Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.28K photos
359 videos
1.99K files
3.34K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)

👉Great Today Tip 👆👆👆
.
➡ለዛሬ የተለያዩ ጠቃሚ ምስሎች እንካቹ ብሎናል
.
🅾አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
Do you think the gradient is proper? Valid reason in discussion group
▶️ከተማ መቐለ❤️
፡
👉የናንተ ከተማም ላኩልን
፡
🙏ወብ ምሽት ተመኘን😍
For any softwares, search on www.getintopc.com
👉የ ዕለቱ ግላዊ ዕይታ ... የናንተ ዕይታም @COTMp ፃፉልን
.
▶️በሀገራችን የግንባታ ስራዎች ጥራት ማጣት ችግር ወነኛ ተጠያቂ አማካሪዉ ነዉ። ችግሩ በዋነኛነት የሚነሳዉ ከዲዛይኑ በጥራት አለመሰራት ነዉ። የዲዛይን ችግር ብዙ ችግሮች ያስከትላል።
.
1ኛ) ዲዛይኑ ራሱ ትክክል ላይሆንና ተገንብቶ አልቆ የማይሰራ ወይም ወድያዉ የሚበላሽ ሊሆን ይችላል። ባደጉት ሀገሮች እንድህ አይነት ፕሮጄክቶችን ''White Elephant'' ይሉታል። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂ አማካሪዉ ነዉ። ኮንትራክተሩስ ብትሉ በርግጥ አንዳነድ ብቃትና ልምድ ያላቸዉ ገና የጨረታ ዶክመንቱን ሲያዩ ዲዛይኑ ትክክል እንዳልሆነ የሚገባቸዉ አሉ። ብዙዎቹ ዲዛይኑ እንዲስተካከል ይጠይቃሉ ግን መልስ ስለማያገኙ ትተዉ ዋጋ ይሞላሉ ወይንም መወዳደሩን ይተዋሉ። ስግብግቦቹ ተወዳድረዉ ካሸነፉ ወደ ስራ ገብተዉ በየቀኑ የስራ ትእዛዝ አየወሰዱ መረጃና ማስረጃ በጥንቃቄ እየያዙ የሰሩትን ሰርተዉ ገነዘባቸዉን ተቀብለዉ ይሄዳሉ ስለዉጤቱ ግድ አይላቸዉም የኔ ችግር አይደለም የዲዛይኑ ነዉ ይላሉ። ተጠያቂነቱን የአማካሪዉ ያደርጋሉ ማለት ነዉ።
.
2ኛ) የዲዛይን ጥራት ችግር BOQ በጥራት እንዳይዘጋጅ ያደርጋል። በየአይተሙ የኳንቲቲ መብዛት ወይም ማነስ፣ ወይም ጭራሽ BOQ ዉስጥ አለመካተት ያስከትላል። ይህ ደግሞ ስራ ዉስጥ ከተገባ ቡሃላ Variation, price qoutation, additional work order..... ምናምን የሚባሉ ችግሮች ያስከትልና በየግዜዉ በዉሳኔ መዘግየት ስራ እየቆመ አየተሰራ ረጅም ግዜ፣ ከታሰበዉ በላይ ወጪ ና አንዳንዴም አስከመቋረጥ የሚደርስ ችግር ያስከትላል። ይህም በዋነኛነት አማካሪዉ ያመጣዉ ችግር ነዉ።
.
3ኛ) መጀመሪያ የዲዛይን ስህተት ቢኖረዉም ወደ ስራ ሲገባ ከፍተኛ ክትትል በማድረግ ዲዛይኑን On ground ቼክ አያደረገ(እዚህ ጋ ኮንትራክተሩም ቼክ የማድረግ ሀላፊነት አለበት) ማስተካከያ እየሰጠ ግንባታዉን ዉጤታማ ማድረግ ያለበት በበላይነት አማካሪዉ ነዉ። ስለዚህ በግንባታ ወቅት ይህ ባለመደረጉ በወነኛነት አሁንም አማካሪዉ ተጠያቂ ይሆናል።
.
4ኛ) ሁሉም ቅድመ ግንባታ ስራዎች Perfect ሆነዉ በግንባታ ወቀት ኮንትራክተሩ ስግብግብ ሆኖ በ poor workmanship, poor quality material, other act of corruption ግንባታዉ ቢበላሽ ይህንን እላዩ ላይ ቆሞ በሀላፊነት በየደቂቃዉ እየተቆጣጠረ እንዳይፈጠሩ ማድረግ በዋነኛነት የአማካሪዉ duty ስለሆነ ከዚህ ጋር በተያያዘ ግንባታዉ ቢበላሽ አሁንም ተጠያቂዉ አማካሪዉ ነዉ።
.
ስለዚህ ለሀገራችን የግንባታ ችግሮች ግንባር ቀደም እና ዋነኛ ተጠያቂ አማካሪዉ/Consultant/ ነዉ።
.
የናንተ ዕይታም DISCUSSION ወይም @COTMp ፃፉልን

@etconp
❤1
👉መሰረት /ፋውንዴሽን/ @COTMp
▶Foundation
1) ቁፋሮ እና አፈር ሙሌት
*መሰረት ሁልጊዜ የተረጋጋ መሬት ላይ ሊቀመጥ ይገባል።
ጥሩ አፈር ካልሆነ በተመረጠ እና ከሌላ ቦታ በመጣ አፈር በሚገባ
ተጠቅጥቆ እና ተደልድሎ ሊቀመጥ ይገባል።
*የተመረጠው አፈር ንብርብር/layer/ በየ 25 ሴ᎐ሜ በሚገባ
ሊጠቀጠቅ ወይም ሊደለደል/compact/ ሊደረግ ይገባል።
*በሚደለደልበት ወቅት በተወሰነ ረገድ እያንዳንዱን ንብርብር
ለተሻለ ጥቅጠቃ እንዲያመች እርጥበት እነዲያገኝ ውሀ
ማርከፍከፍ ያስፈልጋል
2) አርማታ ሙሌት እና የብረት ስራ
*ቀጭን አርማታ/lean Concrete/ ከተመረጠው አፈር ሙሌት በላይ ሊደረግ ይገባል። እንደአስፈላጊነቱም እርጥበተ መከላከያ/water proof/ ሊደረግ ይችላል።
*አርማታ ሙሌት ለመሰረት፣ ቢም፣ ኮለን እና ወለል ስራ የአርማታ ጥንካሬ በትንሹ C25 ሊኖረው ይገባል። (እንደ ስትራክቸራል ዲዛይኑ ሊለያይ ይችላል)
*የቢም ብረት የላይኛው ብረት መሀል ላይ የታችኛው ደግሞ
ኮለን ድጋፍ/support/ ላይ ሊሆን ይገባል። (ማት ፋውንዴሽን ላይ
የዚህ ተቃራኒ ይሆናል)
*ብረት 4D የብረቱን ውፍረት በአራት በማባዛት የሚሰጠንን
ርዝመት በመደረብ መተላለፍ ይተበቅበታል።
*ዲዛይን ላይ በተቆራረጠ መስመር /hidden line/የሚቀመጡ ብረቶች ሁልጊዜ የታች ብረት ሆነው ይቀመጣሉ።
*የአርማታ ሽፋን/concrete cover/አብዛኛውን ግዜ 5ሴ᎐ሜ
ይሆናል ከመሬት በላይ ግን በ 2᎐5ሴ.ሜ ይሰራል።
*በአርማታ ወይም በብረት የሚሰራ ክፍተት መስጫ/spacer/ ልንጠቀም ይገባል።
.
⚡ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።