Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍2
👉ሁሉንም የሸገር ክፍለ ከተሞች የሚያገናኝ የሸገር ታላቁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀመረ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው የሸገር ታላቁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

በአምስት ዓመታት እንደሚጠናቀቅ የተመላከተው150 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገድ÷ ሁሉንም የሸገር ከተማ ክፍለ ከተሞች እንደሚያገናኝ ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያው ዙር በ4 ነጥን 5 ቢሊየን ብር የ38 ነጥብ 5 ኪሎሜትር ግንባታ እንደሚከናወን የተገለጸ ሲሆን÷ ይህም ከኩራ ጅዳ በመነሳት ጣፎ፣ ኮዬ ፈጨ እና ገላን ክፍለ ከተሞችን ያገናኛል ተብሏል፡፡

@etconp
👍24
👉የፕሮጀክቶች መዘግየት ከ16 ቢሊዮን በላይ ብር ተጨማሪ ወጪ አስወጥቷል

የመጀመሪያ ውላቸው ሳይጠናቀቅ በሌላ ጨረታ ወደ ግንባታ የገቡ 13 ፕሮጀክቶች ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ማስከተላቸውን ዋና ኦዲተር ይፋ አደረገ፡፡ የፕሮጀክቶች መቋረጥ የሚያስከትለውን ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ሊቀንስ የሚችል አሠራር ባለመዘርጋቱ በናሙና ከታዩ 41 የተቋረጡ ፕሮጀክቶች ውስጥ በመጀመሪያ ውለታቸው ሳይጠናቀቁ በሌላ ጨረታ ወደ ግንባታ የገቡ 13 ፕሮጀክቶች በመንግሥት ላይ በድምሩ 16 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ማስከተላቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ይፋ አድርጓል፡፡

የፕሮጀክቶች መቋረጥ በመንግሥት ሃብት ላይ እየፈጠረ ያለውን ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ሊቀንስ የሚችል ሥራ አስቀድሞ እየተሠራ ባለመሆኑ የተፈጠረ ችግር መሆኑን ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ አመልክተዋል።

የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ባቀረበው የ2015 ዓ.ም የፌዴል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲትና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ የምክር ቤት አባላት በፕሮጀክቶች መቋረጥ የሚደርሰውን የገንዘብ ብክነት የሚቀንስ አሠራር እንዲዘረጋ እንዲሁም ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠይቀዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሪፖርት ካካተታቸው ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የፌዴራል መንግሥት የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ የተቋረጡ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች አፈጻጸም አንዱ ነበር፡፡

በፌዴራል በጀት የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን ያያዙ ሥራ ተቋራጮች የያዙትን ፕሮጀክት ሳያጠናቅቁ ወይም አፈጻጸማቸው ሳይታይ በሌላ ጨረታ ላይ እንዳይወዳደሩ የሚከለክል አሠራር ሥርዓት ተዘርግቶ ቁጥጥር እና ክትትል አለመደረጉን ሪፖርቱ አንስቷል፡፡

በዚህ ምክንያትም የውል ዋጋቸው በድምሩ 10 ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ 12 ፕሮጀክቶች በሁለት ሥራ ተቋራጮች የተያዙ መሆናቸውንም ነው ያመለከተው፡፡

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በውስን ፕሮጀክቶች ክትትልና የቁጥጥር ሥራ የጀመረ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያ በምትተገብረው የፕሮጀክት ልክ የተደራጀና የተቀናጀ የቁጥጥርና ክትትል ሥራ አለማከናወኑን ጠቁሟል፡፡

በዚህም ምክንያት በናሙና ከታዩ 41 የተቋረጡ ፕሮጀክቶች ውስጥ የ38 ፕሮጀክቶች ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና በውለታቸው መሠረት ያልተወረሰ ወይም ገቢ ያልተደረገ መሆኑን አመልክቷል፡፡

ዋና ኦዲተር በናሙና ከተመለከታቸው 41 የተቋረጡ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለ25 ፕሮጀክቶች ከተከፈለው የቅድመ ክፍያ ብር ሦስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ውስጥ ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ተመላሽ ተደርጎ ለሌላ የልማት ሥራዎች እንዲውል ያልተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በሠራተኞችና በኅብረተሰቡ ጤንነትና ደኅንነት ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል እያደረገ ባለመሆኑም በናሙና የታዩ ግንባታ ላይ ባሉ ሰባት ፕሮጀክቶች ላይ የሚሠሩ ተቋራጮች የቅድመ መከላከል ሥራዎችን አሟልተው እየሠሩ አለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ለ24 ሥራ ተቋራጮች መመሪያው የማይፈቅደው ደረጃ የተሰጠ መሆኑና ለልዩ ሥራ ተቋራጭ የተሰጠው የብቃት ማረጋገጫ ዘርፍ እና በመመሪያው ላይ የተቀመጠው ዘርፍ የማይመሳሰል ሆኖ በኦዲት የተገኘ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

በጠቅላላ፣ በሕንጻ፣ በመንገድና በልዩ ልዩ ሥራ ተቋራጭነት ዘርፍ ኢንቨስትመንት ወስደው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ 261 የውጭ ሀገር ሥራ ተቋራጮች እንዳሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያሳያል፡፡

ሆኖም ግን ከ11 ሥራ ተቋራጮች ውጭ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ሁሉንም የውጭ ሀገር ሥራ ተቋራጮች በምዝገባ መመሪያው ላይ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የብቃት ማረጋገጫ በመስጠት ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ አለመሆኑም ተጋልጧል፡፡

ከ11 ሥራ ተቋራጮች ውስጥም የተቀመጠውን አነስተኛ መስፈርት ሳያሟሉ የብቃት ማረጋገጫው የተሰጣቸው ሦስት ሥራ ተቋራጮች መኖራቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

ባለሥልጣኑ ጊዜያቸውን ጠብቀው በማያድሱ ሥራ ተቋራጮች ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ርምጃ እየወሰደ ባለመሆኑ ዋና ኦዲተር በናሙና ከተመለከታቸው 40 ሥራ ተቋራጮች ማኅደር ውስጥ 36ቱ ጊዜያቸውን ጠብቀው አለማደሳቸውን መታዘቡን በሪፖርቱ አመልክቷል። ለባለሥልጣኑ በላከው ሪፖርትም የቁጥጥር ሥራው እንዲጠናከር ማሳሰቢያ መሰጠቱንም አመልክቷል፡፡

Via ኢፕድ

@etconp
👍9❤5
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍8❤1
👉What is Differential settlement?

⏺What are the Causes of differential settlement?

❇️Differential settlement is the term used in structural engineering for a condition in which a building's support foundation settles in an uneven fashion, often leading to structural damage.

All buildings settle somewhat in the years following construction, and this natural phenomenon generally causes no problems if the settling is uniform across the building's foundation or all of its pier supports. But when one section of the foundation settles at a faster rate than the others, it can lead to major structural damage to the building itself.

Differential settlement is not usually a sign of carpentry construction flaws, although some people view it that way. Instead, the phenomenon results when the soil beneath the structure expands, contracts, or shifts in an uneven fashion, causing the foundation to settle at an uneven rate. Thus, the villain is not the carpentry construction practice, but rather the prior evaluation and preparation of the building site itself and the construction of the foundation.

🚧Causes

Uneven settlement of a foundation is always caused by some form of shifting of the soil beneath the foundation, but this shifting can take place for several reasons.

Soils with weak bearing capacity.

Some soils are weak and highly compressible by nature, and buildings erected on such soils require special footings to spread the load over a wider area.

This tends to be an issue about which local building architects are well familiar, and it is generally addressed during the excavation and construction of the foundation.

Poorly compacted soil. Building sites for commercial or residential structures often consist of land that has been artificially leveled and filled for ease of construction. When properly compacted, this fill soil can provide a perfectly solid base for supporting foundations, but when not compacted, the soil may settle and compress unevenly under the foundation, leading to structural damage.

Changes in soil moisture. Soil that is either too dry or too wet can cause foundation settlement. When moisture builds up, soils saturate and lose their load-bearing capacity. Dry soils shrink in volume. Either situation can cause uneven settling of the foundation.

Soil moisture changes can come about due to prolonged drought or by mature trees and other plantings that draw moisture from the soil. In rare instances, leaking in subfloor heating, ventilation, and air-conditioning ductwork can affect the soil moisture beneath the foundation.

Trees and vegetation. Large trees, shrubs, and other vegetation planted along a building's foundation or close to it can gradually draw the moisture out of the soil and cause it to shrink.

This situation is more common with shallow foundations than with basement-level foundations that extend down many feet. When foundation settlement begins to occur several decades after construction, the soil has likely shrunk because large trees are drying out the soil.

Soil consolidation

The weight of a building on the underlying soil, especially fill soils that were added just prior to construction, will naturally compress the soil. Clay soils, in particular, become very dense as moisture is squeezed out. As the soil consolidates and shrinks, the foundation settles downward, a movement that can cause cracks and other structural damage.

Vibration

Vibration of the soil from seismic activity or even from nearby road traffic can cause soils to settle or shift unevenly, leading to structural damage to the building.

📌Symptoms

Symptoms of differential settlement may appear fairly soon after a building's construction, or they may take decades to make themselves known. Obvious signs include cracks in the concrete slab or foundation walls supporting the building, or doors and windows that are out of square or hard to open and close.

@etconp
👍12❤3
👉የጠቅላላ ሁኔታ ኮንስተራክሽን ውል (General Condition of contract)
.
▶የኮንስትራክሽን ሳይት ላይ አንድ ህንፃ ተቌራጭ ስራውን ለማከናወን ወደ ኮንስትራክሽን ሳይት የሚያስገባቸው የህንፃ
ግብዓቶች ከኮንስትራክሽን ሳይት የማስወጣት መብቱ ምን ያህል
ነው ድረስ ነው?
▶አማካሪ/መሐንዲሱ/ ስራው አልቌል ብሎ እስካልተስማማ
ድረስ እቃ ወይም ሰራተኛ ለማመላለስ ከሚወጣ መኪና በስተቀር ማንኛውም ለፕሮጀክቱ የተመደበ የህንፃ ግብዓት ከኮንስትራክሽን ሳይት እንዳይወጣ በደብዳቤ መከልከል ይቻላል።

🔰83. Ownership of plant and material
🔰83.1 All equipment, temporary works, plant and materials provided by the Contractor shall, when brought on the Site, be deemed to be exclusively intended for the execution of the works and the Contractor shall not remove the same or any part thereof, except for the purpose of moving it from one part of the site to another, without the consent of the Engineer Such consent shall, however, not be required for vehicles engaged in transporting any staff, labor, equipment, temporary works, plant or materials to or from the Site.

@etconp
👍20👏1💯1
👉Good morning Ethiopia

🚧unsafe Demolition

@etconp
👍11😢3❤2
11.  The strength and quality of concrete, depend upon :
Anonymous Quiz
6%
A.grading of aggregates
1%
B. surface area of aggregates
2%
C. shape of aggregates
91%
D. all the above
👍26
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
❤2👍1
👉መንግሥት ለፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች ግንባታ ከ2017 ረቂቅ በጀት 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መድቤያለኹ ማለቱን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል።

መንግሥት አዳዲስ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች መገንባት ያስፈለገው፣ ባኹኑ ወቅት የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች ለቢሮ ኪራይ የሚያወጡት ገንዘብ ከፍተኛ በመኾኑ፣ ኪራዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄዱና መስሪያ ቤቶች በተመቻቸ ኹኔታ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ታስቦ እንደኾነ ገንዘብ ሚንስቴር ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል።

የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችን ግንባታ የሚመራው፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ነው።

መንግሥት በቀጣዩ በጀት ዓመት ለስንት የፌደራል መስሪያ ቤቶች ቢሮ መገንባት እንዳቀደ እና ባኹኑ ወቅት ለፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች የቢሮ ኪራይ ምን ያህል ገንዘብ እያወጣ እንደኾነ እንዳልገለጠ ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

ቋሚ ኮሚቴው፣ አዲስ ቢሮዎችን ወይም ሕንጻዎችን የመገንባት አዋጭነቱ በጥናት የተደገፈ ነው ወይ? በማለት ላቀረበው ጥያቄ፣ የገንዘብ ሚንስቴር ሃላፊዎች ጉዳዩ የአዋጭነት ጥናት አያስፈልገውም በማለት መልሰዋል ተብሏል።

@etconp
👍8
👉መሬት ረገጥ ሀብት ግዢ አንዳንድ ጥንቃቄዎች።

✳️Precautions in real estate purchase

🚧መሬት ረገጥ ሀብትን (real estate) ስንገዛ ማሰብና መከወን ያሉብን ቴክኒካዊ ጉዳዮች በ 22 ዝርዝሮች ተቀምጠዋል።  በብዙ ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ስናረግ እንደዚህ በጥልቀት ማየት የሚኖርብን ሲሆን እነዚህ ዝርዝሮች ከ አሻሻጮቹም ሆነ ከነጋዴዎቹ እውቀት በላይ በመሆናቸው ልፋት አከል ስራዎች ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪም አብዛኞቹ መሬት ረገጥ  ሀብቶች የሚሸጡት በአካል በአገር ውስጥ ለሌሉ ደንበኞች ሲሆን ባለሀብቶቹ ከማከራየት ባለፈ እንደኢንቨስትመንት ስለሚያዩአቸው እንደተዘረዘሩት የሚጨነቅ ገዢም ሆነ ገንቢ እንዲሁም ተከራይ አይገጥሙንም። (ያከራየኝ ሰው ቤቱንም አይቶት አያቅም ሲባል አልሰማችሁም)

በቅርቡ ግን ሁላችንም በሰማይ ላይ ተንጠልጥለን መኖራችን ስለማይቀር ሁሉም ቴክኒካዊ ዝርዝሮች  ሁላችንንም አንድ  በአንድ እንደሚያገቡን እሙን ነው። ስለዚህ እነዚህን ጥያቄዎች ለማወቅ አልሚዎችን ስንጠይቅ እንደደፋር ተቆጥረን  " ትገዛ እንደሆነ ግዛ አንተ ምን ስለሆንክ ነው የምትጠይቀው? " አይነት መልስ ልናገኝ እንደምንችል ይገመታል።

ወደዝርዝሩ

1. የአልሚ እና የገዢ ውሉን ህግ ለህግ አዋቂ ከፍሎ ማስመርመር።

2. የአልሚውን የበፊት የማልማት ዝናን መፈተሽ።

3. ከተቻለ የተገነባን  ሀብት መግዛት።

4. የተገነባ ሀብት ከሆነ የቤቱን ፕላን በህንጻ ነዳፊ ማስመርመር። ( እሳት ማጥፍያ ውሀ ስርአት ፣ የእሳት አደጋ ግዜ ማንቅያ ፣ በእሳት ግዜ አደጋ ማምለጫ ደረጃ እሳትና ጭስ የመቋቋም  ስርዓት  ፣ የምግብ ማብሰያ እና መታጠብያ ቤት ሽታ ማስወገጃ ፣ በቂ ተሽከርካሪ ማቆምያ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረግያ ወዘተርፈ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።)

5. የህንጻ አስተዳደር (facility management) ተገማች ወርሀዊ ወጪ ስንት እንደሆነ መጠየቅ።

6. የመነሻ አፈር ምርመራን፣ የግንባታ ወቅት ተከታታይ የብረት እና አርማታ ምርመራ ምስክር ወረቀትን ጠይቆ ማየት።

7. የኤሌክትሪክ ገመዶችና ስርዓቶችን በባለሙያ ማስመርመር። ተጠባባቂ ሀይል አመንጪ መኖሩን እና አቅሙን መጠየቅ። ቁመተ ረጅም ህንጻ ከሆነ ስለመብረቅ መከላከያ ስርአት መጠየቅ።

8. የፍሳሽ መስመር ላይ በተጓዳኝ የሚዘረጋ የማስተንፈሻ ትቦ እና ስርዓት መኖሩን ማረጋገጥ (የፍሳሽ ሽታ ማስወገጃ ዘዴ)

9. ህንጻው የከተማ የፍሳሽ መስመር አጠገቡ መኖሩን ማጣራት (አለበለዝያ በየወቅቱ የፍሳሽ ማስመጠጫ ተሽከርካሪ አዋኪነትን መቀበል)

10. በቂ ውሀ ማከማቻ እና አቅርቦት ስርአት እንዳለው በባለሙያ ማጣራት።

11. የፍሳሽ ማስወገጃ የቁመት ትቦዎች የሚያልፉበት ድምጽ በማያሳልፍ  በተከለለ ቀዳዳ እንደሚያልፍ ማረጋገጥ። (እነዚህ ትቦዎች በድምጽ ስለሚረብሹ በየመታጠብያ ክፍሉ ተጋልጠው መገኘት የለባቸውም)

12. ለተሽከርካሪ መንገድ ቀረቤታ ካለው የድምጽ መከላከያ እርምጃዎች ምን እንደሆኑ ማጣራት።

13. ለሳተላይት ርቀት ማያ (TV) ወይም ለ በይነመረብ ፕሮቶኮል ርቀትማያ (IPTV) የተዘጋጀ መስመር እንዳለው ማረጋገጥ (አለበለዝያ ሁሉም ሰው የሳተላይት ሰሀኑን ሰገነት ላይ ሰቅሎ የህንጻው መልክ እንደሚበላሽ መቀበል)

14. የተጣራ እና ያልተጣራ የሚሸጥ የቤት ስፋትን ማጣራት። (መተላለፍያ፣ ደረጃ፣ ተሽከርካሪ ማቆምያ ወዘተርፈ.... በነዚህ ስፋቶች መካተት አለመካተታቸውን ማጣራት)

15. ከፍታ ተሽከርካሪ (lift) ሰው መጫን አቅምን  ብዛትን  እና ፍጥነትን ማጣራት።

16. የጥያራ  ማረፍያ (airport) በአካባቢው ካለ  ጥያራው የሚያስነሳውን አዋኪ ድምጽ ዴሲቤል በተንቀሰቃሽ ስልክ መለካት።

17. አካባቢው ከቤተእምነቶች በድምጽ ማጉልያ የሚወጡ ድምጾች እንዳሉ ማረጋገጥ።

18. የሚገዛው ቤት ዋና ዋና ክፍሎች አቅጣጫን ማወቅ። (ለምሳሌ ወደሰሜን የሚከፈት ክፍል በፍጹም ጸሀይ የማያገኝ ከመሆኑ የተነሳ በአርማታ በተሰራ ህንጻ ውስጥ ፣በአዲስአበባ ከተማ አውድ እጅግ ቀዝቃዛና የሚደብት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።)

19. የሚቻል ከሆነ አልሚው የመስኮቶች ክፍተት ላይ ትንኝ-ከላ ወንፊትን ከመስታወቶች አዳብሎ እንዲሰራ ማመላከት

20. አካባቢው በቋሚነት ከሚከሰት መጥፎ ሽታ ነጻ እንደሆነ ማረጋገጥ።
21. ልማቱ ላይ እጅግ የበዛ አባወራ እንዲኖርበት የተነደፈ ከሆነ ወደልማቱ የሚወስዱ ተመጣጣኝ ስፋት ያላቸው መጋቢ መንገዶች እንዳሉ ማረጋገጥ።

22. በመጨረሻም ባለብዙ ወለል ባለብዙ መኖርያ  የጋራ መኖርያቤት የሚሰራ ከሆነ እና እንደባህላችን በቀስታ ተቁላልተው የሚሰሩ ምግቦች የሚበስሉባቸው ማብሰያ ክፍሎች የሚኖሩ ከሆነ ማብሰያ ክፍሎች ውስጥ ያለውን የሽታ ማስወገጃ ስርአት በጥልቅ መመርመር ያስፈልጋል። አንደኛ ካንዱ ቤት ወደአንዱ ቡና እና ወጥ ሽታ እንዳንቀባበል ሲሆን።😁 ሁለተኛው ደግሞ ሽታዎች  ከምግብ ማብሰያ ወደመኝታ እና እንግዳ መቀበያ እንዳይገቡ ሲባል ነው።

Via ዳዊት በንቲ

@etconp
👍24❤2🕊1
👉ዘመን ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ማስፋፊያ ሊያካሂድ ነው

🚧የማስፋፍያ ፕሮጀክት ሕንፃ ንድፍ ውድድር አሸናፊ ታውቋል

☄የዘመን ባንክ ያዘጋጀውን የዋና መሥርያ ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት የሕንፃ ንድፍ ውድድር አለበል ደስታ አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች አሸንፏል።

📌የሽልማት ሥነ ስርዓቱ በአዲስአበባ ሂልተን ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፣ ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ አሸናፊዎች ሽልማት የሰጡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኤርምያስ እሸቱ ናቸው።

📌በሕንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የንድፍ ውድድር አንደኛ ከወጣው አለበል ደስታ አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች ቀጥሎ የማ አርክቴክቸር ሁለተኛ እንዲሁም ኢንላብስ ቢዝነስ ሶስተኛ ሊወጣ ችሏል።

✳️ውድድሩን በበላይነት ያስተናበሩት አንጋፋው ህንጻ ነዳፊ ውሂብ ከበደ ሲሆኑ፣ ዳኞች ደግሞ ዶክተር ኢንጅነር ውብሸት ብርሀኑ - ህንጻ ነዳፊ፣ ወ/ሮ ማርሸት መንግስቱ -ህንጻ ነዳፊ፣ አቶ ዳዊት በንቲ ህንጻ ነዳፊ ሲሆኑ አቶ ዘሪሁን ይልማ - መዋቅር ነዳፊ አራተኛው ዳኛ ነበሩ።

🚧ዘመን ባንክ በ1.5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ያስገነባው ባለ 36 ወለል የዋና መስሪያ ሕንፃ ያስመረቀው ከስድስት ወር በፊት ግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑ ይታወሳል።

✳️በ2,300 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈው ህንጻው÷ የስብሰባ አዳራሾች፣ የአካል ብቃት ማጎልበቻ ክፍሎች፣ 6 አሳንሰሮች፣ 200 መኪና የሚይዙ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችና ሌሎች ክፍሎች አሉት ተብሏል፡፡

❇️ዘመን ባንክ ከ15 ዓመታት በፊት በ87 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ካፒታል የተመሠረተ ሲሆን፥ አሁን ላይ ከ100 በላይ ቅርንጫፎቹ 35 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ገንዘብ እንዳለው ተመላክቷል::

https://www.facebook.com/ethioconp

@etconp
👍8❤6
👍13😢1👌1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍3❤2
👉TYPES OF ROAD CURVES

🚧The curves in roadway is categorized as follow :-

⏺1. Horizontal Curve
⏺2. Vertical Curve

📌1. HORIZONTAL CURVE

🔰A horizontal curve offers a changeover among two tangent strips of roadway, facilitating a vehicle to settle a turn at a sluggish rate in spite of a sharp curve.

☄The horizontal curve is again categorized as follow :-

❇️A. Simple Curve

❇️B. Compound Curve

❇️C. Reverse Curve

❇️D. Transition Curve

✅A. SIMPLE CURVE

✳️A simple arc is arranged in the road to set a curve among the two straight line.

✅B. COMPOUND CURVE

✳️This type of curve is formed by combining two simple curves jointly. They curve in the equivalent direction.

✅C. REVERSE CURVE

✳️It is formed by combining two simple curves jointly to curve in the opposite direction.

✅D. TRANSITION CURVE

✳️This type of curve comprises of continuously changing radius that is applied to attach a circular arc to a straight line.

📌2. VERTICAL CURVE

⏺It offers a changeover among two sloped roadways, facilitating a vehicle to settle the elevation rate change at a successive rate in spite of a sharp cut.

👍The Vertical curve is again sub-categorized as follow :-

✳️A. Sag Curve

✳️B. Crest Curve

✅A. SAG CURVE:-This type of curve alters the alignment of the road from uphill to downhill.

✅B. CREST CURVE:-This type of curve alters the alignment of the road from downhill to uphill.

@etconp
👍20❤3
👉ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ሁለቱን አገሮች የሚያገናኝ 220 ኪሜ ርዝመት ያለው መንገድ ሊገነቡ ነው።

🚧738 ሚሊዮን ዳላር የሚያወጣውን መንገድ ለመገንባት የተስማሙት በ ግንቦት 2023 እኤአ ነበር።

✳️የ ደቡብ ሱዳኑ Transitional National Legislative Assembly (TNLA) የኢትዮ ሱዳኑን የድንበር አቋራጭ መንገድ ግንባታ ስምምነት በ June 25 ያጸደቀው ሲሆን ስምምነቱን ለማጽደቅ ለአገሪቱ መሪ ለፕሬዚደንት ሳልቫኪር አቅርቦታል።

Via የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@etconp
👍14