Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የግንባታ ሼል  ውል አፈጻጸም ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑ ዋና ዋና  ባለድርሻ አካላት፡

➡️የስራው ባለ ቤት/Client or Employer/

*⃣ግለሰብ ወይም ማህበር ወይም ድርጅት ወይም የመንግስት ተቋም ሊሆን የሚችል ሲሆን የሥራው ባለቤት ከመሆኑ አንጻር ሥራውን ለማከናወን የሚችል ሥራ ተቋራጭና አማካሪ መሃንዲስ መቅጠር እና ለግንባታ ሥራው የሚያስፈልገውን የገንዘብ ሀብት የሚያዘጋጅና ዋጋ የመክፈል ሃላፊነት ያለበት አካል ነው፡፡

➡️ሥራ ተቋራጭ:-

*⃣ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን ግብዓቶች በሙሉ በሟሟላት የግንባታ ሥራውን  በተባለው ጊዜና በተቀመጠው የጥራት ደረጃ ለመስራት ተዋውሎ የሚሰራ ነው፡፡

➡️መሃንዲስ(አማካሪ):-

*⃣ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ውለታውን እንዲያስተዳድር የሚቀጠር ነው፡፡ምንም እንኳን አማካሪ መሃንዲሱን የሚቀጥረውና ክፍያ የሚፈጸምለት በአሰሪው ቢሆንም፤ አማካሪው ውሉን በማስተዳደር ሂደት ውስጥ በቅን ልቡና በፍጹም ፍትሃዊነት ለሁለቱም የሚሰራ ነው፡፡

➡️የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅቶች (Insurance Companies):-

*⃣አንድ ሥራ ተቋራጭ በጨረታ ለመሳተፍ፣ ወደውል ለመግባት፣ ክፍያዎች ለማግኘትና በሌሎች አሰሪው ድርጅት ለደህንነቱ መጠበቂያ ከስራ ተቋራጩ እንዲቀርብለት የሚጠይቀውን የመተማመኛ የመድን ዋስትናዎች ለሥራ ተቋራጩ የሚያቀርብ አካል ነው።

*⃣ከዚህ በተጨማሪ ሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ ለንብረቱ፣ ለገንዘቡ፣ ለስራውና ለሰራተኞቹ ደህንነት የሚጠይቃቸውን የመድን ዋስትናዎችንም (for Contractor’s all risks) የሚያቀርብ ይሆናል።

*⃣አንድ የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅት አይነቱ ተለይቶ ለታወቀ ጉዳይ ለሥራ ተቋራጩ የመድን ሽፋን ሰጠ ማለት በአሰሪው ድርጅትና በሥራ ተቋራጩ በኩል ሊኖር የሚችለውን የአደጋ ስጋት ለመሸከም ሃላፊነት የሚቀበል ይሆናል ማለት ነው።

*⃣ለወደፊት ስለግንባታ ፕሮጀክቶች የመድን ዋስትናዎች (Construction Insurances) በተብራራ ሁኔታ በምናቀርበው ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡

➡️ባንኮች:-

*⃣ለሾል ተቋራጩም ይሁን ለስራው ባለቤት ለፕሮጀክቱ ማከናወኛ የገንዘብ ፍላጎቶችን በማመቻቸት የሚሰሩ ናቸው፡፡ ባንኮች እንደ የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ የባንክ ዋስትናም በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡ 

➡️አቅራቢዎች (Suppliers):-

*⃣እነዚህ ባለድርሻ አካላት ለግንባታ ሼል ከመጀመሪያ እስከ ሥራው ፍጻሜ የሚያስፈልጉ ማናቸውንም ዓይነት የግንባታ ሼል ግብዓቶችን፣ ማሽነሪዎችን ወይም የግንባታ ሼል ቁሳቁሶችን በሽያጭና በኪራይ  የሚያቀርቡ ናቸው፡፡

➡️ፈቃድ ሰጪ አካላት (Permitting bodies):-

*⃣ለግንባታ ሥራው የግንባታ ቦታ በመፍቀድ፣ የግንባታ ፈቃድ በመስጠት፣ የግብዓት ማውጫ ካባዎችን ፣የማምረቻ የማከማቻና የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ፈቃድ በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡

➡️የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅራቢ ተቋማት (Public):-

*⃣ለግንባታ ሥራው እንደ ውሃ፣መብራት፣ስልክ የመሳሰሉ ለግንባታ ሥራዎች የመሰረታዊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ አካላት ናቸው፡፡

@etconp
👍14
👉የፌደራል የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ

➡️የፌደራል የመሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን እና ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በጋራ ለማከናወን የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ።

➡️ሥምምነቱን የፌደራል የመሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንንና የኢትዮ- ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ መፈራረማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@etconp
👍9
👉በሀገራችን ኢትዮጵያ በግንባታው ዘርፍ የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች:

➡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የማጭበርበር አመለካከትና ተግባር የሚስተዋልበት ነባራዊ ሁኔታ መኖሩ

➡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰለጠነና የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ኃይል እጥረት ያለ መሆኑ

➡️የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ስራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተሳለጠ ያለመሆኑ

➡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሠማሩ አማካሪዎችና ተቋራጮች መካከል ተወዳዳሪነት በሚፈለገው ደረጃ ማድረስ ያልተቻለ መሆኑ

➡️ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ሠንሠለት ያልተዘረጋ መሆኑ

➡️ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መስፋፋትና መጠናከር የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጥር የፋይናንስና የማሽነሪ አቅርቦት ሥርዓት የተጠናከረ ያለመሆን

➡️የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዋና ዋና ባለሚናዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ለዘርፉ የተፋጠነ ዕድገት በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ ያለመፈጠሩ

➡️የህንፃ ግንባታና መጠቀሚያ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አገልግሎት የተጠናከረ ያለመሆን

➡️ፈርጀ ብዙ ሥራዎች ከኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሥራዎች ጋር ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገብሩበት ሥርዓት ያለመዘርጋቱ

➡️የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም ወይም ፓኬጅ አዘጋጅቶ በተሟላና በቀጣይነት ያለመተግበር

➡️ለባለሞያዎችና ስራተቋራጮች የሚደረግ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እጅግ አናሳ መሆኑ

📩እርስዎም ሀሳብዎን ያስቀምጡ

Via Abel

@etconp
❤8👍7
👉የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች 8 ቁልፍ ሚናዎች እና ኃላፊነቶች

➡️1. እንቅስቃሴ እና ሀብት ዕቅድ

*እቅድ የፕሮጀክት ቀነ-ገደቦችን ለማሟላት አስፈላጊ ነው ፣ እና ብዙ ፕሮጄክቶች በጥሩ ዕቅድ ምክንያት ይሳካል። በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ ፣ ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች የፕሮጀክቱን ወሰን ይገልፃሉ እናም የሚገኙትን ሀብቶች ይወስናሉ ፡፡ ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እንዴት የቡድን ወይም የቡድን አቅሞችን በእውነተኛ ጊዜ ማዋቀር እና መገምገም እንደሚችሉ ያውቃሉ ፡፡

*⃣ከዚያ ፕሮጀክቱን ለማስፈፀም እና እድገቱን ለመቆጣጠር ግልፅ እና እጥር ምጥን ዕቅድ ይፈጥራሉ ፡፡ ፕሮጀክቶች በተፈጥሮ ሊተነበዩ የማይችሉ ናቸው ፣ ስለሆነም ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ፕሮጀክቱ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማስተካከያዎችን እንዴት እንደሚያደርጉ ያውቃሉ ፡፡

➡️2. የፕሮጀክት ቡድን ማደራጀት እና ማነሳሳት

*ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ቡድኖቻቸው በዝርዝር የተመን ሉህዎች ፣ ረጅም ማጣቀሻዎች እና በነጭ ሰሌዳዎች እንዲታሰሩ አያደርጉም። ይልቁንም ቡድኖቻቸውን የፊት እና የመሃል ላይ አደረጉ፡፡
*⃣ቡድኖቻቸውን ሙሉ አቅማቸውን ለማሳካት ግልጽ እና ቀጥተኛ ዕቅዶችን ያዳብራሉ እንዲሁም ቢሮክራሲን በመቁጠር ቡድኖቻቸውን ወደ የመጨረሻ ግብ ለመምራት ግልፅ መንገድን ይመራሉ ፡፡

➡️3. የጊዜ አያያዝን መቆጣጠር

*ደንበኞች ብዙውን ጊዜ የፕሮጀክቱን ስኬት ወይም ውድቀት በሰዓቱ ማድረሱ ላይ ይፈርዳሉ ስለዚህ የስምምነት ቀኖችን መገናኘት ድርድር የሚደረግ አይደለም።
*⃣ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ተጨባጭ ቀነ-ገደቦችን እንዴት ማቀናጀት እንዳለባቸው እና እንዴት ለቡድኖቻቸው በተከታታይ እንዴት መገናኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ ፡፡

🌟የሚከተሉትን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ያውቃሉ-

*እንቅስቃሴን ይግለጹ ቅደም ተከተል እንቅስቃሴ የእንቅስቃሴውን ቆይታ ይገምቱ መርሐግብር ያዘጋጁ የጊዜ ሰሌዳ ይኑራቹ

➡️4. ወጪ መገመት እና በጀቱን ማጎልበት

*ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች አንድን በጀት በተያዘለት በጀት ውስጥ አንድ ፕሮጀክት እንዴት ማቆየት እንደሚችሉ ያውቃሉ ምንም እንኳን አንድ ፕሮጀክት የደንበኞቹን ፍላጎቶች የሚያሟላ እና በሰዓቱ ቢቀርብለት እንኳን ከበጀት በላይ ቢወጣ አሁንም ውድቀት ይሆናል።
*ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ብዙ ጊዜ በጀቱን ይገመግማሉ እና ግዙፍ የበጀት አጠቃቀምን ለማስወገድ አስቀድሞ ያቅዱ ፡፡

➡️5. የደንበኞችን እርካታ ማረጋገጥ

*በመጨረሻ አንድ ፕሮጀክት ስኬት የሚሆነው ደንበኛው ደስተኛ ከሆነ ብቻ ነው።
*⃣የእያንዳንዱ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ቁልፍ ከሆኑት ኃላፊነቶች አንዱ እርግጠኛ አለመሆንን ለመቀነስ ፣ ማንኛውንም አላስፈላጊ የሆኑ ድንገተኛ ነገሮችን በማስወገድ እና በተቻለ መጠን ደንበኞቻቸውን በፕሮጀክቱ ውስጥ ማሳት ነው።
*⃣ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ውጤታማ የሆነ ግንኙነትን እንዴት ጠብቆ ማቆየት እና የኩባንያውን ደንበኞች ወቅታዊ ማድረጉን እንዴት ያውቃሉ።

➡️6. የፕሮጄክት ስጋት ትንተና እና ቁጥጥር

*ፕሮጀክቱ ትልቅ ከሆነ ፣ የመነሻ ዕቅዱ አካል ያልሆነ መሰናክሎች እና መሰናክሎች የመፍጠር እድሉ ሰፊ ነው። Hiccups መከሰት የማይቀር ነው ፣ ግን ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ፕሮጀክቱ ከመጀመሩ በፊት እንዴት በጥንቃቄ እና በጥልቀት እንደሚረዳ ፣ እንዴት ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ለይቶ እንደሚገመግሙ ያውቃሉ ፡፡ ከዛ አደጋዎችን እንዴት ማስወገድ ወይም ቢያንስ የእነሱን ተፅእኖ ለመቀነስ እንደሚችሉ ያውቃሉ ፡፡

➡️7. መሻሻል መከታተል

*⃣በመነሻ ደረጃዎች ውስጥ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች እና ቡድኖቻቸው የተፈለገውን ውጤት የማስገኘት ግልፅ ራዕይ እና ከፍተኛ ተስፋ አላቸው ፡፡ ሆኖም ፣ ወደ ማጠናቀቂያው መስመር የሚወስደው መንገድ በጭራሽ በጭራሽ በጭራሽ አይደለም።
*⃣ነገሮች በእቅዱ መሠረት የማይሄዱ ከሆነ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሁለቱንም ወጭዎች እና የቡድን አፈፃፀም መከታተል እና መተንተን እና ሁል ጊዜም የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት።

➡️8. ሪፖርቶችን እና አስፈላጊ ሰነዶችን ማስተዳደር

*በመጨረሻም ፣ ልምድ ያላቸው የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች የመጨረሻ ዘገባዎች እና ትክክለኛ ሰነዶች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ ያውቃሉ።
*ጥሩ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ሁሉም የፕሮጄክት መስፈርቶች ተሟልተዋል እንዲሁም የፕሮጀክቶቹ ታሪክ ፣ ምን እንደተደረገ ፣ ማን እንደተሳተፈ እና ለወደፊቱ በተሻለ ምን ሊከናወን እንደሚችል ጨምሮ አጠቃላይ ሪፖርቶችን ማቅረብ ይችላሉ ፡፡

#ConstructionManagment

Via Abeselom melese

@etconp
👍12
የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል 1 የማሻሻያ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ በረራ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ሲካሄድለት የነበረው የማሻሻያ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል አንድ በግንባታ ላይ በነበረበት ወቅት የሀገር ውስጥ መንገዶች የዓለም አቀፍ በረራዎች ተጓዦች የሚጠቀሙበትን ተርሚናል ሁለት ሲጠቀሙ ቆይተዋል።

በቻይናው ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) ግንባታው የተከናወነው ተርሚናል አንድ በ16 ሺህ 689 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ መሆኑን ከግንባታው ተቋራጭ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@etconp
👍7
Ethio Construction Engineering
Northern Ethiopia cultural housing style - ከጥንት ከ አክሱማውያን ዘመን ጀምሮ ሲወርድ ሲዋራረድ የነበረ የቤት አሰራር ዘይቤ ነው። - ድንጋይ በ ጭቃ በማጣበቅ ከ አንድ በላይ ወለል(multistory) በመስራት ከሌሎች ባህላዊ የቤት አሰራሮች ይለያል። - ባህላዊው አሰራር ጣራው ሚለብሰው በ ሳር ነው። ይሄን አይነቱን ቤት ለመስራት ቅደም ተከተሎች ፩. ከ…
Southern Ethiopia cultural housing style

ደቡብ ኢትዮጵያ የሚታወቁበት የቤት አሰራር ጎጆ ቤት ነው። የተለያዩ ኪነህንፃ ይዘት ያላቸው ግን በስያሜ ጎጆ ተብለብ ይጠራሉ። ከ ቦታ ቦታ የተለያየ አይነት ጎጆ አለ፣ ባህላቸውን ይገልፃል ያሉትን ጎጇቸው ያንፀባርቃሉ።

ይህ አይነቱ ቤት እንዴት ይሰራ ይሆን?

፩. ምሶሶ የሚቆምበትን ቦት መለየት ምክንያቱም
ጎጆ ቤት ክብ ነው ስለዚህ ምሶሷችን መሀል(at
the radial point) ላይ ነው የሚያርፈው ስለዚህ
ወፈር ያለ እንጨት እናዘጋጃለን።
፪. ምሶሷችንን ማቆም
፫. ለውጫዊ ግድግዳ አጠር ያሉ እንጨቶችን
ዙሪያውን ማቆም (በጣም መጠጋጋት አለበት)
ከዛ ቱንቢ እንጥላለን
፬. ምሶሶውን ከ ውጫዊ እንጨቶች ጋር በ እንጨት
ማገናኘት ስለዚህ ሲገናኙ roof truss እናገኛለን
እዛው ላይ ቀጫጭን እንጨቶችን እንመታለን
እንደ purlin ሞራሌ(ጣውላ) አንጠቀምም ለሳር ከሆነ ቆርቆሮ ከመታን ግን ሞራሌ አስደግፈን ነው ከዛን ሸራ እናለብሳለን(ለሳር ጎጆ) ከዛን ሳር እናለብሳለን ጣራችንን ጨረስን
፭. ግድግዳችን ከፈለግን በጭቃ እንመርጋለን ወይም ሳር እናለብሰዋለን ወይም ደግሞ ቅርጮ እንደምርጫችን።

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE
👍5
👉የአዲስ ኮንክሪት ጥሩ ባህርያት /Properties of Fresh Concrete/

➡️ኮንክሪት ለመብላለት/ለመደባለቅ/Mix/፣ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ/to transport/፣ለማስቀመጥ/deposit/ እና ለመጠቅጠቅ/Compact/Vibrate/ ቀላል ወይም ምቹ ሆኖ ሲገኝ ጥሩ ነው።

➡️የእነዚህ ጥምር ውጤት ኮንክሪቱ ከስራ ምቹነቱ ባሻገር ኮንክሪቱ ላይ የመግጠጥ ችግር እንዳይከሰት /resistance to segrigation/ የሚረዳ ይሆናል።

➡️ከላይ የገለፅናቸውን ባህርያት ያሟላ ኮንክሪት «ምቹ»/Workable/ ነው ብለን የምንጠራው ይሆናል። እንዚህን ባህርያት የሚያሟላ መሆኑን የምናተጋግጥበት የስራ ምቹነት/ፅኑነት ምርመራ/ workability test/ Consistancy test ይባላል።

➡️የኮንክሪት workability ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

*1ኛ.የውህድ ምጣኔ ትክክል አለመሆን/Mix ratio/

*⃣2ኛ. የጠጠር ወይም የአሸዋ የግርድፍ መጠናቸው/Gradation/ ወይም ቅርፅ/Shape/ልክ ያለመሆን

➡️የኮንክሪት workability እንዴት ማወቅ እንችላለን?

*በሳይት እና በቤተ ሙከራ ይህን የምናረጋግጥባቸው 4 መንገዶች አሉ።እነዚህም:

➡️1. Slump test
➡️2.Compacting factor test
➡️3.Veebee test እና
➡️4.Vibro workability test ናቸው።

🌟ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት/Slump test/Cone test/Sand test/

➡️የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በቀላሉ በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት
ሲሆን የኮንክሪትን ለስራ ያለውን ምቹነት (Workability) እና ፅኑእነት
(Consistency) ለመለካት ይጠቅማል።

➡️ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ወቅት መሰራት ያለበት ሲሆን በምን ዓይነት የጊዜ ልዩነት ወይም በየስንት መጠን መሰራት እንዳለበት በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል።

➡️ስላምፕ ቴስት በቀላል ወጪ የሚሰራ በመሆኑ ተመራጭ የመፈተሻ መንገድ ነው። በዚህ ምክንያት ከ1922GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።

➡️የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ውጤት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች
(Factors influencing slump test result)

*1- ለኮንክሪቱ  የተጠቀምናቸው ግብአቶች ባህርይ።

🌟ለምሳሌ:  ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት
፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም.

*2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠንና አይነት መስተጋብር.

*3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም።

*⃣4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ

*⃣5- የኮንክሪቱ ሙቀት መጠን /temperature/

*⃣6- የተጠቀምነው የውሃ መጠን

*⃣7- ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ

🌟Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች ምን ምን ናቸው?

➡️ጉርድ የኮን ቅርፅ/Truncated cone/

*⃣ይህ ቅርፅ ማውጫ 30cm የታችኛው ዲያሜትር 20 cm የላይኛው ዲያሜትር 10cm ዲያሜትር ነው

➡️Plate/መደብ/

*⃣ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው
መጠቅጠቂያ ብረት/Compaction rod/

🌟የስራ ቅደም ተከተሉ እንዴት ነው?

*⃣1ኛ. መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት።

*⃣2ኛ. ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን/plate/ ላይ ማስቀመጥ።

*3ኛ. የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት መሙላት።

*⃣4ኛ. እያንዳንዱን የኮንክሪት ሌየር 25 ግዜ በመጠቅጠቂያው ብረት መምታት የአጠቃጠቅ ጉልበታቱ እኩል መሆን አለበት።

*⃣5ኛ. ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ስፋት ባለው ጫፍ ላይ ያለ ትርፍ ኮንክሪትን በቅርፅ ማስወገድና መለሰን።

*⃣6ኛ. በርጋታ  ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ወደላይ በመሳብ ከኮንክሪቱ ማለያየት።

*⃣7ኛ. ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold) ያለውን የርዝመት ልዩነት መለካት።

🌟ማስታወሻ:

*⃣ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን መከወን አለብን።

🌟ከቴስት በኋላ የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች:/Results to be/[

➡️True Slump:

*⃣ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ትክክለኛው ልኬት ነው።

🌟ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ ቁመት ከቅርፅ ማውጫው አንፃር የምናገኘው ልዩነት ነው።

➡️Zero Slump:

*ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃና
ሲሚንቶ /water-cement ratio/ያለው መሆኑን ያሳያል።

➡️Collapsed Slump:

*⃣ይህ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃና ሲሚንቶ/water-cement ratio/ ምጣኔ ትልቅ መሆን ያሳያል።የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ እና High workability mix መሆኑን ያሳየናል።

➡️Shear Slump

*⃣ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤቱ ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።
…………………………………

🌟ከወደፊት ሌሎች የኮንክሪት ለሾል  ያለው ምቹነት ላይ ያለውን ደረጃ የምንመዝንባቸው የቴስት ዓይነቶች የምናቀርብ ይሆናል።

📩ጥያቄ ወይም አስተያየት ካልዎት
@ETCONp_Bot ላይ ፃፉልን

@etconp
👍27👌3🥰1🤣1
✋ሰላም አዲስ ለተቀላቀላቹን የዚህ ቻናል ቤተሰቦች

🔖ይህ ቻናላቹ ዲጂታል ላይብረሪ እንዳለው ያውቃሉ?

📚ይህም ዲጂታል ቤተመፃህፍት በውስጡ የ ኮንስትራክሽን ሶፍትዌር ሴትአፖች ጨምሮ ሙሉ የ ARCH, COTM እና CIVIL መፅሀፍቶችን የያዘ በተጨማሪ ኢንትራንስ ኤግዛም አለዉ።

🚧ይህ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሲሆን ለቀጣይ በአስተያየታቹ መሰረት ብዙ ነገር ምናስተካክል ይሆናል።

👉ይህን link በመጫን ወደ ቤተመፃህፍቱ ልትሄዱ ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇
👉🏿 https://t.me/ETCONpDigitalLibrary_Bot
🙏11👍5❤1🤡1
Ethio Construction Engineering
✋ሰላም አዲስ ለተቀላቀላቹን የዚህ ቻናል ቤተሰቦች 🔖ይህ ቻናላቹ ዲጂታል ላይብረሪ እንዳለው ያውቃሉ? 📚ይህም ዲጂታል ቤተመፃህፍት በውስጡ የ ኮንስትራክሽን ሶፍትዌር ሴትአፖች ጨምሮ ሙሉ የ ARCH, COTM እና CIVIL መፅሀፍቶችን የያዘ በተጨማሪ ኢንትራንስ ኤግዛም አለዉ። 🚧ይህ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሲሆን ለቀጣይ በአስተያየታቹ መሰረት ብዙ ነገር ምናስተካክል ይሆናል። 👉ይህን link…
🌟ውድ ቤተሰቦቻችን ዲጂታል ላይብረሪው እንዴት አገኛችሁት ምንስ ይጨመር @COTMp ላይ ሀሳባቹ እና ጥያቄያቹ ፃፉልን።

@etconp
👍6👏3❤1
👉አንድ የስራ ተቆጣጣሪ ባለሞያ የኮለን ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት ፎርምወርክ ስራው ላይ መሟላታቸውን ማረጋገጥ የሚገባው መሰረታዊ ነጥቦች

➡️1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity

*⃣የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት/self weight/፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ስራ ይሆናል።

➡️2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/

*⃣ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ሌላ አስፈላጊ ስራ ነው::

➡️3.አቀባዊ ሊኛ/Vertical alignment/

*የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን ማረጋገጥ አለበት።

➡️4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/

*የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው ሆኖ መቀመጡን ማረጋገጥ አለበት።

➡️5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/

*በዲዛይኑ መሰረት የኮለኑን ወርድና ስፋት ከፎርምወርኩ አቀናንሶ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ።

➡️6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/

*ከታወቀ መነሻ በመነሳት አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ።

➡️7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/

*ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

➡️8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት
/Concrete cover/

*ለኮንክሪት ሽፋን ዲዛይኑ የሚጠይቀው ተገቢ መጠን፣ በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው።

@etconp
👍34❤4👌3
👉ስለ አንድ ህንጻ አጠቃላይ ይዘቶች

🏠የአንድ ህንፃ ክፍል በዋናነት በሁለት ይከፈላል።

➡️1.ታችኛው መዋቅር/Sub structure/: ከመሬት በታች የሚገኘው የህንጻ ግንባታ ክፍል ሲሆን

➡️2.ላይኛው መዋቅር/Super structure/: ከመሬት በላይ የሚገኘው የህንጻ ግንባታ ክፍል ሲሆን

🏠አንድ ህንጻ የሚኖሩት መሰረታዊ ይዘቶች/Basic Components/
*መሰረት/Foundations/
*⃣ግድግዳዎች/Walls/
*⃣ወለሎች/Floors/
*⃣በርና መስኮቶች
*ደረጃዎች
*⃣ጣሪያዎች

*የተለያዩ አገልግሎት ላይ የሚው የማጠናቀቂያ ስራ ግብዓቶች

🏠አንድ ህንጻ የታሰበለትን የተሟላ አገልግሎት እንዲያስገኝ በዲዛይን ወቅት መታወስ ስለሚገባው መሰረታዊ ሁኔታዎች/Design and Performance requirements/

➡️1.ህንጻው በቂ ጥንካሬና ፅኑነት ሊኖረው የሚገባ ሆኖ ዲዛይን መደረጉን/Strength and Stability/

➡️2.የመለጠጥ ወይም የመኮማተር ርጋቴው ታሳቢ መደረጉ/Dimensional Stability/

➡️3.የተጠቃሚውን ምቾት ያገናዘበ /Comfort and Convenience/

➡️4.ርጥበትና የፍሳሽ ስርገትን የመከላከል ብቃት ሊኖረው የሚገባ መሆኑ/Resistance to Moisture Protection/

➡️5.እሳት የመቋቋም ብቃት /Fire protection/

➡️6.የሙቀት ክለላ/Heat thermal/ insulation

➡️7.በቂ ብርሃንና አየር የሚያስገባ መሆኑ/light and Ventilation/

➡️8.የድምፅ ክለላ/Sound Insulation/

➡️9.ለረጅም ጊዜ ዘላቂ ስለመሆኑ/Durability/

➡️10.ጥበቃ/ደህንነት/Security/

➡️11.በብል በቀላሉ የማይጠቃ መሆኑ/Protection to Vermin and termites/

➡️12.ወጭ ቆጣቢ መሆኑ/Building Economy/

@etconp
👍24❤3
' ወጂዝ ሪል ስቴት ' በከፍተኛ የጥራት መመዘኛ እንደገነባቸው የገለፃቸውን 53 á‹¨áŠ á“áˆ­á‰łáˆ›áŠ“ የንግድ ሱቅ ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች ማስረከቡን ገልጿል።

" በሪል ስቴት ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እያከናወንኩ ነው " ያለው ወጂዝ ሪል ስቴት ፤ ግንባታቸው የተጠናቀቀላቸውን (የዋና መግቢያ በር ፣ የመስኮት መስታወት እንዲሁም የመጨረሻ የቀለም ቅብ) ብቻ የቀሩት በቤተል አካባቢ የሚገኙ በድምሩ 53 ባለ-ሶስት መኝታ አፖርታማ ቤቶችንና የንግድ ሱቆችን ለደንበኞቹ ማስረከቡን አመልክቷል።

በመኖሪያ አፖርትመንቶቹ ግንባታ ሂደት ወቅት በርካታ ደንበኞች በውል መሠረት በወቅቱ ክፍያቸውን ያለመፈፀምና ክፍያ የሟቀረጥ ክፍተቶች መፍጠራቸው እንዲሁም በኮቪድ ወረርሺኝ ወቅት በተፈጠረው የስራ መቀዛቀዝ የርክክብ ጊዜውን በመጠኑ መዘግየቱ ተመላክቷል።

ሪል ስቴቱ በቅርቡ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ በሚገኙ #ሌሎች ሳይቶቹ  ለህጋዊና ውላቸውን በአግባቡ በመፈፀም ላይ ለሚገኙ ደንበኞቹ ቁልፍ የማስረከብ ሾል እንደሚሰራ አሳውቋል።

Via ዋልተንጉስ ዘሸገር

@etconp
👍5👏1
👉ስለ አፈር ጥቅጠቃ ስራ/Soil Compaction/ በጥቂቱ ...

➡️Soil Compaction: - በሜካኒካል መንገድ የአፈርን የመሸከም አቅምን የምንጨምርበት መንገድ ነው።

➡️እንዴት?

🌟አፈሩን ስንጠቀጥቅ የአፈር ፓርቲክሎች  ጥግግቶሽ ወይም ትፍፍግ density/ እንዲጨምር እናደርጋለን።
*⃣ይህም በአየርና ውሃ የተያዙ ቦታዎች /water and air voids/በአፈር እንዲተኩና እየዲቀንሱ ማድረግ ማለት ነው።

➡️ይህም በመሆኑ:

*⃣የአፈሩን የመሸከም አቅም/Load bearing capacity of soil/ ከፍ እናደርጋለን።

*⃣በውስጡ የውሃ ማንሸራሸር አቅሙን/permeability/ እንቀንሳለን።

*⃣ስምጠት እንዳይኖር ያደርጋል/reduce future settlement/

➡️የደረቅ አፈር ከፍተኛ እፍግታ መጠን/Maximum dry density of soil/

*⃣የደረቀ አፈር /ከድንግል መሬት/ ከፍተኛ እፍግታ መጠን/density/=1900kg/m3 ነው።

➡️በሰው ሰልሽ ጥቅጠቃ/Artificial Compaction/ በላቦራቶሪ ሙከራ  የምናገኘው እፍግታ /Proctor density/ ደግሞ ቢያንስ 95% እንዲመጣ ይጠበቃል።ከ95% በታች ከመጣ ወዳቂ ሆኖ የጥቅጠቃ ስራው እንደገና መሰራት ይኖርበታል።

🌟ማስታወሻ:- ደረቅ አፈር ስንል በማድረቂያ ማሽን/Oven/ ውስጥ የደረቀ ማለታችን ነው።

➡️የአፈር እፍግታ ማወቂያ መንገዶች/methods of testing soil density/

*⃣በዋናነት በሁለት ይመደባሉ።

▶️በሳይት ላይ የሚተገበሩ /Field test/: Sand cone test, Rubber balloon method, Nuclear density, Time domain reflectometry, Shelby tube/ባብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል/ናቸው።

▶️በቤተ ሙከራ የሚተገበሩ/Laboratory tests/: Proctor test, Modified proctor test... 

↪️አሁን ደሞ በሳይት ላይ የአፈርን እፍግታ ስለምንፈትሽበት መንገድ እናያለን።

➡️Field density of soil/Cone test/Sand replacement test/

⏯ተጠቅጥቆ የተጠናቀቀውን አፈር በሳይት ላይ እፍግታውን የምንፈትሽበት መንግድ ነው።

⏺የሚያስፈልጉ እቃዎች/Apparatuses/

⏭የአሸዋ እቃ/ክብ ጀሪካን መሳይ/Sand pouring cylinder equipment/: ዲያሜትሩ 15cm ቀመቱና 45cm የሆነ ጃር

⏭መቆፈሪያ፣ማፅጃና ማስተካከያ እቃ/Tools for levelling and excavation/

⏭ማንኛውም ማጠራቀሚያ ሰሃን ወይም ሳጥን/Container/:

⏩ንፁህ አሸዋ

⏩ወንፊት

⏩ሚዛን/Balance/

⏩ዳታ መመዝገቢያ ቅጽ

⏹የስራ ቅደም ተከተል/Procedure/

▶️1ኛ.የአሸዋ ጃሩንና አፈር ለማውጫ የተዘጋጀውን ሰሃን ባዶውን መመዘንና መመዝገብ።

▶️2ኛ. ጃሩን አሸዋ መሙላትና ከነአሸዋው መመዘንና በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ መሙላት።

▶️3ኛ. በ15cm ዲያሜትርና በ20cm ጥልቀት የተጠቀጠቀውን ሙሊት አፈር በጥንቃቄ መቆፈርና ሳይባክን እያወጡ በተዘጋጀው ሰሃን ላይ በማድረግ መመዘንና መመዝገብ።

🌟ማስታወሻ:- የጉድጓዱን ልክ ለመወሰን በልክ የተዘጋጀ ፕሮፋይል ልንጠቀም እንችላለን።ምስል 5 ን ይመልከቱ

▶️4ኛ. የአሸዋ ጃሩን ከታች በምስል 1 ላይ በተቀመጠው መሰረት በማድረግ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ላይ በማድረግና መዝገያውን በመክፈት አሸዋው ጉድጓዱን እስኪሞላ ጠብቆ መዝጊያውን በመቆለፍ ጃሩን ማንሳትና ቀሪውን መመዘንና መመዝገብ።

▶️5ኛ. አሸዋውን ደግሞ ለመጠቀም ካስፈለገ ከጉድጓዱ ጠርጎ ማውጣትና በወንፊት እየነፉ በስቀመጫው እቃ ማከማቸት።

▶️6ኛ. የተሰበሰበው ዳታ በመጠቀም. የሳይት ላይ እፍግታውን/Bulk density/ ማወቅ እንችላለን።

▶️7ኛ. ከፍተኛው የደረቅ እፍግታ ልኩን/MDD/ በቤተ ሙከራ ለመስራት ከሰሃኑ ላይ ለናሙና 1/3ኛ ያህሉን በንፁህና ደረቅ ላስቲክ በማድረግ ማዘጋጀት።

🌟ማስታወሻ:-የተወሰደው ናሙና ባእድ ነገር እንዳገባበትና ከሌላ ናሙና ጋር ለመለየት እንዲያስችለረ በጥንቃቄ መታሸግና እላዩ ላይ መለያ ኮድ መጻፍ ይገባል።

⏩እንደስራው ደረጃና የሳይቱ ስፋት መጠን ከላይ የተጠቀሰውን አካሄድ ቢያን ሶስትና ከዚያ በላይ በመሃንዲሱ በተመረጡ ቦታዎች ላይ መስራት ይገባል።

➡️የአፈር ጥቅጠቃ ስራ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

▶️የአፈሩ ዓይነት/soil type/

🌟ለምሳሌ: ኮረታማ/ጠጠርማ/Gravel/Granular/ አፈር ለመጠቅጠቅ ምቹና በጣም ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ሲሆን፣በተቃራኒ ጥቁርና ብስባሽ ያለው አፈር ደግሞ ለመጠቅጠቅ የማይሆንና የማይች በመሆኑ ለማንኛውም ስትራክቸራል ሙሊት ስራ የማይመረጥ ነው ይሆናል ማለት ነው።ከታች በምስል 4 ላይ የተቀመጠውን ይመልከቱ።

▶️የአፈሩ ውሃ ይዘት/soil water content/:

🌟አፈሩ በጣም ውሃ ያዠ ወይም ከልክ በላይ የደረቀ መሆን የምንፈልገውን እፍግታ ማግኘት እንዳንችል ያደርጋል ማለት ነው።

▶️የጥቅጠቃ ሃይል/Compaction Effort/

#Foundation

@etconp
👍27❤1💯1
👉አለምአቀፍ የህንጻ ንድፍ ውድድር

➡️በሴኔጋል ለሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የንድፍ ውድድር ተዘጋጅተዋል ተማሪዎች፣ ህንጻነዳፊዎች፣ የንድፍ ባለሙያዎች በተጨማሪም ማንኛውም ለችግሩ መፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ የሚችል ሰው የተጋበዙ ሲሆን አሸናፊዎች የገንዘብና የአለምአቀፍ ኢንተርንሺፕ ልምምድ ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።

▶️ውድድሩን በነጠላም ሆነ በጋራ መሳተፍ ይቻላል።

🌟ውድድሩን ለመካፈልና መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ድረገጽ ይጎብኙ።

🔖www.kairalooro.com

🎁መልካም እድል🎉

👉2023’s Edition – Primary School in Africa

➡️We are glad to announce the opening of a new contest for a Primary School in Senegal, Africa.
*⃣The competition is open to students, architects and designers from around the world.

➡️Competition Awards:

*⃣1st prize: 5.000€ + Internship at Kengo Kuma in Japan + Construction.
*⃣2nd prize: 2.000€ + Internship at Benedetta Tagliabue EMBT Architects in Spain.
*⃣3rd prize: 1.000€ + Internship at SBGA - Blengini Ghirardelli in Italy.

➡️Others awards: 2 honourable mentions, 5 special mentions, 20 finalists, 20 Top 50.

➡️The registration will open on 13rd January 2023. Participation is open to architects, students, designers, engineers and anyone who wants to propose a solution to the theme. It is possible to participate in the competition individually or in teams.

*⃣We are looking for a new school model that can protect and foster the development of every child’s potential!

➡️All competition proceeds will be donated to support charity projects by Balouo Salo - Humanitarian Organization in Africa aimed to improve life condition if rural communities.

🌟To join the competition, visit our official website: www.kairalooro.com

@etconp
👍4🙏4
👉Ethiopian Association of Civil Engineers EACE invites you to participate in short training: Construction project management overview

🌟By Dr. Denamo Addissie

🏷Register online

https://forms.gle/DfHzG5LBtriEKrVbA

@etconp
👍7
👉የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ።

➡️የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል።

@etconp
🥰1