Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ማስታወቂያ

በቢሮው የስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆናችሁና ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ ማህበራት በሙሉ:-

አጠቃላይ የስራ ዕድል መረጃውን በአግባቡ ለማደራጀት ይቻል ዘንድ ከታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በ3 ቀናት ውስጥ ለቢሮው እንድታቀርቡ ጥሪ ተላልፏል።

ሰኔ 01/2015

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

@etconp
👍4❤1🙏1
👉የ ምርምር ወረቀት መፈለግያ

🌟በተለያየ የትምህርት ደረጃ ላሉ እና የምርምር ጽሁፍ ክለሳ ለሚያደርጉ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ የምርምር ወረቀት የመፈለግያ መተግበርያ ድረገጽ ተያይዟል፡፡

https://www.scinapse.io

@etconp
❤2👍2
🇪🇹 ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት ማምረቻ ጅምላ እና ችርቻሮ መሸጫ

🛠 በበቂ ሁኔታ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች እደ ምርጫቹ ታገኛላቹ ከበቂ ሀሳብ ጋር

1🔩ፕሌት በሚፈልጉት ሳይዝ ቆርጠን ቀዳዳ አበጅተን እንሰጦታለን

2🧲ጄቦልት በሚፈልጉት የጥርስ መጠን እናም የቁመት መጠን ጥርስ አውጥተን አጥፈን እሰጦታለን

3🪚እንዲሁም ላሜራ 1ሚሊም እስከ 12 ሚሊም ለማስቆረጥ ካሰቡ እኛው ቆርጠን እናስረክባለን

4 ⚙ማንኛውም ላሜራ እንዲሁም ሌላ ብረት ቀዳዳ ሚበሳ ካሎት እበሳለን

5🌈ያጡት እቃ እኛ በሚገርም ሁኔታ ሞደፊክ እናረጋለን


🧰እደው ምን አለፋውት ላሜራ መቁረጫ ቶርኖ ምን ለሁሉም ይጠይቁን ከብቁ ባለሞያ ጋር ሁሉም አለ

ሌላው ብቻ ሚፈልጉት ይዘዙን በታማኝነት በተባለው ቀን ያገኛሉ

📦📦📦መልካም ስራ ለራስ ነው 💌
በዚህ ይደውሉ 0913061530
0923764834 ፀግሽ ፕሌት
👍1
👉በኮንስትራክሽን ውል አሰሪው የተቋራጩን ክፍያ አዘግይቶ መክፈል ጉዳይ /Delay payment/
------------- ---------------
▶️የኮንስትራክሽ ውል መሰረታዊ ባህሪው ሲታይ በዋናነት አሰሪና ተቋራጭን በተዋዋይነት የሚይዝ ሲሆን ጉልህ የሆነው ግዴታቸው ሲታይ ደግሞ ተቋራጩ በውሉና ዲዛይኑ/ስፔስፊኬሽኑ መሰረት ግንባታውን የማከናወን ሀላፊነት የሚኖርበት ሲሆን ክፍያ የመክፈል ጉዳይ ደግሞ ለአሰሪው ዋናውና ትልቁ ግዴታው ነው፡፡የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610፣3019እና 3020 እንዲሁም 3244 ተገናዝቦ ሲታይ ይሄን ሁኔታ ያስገነዝባል፡፡
*የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ "ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስለሚፈጽሙት ስራዎችና ስለዋጋው ካልተስማሙ በቀር የተቋራጭነት ውል አለ አይባልም" በሚል የተደነገገው በኮንስትራክሽን ውል ለተቋራጩ የሚከፈለው ክፍያ ጉዳይ የውሉ መሰረታዊ ነጥብ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ ስለክፍያ አይነቶች የህጉን ጉዳይ ወደፊት በሌላ ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡
*አሰሪው ለተቋራጩ ክፍያ የመክፈሉን ሁኔታ ያለበቂ ምክንያት ማዘግየት አይችልም፡፡
*አማካሪ መሀንዲሱ በተለይ ከተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ በቀረበለት ጊዜ የማረጋገጥና የማጽደቁን ስራ በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማጠናቀቅ ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(d)
*አሰሪው መስሪያ ቤት ደግሞ በአማካሪ መሀንዲሱ የጸደቀ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(e)
*አማካሪ መሀንዲሱ በተቋራጩ የቀረበውን የክፍያ ጥያቄ በሰባት ቀናት ውስጥ የማረጋገጥና የማጽደቅ ስራ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*በዚህ ረገድ የመመሪያው አንቀጽ አንቀጽ 28.5(f) ግልጽ ምላሽ አስቀምጧል፡፡
*ይሄውም ተቋራጩ በዚህ ምክንያት ከአሰሪው ላይ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ የጠየቀ እንደሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ይህን ተጨማሪ ክፍያ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል፡፡
*ሆኖም ግን አማካሪ መሀንዲሱ ለሚሰጠው አገልግሎት ከሚከፈለው ክፍያ በላይ የሆነ ክፍያ ለመክፈል ሀላፊነት አይኖርበትም፡፡
*በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636 የአማካሪ መሀንዲሱን የእውቀት ስራ ውል ግዴታ ይደነግጋል፡፡ይሄውም አማካሪው "የኪነ ጥበብን ደንቦች በማፍረስ ጥፋት ጥፋት ካላደረገ በቀር በአሰሪው በኩል ስራ ተቋራጩን ሀላፊነት አይነካውም" በሚል ተቀምጧል፡፡(2636(2)) እንደዚሁም አማካሪው ሳይሰራ ከመቅረቱ የተነሳ ወይም በአሰሪው ላይ ጉዳትን የሚያመጣ ስራ ያደረገ እንደሆነ አጥፊ ነው ለመባል እንደሚችል የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636(3) ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ አማካሪው ክፍያ የማረጋገጥ እና የማጽደቅ ስራውን በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባለማከናወኑ አሰሪው ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል በተቋራጩ የተጠየቀ እንደሆነ አማካሪው አጥፊ ነው ሊባል ያስችለዋል ማለት ነው፡፡
*አሰሪው በአማካሪው የጸደቀው የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14 ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*አሰሪው ያለበቂ ምክንያት ክፍያ ያዘገየ እንደሆነ ለተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ ለመክፈል ሀላፊነት እንደሚኖርበት የፌዴራል የግዥ መመሪያ/Federal public procurement directive/ አንቀጽ 28.5(g) ይደነግጋል፡፡
*ተጨማሪ ክፍያ ሲባልስ ምንን ያጠቃልላል? የሚለው ሲታይ በዋናነት ወለድ የመክፈል ሀላፊነትን የሚመለከት ይሆናል፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3268 ተቋራጩ መክፈልን በማዘግየት የሚታሰበውን ወለድ እንዲያገኝ መብት ይሰጠዋል፡፡የወለዱ መጠንም በውል ያልተወሰነ የሆነ እንደሆነ በአንቀጽ 1751 መሰረት ህጋዊ ወለድ በአመት 9(ዘጠኝ) በመቶ ሆኖ የሚሰላ ይሆናል፡፡
*ሌላው እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነጥብ ተዋዋዮች በውላቸው ላይ ክፍያን ማዘግየት የሚኖረውን ውጤት አስመልክቶ የቅጣት ስምምነት/penality clause/ ያካተቱ ከሆነ የፍትሀብሄር ህጉ አንቀጽ 1889 እና ተከታዮቹ ድንጋጌ እውቅና ስለሚሰጠው እና በአንቀጽ 1731 መሰረት ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ስለሚቆጠር ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
*አንዳንድ ክልሎችም በዚህ ረገድ በግዥ መመሪያቸው ላይ ዝርዝር ውጤቱን ያስቀምጣሉ፡፡
*አሰሪው ክፍያ በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ከወለድ ባለፈ ሌላም ጉዳት የደረሰበት ተቋራጭስ ከጉዳቱ ጋር እኩል የሆነ ኪሳራ ሊከፈለው አይገባም ወይ? የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይችላል፡፡ምክንያቱም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2091 እና 1790(2) ለደረሰው ጉዳት ሀላፊ መሆኑ በህግ የታወቀ ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሳ ሀላፊነቱን ያመጣው ጉዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን አለበት በሚል በግልጽ ይደነግጋል፡፡
▶️በአጠቃላይ አሰሪው በማናቸውም ምክንያት የተቋራጩን ክፍያ በሚያዘገይበት ጊዜ ተቋራጩን ለውድቀት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ምክንያቱም በሀገራችን አብዛኛው ተቋራጭ ድርጅት የፋይናንሽያል ማኔጅመንት ስርአት የለውም፡፡ተቋራጮቻችን የገንዘብ አቅማቸውም ደካማ ነው፡፡አብዛኛው ተቋራጭ ለአንዱ ፕሮጀክት የሚወስደውን የቅድሚያ ክፍያ ሌላ ፕሮጀክት ላይ ይጠቀምበታል፡፡በዚህ ምክንያት አንድ ተቋራጭ ሲከስር ብዙ ሰራተኛ እንደሚበተን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ስለዚህ በአሰሪዎች በኩል ተቋራጮች የሰሩበትን ክፍያ በወቅቱ እና በተሰራው ስራ ልክ አንዲከፈላቸው ለማድረግ እና በህጉ የተቀመጠው የክፍያ የጊዜ ገደብ እንዲከበር ጠንከር ያለ አቋም ወስዶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

#ConstructioLaw

https://t.me/COTMp
👍7
👉በኮንስትራክሽን ውል ጉዳይ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate ምን ይላል? ©በ ጉባዔ ኣሰፋ
፡
▶️የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ በአሰሪው በሚመደብ አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና በተቋራጩ ተረጋግጦና ተማምነውበት የሚፈረም ሲሆን ለተቋራጩ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠንም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡
*የክፍያ ምስክር ወረቀት ጋር ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪ አባሪ ተደርጐ ይያያዛል፡፡
*ቴክ ኦፍ ሽት የአሰሪው አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና የተቋራጩ መሀንዲስ በግንባታ ቦታ በአካል የሳይት ቪዚት በማካሄድ የተሰራውን ስራ መጠን እና አይነት ከለቀሙ በኋላ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ከተመለከተው የእያንዳንዱ ስራ አይተም ዩኒት ሬት/ነጠላ ዋጋ አንጻር በዝርዝር በተናጠል በዋጋ የሚያስቀምጡበት የተሰራውን ስራ መጠን እና የገንዘብ መጠን ገላጭ ዝርዝር ሰነድ ነው፡፡
*ግራንድ ሳመሪ ደግሞ በዋናነት የግንባታወችን ዝርዝር/ብሎክ በማስቀመጥ የውሉን ዋጋ፣አስቀድሞ የተከናወነ ስራ መጠን፣አሁን የተከናወነ ስራ መጠን እና አጠቃላይ በተቋራጩ የተሰራውን የግንባታ ስራ መጠን ይጠቅሳል፡፡
*የክፍያ ሰርተፍኬት በአብዛኛው በአንድ ገጽ ተጠቃሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በይዘት ደረጃ ግን ብዙ መረጃወችን አምቆ የያዘ ሰነድ ነው፡፡
*የክፍያ ሰርተፍኬት በተለይ ክፍያው የመጀመሪያ ዙር፣ሁለተኛ ዙር እያለ በሚታወቅበት መንገድ የሚዘጋጅ ሲሆን የመጨረሻ ዙር ክፍያ የሚባልም አለው፡፡
*የመጀመሪያ ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በአብዛኛው ከቅድሚያ ክፍያ በኋላ ሲሆን ክፍያውም ለተሰራ ስራ የሚፈጸም ነው፡፡
*የመጨረሻ ዙር ክፍያ ደግሞ ግንባታው ተጠናቆ ጊዜአዊ ርክክብ/provisional acceptance/ ከተከናወነ በኋላ በህግ ከተቀመጡ ተቀናሾች በስተቀር ቀሪውን የስራ ክፍያ ጠቅልሎ አካቶ ወዲያውኑ በግንባታ ውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡
*የክፍያ ሰርተፍኬት የፕሮጀክቱን ስም፣ቦታ፣አሰሪውን፣ተቋራጩን፣አማካሪውን ይጠቅሳል፡፡ ዋናውን የውል ገንዘብ መጠን፣ተቀጽላ ስራዎችን፣ቫሬሽንን እና የተከናወነውን የስራ መጠን ያመለክታል፡፡ውሉ የተደረገበትን ጊዜ እና ኮመንስመንት ዴት ይጠቁማል፡፡
*በተጨማሪም የቅድሚያ ክፍያ መጠን እና አድቫንስ ሪፔይ ያመለክታል በዚህም አስቀድሞ የነበሩ የክፍያ ቁጥሮችን ጭምር ይጠቁማል፡፡
*እንደዚሁም የሪቴንሽን መጠን እና የቅጣት መረጃንም የሚሰጥ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ሁሉ መረጃ በያዘ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ አሰሪው/ተቆጣጣሪው/አማካሪው እና ተቋራጩ የሚፈራረሙበት ይሆናል፡፡
*ስለዚህ የክፍያ ሰርተፍኬት ጸደቀ ማለት በሰርተፍኬቱ ላይ የተመለከተው ስራ ስለመሰራቱ እና ዋጋውንም ጭምር አሰሪውና ተቋራጩ አምነውበታል ማለት ነው፡፡
*እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የአሰሪው ዋና ግዴታ ለተቋራጩ በወቅቱ ክፍያ መፈጸም ነው፡፡
*የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ ክሎስ 28.5 ላይ ስለኮንስትራክሽን ስራዎች ክፍያ እንዴት መፈጸም እንደሚገባው ይዘረዝራል፡፡
*በዚህ ረገድ በተለይ ክሎስ 28.5(a) ላይ የተቀመጠው እንደሚያስገነዝበው በኮንስትራክሽን ስራዎች ጉዳይ ክፍያ የሚፈጸመው በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠና የጸደቀ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ እንዲቀርብ በማድረግ መሆኑን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
*እንግዲህ የክፍያ ጥያቄ የሚያቀርብ በመጀመሪያ ተቋራጩ እንደመሆኑ አማካሪው/ተቆጣጣሪው መሀንዲስ የሳይት ቪዚት በማካሄድ የክፍያ ጥያቄውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ የክፍያ ሰርተፍኬቱን፣ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪውን ጨምሮ የሚያጸድቅና አረጋግጦ የሚፈርምበት እና በማህተምም የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
*አማካሪው/ቶጣጣሪው በተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበለት በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማረጋገጡን ስራ ማጠናቀቅ እንደሚገባው በዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(d) ላይ በአስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡
*እንደዚሁም አሰሪው ደግሞ በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያውን መፈጸም እንደሚገባው በአስገዳጅ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡
*እንግዲህ ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በእጁ ይዞ እያለ እና አሰሪውም ደርሶት እያለ ሳይከፍለው ያዘገየበት እንደሆነ በግንባታ ውሉ እና የውል አካል በሚያደርጉት ጀኔራል ኮንዲሽን በተመለከተው አግባብ ተቋራጩ ኪሳራ ከአሰሪው ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል ዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(g) በግልጽ እና በአስገዳጅ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
*ፒፒኤ 2011 ክሎስ 59 እንደዚሁ የኮንስትራክሽን ጉዳይ የስራ ክፍያ የሚፈጸመው በክፍያ ሰርተፍኬት አማካይነት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡
*በአጠቃላይ ከላይ የተመለከተው የክፍያ ሰርተፍኬት ባህሪ እና የፒፒኤ ድንጋጌ የሚያስገነዝበው ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በአማካሪው/ተቆጣጣሪው እስከጸደቀለት ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ክፍያ ሊፈጸምለት እንደሚገባ ነው፡፡ አመሰግናለሁ

#ConstructionLaw

@etconp
👍20❤2👏1👌1
@etconp payment certificate - Copy.xlsx
204.9 KB
Payment certificate

አብዛኞቻችሁ በጠየቃችሁን መሰረት payment certificate እንካችሁ ብለናል።

Payment certificate’ቱን ምታገኙት payment በሚል sheet ነው።

ለጓደኞቻችው በማጋራት አጋርነታችሁን አሳዩን 🙏።

Payment certificate

@etconp
👍17❤2
🌟Picture Of The Day

👉Safety Helmet color Code Guide

⚡️በዚህ ኣጋጣሚ ፊልም ሰሪዎቻችን ፊልም ላይ ብትጠነቀቁ።

@etconp
👍8👏2
Abutment design

1. Lold calculation
2. Load from superstructure
3. Earth pressure
4. Braking
5. Temperature
6. Friction
7. Live load from surcharge
8. Seismic load

I’ll post it one by one

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Twitter:- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432
👍13
🇪🇹 ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት ማምረቻ ጅምላ እና ችርቻሮ መሸጫ

🛠 በበቂ ሁኔታ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች እደ ምርጫቹ ታገኛላቹ ከበቂ ሀሳብ ጋር

1🔩ፕሌት በሚፈልጉት ሳይዝ ቆርጠን ቀዳዳ አበጅተን እንሰጦታለን

2🧲ጄቦልት በሚፈልጉት የጥርስ መጠን እናም የቁመት መጠን ጥርስ አውጥተን አጥፈን እሰጦታለን

3🪚እንዲሁም ላሜራ 1ሚሊም እስከ 12 ሚሊም ለማስቆረጥ ካሰቡ እኛው ቆርጠን እናስረክባለን

4 ⚙ማንኛውም ላሜራ እንዲሁም ሌላ ብረት ቀዳዳ ሚበሳ ካሎት እበሳለን

5🌈ያጡት እቃ እኛ በሚገርም ሁኔታ ሞደፊክ እናረጋለን


🧰እደው ምን አለፋውት ላሜራ መቁረጫ ቶርኖ ምን ለሁሉም ይጠይቁን ከብቁ ባለሞያ ጋር ሁሉም አለ

ሌላው ብቻ ሚፈልጉት ይዘዙን በታማኝነት በተባለው ቀን ያገኛሉ

📦📦📦መልካም ስራ ለራስ ነው 💌
በዚህ ይደውሉ 0913061530
0923764834 ፀግሽ ፕሌት
❤1
🫴በጠየቃቹን መሰረት

🚧መያዥያ ገንዘብ (Retention money) እና
ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT) አብራሩልን ላላቹ

💫ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT)

➡በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል

▶️ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።
▶️በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።
▶️ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።
▶️ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።

💫መያዥያ ገንዘብ (Retention money)

➡️ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ/defect liability period / ሀላፊነት
ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ
ገንዘብ ነው።

▶ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።

▶ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።

▶በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው።

▶️ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በአርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

@etconp
👍11
👉ROLES OF A QUANTITY SURVEYOR
~~~
▶Quantity surveyor calculates the cost by calculating the quantity of material required for any and every activity involved in construction.
He/She is also involved:in planning and contracting related job which is
mainly involved in the construction cost calculation.
➡The role of a quantity surveyor are listed below:👇
1. Estimating.
2. Cost planning.
3. Preparing, negotiating and analyzing costs for
tenders and contracts.
4. Procurement advice.
5. Preparing Bill of Quantities (BOQ).
6. Monitoring Budget.
7. Preparation of Payment Invoice and certification.
8. Assessment of variations
9. Dispute resolution.
10. Preparing feasibility studies.
11. Cost control.
12. Value engineering.
13. Advice on cost limits and budgets
14. Whole life cycle costing.
15. Valuation for insurance purposes.
16. Project management.
17. Advice on contractual disputes.
18. Preparation of final account.
19. Site visits, assessments, and projections for
future work.
20. Analysing completed work and arranging
payment to contractors.
21. Allocating upcoming work to contractors.
Besides these, quantity surveyors may choose to
specialize in a specific area of the construction
industry and focus on areas like costing advice,
property taxation, application to funding sources, maintenance of existing buildings, etc.
.
👇👇👇👇👇
Join for more Discussion via the link below;
t.me/COTMp
👆👆👆👆
👍10❤1