Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉CELLULAR CONCRETE

🌟It is a light weight concrete produced by introducing large voids in the concrete or mortar. Its density varies from 3 kN/m3 to 8 kN/m3 whereas plain concrete density is 24 kN/m3.

▶️It is also known as aerated foamed or gas concrete.

📌Properties of cellular concrete: It has the following properties

1. It has low weight.
2. It has good fire resistance.
3. It has good thermal insulation property.
4. Thermal expansion is negligible.
5. Freezing and thawing problems are absent.
6. Sound absorption is good.
7. It has less tendency to spall.

🌟Uses of Cellular Concrete

1. It is used for the construction of partition walls.
2. It is used for partitions for heat insulation purposes.
3. It is used for the construction of hollow filled floors

https://www.facebook.com/etconp/

https://youtube.com/@Etconp432
👍8❤1
👉ተቋራጮችን ከመንግስት ግዢ አቅራቢዎች ዝርዝር ማገድ

✨[Suspension from Suppliers List]

▶️በመንግስት ግዢ ወቅት በሚፈፀሙ የስነ-ስርዓት ግድፈቶች ምክንያት ጥቅሜ ተነክቶብኛል የሚል አቅራቢ ወይም ተጫራች  ለግዢ ፈፃሚው የመንግስት አካል ወይም ለአቤቱታ አጣሪው ቦርድ አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዳለው የአዋጁ አንቀፅ 70(1) እንዲሁም የመመሪያው አንቀፅ 43 ይገልፃሉ፡፡ ነገር ግን አቤቱታ የማይቀርብባቸው ጉዳዮችም እንዳሉ አንቀፅ 70(2) እና 44 በዝርዝር ያስቀምጣሉ፡፡   

ነገር ግን የዚህ ፅሁፍ አላማ በግዢ ፈፃሚ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለኤጀንሲው በሚያቀርቡት አቤቱታ ላይ ተመሰረቶ ኤጀንሲው ተቋራጮችን ከተጫራቾች ወይም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ሊያግድ ስለሚችልበት ሁኔታዎች ለመወያየት ስለሆነ ተጫራቾች ስለሚያቀርቡት አቤቱታ እና ስለአፈታት ስርዓቱ በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለው፡፡

የግዢ ፈፃሚ የመንግስት መስሪያ ቤት በተጫራቾች ወይም በአቅራቢዎች ሕገ-ወጥ ተግባር ወይም ሕጋዊ ጥቅሜን የሚነካ ተግባር ተፈፅሞብኛል ብሎ ሲያምን በአዋጁ አነቀፅ 12 መሰረት ለተቋቋመው የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቤቱታውን ማቅረብ እንደሚችል አንቀፅ 76(1) እንዲሁም የመመሪያው አንቀፅ 48(1) ይደነግጋሉ::

አንቀፅ 15(7) በዕጩ ተወዳዳሪዎችና በአውራቢዎች ላይ የመ/ቤቶች የሚያቀርቡትን አቤቱታዎች መርምሮ ውሳኔ መስጠት የኤጀንሲው አንዱ ተግባር መሆኑን ይገልፃል፡፡

በዚህም መሰረት ኢጀንሲው አቤቱታ ሲቀርብለት አቤቱታ ለቀረበበት ወይም ለተከሳሽ ዕጩ ተወዳዳሪ ወይም አቅራቢ አቤቱታ መቅረቡንና የአቤቱታዉን ይዘት የሚገልፅ ማስጠንቀቂያ በመላክ ያሳውቃል፡፡ ይህም የተከሳሽ በአስተዳደር ዉሳኔ አሰጣጥ ላይ የመሰማት መብቱን እነዲጠበቅ ይረዳል፡፡ ይህ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ‹ተከሳሽም› በ5 የስራቀናት ውስጥ የፅሁፍ መልሱንና የሰነድ ማስረጃዎችን ለኤጀንሲው ማስገባት እንዳለበት ከመመሪያው አንቀፅ 48.3 ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡

ኤጀንሲውም አቤቱታውን በተቀበለ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ መርምሮ ውሳኔ በመስጠት ለተከራካሪዎቹ በፅሁፍ ማሳወቅ እንዳለበት የአዋጁ አንቀፅ 76(4) ከመመሪያው አንቀፅ 48.4 ጋር ይገልፃሉ፡፡ ለአቤቱታውም ሊሰጡ የሚችሉት ዉሳኔዎች አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ፤ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት፤ ወይም ዕጩ ተወዳዳሪውን ወይም አቅራቢውን በመንግስት ግዢ ላይ እንዳይሳተፍ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ከተወዳዳሪነት ወይም ከአቅራቢነት ማገድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ተቋራጮች በቀረበባቸው አቤቱተታ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ በማንኛውም የመንግስት ጨረታ ላይ እንዳይወዳደሩ ሊታገዱ ይችላሉ ማለት ነው፡፡

ተጫራቾች ከማንኛውም የጨረታ ውድድር ሲታገዱ በተለምዶ በጥቁር መዝገብ ወይም “Black List” ውስጥ ገቡ ይባላል፡፡ ዋናው ነገር ደግሞ ምን ምን ዓይነት ጥፋቶች ናቸው ተጫራቾችን በጥቁር መዝገብ እንዲገቡ የሚያደርጓቸው? የሚለው ነው፡፡

እነዚህም ነጥቦች በመመሪያው አንቀፅ 48.5.1 እና 48.5.2 ላይ በዝርዝር ተቀምተጠዋል፡፡ በአንቀፅ 48.5.1 እንደተዘረዘሩትም የጨረታ ግምገማውን ውጤት ለማበላሸት ወይም ለመለወጥ አስበው  ለግዢ ሰራተኞች ሙስና መስጠት፤ የውሸት ወይም ተቀባይነት የሌላቸውን መረጃዎች በማቅረብ ማጭበርበር፤ የኤጀንሲው እግድ እያለባቸው በግዢ ላይ መሳተፍ/መወዳደር እንዲሁም ተጫራቾች ወይም አቀራቢዎች በዉሉ ከተገለፀው ጥራት የወረደ ዕቃ፤ ስራ፤ ወይም አገልግሎት በማጭበርበር ወይም ከገዢ ሰራተኞች/ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ያቀረቡ እንደሆነ ኤጀነሲው ከሁለት ዓመት ጀምሮ እስካልተወሰነ ጊዜ ድረስ በማንኛውም የመንግስት ግዢ ላይ እንዳይሳተፉ ሊያግዳቸው ይችላል::

ከእነዚህም ምክንያቶች በተጨማሪ ተጫራቾች ፍትሃዊ የዋጋ ወድድር ጥቅምን ለማሳጣት ከተወሰኑ ተጫራቾች ጋር በመመሳጠር የዋጋ ተመን ካወጡ/ከጣሉ፤ የግዢ ባለሙያዎች ወይም የግዢ ፈፃሚ መንግስት መ/ቤት ሰራተኞች ላይ የአካል ጉዳት ለማድረስ የዛተ/ያስፈራራ ወይም ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ወይም በኤጀነሲው  የተጣለበት እግድ ከተነሳበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመታት ዉስጥ ሌላ ማንኛውም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ሊያሳግድ የሚችል ጥፋት የፈፀመ እንደሆነ በተመሳሳይ ከሁለት ዓመት ጀምሮ እስካልተወሰነ ጊዜ ድረስ ሊታገድ ይችላል ማለት ነው፡፡

በአጭሩ ሙስና፣ ማጭበርበር፣ መመሳጠር፣ ወይም ዕግድን ጥሶ በጨረታ ላይ መወዳደር ተጫራቾችን/አቅራቢዎችን ከአቅራቢነት ዝርዝር ሊያሳግዳቸው ይችላል ማለት ነው፡፡

በሌላ በኩለ ደግሞ አንቀፅ 48.5.2 ላይ እንደተገለፁት ከመንግስት ጋር የግዢ ውል የተዋዋለው አቅራቢ በዉሉ የተገለፁትን ዕቃዎች፡ ስራዎች ወይም አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ባለማቅረቡ ምክንያት የግዢ ፈፃሚው መ/ቤት ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ጉዳት [Direct or Consequential Loss] ያጋጠመው እንደሆነ ወይም የመ/ቤቱን ስራ ያጓተተ ወይም ያፋለሰ እንደሆነ አቅራቢው ከአቀራቢዎች መዝገብ ላይ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ሊታገድ ይችላል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የጨረታ ውድድር እንዳሸነፈ በመ/ቤቱ የተገለፀለት አቅራቢ ውሉን ለመዋዋል ባለመቻሉ ወይም እምቢተኛ በመሆኑ ምክንያት መ/ቤቱ በዉሉ የተገለፀውን ዕቃ፣ ስራ ወይም አገልግሎት ከሌላ አቅራቢዎች ለመግዛት ሲል ጉዳት ያጋጠመዉ ወይም ስራዉን ያጓተተ ወይም ያፋለሰ እንደሆነ እነዲሁም የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው አቀራቢ በሶስት ዓመት ውስጥ ሌላ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሊያስጥ የሚችል ጥፋት ፈፅሞ ከተገኘ ኤጀንሲው አቅራቢውን ከአቀራቢዎች መዝገብ ላይ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ሊያግደው ይችላል፡፡

ከአቀራቢዎች ዝርዝር መዝገብ ላይ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ መታገድ ውጤቱም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ተጫራቹ ወይም አቅራቢው በማንኛውም የመንግስት ግዢ ላይ መወዳደር አይችልም፡፡

እነዚህ በኤጀንሲው የሚጣሉት የዕግድም ይሁን የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ቅጣቶች ግዢ ፈፃሚውን የመንግስት መ/ቤት በአቅራቢው ወይም በተጫራቹ ምክንያት የደረሰበትን የገንዘብ ኪሳራ ከመጠየቅ አያግደውም፡፡

@etconp
👍10
A bridge pier is a type of structure that extend to the ground below or into the water. It is used to support bridge superstructure and transfer the loads to the foundation. The bridge piers can be constructed to be substantially attractive and strong in order to withstand loads.

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
❤7👍6
👍13🏆5😢2👌1
👉የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በአጋርነት ተመርጧል

🌟ኢንስቲትዩቱ የተጠየቀውን ዓለም አቀፍ መሥፈርት በማሟላቱ የኘሮጀክት ማኔጅመንት አቅም ግንባታ ተቋም ሆነው በአጋርነት ተመርጧል።

🌟የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አሜሪካ ከሚገኘው የኘሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከሰኔ 23ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የኘሮጀክት ማኔጅመንት ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ማዕከል ሆኖ በአጋርነት መመረጡን አሳውቋል።

🌟የተመረጠውም የተጠየቀውን መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ ነው በመሆኑም ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸው የኘሮጀክት ማኔጅመንት ባለሙያዎች ስልጠና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው ባለሙያዎች እንዲፈሩ ያደርጋል።

🌟ከዚህ በፊትም ተቋሙ የአውቶዴስክ ስልጠና ማዕከል (Authorized Training Center) ሆኖ መመረጡ ይታወሳል።

Via የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት

@etconp
👍15👏2👌2
👉የኢትዮጵያ  አየር መንገድ  የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ለሚገነባው መታሰቢያ ሀውልትና ፖርክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና አሸናፊው ኮንትራክተር Elmi Olindo Contractors PLC ጋር ስምምነት ፈጽመዋል።

🌟አለበል ደስታ አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች ድርጅት የተሰራው ዲዛይኑ በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ግምቢቹ ወረዳ በ4 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን በስምምነቱ ወቅት የተጎጂ ቤተሰቦች ተወካዮችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

@etconp
👍4❤1
የግንባታ ስራ የሚያከናውኑ ማሽነሪ ኦፕሬተሮችና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ለመንገድ ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተገለጸ።

መንገዶች ላይ ጉዳት በሚያስከትል ሁኔታ ጭነት በሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎችና የኮንስትራክሽን ግንባታ ማሽነሪ ኦፕሬተሮች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ።

በከተማችን በተለያዩ ስፍራዎች ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑ ይታወቃል ከግንባታዎቹ ጋር ተያይዞ ሲሚንቶ የሚያቦኩ ተሽከርካሪዎች የተቦካ ሲሚንቶ መንገድ ላይ በማፍሰስ እንዲሁም ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ከጭነት አቅም በላይ አፈርና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን መንገዶች ላይ በማፍሰስ እና ጭቃ በጎማቸው ይዘው ወደ ጎዳና የሚወጡ አሽከርካሪዎችም ሆኑ ባለንብረቶች ለመንገዶች ደህንነት ማድረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ መንገዶች ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው ባሸገር ለትራፊክ መጨናነቅ መንስኤ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

ፖሊስ አጥፊዎቹ ከጥፋታቸው እንዲታረሙ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ መቆየቱን አስተውሷል።

በጥፋቱ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከለካል የአዲስ አበባ ፖሊስ እርምጃ እንደሚወስድ አሰጠንቅቋል።

የግንባታ ስራ የሚያከናውኑ ማሽነሪ ኦፕሬተሮችና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ጭነት በሚጭኑበት ወቅት የመንገድ ደህንነት ህጉ በሚያዘው መሰረት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበቸው እንዲሁም መንገዶቹን በጭቃ የሚያበላሹ፤ የተሽከርካሪዎችንም የጎማ ፅዳት የመጠበቅ ግዴታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ያለው ፖሊስ ይህንን መልእክት በመተላለፍ ጥፋት ላይ በሚገኙ አሽከርካሪዎችም ሆኑ ባለንብረቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።  

@etconp
👍8
👉የህንጻ ግንባታ ላይ የሚታዩ ችግሮች /Defects in Building Construction/

🚧የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ለሚታዩ ችግሮች ዋና ዋና የመከሰቻ ምክንያቶች:
/Major Causes of defects in construction/

🌟1ኛ.ጥራታቸውን ያልጠበቁ የግንባታ ግብዓቶችን መጠቀም

⏺ከአመራረት፣ ከአያያዝ ችግር ወይም የአገልግሎት ጊዜያቸው በማለፉ ምክንያት ጥራታቸው የጎደለ የግንባታ ግብዓቶችን መጠቀም በግንባታ ስራው ላይ የተለያዩ ከቀላል እስከ አደገኛ ችግር የሚያመጣ ይሆናል።

🌟2ኛ.ቸልተኝነት ወይም ደካማ የስራ ቁጥጥር

⏺ሁሉም ነገር በተሟላበት ሁኔታ የተቆጣጣሪ ባለሞያዎች ለስራ ቁጥጥሩ ካላቸው ደካማ አቀራረብ የተነሳ በታችኛው የሰው ሃይል የተሰሩ ስህተቶችን በጊዜው ማረም ሳይቻል ቀርቶ በሂደት ችግሮቹ ስር ሰደው እስከ የከፋ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ይሆናል።

🌟3ኛ. ከባለሞያዎች የብቃት/ልምድ ማነስ ምክንያት ችግሮች ይከሰታሉ።

⏺በተወሰነ መጠን ስልጠና ካላቸው ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ ስልጠና ያላቸው ባለሞያዎች ስራን የመረዳት አቅማቸው ደካማ ከመሆኑ ወይም ከሚሰሩት ስራ ጋር ተዛማጅ የሆነ በቂ የሆነ የስራ ልምድ የሌላቸው ሲሆንና ስራን በነሲብ/በግምት በመስራት ምክንያት ስህተቶች ሊከሰቱ ይችላሉ።

🌟4ኛ. ከዲዛይን ስህተት

⏺ስህተት ያለበትን ዲዛይን አስቀድሞ በሚገባ ሳይታይና ጥያቄ ሳይቀርብበትና ማስተካከያ ሳይደረጋበት /Without Clarification and design Modification/ወደ ስራ ትግበራ መግባት ስራው ከጠናቀቀ በኋላ የእርምት ርምጃ መውሰድ ባብዛኛው አዳጋች ስለሚሆን በሂደት አደገኛ ችግር ያመጣል።

🌟5ኛ. ለስራ ምቹ ባልሆነ የአየር ጠባይ መስራት

⏺አንድአንድ የግንባታ ስራዎችን ለማከናወን የተመቸ የአየር ጸባይን መጠበቅ ግድ የሚሆንበት አስተዳጅ ምክንያቶች አሉ።

▶️ለምሳሌ ዝናብ እየዘነበ የኮንክሪት ሙሊት ስራን ማከናወን በተለይ እንደ የወለል ስላብ ፣ደረጃና ራምፕ ያሉ horizontal structural members /በቀጣይ ክፍሎች የምንመለከታቸው/የተለያዩ የኮንክሪት ችግሮችን ያመጣሉ።

🌟6ኛ. ማጭበርበር

⏺ላልተገባ ጥቅም ሲባል በ ባለሞያዎች፣በተቋራጮች፣ወይም በተቆጣጣሪ ባለሞያዎች አሻጥር ጥራታቸው የጎደለ የግንባታ ግብዓቶችን በመጠቀም፣ ወይም ከተቀመጠ የስራ ጥራት ደረጃ ልክ/Standard/ በታች  ስራው እንዲሰራ ማድረግ በቀጣይ ችግሮች እንዲከሰት የሚያደርግ ይሆናል።

▶️ለምሳሌ: ከደረጃ በታች የሆነ የሙሊት አፈርን ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ስራ ላይ እንዲውል መፍቀድ ቀጣይ የህንጻው አጠቃላይ ደህንነት ላይ የሚያመጣውን ችግር መገመት አይከብድም።

🌟7ኛ. ከተፈቀደው በላይ የሚመጣ ጫና

⏺ህንጻው ሊቋቋም ከሚችለው ጫና መጠን/Design loads/ በላይ ህንጻው ላይ የሚመጡ ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ሰራሽ ጫናዎች የህንጻው ደህንነት ላይ እስከ ከፋ ችግሮችን ሊያመጡ ይችላሉ።

🙏አብሮነት አይለየን🙏

💫ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ❤️

https://youtube.com/@Etconp432

https://www.facebook.com/etconp/
👍9❤4🏆3💯1
👉የግንባታ ሥራዎች አጠቃላይ ፍረጃ/Major Category of construction projects/

🌟የትራንስፖርትና የመገናኛ ግንባታ ሥራዎች /Transport and Communication /:-

▶️የአውራ ጎዳና ግንባታዎች፣ የገጠር መንገዶች፣ የባቡር ሀዲድ፣የአየር ማረፊያ፣ የስልክ ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ ሥራና የመሳሰሉት የሚገኙበት ነው፡፡

🌟የውሃና ኢነርጂ ሥራዎች ግንባታ /Water and Energy works /:-

▶️የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣ የመስኖ ግንባታ፣ የመጠጥ ውሃ ማጣሪያና የመስመር ዝርጋታዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃና ማጣሪያ፣ የጎርፍ መውረጃ ፣ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ የነዳጅ ማውጣት ሥራ የማሳሰሉትን ያካትታል፡፡

🌟የህንጻ ግንባታ ሥራዎች /Buildings/:-

▶️የጤና ተቋማት ግንባታዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ፋብሪካዎች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሥራ ህንጻዎች እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

👉Facebook:-
https://www.facebook.com/etconp/

👉YouTube:-
https://youtube.com/@Etconp432
👍5🏆4👌1
📩በ ውስጥ መስመር ከ አንድ ወዳጃችን የተጠየቅን ጥያቄ

🌧ከ ክረምት ጋር በተያያዘ የውሃ ስርገትና ርጥበትን እንዴት ልከላከል /Damp Prevention/

💧የውሃ ስርገትና ርጥበትን የመከላከልያ ሌሎች የተለመዱ መንገዶች/Typical Membrane Damp-proofing Agents/

⭐️1ኛ. የኮንክሪት ግግር መደብ/Application thin Concrete layer(s) /

▶️አነስተኛ ርጥበት የሚፈጥር የውሃ ስርገት መኖሩ ሲገመት ማለትም የውሃ ፍሰቱ/እዠት በሚኖርበትና ጊዜ በ1:2:4 የውህድ ምጣኔ የተዘጋጀና ከ4-5cm ውፍረት ያለው የኮንክሪት ግግር መደብ/Mass concrete/ልንጠቀም እንችላለን።

▶️የኮንክሪት ግግር መደቡን የስርገት መከላከል አቅም የበለጠ ከፍ ለማድረግ 2 ዙር/2 coat/ ሙቅ/የቀለጠ ቢቱሚን/hot bitumen/Primer መቀባት ውጤቱን የተሻለ ያደርገዋል።

🌟2ኛ. ሞርታር/Mortar/

▶️ለሌሎች የውሃ ስርገት ስራዎች ደጋፊ/ማረፊያ እንዲሆንና የበለጠ ውጤት ለማግኘት ከስር የሚነጠፍ በሲሚንቶና አሸዋ ቅይጥ የሚዘጋጅ ነው።

▶️እንደ ተደራቢው ክርታሱ/membrane/ዓይነት ከ2-5cm ውፍረት ባለው በፈረካስ/trowel finish/ ወይም በሊሾ /screed finish/ማጠናቀቅ ይቻላል።

⏺ከተደራቢው ክርታስ ጋር በቀላሉ ለማያያዝ 2 ዙር/1 coat/ ሙቅ/የቀለጠ ቢቱሚን/hot bitumen/Primer መቀባት ውጤቱን የተሻለ ያደርገዋል።

🌟3ኛ. ልዩ ጡቦች/Bricks/

▶️ውሃ የመምጠጥ አቅማቸው ከፍተኛ ሆነው በልዩ ሁኔታ የተመረቱ ጡቦችን መጠቀም አንዱ የውሃ ስርገትን መከላከያ መንገድ ሲሆን፣የውሃ ፍሰቱ/እዠት በሚኖርበትና ቦታ ብቻ ነው መጠቀም የሚፈቀደው።

🌟4ኛ.የጥብቅ ድንጋይ ንጣፍ/Stones/
ለምሳሌ: ግራናይት

🌟5ኛ. በወፍራሙ የተጋገረ የቢቱመን ንጣፍ/Hot laid bitumen/

▶️እና ሌሎች እንደ Mastic Asphalt
፣Metal sheets የመሳሰሉት አማራጭ የውሃ ስርገትና ርጥበት የመቀነሻና መከላከያ መንገዶችን በዲዛይን ባለሞያዎች ምክርና እገዛ በመታገዝ ብቻ መጠቀም እንችላለን።

https://youtube.com/@Etconp432

https://www.facebook.com/etconp/
👍18🙏3🏆1
በጊዜ እጥረት ምክንያት ዛሬ መሙላት የጀመርኩትን ግሬድ ቢም ማጠናቀቅ ስላልቻልኩ ከአክሲስ F ወደ G, L/3ኛ ላይ Construction joint በመተው ማቆም ተገድጄአለው። ነገ በዓል ነው። ከነገወዲያ ደግሞ እሁድ ነው።በትርፍ ሰዓት ሰራተኞችን ማሰራት አልፈለኩም። የጀመርኩትን ኮንክሪት ካቆምኩበት ሰኞ ለመቀጠል የበለጠ ውጤታማው መንገድ የቱ ነው?
Anonymous Poll
3%
በቀጥታ ያቆምኩበት ጆይንት ላይ አዲሱን ኮንክሪቱን መሙላት መቀጠል።
33%
ጆይንቱን በደንብ በብሩሽ ማፅዳት፣ በሲሚንቶና ውሃ ወህድ/cement paste/ በሚገባ መቀባትና አዲሱን ኮንክሪት መሙላት መቀጠል።
74%
ጆይንቱን በደንብ በብሩሽ ማፅዳት፣ ማጣበቂያ ኬሚካል/Bonding Chemical/በመጠቀም ጆይንቱን በሚገባ መቀባትና አዲሱን ኮንክሪት መሙላት መቀጠል።
❤18👏4👌3👍2
በአንድ ተዋዋይ ወገን ከውል ማፈንገጥ ምክንያት ውል ያልተፈጸመለት ወገን ራሱን ለመጠበቅ ከሚከተሉት አማራጭ መብቶች የቱን ሊጠቀም ይችላል?

(ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጥር 1771)
Anonymous Quiz
43%
ለደረሰበት ጉዳት ተመጣጣኝ የጉዳት መቀጮ መጠየቅ
3%
ውል አስገድዶ ማስፈጸም
10%
ውል እንዲፈርስለት መጠየቅ
44%
ሁሉንም አማራጮች መጠቀም ይችላል
👍15
የኮንክሪት ስትራክቸሮች ላይ የተለያዩ ከቀላል/negligible defects/ እስከ የከፋ ደረጃ ያለቸው ችግሮች/sever defects/ሲያጋጥሙ እናያለን።

በእርሶ አስተያየት የትኛው የኮንክሪት ስራ ላይ ለሚከሰረቱ የተለያዩ ችግሮች ምክንያት አይሆንም ብለው ያስባሉ።
Anonymous Quiz
11%
የግንባታ ግብዓቶች የጥራት ችግር/use defective building materials/
5%
ቸልተኝነት/Negligence/poor supervision/
6%
ደካማ የሞያ ብቃት/Poor workmanship/
9%
የዲዛይን ስህተት/Design problem/
12%
የከፋ የአየር ጠባይ ለውጥ/Harsh weather condition/
11%
ማጭበርበር/Fraud/
38%
የባጀት እጥረት/Financial shortage/
9%
ከዲዛይን በላይ የክብደት ጫና/Over loading/
👍9👏1
👉እንሆ ከ ኮንስትራክሽን ሕግ ጋር የተያያዙ ፋይሎች ተጠቀሙበት

🚧ሌሎች ምትፈልጉት ፋይል ካለ አናግሩን እንልክላቹዋለን

🌟ለምትወዱዋቸው በማጋራት ኣዳርሱልን🙏

👇👇👇👇👇👇
🙏7👍1