Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የባሕርዳር ስታዲየም ግንባታ የፊፋ ደረጃዎችን በሚያሟላ መልኩ እየተከናወነ ነው – ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ

🚧የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡

▶️ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የባህርዳር ስታዲየም ደረጃውን ጠብቆ እንዲሰራ የክልሉ አመራሮች የወሰዱት ቁርጠኝነት ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆን ነው።

🏷ስታዲየሙ የስፖርት ቱሪዝም እና የክልሉ ምጣኔ ሃብት እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አንስተዋል፡፡

💫የባሕርዳር ስታዲየም የፊፋ ደረጃዎችን በሚያሟላ መልኩ ጥራቱን ጠብቆ እየተሠራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

🚧የተጀመሩ ስታዲየሞች ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁና ለተሰሩበት ዓላማ እንዲወሉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መጠየቃቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Via FBC

@etconp
👍6
👉የእግር ኳስ ተወዳጅነትን ተከትሎ በመላው አለም የስታዲየሞች ግንባታ እየተጧጧፈ ይገኛል።

🏷የቴክኖሎጂው ፈጣን ዕድገት የስታዲየሞችን ግንባታ ቀላልና ውስብስብ እንዳይሆንም አድርጓታል።

🚧ቻይና በቅርብ ገንብታ ለአገልግሎት ያዘጋጀችው ስታዲየም  "Qingdao Citizen Fitness Center" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ 60 ሺህ ሰዎች ተቀምጠው ጨዋታዎችን መመልከት የሚችሉበት ነው።

⭐️በተጨማሪም ከዚህ ስታዲየም ውጪ 15 ሺህ ተመልካቾች መያዝና የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች መከታተል የሚችሉበት ምቹ ቦታዎችንም በድምር የያዘ መሆኑ ታውቋል።

@etconp
👍4❤3
👍4❤1
❤5👍3
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍4❤1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍4❤1
👉World Top Ten Construction Contractors

🏷Construction Digital የተባለው መጽሔት የዓለማችንን አስር ግዙፍ ሥራ ተቋራጮችን ዝርዝር በ July 03,2024 ዘገባው ላይ አውጥቷል፡፡

🚧10ኛ.China Communications Construction (CCCC)

⏺17.38 ቢሊዮን ዶላር  የገበያ ዋጋ ያለው ዓለም አቀፍ የመሠረተ ልማት ኩባንያ ሲሆን፣ በትራንስፖርት መሠረተ ልማት፣ የባሕር ላይ የኮንስትራክሸን ስራዎች እና በከባድ ማሽነሪዎች ማምረቻ ላይ የታወቀ ድርጅት ነው።

🚧9ኛ.China Railway Group (CREC)

⏺በቻይና የመሰረተ ልማት እድገት ውስጥ ቁልፍ ሚና ያለው CREC በአፍሪካ እና በደቡብ ምስራቅ እስያ ዋና ዋና ውሎችን በማረጋገጥ በአለም አቀፍ የግንባታ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።

▶️የገበያ ዋጋውም 21.60 ቢሊዮን ዶላር  ነው ፡፡

🚧8ኛ: Pulte Group

⏺በአትላንታ፣ ዩኤስኤ የሚገኘው የቤት ገንቢ የሆነው Pulte Group  የገበያ ዋጋው  21.98 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ኩባንያው በስማርት የቤት ቴክኖሎጂ እና ኃይል ቆጣቢ ዲዛይኖች /smart home technology and energy-efficient designs/  ላይ ያተኩራል።

🚧 7ኛ: NVR

⏺ዋና መሥሪያ ቤቱን በቨርጂኒያ፣ ዩኤስኤ ያደረገ የቤት ግንባታ ኩባንያ ሲሆን የ23.36 ቢሊዮን ዶላር  የገበያ ዋጋ አለው።

🚧 6ኛ: Ferrovial

⏺70,000 ሠራተኞች ያሉት የስፔን ሁለገብ  ሾል ተቋራጭ ነው፡፡

▶️28.54 ቢሊዮን ዶላር  የገበያ ዋጋ ያለው ኩባንያው  በመሰረተ ልማት ልማት ግንባታ ዓለም አቀፍ ታወቂነት ያለው ኩባንያ ነው።

▶️ሌላኛው የስፔን የኮንስተራክሽን ካምፓኒ እን በዓለማችን ታዋቂ የእግር ኳሽ ክለብ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ባለቤትንት የሚተዳደረው ACS Group እጅግ ታዋቂ ከሆኑ የዓለማችን የኮንስትራክሽን ካምፓኒዎች ተርታ የሚመደብ ነው፡፡

🚧 5ኛ: China State Construction Engineering (CSCEC)

⏺31.24 ቢሊዮን ዶላር የገበያ ዋጋ ያለው ኩባንያ ሲሆን እንደ ቤጂንግ ብሄራዊ ስታዲየም እና ዱባይ ቡርጅ ካሊፋ ባሉ ታዋቂ ፕሮጀክቶችን በመስራት ይታወቃል፡፡

▶️ይህ ኩባንያ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በደቡብ ምስራቅ እስያ ያሉ ዋና ዋና የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ አስተዋጽኦ አለው።

🚧 4ኛ: Lennar
ዋና መሥሪያ ቤቱን ሚያሚ፣ ዩኤስኤ አድርጎ የሚንቀሳቀስ 39.11 የአሜሪካ ዶላር ቢሊዮን ዶላር የገበያ ዋጋ ያለው ኮርፖሬሽን ነው፡፡

⏺በዘመናዊ የቤት ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ተቋም ነው።

🚧 3ኛ: D. R. Horton
የአሜሪካ ትልቁ የቤት ገንቢ Horton 44.52 ቢሊዮን ዶላር የገበያ ጣሪያ አለው።

⏺በተመጣጣኝ የቤት ልማትና የመሬት ልማት Affordable housing and Land development/ ላይ ትኩረት በማድረግ ይንቀሳቀሳል።

🚧 2ኛ: Larsen & Toubro (L&T)
በህንድ ውስጥ ግንባር ቀደም የምህንድስና እና ኮንስትራክሽን ኩባንያ የሆነው Larsen & Toubro (L&T) 59.61 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የገበያ ዋጋ ያለው ሲሆን 140,000 ሰዎችን በተለያዩ ዘርፎች ቀጥሮ ያሰራል።

🚧 1ኛ: Vinci
በዓለም ላይ ትልቁ የግንባታ ኩባንያ የፈረንሳይ ተቋም የሆነው Vinci በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና በከተማ ልማት ውስጥ ግንባር ቀደም መሪ ድርጅት ነው።

⏺እንደ አትላንቲክ ድልድይ እና ደቡብ አውሮፓ የአትላንቲክ የባቡር መስመር ባሉ ታዋቂ ፕሮጀክቶች ታወቃል፡፡62.53 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የገበያ ዋጋ አለው፡፡

@etconp
👍30
👉በመላው አለም መንገዶች በአስፓልት ወይንስ በሲሚንቶ ኮንክሪት ቢገነቡ በተሻለ ሁኔታ አዋጪ የሚሆነው የትኛው ነው በሚል የሚካሄዱ ክርክሮች ጠንከር ያለ ሙግት የሚስተዋልባቸው ናቸው።

🏷እንደ ኢትዮጵያ ለመሳሰሉ ከፍተኛ ሲሚንቶ የማምረት እምቅ ላላቸው ሀገራት መንገዶቻቸውን አሁን እንደሚስተዋለው በአመዛኙ በአስፓልት ኮንክሪት ብቻ ከመገንባት የሲሚንቶ ኮንክሪትን እንደ አማራጭ ቢወስዱ አዋጭነቱ የላቀ ነው።

🚧የአስፓልት እና የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገዶች አዋጪነትን በተመለከተ ከታች የቀረበውን ሃሳብም መጠነኛ ግንዛቤን የማስጨበጥ አቅም አለው፦

⭐️Cement Concrete Roads vs. Asphalt Concrete Roads:

🌟A. Comparison

⏺Both cement concrete and asphalt concrete are popular choices for road construction, each with its own unique advantages and disadvantages. Let's compare their uses:  

🔰Cement Concrete Roads

▶️Durability: Known for their durability and longevity, cement concrete roads can last up to 40 years or more with proper maintenance.  

▶️Strength: They are well-suited for high-traffic areas and heavy loads, such as highways and commercial districts.

▶️Maintenance: While initial construction costs might be higher, cement concrete roads often require less frequent maintenance compared to asphalt.

▶️Appearance: They typically have a smoother and more uniform appearance.

▶️Environmental Impact: The production of cement can have a higher environmental impact than asphalt, but the overall life cycle assessment can vary depending on factors like transportation distances and maintenance requirements.

🔰Asphalt Concrete Roads
Flexibility: Asphalt is more flexible than concrete, making it better suited for areas with frequent temperature fluctuations.

▶️Construction Speed: Asphalt roads can often be constructed more quickly and at a lower initial cost than concrete.

▶️Maintenance: While they may require more frequent maintenance, repairs are generally less expensive and can be completed more quickly.

▶️Noise Reduction: Asphalt roads can be engineered to reduce noise levels, making them a good choice for residential areas.

▶️Environmental Impact: Asphalt production generally has a lower environmental impact than cement, but factors like transportation and maintenance can influence the overall assessment.

📜Choosing the Right Material

⏺The best choice between cement concrete and asphalt concrete depends on various factors, including:

▶️Traffic volume and load

⏺For high-traffic areas with heavy loads, cement concrete is often preferred.

⏺Climate: Asphalt is more suitable for areas with frequent temperature fluctuations.

⏺Maintenance budget: Consider the long-term costs of maintenance and repairs.

⏺Environmental considerations: Evaluate the environmental impacts of both materials.

⭐️In many cases, a combination of both materials can be used to optimize performance and cost-effectiveness.

⏚For example, cement concrete might be used for the base layer of a road, while asphalt is used for the surface layer to provide a smoother ride and reduce noise.

@etconp
👍19❤3😢1
👉የአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች

🏷በአዲስ አበባ በቅርብ አመታት ውስጥ በመገንባት ካሉና ገና ከሚገነቡ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎችን ሳይጨምር፣ ከሰማይም ይሁን ከምድር ከፍ ብለው ከሚታዩ ዘመናዊ የአዲስ አበባ ረጃጅምና አዳዲስ ሕንፃዎች መካከል አብዛኛዎቹ ንብረትነታቸው የባንኮች ነው።

💫በዚህም ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ብሔራዊ ቴአትር ድረስ ያለው ኮሜርስ ወይም ሰንጋተራ ተብሎ በሚታወቀው እንዲሁም በስቴዲየም አቅራቢያ ባሉ ተቀራራቢ ስፍራዎች በአገሪቱ ያሉ ባንኮች ባስገነቧቸውና እያስገነቧቸው ባሉ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ደምቋል።

⭐️በከተማዋ አራቱም አቅጣጫዎች ቢሆኑ ጎልተው ከሚታዩት መካከል አዲሱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ፣ ጥቂት ዓመታት ያስቆጠረውን የአዋሽ ባንክንና የወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ረጃጅም ሕንጻዎችን መጥቀስ ይቻላል።

❇️አዳዲሶቹ የሕብረት፣ ዳሸን ባንክ፣ ዘመን ባንክና ንብ ባንክ ሕንፃዎችም አንገታቸውን አርዝመው ከሚታዩት መካከል ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪ የሌሎች ባንኮች ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች በአካባቢው በቀለው እንደሚታዩ መናገር ይቻላል።

🚧ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ባለው ሰፊ መሬት ላይ የሚገነባውና ከ60   ወለሎች በላይ የሚኖረው የአቢሲኒያ ሕንፃ እና በሜክሲኮ ዲ አፍሪካ ሆቴል አካባቢ የሚገነቡት የዓባይና ብርሃን ባንክ ሕንፃዎችን ጨምሮ የግሎባል ባንክ በሜክሲኮ፣ የኦሮሚያ ባንክ ደግሞ በጎማ ቁጠባ አካባቢ ግንባታቸው እየተከናወነ ከሚገኙት መካከል ይጠቀሳሉ።

@etconp
👍8❤4
👍12❤1🏆1
#ሪልስቴት

"ቤት ገብተው የሚኖሩ ሰዎች አሉ በጣም ነው የሚያሳዝኑት መብራትና ውሃ ስለሌለ እንጀራ ጋግረው አያውቁም እሱን እያየን ለመግባት ተቸግረል" -

የኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች


"...ለፕሬስ መግለጫ አልሰጥም  " - ኖህ ሪልስቴት

👉የኖህ ሪልስቴት ሀያት ግሪን ቤት ገዢዎች ድርጅቱ በውሉ መሠረት የቤቱን መሠረተ ልማት እንዳላሟላላቸው በድጋሚ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አቀረቡ፡፡

⏺ቅሬታቸውን ያቀረቡ በርካታ ገዢዎች፣ ድርጅቱ በገባው ውል መሠረት መብራት፣ ውሃ፣ ጀነሬተር መሠረተ ልማቶች ባለሟሟላቱ ችግር ላይ እንደወደቁ ገልጸዋል።

▶️መሠረተ ልማቱ ሳይጠናቀቅ የቤት ኪራይ ሽሽት ቤታቸው የገቡ ገዢዎች ያለ መሠረተ ልማት ከ1 ዓመት በላይ እንተቀመጡ በምሬት ተናግረዋል፡፡

⏺መሠረተ ልማቱ እስከሚጠናቀቅ በኪራይ ቤት ሆነው እየጠበቁ ያሉ ገዢዎችም፣ ቤቱን ለመግዛት እስከ 4 ሚሊዮን ብር አውጥተው ሳለ መሠረተ ልማቱ ባለመጠናቀቁ አሁንም በቤት ኪራይ ወጪ እየተበዘበዙ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

▶️ወደ ቤታቸው ያልገቡበትን ምክንያት ሲያስረዱም፣ " ቤት ገብተው የሚኖሩ ሰዎች አሉ በጣም ነው የሚያሳዝኑት መብራትና ውሃ ስለሌለ እንጀራ ጋግረው አያውቁም እሱን እያየን ለመግባት ተቸግረል " ነው ያሉት።

⏺ከዚህ ቀደም መሠረተ ልማቱን በወር ከ15 ቀን ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ በሚዲያ በኩል ቃል ገብቶላቸው እንደነበር አስታውሰው፣ ግን ምንም ሳይሰራ ወራቶች እንደጠቆጠሩ ተናግረዋል።

⏺ውሃው ግቢ ውስጥ ገብቷል ከተባለ ብዙ ጊዜ እንዳስቆጠረ፣ ነገር ግን አገልግሎት ላይ እንዳልዋለ፣ በዚህም የከፋ ችግር ለማሳለፍ እንደተገደዱ ነው የገለጹት፡፡

⏺ድርጅቱ ይባስ ብሎ ቤቱ ሳያጠናቅቅ ጥበቃዎችን እያስወጣ መሆኑን፣ የከተማዋ ከንቲባ ሳይቱን የመረቁት ሳይጠናቀቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

⏺ላደረባቸው ቅሬታ ምላሽ ቢሮ ድረስ ሂደው ቢጠይቁም አጥጋቢ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው አስረድተው፣ አሁንም መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

⏺ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅናቸው የኖህ የህግ አማካሪና ጠበቃ አቶ የሴፍ ደስታ፣ አጭር የመከላከያ ሀሳብ ከመስጠት ውጪ በቀጥታ ለቅሬታው ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

" በጠበቃቸው አማካኝነት እየተከታተሉ ስለሆነና ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመሄድ ዕድል ስላለው የድርጅቱን የመከራከር መብት የሚያጣብብ ስለሚሆን ለፕሬስ መግለጫ አልሰጥም " ነው ያሉት።

⏺ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ስለቅሬታው ጠይቀነው በሰጠን ምላሽ፣ " ትክክል ነው የመብራት፣ የውሃ፣ ታንከር ጥያቄ አለ " ብሎ ይህ የገጠመው በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ገልጾ ነበር።

⏺በወቅቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤቱን መቼ አጠናቃችሁ ታስረክቧቸዋላችሁ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡት ምሌሽ፣ " ነገ ቢሆን ደስ ይለኛል 654 ቤቶችን ሰርተን መብራት ለማስገባት የምንዘገይበት ምክንያት እኔ ራሱ አልገባኝም " ነበር ያሉት።

" ስለዚህ በጣም በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለመስራት እየሞከርን ነው " ማለታቸው ይታወሳል፡፡

Via TIKVAH

@etconp
👍19😢4
👉ይህ ግዙፍ የአፓርትመንት ኮምፕሌክስ መጠሪያ ስሙ Novy Okkervil ይባላል፤ በሩሲያ ነው የሚገኘው።

🏷እ.ኤ.አ በ2015 የተገነባው የመኖሪያ መንደር ከአለማችን ከሚገኙ ተመሳሳይ ግንባታዎች በቀዳሚነት እንደሚገኝ ይነግርለታል።

💫በዚህ መንደር ውስጥ ወደ 18 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ይኖርበታል።

⭐️እያንዳንዱ ሕንፃ ባለ 25 ወለል ሲሆን፣ በጠቅላላው ወደ ሕንፃው ለመግባትም ሆነ ለመውጣት 35 በሮች አሉት።

@etconp
❤9👍5🙏1
👉የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ መከናወን ጀምሯል

💫ውይይቱ ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን በሚል መሪ ቃል የሚከናወን ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ከ30 በላይ የተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎች፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል::

⭐️በአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በመከናወን ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከመላው አለም የተውጣጡ እንግዶችም በመታደም ላይ ይገኛሉ::

Via Mayor office of Addis Ababa

@etconp
👍8
👉What Is a Cost-Plus Contract?

🏷A Cost-Plus contract is an agreement where a contractor is reimbursed for expenses incurred during a project, plus a specified profit margin. This type of contract is commonly used in construction when the project scope or costs are uncertain.

⏺In a Cost-Plus contract, contractors are paid for both direct and indirect costs, along with an agreed-upon profit margin.

💫There are different types of Cost-Plus contracts

- Cost-Plus Award Fee
- Cost-Plus Fixed Fee
- Cost-Plus Incentive Fee
- Cost-Plus Percent-of-Cost

⭐️The advantages of Cost-Plus contracts include reduced risk for contractors and increase the focus on quality over cost.

🌟Some disadvantages of Cost-Plus contracts are unpredictable final costs, potential for extended project timelines, and the need for extensive documentation to justify all related costs.

❇️Cost-Plus contracts are especially useful in projects with uncertain scopes or budgets, as they allow for flexibility while ensuring that contractors are compensated for their work and costs.

⏺Cost-Plus contracts are mainly used in research and development projects and by governments since such projects mainly seek highly qualified contractors to fulfill the tasks.

@etconp
❤7👍3
ትኩረቱን በጨረታ ሰነድ ዝግጅት ላይ ያደረገ የዓቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል


🏷150 ለሚሆኑ ሾል ተቋራጮች፣ አማካሪዎችና ማሕበራት እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና ከጨረታ ሂደት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ማለትም  የጨረታ ጥሪ ጋዜጣ ዋና ዋና ነጥቦች፣ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ሰዓቶች አረዳድ፣ የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርትን ተመርኩዞ የሚዘጋጅ የመወዳደሪያ ሰነድ ዝግጅት ፣ ከጨረታ ሊያሰርዙ የሚችሉ ተግባራት እንዲሁም ቅሬታ/አቤቱታ አፈታት ስርዓትና ሌሎችም ተያያዥ  ነጥቦች ተተንትነው እየቀረቡ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

@etconp
👍12❤4