Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በ Mix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል :-

[1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ
.
አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን።
.
[2] - መኮማተር (Shrinkage )
.
ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking)   ያስከትላል ።
መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ።
.
[3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ
.
Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል።
.
[4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ
.
ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል።

.
[5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing )
.
ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት።
ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ መጠጣት አለበት ።
«ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች😁
.
[6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን
.
በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል።
.
[7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።

@etconp
👍11❤7🙏3👌3🐳1
ዛሬ ዘለግ ያለ ፅሁፍ ይዘን መጥተናል

ETCONp አርኣያ ሰብ

በገበታ ለሀገር ከእየተገነቡ ካሉ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የሚገኝበት የኮንታ ዞን በተፈጥሮ ሀብቶች የታደለው ነው።

ኮንታ ግን በተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሳይሆን በሙያቸው የተካኑ አርክቴክቶችም አግኝቷል።

በ እነዚህ አርክቴክቶች ዲዛይን የተደረገው እና በቅርቡ ተመርቆ ይፋ የተደረገው የሃላላ ኬላ ሪዞርት በርካቶችን አስደምሟል።

በደቡብ ምዕራብ ክልል፣ በኮንታ ዞን የኮይሻ ፕሮጀክት ይገኛል። ታድያ ከዚህ ፕሮጀክት ጀርባ እነማን አሉ? ቢቢሲ ከእነዚህ መካከል ወጣቱን አርክቴክት ኃይሌ ታደሰን አግኝቷል።

በቅድሚያ ግን ስለ ኮይሻ ፕሮጀክት ጥቂት ነገር እንበል።

Via BBC Amharic

@etconp
👍8❤2
ገፅ 1

ይህ የመዝናኛ ስፍራ ልማት የኮይሻ ዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ ልማት የሚባለው ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሲሆን በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ የሚገኝ ነው።

አካባቢው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ መገኛ ሲሆን፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦችም መኖሪያ ነው።

በሚያዝያ ወር መጀመርያ ላይም በደቡብ ምዕራብ ክልል ውስጥ የሚገኘው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የሐላላ ኬላ ሪዞርት በይፋ ተመረቋል።
ገበታ ለሀገር በሚባለው ፕሮጀክት ስር የሆነው እና አዲስ በተመሠረተው ክልል ውስጥ የሚገኘው ይህ የመዝናኛ ስፍራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተመርቆ ተከፍቷል።

ይህ ሪዞርት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የህወሓት ተወካዮች ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት በመገናኘት የተነጋገሩበት ስፍራ ነው።

“ይህ ፕሮጀክት የአካባቢውን ታሪክ እና ባህል የተፈጥሮን እና የሰው ሰራሽ ሀብቶች አጣምሮ የያዘ ነው” ይላል ፕሮጀክቱን ዲዛይን ያደረገው አርክቴክት ኃይሌ።

በክልሉ እየተሰሩ ካሉ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ውስጥ ትልቁ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ መሆኑን አርክቴክቱ አክሎ ይናገራል።

ከዚህም ባሻገር ረዥም እድሜ ያስቆጠረው እና ሰው ሰራሹ ልማት ሃላላ ኬላ የተባለው የድንጋይ ካብ እዚሁ ውስጥ ይገኛል።

“በዳውሮ ሕዝብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ የተገነባው የድንጋይ ካብ ወይንም ኬላ በግምት 1200 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ነው።

መጠሪያውንም ከመጨረሻው ንጉሣቸው ያገኘ ነው። እነርሱ ‘ካቲ ሃላላ ኬላ’ ይሉታል።”

በተጨማሪም የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ፣ እንዲሁም የኮይሻ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የዚሁ ትልቁ ፕሮጀክት አካል ናቸው።
በሃላላ ኬላ ፕሮጀክት ውስጥ በአምስተኛነት ደረጃ የታቀፈው ፕሮጀክት ጫራ የሚባል ማኅበረሰብን ማዕከል ያደረገ ነው።

“የጫራ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ ከአፈር ውስጥ ብረት የማውጣት እውቀት ያለው ሲሆን፣ እስከ ዛሬ ድረስም ይህንን ሙያ እየሰሩ ይገኛሉ። ይህ ማኅበረሰብ የራሱ የሆነ ባሕል እና ክህሎት ያለው ሕዝብ ነው።”
እነዚህ ልማቶች በአምስት ክላስተሮች በመክፈል ዲዛይኑን እንደሰሩ አክርቴክት ኃይሌ ይናገራል።

ከዚህ በተጨማሪ እነዚህን የልማት መዳረሻዎችን ደረጃ በደረጃ እስከ 25 ዓመታት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ ሠርቶ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ “በአጭር ጊዜው የሦስት ዓመት ፕሮጀክት ውስጥ ሃላላ ኬላ እና ጨበራ ሪዞርቶች ይገኛሉ።”


Via BBC Amharic

@etconp
👍3🙏2🤮1
ገፅ 2

አርክቴክት ኃይሌ ማን ነው?

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በግንደ በረት ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ካቺሲ ውስጥ ነው ተወልዶ ያደገው።

የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም ተምሮ ያጠናቀቀው በትውልድ አካባቢው ነው።

በኋላም በወለጋ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸር የትምህርት ዘርፍ አምስት ዓመት ካጠና በኋላ በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል።

ከተመረቀ በኋላም ለሁለት ዓመታት በሐዋሳ እና በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት አገልግሏል።

ከዚያም የሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸራል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፍ አጠናቅቋል።

ተመርቆ እንደጨረሰም የራሱን የግል ድርጅት ‘ሉላ ኢንጂነሪንግ’ በሚል ስያሜ በማቋቋም እየሠራ መሆኑን ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።

“ተወልጄ ያደግኩት ገጠር ውስጥ ነው” የሚለው ኃይሌ፣ በኮንታ አካባቢ ያለው የተፈጥሮ ውበት እንደሚማርከው ይናገራል።

“የአፍሪካ ተራራዎች ተሰብስበው ዳውሮ ከትመዋል ይላሉ ሰዎች” በማለት አካባቢው በተፈጥሮ ሀብት የታደለ መሆኑን ይገልጻል።

በሌላ በኩል የዳውሮ ሕዝብ ያለው ባህል፣ ትውፊት እና ሕግጋት ከዚህም ባሻገር በአካባቢው ያለው ሰላም አስተማማኝ መሆኑንም ይጠቅሳል።
ከዚህ በተጫመሪ ሕዝቡ ለእንግዳ የሚያደርገው አቀባበል የተለየ መሆኑ አካባቢው ለጎብኚ ምቹ እና ሁሉን የያዘ እንደሆነ ይመሰክራል።

አርክቴክት ኃይሌ እንደሚለው ለእነዚህ ፕሮጀክቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አማካኝነት በቅርበት የሚደረገው ክትትል እና የአካባቢው ሰላም ሥራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ አድርጓል።

Via BBC amharic

@etconp
👍7🤣1
ገፅ 3

የአርክቴክት ኃይሌ ሚና ምን ነበር?

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ ከዓመታት በፊት በመሠረተው ድርጅቱ አማካይነት በዚህ ፕሮጀክት እና በሌሎችም ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ከተሳተፉት አካላት መካከል ነው።

‘ሉላ ኢንጂነሪንግ’ የተባለው የእርሱ ድርጅት እና ሌላ ‘ስታዲያ ኢንጂነሪኒግ’ የተባለው ድርጅት በጥምረት የእነዚህን ፕሮጀክቶች ዲዛይን በመሥራት እንዲሁም ቁጥጥር በማድረግ ተሳትፈዋል።

“እነዚህን በክላስተር የተከፈሉትን ዲዛይኖች ‘ኮንሰፕት ዲዛይን’ ከማዘጋጀት ባለፈ የዲዛይን ቁጥጥር እና ክትትል እንድንሰራ ነው ኮንትራት የገባነው” ይላል።

እንደ ግሉ ደግሞ ኃይሌ የአርክቴክቸራል ቡድን መሪ በመሆን እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳትፎ ማድረጉን ይናገራል።
“እድሜዬ 31 ነው፤ ዛሬ ደረስኩባቸው ብዬ የማስባቸው ነገሮች፣ ፍላጎቴን እና ጥረቴን አንድ ላይ አጣምሬ ሳያቸው ትንሽ የዘገየሁ ይመስለኛል” በማለት በራስ መተማመን በዚህ ፕሮጀክት ላይ መሳተፉን ይናገራል።

“ትልቁ ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው” የሚለው ይህ ወጣት፣ ከልጅነቱ ጀምሮ ለአርክቴክቸር ትምህርት፣ ፍቅር እና ልዩ የሆነ ፍላጎት ማሳደሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ለመብቃት ረድቶታል።

አርክቴክት ኃይሌ በትምህርት እና በሥራው ላይ ከመበርታቱ ባሻገር በዚህ ዘርፍ በተቻለው መጠን ሌሎች ቦታዎች ያሉ ተሞክሮዎችን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል።

“ይህንን ፕሮጀክት ከማግኘቴ በፊት ኬንያ እና ታንዛኒያ ሄጄ ነበር። የእኛ አገር ፓርኮች እንዴት መልማት አለባቸው የሚለውን ተሞክሮ ለመውሰድ ማሳይ ማራ እና ሰረንጌቲ ፓርኮችን ጎብኝቻለሁ።”

ከዚህ በተጨማሪም እንደሀገር ተይዞ እየተሠራ ያለውን በአማራ ክልል የሚገኘውን የጎርጎራ የቱሪዝም ልማት መዳረሻ ዲዛይንንም እንደሠራ ጠቅሷል።
አርክቴክት ኃይሌ የዚህን ፕሮጀክት ዲዛይንንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት በኮይሸ ተገኝቶ ማቅረቡንም ተናግሯል።

ቀጣይነት ያለው ዲዛይን አርክቴክት ኃይሌ ስለ ወደፊት ህልሙ እና አሁን እየሠራው ስላለ ሥራ ሲጠየቅ ቀጣይነት ስላላቸው ፕሮጀክቶች በተደጋጋሚ ይናገራል።

“አባቶቻችን ማንኛውንም ልማት ሲሰሩ ከተፈጥሮ ጋር እንዲስማማ አድርገው ነው። ተፈጥሮን የሚጎዳ ማንኛውንም ነገር አያበረታቱም” የሚለው ኃይሌ፣ ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ ዓለማችን ፈተና እየገጠማት እንደሆነ ያስታውሳል።
አክሎም “ቀጣይነት ባላቸው ነገሮች እሳቤ ከዚህ በፊት የተበላሸው ወደኋላ እንዲመለስ፣ እንዲሁም ዛሬ እየተገነባ ያለው ደግሞ ተሻሽሎ አንዲገነባ ይታሰባል።”

ነገር ግን እሱ እንሚታዘበው ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ አይነት ግንባታዎች የተበላሸውን ለማስተካከል፣ የወደፊተንም ለመጠበቅ መደረግ ያለበትን ማዕከል ያደረጉ አይደሉም።
“ፕሮጀክቶች ያለጥናት ይታቀዳሉ። ይገነባሉ። መጀመሪያ እና መጨረሻቸው አይታወቅም። ወደፊት ለምትሄደው ዓለምም እየሠራን አይደለም። አባቶቻችን ያወረሱንንም ያህል እየሠራን አይደለም። እንደ አገር መካከል ላይ [ተንጠልጥሎ] የቀረ ነገር አለን።”

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ እንደሚለው በኦሮሞ አባቶች ባሕል መሠረት “. . . አምስቱ ኦዳዎች በማለት ለእኛ እንዳወረሱን፣ እኛም ደግሞ ለመጪው ትውልድ መቆየት የሚችሉ ቀጣይነት ያላቸው ግንባታዎችን ማቆየት አለብን የሚል ፍላጎትም ተስፋም አለኝ::

ተፈፀመ

Via BBC Amharic

@etconp
👍9🤣1
In designing a structure with a shear wall, the most important point is choosing the location of the wall. To reduce the drift of the structure by reducing the distance between the center of mass and the center of stiffness.

@etconp
🙏6👍4❤1
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተ መንግሥት ግንባታ በአዲስ አበባ ሊጀመር ነው::

በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኝ ከስድስት ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ፤ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቤተ መንግሥት ሊገነባ ነው።

በግንባታው ማስጀመሪያ መርሃግብር በዛሬው ዕለት የተከናወነ ሲሆን፤ በመድረኩም የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያና የፌዴራል አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሲንቄ እናቶች ተገኝተውበታል።

የቤተ መንግሥቱ አጠቃላይ የግንባታ ሥራ በኹለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ግንባታው ኹለት ምዕራፎች እንዳሉትም የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

የታቀደውን ቤተ መንግሥት ለመገንባት ከቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (CCECC) ጋር የውል ስምምነት የፈጸመ ሲሆን፤ ኩባንያውን በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቋል።

ለቤተ መንግሥቱ ግንባታ የተመደበው ዋጋን አስመልክቶ እስከአሁን የተገለጸ ነገር የለም።

@etconp
👍9💔8🤮3
👉የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለ 62 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው።

🚧የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለ 62 ወለል የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት በዛሬው ዕለት መፈራረሙን ገልጿል።

🚧በ197 ሺህ 800 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፈውና 445 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት የተመደበለት ይህ ህንጻ ሲጠናቀቅ 327 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት ይኖረዋልም ተብሏል፡፡

🚧የዲዛይንና የቁጥጥር ሥራውን የሚያከናውነው ዳር አል ሃንዳሳህ ሼር እና ፓርትነር ኩባንያ (Dar Al Handasah Shair and Partners) መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

🌟ማስታወሻ : በመዲናዋ ትልቁ ህንጻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ያስመረቀው ባለ 48 ወለል ህንጻ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ባለ 65 ወለል ህንጻ፤ እንዲሁም የአቢሲኒያ ባንክ በበኩሉ 60 ወለል ህንጻ እንደሚገነቡ መግለጻቸው ይታወሳል።

@etconp
👍10❤1
#TheBig5ConstructEthiopia

Join us as we explore the role of project management in the built environment. Dr. Abraham Assefa Tsehayae, an esteemed Assistant Professor in the School of Civil and Environmental Engineering, will share his insights on the major challenges to successful program implementation, the impact of a Project Manager's personality on project delivery, and the importance of adapting project tools and systems to meet client needs. Don't miss out on this informative discussion!

19 May 2023 | 10:30 - 11:00

Register now: https://bit.ly/3oI8P6L
🙏5❤1
ለመጀመሪያ ጊዜ 26 የአለም ሀገራት የሚሳተፉበት የኮንስትራክሽን አውደርእይ ሊካሄድ ነው

ይሄ የተባለው በዛሬው እለት የከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ጫልቱ ሳኒ የኮንስትራክሽን አውደርእይ በተመለክተ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው

በመገለጫቸው የኮንስትራክሽን ዘርፉ 19 በመቶ ያህል በኢኮኖሚ  እድገት ላይ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቅሰው ሆኖም የተለያዩ የግብአት ችግሮች በተለይ የሲሚንቶ እጥረት  ለዘርፉ ማነቆ መሆኑን መግለፃቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ይህንን እና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል የተባለለት ቢግ 5 ኮንስትራክሽን ሲምፖዚየም እና የንግድ ትርኢትን መዘጋጀቱን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ይህም የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ DG ኢቨንትስ እና ከሀገር አቀፉ አጋር ኢትኤል ኢቨንት እንዲሁም የሲምፖሲየሙ ስትራቴጂክ አጋር ከሆነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ከግንቦት 10 እስከ 12 ቀን 2015 በሚሊኒዬም አዳራሽ  በጋራ እንደሚያካሂዱት አንስተዋል።

ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ  የሚካሄደው ሲምፖዚየም 26 የአለም ሃገራት ብሎም  116 አለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን 6000 ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የግንባታው ዘርፍ ማነቆ የሆነውን ከአቅም ውስንነት ጋር የሚያያዙ ችግሮችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው ክፍተት የሚፈታበት ይሆናል ሲሉ አክለዋል።

ይህ ኮንስትራክሽን ዘርፉ ማነቆ የሆነበትን የግብአት  እጥረት በተለይ የሲሚኒቶ እጥረት ዙሪያ አለም የደረሰበትን  የአመራረት ሂደት በዘርፉ ከተሰማሩት ልምድ እንዲወስዱ እድል ይሰጣል።

በመርሃ ግብሩ አምራች ተመራማሪዎች ፣ገዢና አቅራቢዎች ፣ከቱሪዝም ብሎም ከተማን ከማነቃቃት አኳያ እንዲሁም የኢትዮጲያን የገጽታ ግንባታ የምናሳይበት ነው ተብለዋል።

@etconp
👍6