👉በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ ጥንታዊ ከተሞች አንዷ የሆነችው ስፔን ውስጥ የምትገኘው ማላጋ ዕድሜዋ ከ2800 አመት በላይ እንደሆነ ይነገርላታል።
💫በማላጋ ከ590 ሺህ በላይ የሚሆን ህዝብ በውሃ ዳርቻ ላይ የሚኖርባት ከተማ ነች።
🚧Zaha Hadid Architects በቅርቡ ይፋ ያደረገው አስደናቂ የኪነ ሕንፃ ፕሮፖዛል በጥንታዊቷ ማላጋ ለግንባታ ዝግጁ ሆኗል።
🏷El Bulto በሚል መጠሪያ ጠቅላላ የፕሮጀክቱ ፕሮፖዛል የቀረበ ሲሆን፣ Sierra Blanca Estates የሪል ስቴት ኩባንያ በባለቤትነት እንደሚያስገነባው ታውቋል።
@etconp

❤14
👉የኮሪደር ስራን የሚቆጣጠር መስሪያ ቤት ተቋቋመ
🚧የአዲስ አበባን የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች እና የኮሪደር ስራን የሚቆጣጠርና የሚመራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተቋቋመለት፡፡
የተቋቋመው መስሪያ ቤት እስካሁን የተሰሩና ከዚህ በውሃላም የሚሰሩ የወንዝ ዳርና የኮሪደር ልማት ስራዎችን የሚመራና የሚቆጣጠር ነው ተብሏል።
በዚህም የኮሪደርና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች መቆጣጠርና ማስተዳደር ባለስልጣን ተቋም በከተማ አስተዳደሩ ተሰምቷል።
ለአዲስ አበባ የመጀመሪያው የሆነውና በግንባታ ላይ ያለው ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ መናፈሻ የሚደርሰው የ21.5 ኪ.ሜ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ስራ 90 በመቶ መድረሱን የከተማዋ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚና የ የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት ምክትል አስተባባሪ አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ ተናግረዋል።
በተጨማሪም እስከ መጪው ጥቅምት ወር መጨረሻም አጠቃላይ ስራው ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ከዚህ በኋላም ስራውን የሚቆጣጠርና የሚከታተል ተቋም መቋቋሙን ተከትሎም የወንዝ ዳር ፕሮጀክቱ ያለምንም መቆራረጥ በቋሚነት የሚሰራ እንደሚሆንም ተናግረዋል።
Via ሸገር ሬድዮ

❤8
👉የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋና ከተማዋን ዋሽንግተንን ለማስዋብ 2 ቢሊዮን ዶላር በጀት እንደሚያስፈልጋቸው ተናገሩ።
💫ፕሬዚዳንቱ ዋሽንግተንን ንፁህ እና ውብ ለማድረግ ያስችላል ላሉት የከተማ ማስዋብ እቅድ ለአሜሪካ ኮንግረስ የ2 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ጥያቄ እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል።
ትራምፕ ይህን እቅድ ይፋ ባደረጉበት ወቅት፥ አሁን ያሉት የከተማዋ መብራቶች በአብዛኛው ያረጁና የተሰበሩ ናቸው ብለዋል።
መንገዶቹ ተበላሽተዋል፣ ፓርኮቹ አረንጓዴና ዓይን የሚስቡ አይደሉም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አዲሱ እቅድ ይህን እንደሚያስተካክል፣ ከተማዋን ውብ፣ ፅዱና ሰላማዊ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ትራምፕ ዋሽንግተንን ከመቼውም የበለጠ ሰላማዊ፣ እንከን የለሽ እና ውብ ገፅታን የተላበሰች ያደርጋታል ያሉት እቅዳቸው የከተማዋ መንገዶች እድሳት፣ በፋውንቴን የተዋበ የህዝብ ፓርክ ግንባታ፣ የመንገድ መብራቶችን በአዲስ መቀየር፣ የከተማዋ መለያ የሆኑ ሐውልቶችን ማደስ እና ማፅዳትን ያካተተ እንደሆነ ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ ዋሽንግተን ዲሲን ለማደስ እና ለማስዋብ ያወጡት ይህ እቅድ ከዋና ከተማዋ በ4.8 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ያለውን አካባቢ የሚያካልል ሲሆን ትግበራውም በ12 ወራት እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
Via ዋሲሁን ተስፋዬ

❤9👍5
ADVERTISMENT
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)
🔅 የተለያዩ [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።
♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።
☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1
አድራሻ፦ ቁ 1.መርካቶ
ቁ.2 አየር ጤና ኪዳነ ምህረት
ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።

❤4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉ቡርጅ ከሊፋ
📍ዱባይ
💫ቡርጅ ከሊፋ እኤአ በ2010 ግንባታው የተጠናቀቀ 829.8 ሜትር ቁመትና 163 ወለሎች ያሉት የአለማችን ረጅሙ ህንጻ ነው፡፡
⏺ህንጻው በቀድሞው የተባበሩት ኤሚሬቶች ፕሬዚደንት ሼክ ከሊፋ ቢን ዘይድ አል ናህየን የተሰየመ ነው፡፡
⏺ይህ የሆነው ደግሞ በግንባታው ወቅት በአለም ላይ በነበረው የፋይናንስ ቀውስ አልሚው ኤማር ፕሮፐርቲስ ገንዘብ በቸገረው ግዜ የኤሚሬቶቹ ፕሬዚደንት ሼክ ከሊፋ ለስራው የፌደራል ገንዘብ ስላዋጡ የዱባዩ መሪ መሀመድ ቢን ራሺድ የህንጻውን ስም ከቡርጅ ዱባይ ወደቡርጅ ከሊፋ ቀየሩት።
🚧ህንጻው ለዱባይ ምልክትነት ከሚያገለግሉት ጥቂት ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
❇️ሊፍቶቹ ከመሬት ወደ 125 ኛው ወለል ጎብኚዎችን ጆሮ ጭው በሚያደርግ ፍጥነት ለማድረስ አንድ ደቂቃ ብቻ ነው የሚፈጅባቸው፡፡

❤6👍1
👉በምስራቅ ቻይና ሻንዶንግ ግዛት ቺንግዳኦ ውስጥ በአለም የመጀመሪያው እጅግ በጣም ከበካይ ጋዝን ነፃ የሆነ (zero carbon) ሕንፃ ሥራ ጀመረ።
💫117 ሜትር ከፍታ ላይ የቆመው ሕንፃው 100 ፐርሰንት አረንጓዴ ኃይልን ብቻ ለመጠቀም የሚያስችሉ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች የተገጠመለት ነው።

❤6
👉እስኪ እንወያይበት
💫አንድ ስራ ተቋራጭ አንድን ህንጻ per contract requirement (design and specification) ስራውን ያለጉድለት ሰራቶ ቢያጠናቅቅ ነገር ግን በህንጻ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 ዓንቀጽ 16(2) የተደነገገው የመገልገያ ሕንጻው ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ያልሆነና እንደሆነ ርክክብ መፈጸም ይቻላል?
⏺በህግ ወይም በህንጻ ስታንዳርድ የተቀመጡ መስፈርቶች አለማሟለት እንደ defect ተቆጥሮ በremark on legal requirement ተይዞ በሕጉ አግባብ መታረም አለበት ወይስ በውሉ መሰረት ስለሰራ በቀጥታ ( technical and contractual remark) በመያዝ ብቻ ርክክብ መፈጸም ይቻላል?
📩ሀሳብ እና አስተያየታቹ ኮሜንን ቦክስ ላይ አስቀምጡልን🙏

Ethio Construction Engineering
👉እስኪ እንወያይበት 💫አንድ ስራ ተቋራጭ አንድን ህንጻ per contract requirement (design and specification) ስራውን ያለጉድለት ሰራቶ ቢያጠናቅቅ ነገር ግን በህንጻ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 ዓንቀጽ 16(2) የተደነገገው የመገልገያ ሕንጻው ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ያልሆነና እንደሆነ ርክክብ መፈጸም ይቻላል? ⏺በህግ ወይም በህንጻ ስታንዳርድ የተቀመጡ መስፈርቶች አለማሟለት…
👉የዚህ የውይይት ጥያቄ መልስ እንሆ
📜በህጋዊ መርሆዎች እና በኮንስትራክሽን ውል ልምዶች (በተለይም በህንጻ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 ስር ያለውን የኢትዮጵያ ህግ በመጥቀስ)
🚧የህንጻው ተቋራጭ ህንጻውን ህጋዊ በሆነ መንገድ ማስረከብ አይችልም!
📜የተደራሽነት መስፈርቶችን አለማሟላት
ዝርዝር ትንታኔ፦
💫1. የህግ መስፈርቶች የውል ስምምነትን ይሽራሉ
⏺የአዋጅ ቁጥር 1356/2017 አንቀጽ 16(2) ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽነትን ያስገድዳል። ይህ ህጋዊ ግዴታ እንጂ በውል ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም።
⏺የውሉ ዲዛይን/ዝርዝር መግለጫዎች የተደራሽነት ባህሪያትን ባያካትቱም፣ የህግ የበላይነት የውሉን ድንጋጌ ይሽራል። ህግን የሚጥስ ህንጻ፣ ውሉን ቢከተልም፣ በነባሪነት ህግ አያሟላም።
⏺የህግ መርህ፦ ውሎች ተዋዋይ ወገኖች ህጋዊ ግዴታቸውን እንዲጥሱ ሊያስገድዱ አይችሉም።
⏺ከአዋጁ ጋር የሚጋጭ ማንኛውም የውል አንቀጽ ውድቅ ነው።
💫2. ተደራሽ አለመሆን ህጋዊ “ጉድለት” ነው
“ጉድለት” የሚለው ቃል በውል ሰነዶች ላይ ከሚገኙ ልዩነቶች ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ ግዴታ የሆኑ የህግ ደረጃዎችን አለማሟላትንም ያካትታል።
⏺የአዋጁ አንቀጽ 16(4) ጥሰቶች ላይ ቅጣቶችን ስለሚጥል፣ ተደራሽነት ሊታለፍ የማይችል ህጋዊ መስፈርት መሆኑን ያረጋግጣል።
⏺የእጅ ማስረከብ ውጤት: ህግን የማያሟላ ህንጻ ማስረከብ ተቋራጩንም ሆነ የህንጻውን ባለቤት ለህጋዊ ተጠያቂነት (በአካል ጉዳተኞች መብት ህጎች ስር ለሚመጣ ቅጣት፣ ትዕዛዝ ወይም ክስ) ያጋልጣል።
💫3. የ"Handover" ቢደረግ ውጤቱ እስከ የመኖሪያ ፍቃድ ሊያሳግድ ይችላል: ህንጻው የአንቀጽ 16(2)ን የሚጥስ ከሆነ፣ የሚመለከተው ባለስልጣን የመኖሪያ ፍቃድ ለመስጠት ይከለክላሉ።
📍የባለቤት ተጠያቂነት: ባለቤቱ ህንጻውን በህጋዊ መንገድ መጠቀም ወይም ማከራየት አይችልም።
⏺በአዋጅ ቁጥር 715/2011 (የአካል ጉዳተኞች ሥራ ስምሪት) ስር የአድልዎ ክስ ሊገጥማቸው ይችላል።
⏺የተቋራጭ ተጠያቂነት: ተቋራጩ ተገዢነት እስኪሳካ ድረስ የማሻሻያ ወጪዎች፣ መዘግየቶች እና ቅጣቶች ተጠያቂ ሆኖ ይቀጥላል።
💫4. “ማስታወሻ” በቂ ያልሆነበት ምክንያት ስለ ተደራሽ አለመሆን “ማስታወሻ” ጋር ማስረከብ በመሠረቱ ህግን የማያሟላ ንብረትን እንደ መቀበል ይቆጠራል ይህም የህዝብ ፖሊሲ እና ህጋዊ ግዴታዎችን ይጥሳል።
⏺ህጋዊ ስጋትን ለመቀየር አይበቃም (ተቋራጩ ተጠያቂ ሆኖ ይቀጥላል)።
ባለቤቱን ህገወጥ የሆነን ግንባታ በመጠቀም ከሚመጣ ተጠያቂነት አያድነውም።
💫5. ትክክለኛው የሥራ አካሄድ
ከማስረከብ በፊት ማስተካከል: ተቋራጩ የተደራሽነት ጉድለቶችን በራሱ ወጪ ማስተካከል አለበት።
⏺የውል ማስተካከያ: የመጀመሪያው ዲዛይን/ዝርዝር መግለጫዎች ጉድለት ካለባቸው፣ ባለቤቱ የዲዛይን ወጪዎችን ሊሸፍን ይችላል፣ ነገር ግን ተቋራጩ ግንባታውን የማስፈጸም ኃላፊነት አለበት።
⏺የህግ ተገዢነት ሰርተፊኬት: ማስረከብ የአንቀጽ 16(2)ን ጨምሮ ከሁሉም ህጎች ጋር ተጣጥሞ መሰራቱን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ይጠይቃል።

👍3❤2
👉ከጀርመን አደባባይ እስከ ኃይሌ ጋርመንት ያለው የቀለበት መንገድ በከፊል ለትራፊክ ዝግ ሊደረግ ነው
🚧የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት አካል የሆነውን ከሳር ቤት - ጀርመን አደባባይ - ለቡ - ኃይሌ ጋርመንት ኮሪደር ግንባታ በፍጥነት ለማጠናቀቅ በከፍተኛ ርብርብ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በመሆኑም ለግንባታ ሥራው ቅልጥፍና ሲባል ከነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የግንባታ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከጀርመን አደባባይ እስከ ኃይሌ ጋርመንት ያለው የቀለበት መንገድ ክፍል በከፊል ለትራፊክ ዝግ ይደረጋል፡፡
በዚህም ከሳር ቤት - ጀርመን አደባባይ - ለቡ - ኃይሌ ጋርመንት ኮሪደር ግንባታ ስራ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከአየር ጤና ወደ ጋርመንት እና ለቡ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች፤ በጀሞ ሚካኤል አድርጎ ወደ ፉሪ አደባባይ ጋርመት የሚወስደውን መንገድ ሊጠቀሙ ይገባል ተብሏል ።
በተጨማሪም ከሣር ቤት መካኒሳ ወደ ጋርመንት እና ለቡ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ደግሞ በጀሞ ሚካኤል ወደ ፉሪ አደባባይ ጋርመት የሚወስደውን መንገድ መገልገል ይችላሉ።
በሌላ በኩል ከቄራ በጎፋ ወደ ጋርመት እና ለቡ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ደግሞ በጎፋ መብራት ኃይል ላፍቶ የሚወስደውን መንገድ ሊጠቀሙ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
ከማሠልጠኛ እና ሠፈራ ወደ ጀሞ ሚካኤል እና አየር ጤና የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በሀጫሉ መንገድ ወደ ፉሪ አደባባይና ጀሞ የሚወስደውን አማራጭ መንገድ በመጠቀም ለግንባታ ሥራው መፋጠን የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ አሳስቧል፡፡

👍6❤3
👉2 ሺህ 900 ሜትር የሚረዝመው የ አለማችን ትልቁ ድልድይ
🚧በቻይና እየተገነባ የሚገኘው ረጅሙ ድልድይ በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል።
💫በደቡብ ምዕራብ ቻይና ጉዊዡ ግዛት የተገነባው ረጅሙ ድልድይ ወደ ስራ ከመግባቱ አስቀድሞ ፍተሻ እየተደረገለት ይገኛል።
🏷ባለፉት አምስት ቀናት የመጫን አቅሙ የተፈተሸው ይህ ድልድይ የታለመለትን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አስተማማኝ አቅም እንዳለው ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
⏺የድልድይ ግንባታው መሐንዲሶች እንዳሉት÷ የድልድዩን አቅም ለመፈተሽ 96 የጭነት ተሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ ተከታትለው እንዲያልፉበት ተደርጓል።
⏺የድልድዩ ግንባታ የመንገድ ደህንነት መስፈርቶች ጨምሮ ደረጃውን ጠብቆ የተከናወነ ነው ብለዋል።
⏺በዓለም ላይ ረጅሙ ድልድይ ለመባል በፍጻሜ ዋዜማ ላይ የሚገኘው ይህ ድልድይ ከመሬት በላይ ያለውን 1 ሺህ 420 ሜትር ጨምሮ አጠቃላይ ርዝመቱ 2 ሺህ 900 ሜትር ነው።
⏺ይህም በአለም የመጀመሪያው ረጅሙ ድልድይ እንዲሆን ያስቻለው ሲሆን በተራራማ አካባቢ የተገነባ ብቸኛው የዓለማችን ድልድይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
⏺ቻይና ዘመናዊ ድልድዮችን በመገንባት ከዓለም በመሪነት ደረጃ የተቀመጠች ሲሆን በ’ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ’ አፍሪካን ጨምሮ ዓለምን በመንገድ መሰረተ ልማት ለማስተሳሰር እየሰራች እንደምትገኝ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

❤8👍5
👉ነጻ የትምህርት እድል
💫2026 ቼቭኒንግ ስኮላርሺፕ ዩኬ (ሙሉ በሙሉ ወጪው የተሸፈነ)
📜ዝርዝሩን ከታች የተጻፈው ጽሁፍ ላይ ያገኙታል።
⏺Level of study: Master’s
Master's program
⏺Study area: Any
💫Scholarship value:
⏺University tuition fees.
⏺A monthly stipend.
⏺Travel costs to and from the UK.
⏺An arrival allowance.
⏺A homeward departure allowance.
⏺The cost of one visa application.
⏺A travel grant to attend Chevening events in the UK.
🏷Description: Funded by the Foreign, Commonwealth and Development Office and partner organisations, Chevening Scholarships are awarded to individuals with demonstrable leadership potential and strong academic backgrounds. The scholarships offer full financial support to study for any eligible master’s degree at any UK university. Additionally, Chevening scholars gain access to a wide range of exclusive academic, professional, and cultural experiences.
University Programs
Chevening travel grant
Since the programme was created in 1983, nearly 60,000 outstanding professionals, have had the opportunity to develop in the UK through Chevening. There are more than 1,000 scholarships on offer each year, demonstrating the UK’s ongoing commitment towards developing the leaders of tomorrow.Chevening Scholarship covers university tuition fees, a monthly living allowance, an economy class return airfare to the UK, and additional grants and allowances to cover essential expenditure.
⭐️Eligibility: To be eligible for a Chevening Scholarship you must: Be a citizen of a Chevening-eligible country or territory.
⏺Commit to returning to your home country for at least two years after your scholarship ends.
⏺Have at least 2,800 hours of work experience after graduating from your undergraduate degree.
⏺This is roughly equivalent to two years of full-time work, though it may have been completed over a different time period.
⏺Hold an undergraduate degree that qualifies you for a UK master’s programme.
Apply to three different and eligible UK university courses.
Master's program
Chevening travel grant
You are not eligible for a Chevening Scholarship if you:
Hold British or dual British citizenship (unless you are a citizen of a British Overseas Territory or hold BN(O) and are applying from Hong Kong).
Hold refugee status in a country not eligible for Chevening. However, if you are a citizen of an eligible country and hold refugee status in another eligible country, you are eligible for a scholarship.
⏺Are an employee, former employee, or relative of an employee of the UK government, British Embassies/High Commissions, the British Council, or sponsoring UK universities. Employees, former employees, or relatives of an employee of Chevening Partner organisations are eligible to apply, but if the employment took place within the last two years, you cannot receive a Chevening partner award from the organisation from which you work, previously worked, or are affiliated with through relatives.
⏺Have previously studied in the UK on a UK government-funded scholarship.
📩How to apply: apply online
More info: https://www.chevening.org/apply/

www.chevening.org
Apply | Chevening
Apply for a Chevening Scholarship or Fellowship Award
❤11👍3🎉1
👉የኢትዮጵያ ጠቅላላ የመንገድ ርዝመት ከ180 ሺህ ኪ.ሜ በላይ ደርሷል
💫በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅግጅጋ ከተማ ከነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ሀገር አቀፍ የመንገድ ዘርፍ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡
🚧በመድረኩ የውይይት መነሻ ሰነዶች ዋነኛው የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንገድ ዕቅድ አፈጻጸም ይገኝበታል።
⏺በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ቀ2017 ዓ.ም ከ101 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የ1,048 ኪ.ሜ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ፣ የነባር መንገዶች ማጠናከር፣ ደረጃ ማሻሻል እና የከባድ ጥገና እንዲሁም የ10,926 ኪ.ሜ ወቅታዊ እና መደበኛ ጥገና ማካሄድ መቻሉ ተገልጿል፡፡ የጀት ዓመቱ የፊዚካል እቅድ አፈጻጸምም 81 በመቶ ማሳካት መቻሉን የቀረበው የዘርፉ ሪፓርት ያሳያል።
⏺በተጨማሪም በሀገሪቱ ያለው ጠቅላላ የመንገድ ርዝመት በፌዴራል፣ በክልል፣ በከተሞች እና በወረዳዎች የተሰሩ ክረምት ከበጋ የሚያስኬዱ መንገዶችን ጨምሮ አምና ከነበረበት 171,176 ኪሜ አሁን ላይ 180, 232 ሺ ኪ.ሜ መድረሱ ተገልጿል፡፡
🏷ከዚህ ውስጥ 30,824 ኪ.ሜ የፌደራል፣ 36,395 ኪ.ሜ የክልል፣ 44,717 ኪ.ሜ የከተማ እንዲሁም 68,297 ኪ.ሜ የወረዳ መንገድ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
⏺ይህን ተከትሎም በ1000 ስኩዌር ኪ.ሜ ውስጥ ያለው የመንገድ ርዝመት 157 ኪ.ሜ የደረሰ ሲሆን ክረምት ከበጋ የሚያገለግል መንገድ ላይ ለመድረስ ዜጎች በአማካይ እንዲጓዙ የሚጠበቀው ርቀት 4.3 ኪ.ሜ መድረሱ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

👍4❤3