Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍10
✨ሲካሴራም 50
💥ሴራሚክ ንጣፍን ለማስቀመጥ የሚያገለግል ዱቄታማ ማጣበቂያ
💥በውስጡ ከፍተኛ ጥንካሬን ያለው ሲሚንቶ፣ ሲሊከን/ኳርትዝ ንጥረነገር እና የተለያዩ ኬሚካሎችን የያዘ ዱቄታማ ማጣበቂያ ነው።
ጥቅም
📌ውሀን ለሚመጥ ሴራሚክ ንጣፍ ማንጠፊያ
📌በግድግዳ እና በወለል ላይ ለሚሰሩ ንጣፍ ስራዎች

✨SikaCeram -50
💥Powder adhesive to lay ceramic tiles
💥A one-pack premixed adhesive consisting of high resistance cements, selected silicon/ quartz mineral charges and specific additives.
Uses
📌 Laying absorbing ceramic Tiles
📌On walls and floors

📍Head Office
Location: Derar Mall 9th floor opposite to Sahlite Mihret Church

📱+251 929 93 0206
📱+251 929 53 1707  

www.ektceramics.com

#EKTceramics #ethiopia #theklinker #ektceramics #construction #admixture #ceramic #paint #sika #jotun #aquapa #primacera #hanbon #tesaassaabloy #spc #tiles #pprpipe #doorlock #sanitarywares #buildingmaterials
❤3
#ADVERTISEMENTS

💫ከዲዛይን እስከ ፊኒሺንግ ድረስ ብቁ በሆኑ ሰራተኞቻችን በጥራት እየሰራ ደንበኞቻችንን በማስደሰት የሚታወቀው እቴጌ ዲዛይንና ፈርኒቸር አሁንም ጥራታቸውንና ውበታቸውን የጠበቁ ፈርኒቸሮችንና የኢንተሪየር ዲዛይን ስራዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክባችኋለን፡፡

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
✔️ የፊኒሺንግ ስራ
✔️ የዲዛይን ስራ
✔️ የፈርኒቸር ስራ

Etege Design and Furniture, which is known for making our customers happy by working with quality from design to finishing, still maintains its quality and beauty, and we deliver furniture and interior design works at affordable prices.

The services we provide
✔️ Finishing work
✔️ Design work
✔️ Furniture work

አድራሻ፡ ኢምፔሪያል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ከዞላ ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ አባይ ባንክ 1ኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል

📞 ይደውሉልን: 0912270394
0974107073

https://linktr.ee/etegedesign
👍5👌2
👉የቁፋሮ ሥራ (Excavation works) ላይ መረጋገጥ ያለባቸው የቁጥጥር ነጥቦች

🚧የቁፋሮ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቁፋሮዎች፣ አጎራባች ቦታዎች እና የመሬት መንሸራተት መከላከያ ዘዴዎች በባለሙያ ጥናት ሊደረግባቸው ይገባል። ይመረመራሉ።

🏷በመሆኑም በቁፋሮ ሥራ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያው የሚከተሉትን ነጥቦች ትኩረት አድርጎ ማረጋገጥ አለበት።

⏺1. የአጎራባች ወሰንን ከመፍረስ መታደግ፦ በግንባታ ሥራ የመጀመሪያው ተግባር ቁፋሮ ሲሆን ማንኛውም ቦታ አጎራባች የሆነ የሕንጻ ቦታ ወይም መንገድ የሚኖረው ሲሆን ቁፋሮው ወደአጎራባች ወሰን ተጠግቶ የሚከናወን ከሆነ በቁፋሮው መጠጋት አልያም በንቅናቄ (Vibration) የተነሳ የአጎራባች መሬት በመውደቅ ወይም በመንከባለል ለሁለቱም ቦታዎች አደጋ እንዳይፈጥር የሚያስችል ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉን ማረጋገጥ አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ የጎረቤት ወሰን/አጥር/ ቢፈርስ ወይም ሕንጻ ቢወድቅ በመሐንዲሱ የክትትል ድክመት የተነሳ ካሳ እንዲከፍሉ ሊገደዱ ይችላሉ።

⏺2. በሕግ የሚፈቀደውን የውጪ መስመር አለማለፉን ማረጋገጥ፦ ሕንጻው የሚሰራበት የካርታ ቦታ በአካባቢ ልማት (Local development plan) መሰረት ከፍተኛ የኢሌክትሪክ ኃይል (High Electric tension) የሚያልፍበት አልያም የመንገድ ማስፋፊያ ስፋት (Road Widening Area) የሚገባበት ሊሆን ስለሚችል በግንባታ ወቅት የተዘጋጀ አዲስ የፕላን ስምመትን በማመሳከር እንደዲዛይኑ በተፈቀደ ክልል ውስጥ ማረፉን እና በባለቤት ግፊት የተነሳ ያልተፈቀደ ቦታ ላይ አለማረፉን ማረጋገጥ አለበት።

⏺3. በቁፋሮ ክልል ደህንነትን ማረጋገጥ፦ ከቁፋሮው በኋላ ከመሬት ውስጥ ያለው ሥራ (Sub Structure Works) ተጠናቆ የተቆፈረው ክፍል እስኪሞላ ድረስ የሰከረ፣ ወይም የአእምሮ እክል ያለበት፣ ወይም ሕጻናት፣ ወይም ሽማግሌዎች ወደጉድጓድ ገብተው አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከተፈቀደላቸው የግንባታ ሰራተኞች ውጪ ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የታጠረ (Fenced) እና የውስጥ መሸጋገሪያ (Bridge Ladders) የተሰራላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

⏺4. የመሬት ውስጥ ዝርጋታዎች (Underground installations)፦ በሰፋፊ ግቢዎች ውስጥ ለግቢው አግልግሎት የሚሰጡ አስቀድሞ የተዘረጉ የውኃ፣ የኢንተርኔት፣ የመረጃ እና የመብራት ዝርጋታዎች የሚኖሩ ከሆነ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በጥንቃቄ እንዲነሱ አልያም ግንባታው ጉዳት ሳያደርስባቸው እንዲከናወን ማድረግ ይኖርበታል።

⏺5. የቁፋሮውን ልኬት ማረጋገጥ፦ በተለይ በአርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል እና ሳኒታሪ ንድፎች ላይ የተመለከተው ተጓዳኝ የቁፋሮ ሥራ የሚጠይቁትን ልኬቶች ማሟላቱን (ወርዱን፣ ስፋቱን፣ ርዝመቱን፣ ዲያሜትሩን፣ ጥልቀቱን) ጠብቆ ቁፋሮ መንዲከናወን የመቆጠጠርና መከናወኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።

⏺6. ውኃ እንዳይቋጥር ማስደረግ፦ በዝናባማ እና የመሬት ውኃ በሚፈልቅባቸው አካባቢዎች ቁፋሮ እንደተከናወነ ዝናብ ቢዘንብ ቢያንስ የጎርፍ ውሃ እንዳይገባ የመከላከያ ሥራዎች፣ እንዲሁም የመሬት ውስጥ ምንጭ ውሃን የመከላከያ (like: Permeable hardcore layer, geotextile material, channelization...) መንገዶች ተግባራዊ የሚደረጉበት መሆኑን ማረጋገጥና መከታተል አለበት።

⏺7. የቁፋሮ ግብአቶችና ማሽኖችን ደህንነት ማረጋገጥ፦ በቁፋሮ ሥራ መወጣጫ የሚሆኑ የብረት፣ የእንጨት እና የፕላስቲክ ግብአቶችን ብልሽት የሌለባቸው መሆኑ እና ለቁፋሮ ሥራ የቀረቡ የእጅ መሳሪያዎች እና ማሽኖች የደህንነት ችግር የሌለባቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

⏺8. በቂ አየርና ብርሃን የሚገኝበት መሆኑን፦ በጣም ልዩ ሁኔታ የሚባልና በብዙዎቹ ግንባታዎች ላይ የማይገጥም ቢሆንም በውኃ ውስጥ፣ በመሬት ውስጥ ለሚከናወኑ ቁፋሮዎች የሚሳተፉ ሰራተኞች በቂ የሆነ የኦክስጅን አየር ማግኘት ስላለባቸው መሐንዲሱ የአየር ሁኔታውን የሚቆጠጠሩ ማሽኖች፣ አልባሳት እና ብርሃን መቅረባቸውን ማረጋገጥ ማድረግ አለበት።

@etconp

ሌላኛው የቴግራም ቻናላችን: t.me/ETCONpWORK
ሊጽፉልን ካሰቡ፡  t.me/ETCONpBOT
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ethioconp
👍29❤7🕊2
👉ትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜን አሳውቋል።

💫ሚኒስቴሩ በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  (NGAT) ምዝገባ ከሐምሌ 24 እከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም የሚካሄድ እንደሆነ ገልጿል።

🏷የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መማር ፍላጎቱ ያላቸው የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ
https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

@etconp
👍14🙏1
👉 የሾላ ገበያ የተሽከርካሪ ማቆሚያ

🏷የግንባታው ፕሮጀክት 84.2 በመቶ በላይ ደርሷል፤

⏺ከመሬት ስር የሚገነቡ ሁለት ወለሎች እና ከመሬት በላይ አምስት ወለሎች አሉት፤

⏺እያንዳንዱ ወለል በአማካኝ 132 የተለያየ መጠን ያላቸውን ተሽከርካሪዎች የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል፤

⏺በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል፤

⏺ የተሽከርካሪ ማቆሚያው በአጠቃላይ 921 ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የሚስተናገድ አቅም ይኖረዋል፤

⏺መሰረተ ልማቱ በ7 ሺህ 306 ሜትር ስኩዌር ቦታ ላይ ያረፈ ነው፤

⏺ዘመናዊ የደህንነት መቆጣጠሪያ ካሜራ እና የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አስተዳደር ስርዓት (Parking Management System) ያለው፤

⏺ፈጣን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ጣቢያዎች (Fast Electric Car Charging Stations) መሳሪያዎች ይኖረዋል፤

⏺በፕሮጀክቱ ግንባታ ወቅት ከ120 ላላነሱ ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ እድል የተፈጠረ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ከ50 ላላነሱ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል ይፈጥራል፤

⏺ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ለአገልግሎት ሲበቃ በአካባበቢው ላይ የሚስተዋሉትን የተሽከርካሪ ማቆሚያ ችግሮች በመቅረፍ ለትራፊክ ፍሰቱ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታል፤

⏺የፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪ በከተማ አስተዳደሩ በኩል የሚሸፈን ሲሆን 1.5 ቢሊየን ብር የሚፈጅ ይሆናል፤

⏺ የግንባታው ሥራ ተቋራጭ አለም አቀፍ ድርጅት የሆነው ዞንግሚ ኢንጂነሪንግ ነው፤

⏺ግንባታውን እያስገነባ ያለው ተቋም የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ነው።

Via AA Transport Bureau

@etconp
👍11❤4😢1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
❤3👍2
👍7❤3🙏2