቀሪዎቹ 75% ክፍያዎች በሌሎቹ ሦስት ሥራዎች ሂሳብ ስሌት ውስጥ የሚካተቱ ይሆናል።

⏺በተመሳሳይ ሰዓት አንድ ሥራ ላይ ብቻ የመሳተፍ ዕድል የሚኖራቸው ሰራተኞች ላይ ግን የጠቃሚነት ተሳትፎው (Utilization factor) ሁልጊዜ አንድ (1) ነው።

🖱ለምሳሌ፦ የቁፋሮ ሰራተኛ በአንድ ጊዜ ቁፋሮ ብቻ እንጂ እየቆፈረ እያለ ሌላተጨማሪ ሥራ ሊሰራ አይችልም።

@etconp
👍35❤5
Adwa 00 project at the verge of completion

📍 piyassa Addis Ababa Ethiopia 🇪🇹


Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=OGQ5ZDc2ODk2ZA==

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp?mibextid=LQQJ4d
👍8❤4🏆2
👍15❤4💯2
WHAT IS PURPOSE OF A
"COMPOSITE MATERIALS" ?
Composite structure = RC + Frame Steel section Reference CBE headquarter (ንግድ ባንክ ዋና ቢሮ)
Anonymous Quiz
11%
Enhance termal insulation
9%
Provide decorative finishes
71%
Combine the strenghts of different materials
9%
None
👏9❤5🏆2
👍24❤9💯5🕊2
👉The Largest Hotel in the World, Abraj Kudai with a staggering...

🚧10,000 Rooms

🚧4 helipads

🚧Can accommodate 30,000 guest at a time

🚧Spanning 1.4 million square meters is currently under construction in Saudi Arabia.

@etconp
👍17❤4
👉የኮንስትራክሽን ባለሙያ ብቃት ማረጋገጫ

(ክፍል አንድ)

🌟በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የወጣ "የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ቁጥር 648/2013" የሚል ስያሜ የተሰጠው መመሪያ  አንቀጽ 15 (1 እና 2) ላይ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን እና ሙያተኖችን  ሙያተኞች በሦስት ዋና ዋና ምድቦች ከፍሏቸዋል።

🚧ምድብ ሀ፦ አነ ስተኛ ሙያተኛ

   ~ ደረጃ I
   ~ ደረጃ II

🚧ምድብ ለ፦ መለስተኛ ሙያተኛ

   ~ ደረጃ III
   ~  ደረጃ IV

🚧ምድብ ሐ፦ ከፍተኛ ባለሙያ

   ~ ምሩቅ ባለሙያ
   ~ ፕሮፌሽናል ባለሙያ
   ~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል ባለሙያ

🖱የእያንዳንዳቸውን ዘርፎች መለኪያ በዝርዝር በተከታታይ የምገልጽ ሲሆን ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ አራት (ደረጃ I - ደረጃ Iv) ያሉአነስተኛ እና መለስተኛ ባለሙያዎች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ወስደው ያለፉት ሙያተኞች ብቻ መሆን አለባቸው።

🖱ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያላቸው ግን በከፍተኛ ባለሙያ ማዕረግ የሚመደቡ ሲሆን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና መስጠት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያሉት ምስክር ወረቀት ለማግኘት የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ናቸው።  

⏺የባሙያ  ብቃት ማረጋገጫ ወይም ምዝገባ የሚደረገው የትምህርት ተቋሙ ወይም የብቃት ምዘና ማዕከሉ በሰጠው ምስክር ወረቀት ላይ በተጻፈው የሙያ  አይነት (Face value) መሠረት ይሆናል።

⏺የብቃት ማረጋገጫ ወይም ምዝገባ የሚቀርብ የስራ ልምድ በኢንደስትሪው ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊነትን የሚያሳይና ባለሙያው ወይም ሙያተኛው  የተመደበበትን የስራ መደብ፣ የስራው የ ቆይታ ጊዜ፣የስራ ግብር እየተቆረጠ ለሚመለከተው አካል ገቢ እየተደረገ  መሆኑን  ገልጾ የደብዳቤ ቀን ፤  ቁጥር፣  የኃላፊ ፊርማ፣  እንዲሁም የድርጅቱን  ማህተምና አድራሻ የያዘ መሆን ይኖርበታል።

🫵ይቀጥላል ....


@etconp
👍35❤12🙏4💯2
ጀርመን አደባባይን በማንሳት በትራፊክ መብራት የመተካት ሥራ ተጀመረ!

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ አደባባዮች ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ።አሁን ላይ አደባባዮችን በማንሳት በትራፊክ መብራት የመቀየር ሥራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ጀርመን አደባባይ አንዱ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት የማሻሻያ ስራ የተጀመረበት ይህ አደባባይ ከኃይሌ ጋርመንት - መብራት፣ ከአየር ጤና፣ ከጎፋ እንዲሁም ሜክሲኮ ሳር ቤት የሚንቀሳቀሱ አሽከርከሪዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ የአደባባይ ማሻሻያ ስራ መከናወኑ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትና ጫና በአግባቡና በፍጥነት ለማስተናገድ የሚያግዝ ይሆናል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ስራውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማይበዛባቸው ክፍለ ጊዜያት በመስራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። የመንገዱ ተጠቃሚዎችም የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩላቸውን አውንታዊ ድርሻ እንዲወጡ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

@etconp
👍9😢1