Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.24K photos
359 videos
1.99K files
3.23K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉 በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ቀደም ሲል ይሰጡ የነበሩ የምዝገባና ሰርተፍኬሽን አገልግሎቶች መካከል አስር ያህሉ  ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተዘዋውረዋል፡፡

❇️መንግስት ለዜጎች የሚሰጣቸው አገልግሎቶችን ለማሳለጥ የሪፎርም ስራዎችን አያካሄደ ይገኛል፡፡

🎲የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጥራት ያለውና የዜጎችን ርካታ ከፍ የሚያደርግ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎትን በክህሎት፣ በቴክኖሎጂ  እና በመልካም አስተዳደር  የማዘመን ተግባር እየተከናወነ ነው፡፡

⏺ይህንን እውን በማድረግ ፈር ቀዳጅ የሆነውን  የመሶብ አገልግሎት ማዕከል በቅርቡ ስራ ማስጀመሩም ይታወቃል፡፡

⏺በ 23 ተቋማትና 124 የአገልግሎት አይነቶች በአንድ ማዕከል መሰጠት የጀመረው የመሶብ  አንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ በመታገዝ የተገልጋዮችን ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበትን በሚቆጥብ መልኩ ፈጣንና እርካታን ያላበሰ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

⏺በዚሁ መሰረትም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ከ23ቱ ተቋማት አንዱ በመሆን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ አስር የአገልግሎት አይነቶችን በመሶብ አንድ ማዕከል እየሰጠ ይገኛል፡፡

🎲በዚሁ መሰረት ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ይሰጡ የነበሩና ወደ መሶብ አንድ ማዕከል የተዛወሩ የምዝገባና ሰርተፍኬሽን አገልግሎቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

⭐️አዲስ የባለሙያ ምዝገባና አገልግሎት

1.  የባለሙያ ምዝገባ የእድሳት አገልግሎት
2.  የባለሙያ የጠፋ የሙያ ፈቃድ መተካት 
3.  አዲስ የዉሃ ነክ ባለሙያ  ፈቃድ ምዝገባ
4.  እድሳት የውሀ የዉሃ ነክ ባለሙያ  ፈቃድ ምዝገባ
5.  የጠፋ የውሃ ባለሙያ ፈቃድ መተካት
6.  የውሃ ባለሙያ ፈቃድ ደረጃ ዕድገት
7.  አዲስ የውሃ ስራዎች ካምፓኒ የምዝገባና ብቃት ሰርተፍኬት
8.  የውሃ ስራዎች ካምፓኒ ብቃት ሰርተፍኬት ዕድሳት
9.  የውሃ ስራዎች ካምፓኒ ሰርተፍኬት የደረጃ ለውጥ ናቸው፡፡

🚧ክቡራን ተገልጋዮችም እነዚህ አገልግሎቶች ከተቋማችን ወደ መሶብ አንድ ማዕከል መዛወራቸውን በማወቅ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ወደ ተቋማችን በመምጣት እንደይጉላሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

💫የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

@etconp
❤14
Ethio Construction Engineering
👉In building construction, the terms Substructure and Superstructure refer to the two primary divisions of a building, separated by the ground level or plinth level. ❇️Understanding these two components is crucial for comprehending how a building stands,…
📚 Superstructure

⏺The superstructure is the part of the building that is constructed above the ground level or above the plinth level.
⏺It is the visible, usable portion of the building that provides functional space and defines the building's aesthetic.

💫Key Characteristics and Functions:

1. Enclosure and Space Creation: It encloses the functional spaces (rooms, offices, halls, etc.) for various activities, providing shelter and privacy.

2. Load Bearing: It consists of elements that transmit loads (from occupants, furniture, wind, snow, etc.) down to the substructure.

3. Architectural Expression: It determines the building's appearance, layout, and overall design, fulfilling the aesthetic and functional requirements of the occupants.

4. Accessibility and Services: It houses various services like plumbing, electrical, HVAC, and provides access through stairs, ramps, and elevators.

🏷Main Components of Superstructure:

*   Columns: Vertical load-bearing members that transfer loads from beams and slabs to the foundations. They are crucial for framing the structure.
*   Beams: Horizontal load-bearing members that support slabs and walls, transferring their loads to columns or other supporting elements.
*   Slabs: Flat, horizontal structural elements that form floors and roofs, supporting live loads, furniture, and distributing loads to beams and walls.
*   Walls:
    *   Load-bearing Walls: Walls that support loads from floors and roofs above, transmitting them to the foundations. Common in traditional or low-rise masonry construction.

    *   Non-load-bearing Walls (Partitions): Walls that primarily divide internal spaces and do not carry significant structural loads. They can be made of lighter materials like drywall, brick, or concrete blocks.
*   Roof: The uppermost covering of the building, protecting it from weather elements (rain, sun, wind, snow). It can be flat, pitched, or domed, and its design depends on climate, aesthetics, and functional requirements.
*   Parapet Walls: Low walls constructed at the edge of a roof, balcony, or terrace for safety, aesthetic, or to conceal roof mechanicals.
*   Stairs, Ramps, and Elevators: Provide vertical circulation within the building.
*   Doors and Windows: Provide access, ventilation, and natural light, while also contributing to the building's facade.
*   Finishing Materials: Internal and external finishes like plaster, paint, flooring, cladding, etc., that enhance functionality and aesthetics.

🚧Importance of Superstructure:

⏺The superstructure is where the building's purpose is fulfilled. Its design dictates the usability, comfort, safety, and visual appeal of the structure. Proper design and construction ensure that it can safely support its intended loads, provide a durable and functional environment, and withstand environmental forces.

📚 Interrelation and Conclusion

⏺The substructure and superstructure are intricately linked and interdependent. The design of one significantly impacts the other:

*   The loads generated by the superstructure directly determine the design requirements of the substructure.
*   The substructure's ability to support and transfer these loads dictates the feasible size, height, and type of superstructure that can be built upon it.

🎲In essence, the substructure is the hidden but critical anchor, ensuring the building's stability and longevity by dealing with the earth.

⏺The superstructure is the visible, functional part that brings the building to life, serving its occupants and standing tall against the elements.

⏺Both must be meticulously designed and constructed as a single, cohesive unit to ensure the safety, durability, and performance of the entire building.

@etconp
❤11👍4🎉1
👉Honeycombing in concrete

Honeycombing in concrete means there are small holes or gaps in the surface where stones (aggregates) are visible.

This happens when the concrete doesn’t fill the space properly. It weakens the structure, makes it less durable, and also looks bad.

Causes of Honeycombing:

Improper Vibration:
Uneven vibration during concrete placement leads to poor consolidation, trapping air pockets within the mix.

Poor Workmanship:
Incorrect handling of concrete, including failure to ensure proper placement in corners and tight areas, contributes to honeycombing.

Concrete Mix Design:
A poorly proportioned mix with insufficient fines or improper water-cement ratio results in segregation and voids.

Congested Reinforcement:
Closely spaced reinforcement bars obstruct the flow of concrete, leading to insufficient compaction and the formation of voids around the reinforcements.

Formwork Issues:
Gaps or misalignments in the formwork allow the concrete to leak, leaving voids.

✍Yonatan

@etconp
❤16👏8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉አስደናቄ የ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ግኝት

🚜 ሹፌር አልባ የአስፋልት ኮምፓክተሮች በቻይና ሁቤይ ግዛት በአውራ ጎዳና ግንባታዎች ላይ መሳተፍ ጀምረዋል❤

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤9🥰7👍1
This media is not supported in the widget
VIEW IN TELEGRAM
❤4
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን


0904040477
0994941708
“እስከ ወረዳ ድረስ ቡድን ተዋቅሮ ችግር ያለባቸው ግንባታዎች ተለይተዋል፡፡ ከተለዩት 2681ግንባታዎች 1157 ብቻ ናቸው ትንሹን መስፈርት የሚያሟሉት” - ባለስልጣኑ

➡️ከ2015 እስከ ሰኔ 24/2017 ዓ/ም በሥራ ላይ የ142 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል!


የአዲስ አበባ ከተማ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ2015 እስከ 24/10/2017 ዓ/ም ድረስ በመዲናዋ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች 121 ወንዶች፣ 21 ሴቶች በድምሩ 142 ሰዎች በህንጻ ሥራ ላይ እያሉ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው ማለፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡

42 ወንዶችና 10 ሴቶች በድምሩ 52 በለሚኩራ፤ 15 ወንዶችና 2 ሴቶች በድምሩ 17 በንፋስ ስልክ፤ 15 ወንዶችና 2 ሴቶች በድምሩ 17 በቦሌ፤ 13 ወንዶችና አንዲት ሴት በድምሩ 14 ሰዎች በቂርቆስ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በሌሎቹ ክፍለ ከተሞች ህወታቸው ማለፉን የባለስልጣኑ መረጃ በዝርዝር ያስረዳል፡፡

ባለስልጣኑ ህንፃች አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ “እስከ ወረዳ ድረስ ቡድን ተዋቅሮ ችግር ያለባቸው ግንባታዎች ተለይተዋል፡፡ ከተለዩት 2681ግንባታዎች 1157 ብቻ ናቸው ትንሹን መስፈርት የሚያሟሉት” ብሏል፡፡

ባለፉት አስር አመታት በአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በስፋት እየተገነቡ እንደሚገኙ፣ ለአብነትም በ2017 ዓ/ም በከተማዋ 11 ሺሕ 748 አዳዲስና 12 ሺሕ 322 ነባር ግንጻዎች ክትትል እንደተደረገባቸው፣ ግንባታዎቹ ከ581 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት እንዳላቸው የባለሥልጣኑ መረጃ ይገልጻል፡፡

በከተማዋ በግንባታ ሳይቶች ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩ የአደጋ መንስኤዎች እና ስጋቶች ምንድን ናቸው?

-ከከፍታ ላይ መውደቅ
-የኤሌክትሪክ አደጋ
-የእቃ መውደቅ
-የግንባታ መዋቅር ችግር
-የሠራተኞች በቂ ስልጠና አለመውሰድ
-የግል ደህንነት መጠበበቂያ መሳሪያዎች ያለመጠቀም
-የቁጥጥር ችግር፣ የበጅት እጥረት
-ህግ የማስከበር ችግር ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ “በአስር አመት አማካኝ የኢንዱስትሪው እድገት 10%"፣ “በቀጥታና በተዘዋዋሪ በየዓመቱ በአማካኝ የሚፈጠረው የሥራ እድል 1.2 ሚሊዮን” መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ “በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ፈጣን ኢንዱስትሪው እድገት በሠራተኞች የሥራ ላይ ደንነነት ተመሳሳይ ለውጥና መሻሻል እየታየበት አይደለም” ብሏል፡፡

“አልሚዎች ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጭ ለመጨረስ በሚያደርጉት ጥረት የሥራ ላይ ደህንነት ትኩረት በመሆኑ አደጋና ጉዳት እየጨመረ ይገኛል” ብሎ፣ የኮንስትራክሽን እድገት በአጭር ጊዜና በዝቅተኛ ዋጋ ግንባታዎችን ለመጨረስ የሥራ ላይ ደህንነትን አቀናጅቶ መተግበር እንደሚገባ አሳስቧል።

(ዝርዝር መረጃ ከላይ የተያያዘ ሲሆን፣ ተጣለ የተባለውን ቅጣት የተመለከተ ተጨማሪ አለን)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
❤14
ያለፈቃድ የግንባታ ዲዛይን ማስፋፊያ ለሚያደርጉ አካላት በየእርከኑ የ100 ሺሕ ብር ቅጣት ተጣለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው የቅጣት ማሻሻያ በሕንፃ ግንባታ ህግጋት መሰረት በተጣለው የህንፃ ደህንነትና ተያያዥ ቅጣት በተለያዩ ተግባራት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን ገልጿል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የባለስልጣኑ መረጃ እንዲሚያስረዳው፥ የማስፋፊያ ሥራ የዲዛይን ማሻሻያን ስለሚፈልግ፣ ያልተፈቀደ ግንባታ የዲዛይን ጥራት ስለሚጎድለው የመደርመስ አደጋ ስለሚያስከትል ያለፈቃድ የማስፋፋት ሥራ ማከናወን (በየእርከኑ) 100 ሺሕ ብር ያስቀጣል።

እንዲሁም፣ ጥራት ያለው ስካፎልዲንግ፣ ሾርኒንግና መሰል መሳሪያዎችን አለመጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ በግንባታ ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ለማያሟሉ አካላት (በእርከን) 50 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን አመልክቷል።

ቅጣቱ "በየእርከኑ" ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባለስልጣኑ ሲያስረዳም፣ "ለምሳሌ አንድ G+10 ህንጻ 26 የክትትል እርከኖች ይኖሩታል፤ 26*50,000=1,300,000 ይሆናል" ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ያለተቆጣጣሪ ማሰራት ለአደጋ አጋላጭ በመሆኑ የግንባታ ስራዎችን ያለተቆጣጣሪ የሚያሰሩ አካላት (በየእርከኑ) 25 ሺሕ ብር እንደሚቀጡም ተጠቁሟል።

ስቶር፣ ልብስ መሸጫ፣ መመገቢያና ሌሎች የቅድመ ግንባታ መስፈርቶችን ሳያዘጋጁ ሥራ ለሚጀምሩ አካላት የ15 ሺሕ ብር፤ በሚሰጥ የማስታወቂያ ትዕዛዝ መሰረት ተረፈ ምርትን በወቅቱ ለማያነሱ 15 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን የደረሰን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል።

ሕጋዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ የማማከር ኃላፊነትን በአግበባቡ አለመወጣት ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ30 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ፤ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ማከናወን ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ50 እስከ 100 ሺሕ የገንዘብ ቅጣቶች መጣላቸው ተመልክቷል፡፡

እንዲሁም፣ ግባታውን በህዝብ ደህንነት አደጋ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ ከ5 እስከ 10 ዓመታት የእስራት እና ከ20 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት የተገለጸ ሲሆን፣ ጥፈተኛ ሆኖ የተገኘ አማካሪ/ሥራ ተቋራጭ ከ15 ዓመት እስከ ከፍተኛ የእስር ጊዜው ፈቃዱ ይታገዳል ተብሏል፡፡

(የቀድሞው እና የተሻሻለውን ቅጣት፤ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘው የባለስልጣኑ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
❤15