Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.21K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉1. ኪነህንጻ እና ቀለም

🏷1.1 ጥቁርና ነጭ ቀለማት በውስጥ እይታ

▶️ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው በአዲሳባ ከተማ በደንበል ህንጻ ውስጥ የሚገኝ የቶሞካ የቡና መጠጫ ካፌ ነው።

🚧ጥቁርንና ነጭ ቀለምን በመጠቀምና ተቃርኖን በማምጣት ውስጣዊ ስሜቱን ህይወት አላብሰውታል።

🚧በተለይ በእንደዚህ ሰዎች ብዙ ግዜአቸውን በማያጠፉባቸው ቦታዎች ላይ ተቃርኖን መጠቀም ሲመከር ፣ ለመኖርያ ቦታ ውስጣዊ ክፍሎች ግን ተደጋጋፊ ቀለማት ይመረጣሉ።

#Architecture

#ColorAndArchitecture

@etconp
👉ኪነህንጻ እና ቀለም

🏷1.2. ሙሉ ወይም አብላጫ ጥቁር ቀለም።

🚧ከታች በምስሉ ላይ የሚታየው በሊያን ዲዛይን የተሰራ የመኖርያ ቤት ሲሆን የነጭ ተቃርኖ የሌለው ጥቁር ውስጣዊ እይታ ነው።

🚧የቤት ቁሶቹ፣ የተለያዩ አጃቢዎች እንዲሁም ወለሉ ጥቁሮች ናቸው።

🚧በ ቀን በጸሀይ ብርሀን ረጋ የሚያደርግ ቦታ ሲሆን በማታ ደግሞ በወርቃማ ነጥብ መብራት እጅግ የሚያምር አስደማሚ ድባብ ይፈጥራል።

🚧በአገራችን ጥቁርን እጅግም የሚደፍር ዲዛይነርም ሆነ ደንበኛ እንደሌለ እናውቃለን።

#Architecture

#ColorAndArchitecture

@etconp