Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
536 files
3.78K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
🚰 Pump Discharge Calculation 📐⚙️

💫Think you know how much water your pump delivers? 🤔

🪧Pump discharge calculation helps determine the actual flow rate, ensuring the system operates efficiently and meets design requirements.

💧✅ Formula: Q = V / t

📌 Q = Discharge (L/s or m³/s)

📌 V = Volume collected (L or m³)
📌 t = Time taken (s)

✔️ Verifies pump performance
✔️ Detects efficiency loss
✔️ Helps in maintenance planning
✔️ Ensures proper system operation

📊 Accurate calculations lead to reliable performance! ⚡

#PumpDischarge #PumpCalculation #MechanicalEngineering #MEPEngineering #Hydraulics #FireFightingSystem #EngineeringCalculations #IndustrialMaintenance

@etconp
👍3❤2👏1
✅ Barbed wire apolo =2300
✅ wire mesh 2,5m =870
✅ wire mesh 3,5m 2×1 =2820

Call me
✅ 0949434363
✅ 0912955969
❤3
🛣️ Every Great Road Starts with a Strong Foundation! 🏗️

A road is much more than the asphalt you see on the surface. Its strength, durability, and performance depend on a well-designed pavement structure—from the compacted subgrade to the sub-base, base course, binder course, and wearing course. Proper cross-section design, camber (2.5%), shoulders, and drainage ensure safer roads and a longer service life. 🚜📐

🇪🇹 ጠንካራ መንገድ የሚጀምረው በጠንካራ መሠረት ነው!🏗️

💫የምናየው አስፋልት ብቻ አይደለም፤ የመንገዱ ጥንካሬና ዘላቂነት ከSubgrade, Sub-base, Base Course, Binder Course, እና Wearing Course በትክክል ከተገነቡ ይጀምራል። ትክክለኛ የመንገድ መስቀል ክፍል (Cross Section) እና የውሃ ፍሰት ንድፍ ደህንነትንና የመንገዱን ዕድሜ ያሳድጋሉ🌍🚧

#CivilEngineering #RoadConstruction #HighwayEngineering #PavementDesign #Asphalt #Infrastructure #ETCONP #Construction #Engineering #Ethiopia 🇪🇹

@etconp
❤5👍1
Forwarded from Kelemat Ads
💰 Earn Money From Your Telegram Channel

Do you own a Telegram channel with 700+ subscribers?

Turn your audience into income with Kelemat Ads.

✅ Join 140+ Telegram channels across Ethiopia already earning with our platform.

How it works:
• Add the Kelemat Ads Bot to your channel.
• The bot automatically posts relevant ads for you.
• Get paid based on your channel's subscriber count.
• Receive your payment via Telebirr within 48 hours.

No searching for advertisers. No negotiating deals. Just let the Kelemat Ads Bot handle the ads while you earn.

📩 DM @temaripath to join Kelemat Ads and start earning from every ad campaign.
❤3
👉በ28 ዓመታት ውስጥ በ805 ቢሊዮን ብር ወጪ ከ153 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶች ተገንብቷል

🚧ኢትዮጵያ ከዝቅተኛ የመንገድ መሠረተ-ልማት ተነስታ አሁን ላይ ሰፊ፣ ዘመናዊና የኢኮኖሚ ኮሪደሮችን የሚያገናኝ የመንገድ መረብ ባለቤት ለመሆን በቅታለች፤

ይህ በየምዕራፉ የተተገበረው የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራም የሀገሪቱን የጉዞ አቅጣጫ በተቀናጀ መልኩ የመራ ሲሆን፣ የመንገድ ግንባታ ከቁጥር ባለፈ ዘላቂነትና ተደራሽነትን ያረጋገጠ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያስመዘግብ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፤



በ1989 ዓ.ም የተጀመረው ይኸው የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራም በኢትዮጵያ የመንገድ ልማት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የመንገድ አውታሩን ማስፋት፣ ጥራትን ማሻሻል፣ የጥገና ሥርዓትን ማጠናከርና ተቋማዊ አቅምን መገንባት ላይ ያተኮረ ነበር፤

በዚሁ መሠረት ከ1989 እስከ 1994 ዓ.ም በተተገበረው መጀመሪያው የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም፣ ዋና ትኩረቱ አዲስ አበባን ከክልል ዋና ከተሞች፣ ከንግድ ማዕከላትና ከወደብ መስመሮች ጋር የሚያገናኙ አውራ ጎዳናዎችን ማሻሻል ላይ በመሆኑ 8 ሺህ 709 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶና ታድሶ ለአገልግሎት በቅቷል፤

ይህንን ተከትሎ ከ1995 እስከ 1999 ዓ.ም በተከናወነው ሁለተኛው ምዕራፍ ፕሮግራም የመንገድ አውታርን ማስፋት፣ የገጠር ተደራሽነትን ማሻሻልና አዳዲስ መንገዶችን መገንባት ተቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቶት 11 ሺህ 589 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቷል።



ጉዞው በዚሁ ሳይገታ ከ2000 እስከ 2002 ዓ.ም በነበረው ሦስተኛው ምዕራፍ፣ ነባር የጠጠር መንገዶችን ወደ አስፋልት ማሳደግ እንዲሁም አዳዲስ አገናኝና ዋና መዳረሻ መንገዶችን መዘርጋት ላይ በማተኮር አሥራ 2 ሺህ 395  ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶ ለአገልግሎት ውሏል።

የገጠር አካባቢዎችን ከመንገድ አውታር ጋር ማገናኘትና ተደራሽነትን ማስፋት ልዩ ትኩረት ያገኘው ደግሞ ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም በተተገበረው አራተኛው ፕሮግራም ሲሆን፣ በዚህ ወቅት 85 ሺህ 86, ስምንት መቶ ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የተለያዩ መንገዶች ተገንብተዋል።

ከ2008 እስከ 2012 ዓ.ም የነበረው አምስተኛው የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራም ደግሞ የመንገድ ልማትን ከጥራት፣ ከዘላቂነትና ከቴክኖሎጂ ጋር ያስተሳሰረ ምዕራፍ የነበረ ሲሆን፣ በዚሁ ፕሮግራም የመጀመሪያ ሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ በአጠቃላይ 27 ሺህ 210 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ መንገዶች ግንባታ ተከናውኗል።


በመጨረሻም ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም በተተገበረው ስድስተኛው የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራም 28 ሺህ 949 ኪሎ ሜትር የፌዴራል፣ የክልልና የወረዳ መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል።

ይህ መጠነ ሰፊ ክንውን የሀገሪቱን አጠቃላይ የመንገድ አውታር በ1989 ዓ.ም ከነበረበት 26 ሺህ 550  ኪሎ ሜትር ብቻ ተነሥቶ አሁን ላይ ወደ 182 ሺህ 232 ኪሎ ሜትር እንዲያድግ አድርጎታል።

ባለፉት 28 ዓመታት በተተገበሩት በእነዚህ ስድስት ተከታታይ ፕሮግራሞች በአጠቃላይ 805.6 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ግዙፍ መዋለ-ንዋይ ፈሰስ ተደርጓል።

በአጠቃላይ እነዚህ ፕሮግራሞች የመንገድ አውታርን በማስፋት ብቻ ሳይወሰኑ፣ የጥራት ደረጃን ከፍ ማድረግ፣ የገጠርና የከተማ ትስስርን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ኮሪደሮችን ማሳደግና የሀገር አቀፍ ልማትን ማፋጠን የቻሉ የለውጥ ምዕራፎች በመሆን ወደ ተሻለ የዕድገት ጎዳና የምትጓዝ ኢትዮጵያን መገንባት ችለዋል።


Via ERA

@etconp
❤4👍2🥰1
​የዳንጎቴ የ17 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው!

​ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ ላሙ ካውንቲ ለመገንባት ያቀዱት ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት በአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾችና በነዋሪዎች ተቃውሞ እየገጠመው ይገኛል።

​ስለ ፕሮጀክቱ ምን እናውቃለን?

​አቅም: በቀን 700,000 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅም ይኖረዋል ተብሎ ታቅዷል።

​ኢንቨስትመንት: ከ15 እስከ 17 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ የሚባል ፕሮጀክት ነው።

​ለምን ተቃውሞ ተነሳ?

የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች፣ በተለይም ግሪንፒስ አፍሪካ፣ ፕሮጀክቱ የሚከተሉትን ጉዳቶች ያስከትላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል፦

⚠️ የአካባቢ ብክለት: በላሙ የሚገኙ የማንግሩቭ ደኖችን፣ የኮራል ሪፎችንና የባህር ውስጥ የዱር እንስሳትን ሊጎዳ ይችላል።

⚠️ የካርቦን ልቀት: ከፍተኛ የሆነ የበካይ ጋዝ ልቀትን ያስከትላል።

​የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋት
ቀደም ሲል በአካባቢው የተሰሩ ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች፦

​ለነዋሪዎች የፈጠሩት የሥራ ዕድል አነስተኛ መሆኑ፣

​የመሬት ይገባኛል ውዝግብ መፍጠራቸው፣
​እንዲሁም የአካባቢ ብክለት ማስከተላቸው በአሁኑ ፕሮጀክት ላይ ትልቅ ጥርጣሬ ፈጥሯል።

​በመሆኑም፣ መንግስት ገለልተኛ የሆነ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ (Environmental Impact Assessment) ሳይከናወን ለፕሮጀክቱ ፈቃድ እንዳይሰጥ ተሟጋቾች ጥሪያቸውን እያቀረቡ ነው።
​
@etconp
❤10🎉2
JOB VACANCY

Position: OFFICE ENG./QUANTITY SURVEY 🏗️

Company: Sheger Architect, Consulting Architects and Engineers 🏢

Education: BSC/MSC በሲቪል ምህንድስና፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት (BSC/MSC in Civil Engineering, Construction Management) 🎓

Experience: 6/5 ዓመት የሥራ ልምድ (6/5 years experience) 💼

Additional Requirements: Revit, AutoCAD,...etc; CGPA ≥3.2 📐

Salary: በድርጅቱ ስኬል መሠረት (As per Company Scale) 💰

Required qty: 02 👥

Work location: Addis Ababa 📍

Deadline: July 21, 2026 📅

How to apply:
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎችን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። 📝
የመመዝገቢያ ቀን: ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት የሥራ ቀን) ተከታታይ የሥራ ቀናት 🗓️

Email: sheger.architect@gmail.com 📧
Telegram/WhatsApp: 0911249826 📱
ስልክ ቁጥር (Phone): +251 11 562 2543; +251912938990 📞

@etconp
❤12
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን

🚧ስላብ ዲዛይን ስናደርግ Depth ካልኩሌት የሚያደርግላቹ Excel Template ከፈለጋቹ 👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a5cafa5b0526_etconp
👍5❤1
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

የወጣበት ቀን ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም

@etconp
❤1
#ADVERTISEMENT

📲 አንድ ተች ብቻ፤ የእርስዎን ስራ እና ብቃት ያስተዋውቁ!

የቢዝነስ ካርዶች ማተም እና ማደስ አልፎበታል። በNFC ዲጂታል ቢዝነስ ካርድ የሚፈልጉትን ስልክ በማስነካት የእርስዎን ስልክ ቁጥር፣ WhatsApp፣ Telegram፣ Email፣ Portfolio እና ፕሮጀክቶች ወዲያውኑ ለደንበኞችዎ ያጋሩ።
ለኢንጂነሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ ሪል እስቴት ሙያተኞች እና የቢዝነስ ባለቤቶች ተስማሚ !
📞 0931639484
ለማዘዝ እና ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ።
❤2
👉ሙሉ G+2 ህንፃ የምትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ያውርዱ🙏 👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a5dc437caa02_etconp
❤4👏1
👉በአሜሪካ ምድር ዕድሜ ጠገቡ ድልድይ የት ይገኛል?

🚧ነገሩን በጥያቄ እንጀምረው—ለመሆኑ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እስካሁን ድረስ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ አንጋፋ ድልድይ የት እንደሚገኝ ያውቃሉ?

«በአሜሪካ አንጋፋው ድልድይ» የሚለው ስያሜ እንደየአቆጣጠሩና እንደየአሠራሩ የተለያየ ትርጉም ሊኖረው ቢችልም፣ በታሪክ መዝገብ ቀዳሚነቱን ይዞ የሚገኘው «ፍራንክፎርድ አቨንዩ ድልድይ» (Frankford Avenue Bridge)ነው፤
ይህ ድልድይ በፊላደልፊያ ሰሜናዊ ምሥራቅ ግዛት በፔኒፓክ ወንዝ ላይ የተገነባ ሲሆን፣ ዕድሜው ከ 320 ዓመታት በላይ ያስቆጠረና እስከ ዛሬ ድረስ መኪና የሚያስተናግድ ብቸኛ አንጋፋ የድንጋይ ቅስት ድልድይ ነው።

የዚህ ድልድይ ታሪክ የሚጀምረው እ.ኤ.አ በ1697 ከአሜሪካ ነፃነት መታወጅ ከረጅም ዓመታት በፊት ነው፣ የፔንሲልቬንያ መሥራችና እንግሊዛዊው ዊሊያም ፔን በወቅቱ በነበረው የቅኝ ግዛት ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ፣ ከይዞታው ተነስቶ ወደ ታዳጊዋ የፊላደልፊያ ከተማ በቀላሉ መሻገር የሚያስችለው መንገድ እንዲሠራ ጠየቀ፤

በዚህም መሠረት የቅኝ ግዛቱ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. መጋቢት 10 ቀን 1683 ባሳለፈው ውሳኔ፣ በ«ኪንግስ ሃይዌይ» መስመር ላይ በሚገኙ ወንዞች ሁሉ ላይ ድልድዮች እንዲገነቡ አዘዘ፤

ደንቡ ጥብቅ ነበር፤ እያንዳንዱ ድልድይ በ18 ወራት ውስጥ ተሠርቶ መጠናቀቅ ነበረበት፣ ወርዱም 10 ጫማ (ከ3 ሜትር በላይ) ሆኖ ለጋሪና ለፈረስ ትራፊክ አመቺ እንዲሆን በሁለቱም በኩል መከታ (ሀዲድ) እንዲኖረው ተወሰነ፣ የሚገርመው ደግሞ ግንባታው የተከናወነው በደመወዝ በሚሠሩ መሐንዲሶች ሳይሆን በአካባቢው ነዋሪዎች ጉልበት ነበር፤

በወቅቱ በሥራው ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆነ ማንኛውም ነዋሪ 20 ሽልንግ ይቀጣ ነበር። በዚሁ መልክ የሆልምስበርግ ነዋሪዎች ተረባርበው የገነቡት ይህ የፔኒፓክ መሻገሪያ፣ ፊላደልፊያን እንደ ትሬንተን፣ ኒው ዮርክ እና ቦስተን ካሉ ሰሜናዊ ከተሞች ጋር አገናኛት፤

ይህ ድልድይ ተራ መሻገሪያ ብቻ አልነበረም፤ የአሜሪካን ታሪክ በለወጡ ታላላቅ ሰዎች ኮቴ የተረገጠ ታሪካዊ ስፍራ እንጂ። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በፈረስም ሆነ በጋሪ ከኒው ኢንግላንድ ግዛቶች ወደ ፊላደልፊያ የሚጓዙ መሪዎች ሁሉ በዚህ ድልድይ ላይ አልፈዋል፣ ለአብነት ያህል የአሜሪካው ሁለተኛው ፕሬዚዳንት ጆን አዳምስ እና ሌሎች የኮንቲኔንታል ኮንግረስ ልዑካን ይጠቀሳሉ፤

በ1756 በፊላደልፊያና በኒውዮርክ መካከል የመጀመሪያው የጋሪ ትራንስፖርት አገልግሎት ሲጀመር ጉዞው 3 ቀናት ይፈጅ ነበር፣ በ1783 «ፍላይንግ ማሽን» የተባለው ፈጣን ጋሪ ሲፈጠር ግን ጉዞው ወደ አንድ ቀን ወረደ፤


የአሜሪካ አብዮት ሲፈነዳም የዚህ ድልድይ ስም አብሮ ይነሳል፣ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 24 ቀን 1775 ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ከደቡባዊ ቦስተን ተነስቶ ለአምስት ቀናት ያለማቋረጥ የጋለበ አንድ መልዕክተኛ፣ የሌክሲንግተን ውጊያ መጀመሩንና የአሜሪካ አብዮት መቀስቀሱን የሚያበስረውን አስቸኳይ ዜና ይዞ የገሰገሰው በዚህ ድልድይ ላይ ነበር፣ ከአራት ዓመታት በኋላ በ1789 ደግሞ ጆርጅ ዋሽንግተን የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኖ ለመሰየም ወደ ኒውዮርክ የተጓዘው በዚሁ ታሪካዊ መስመር ነበር፤

ጊዜው እየገፋ ሲሄድ ድልድዩም አብሮ ዘመናዊ መልክ እየያዘ መጣ፦


በ1803፦ በድልድዩ ደቡባዊ ጫፍ ላይ የቀረጥ መክፈያ (Toll booth) የተተከለ ሲሆን መንገዱም ለመጀመሪያ ጊዜ ተነጠፈ። ይህ የቀረጥ ጣቢያ እስከ 1892 ድረስ ለአገልግሎት ውሏል፤


በ1893፦ ድልድዩ መጀመሪያ ላይ ለሁለት ጋሪዎች መተላለፊያ ጠባብ ስለነበር፣ የትራም (Trolley) ትራፊክን ለማስተናገድ ሲባል ሰፋ ተደርጎ ተሠራ፤


በ1950፦ ለመኪናዎች (Automobiles) ምቹ እንዲሆን በድጋሚ ተለጠጠ፤


በ2018፦v ድልድዩ ለ5 ወራት ያህል ተዘግቶ ትልቅ እድሳት ተደረገለት። የእግረኛ መንገዱ ታደሰ፣ የድንጋይ ግንባታው ጥገና ተደረገለትና በዚያው ዓመት መስከረም ወር ላይ እንደገና ተከፈተ፤


ይህ ድልድይ በ1970 ብሔራዊ የታሪክ ምሕንድስና መለያ ምልክት (National Historic Civil Engineering Landmark) የተባለ ሲሆን፣ በ1988 ደግሞ በብሔራዊ የታሪክ ሥፍራዎች መዝገብ ላይ ሰፍሯል፤

«የአሜሪካው አንጋፋ ድልድይ» የሚለው ስም እንደየባሕርያቸው ለሌሎችም ይከፋፈላል፤ የፍራንክፎርድ ድልድይ በአጠቃላይ መኪና ለሚያስተላልፍ መንገድ ቀዳሚ ቢሆንም፣ በየምድባቸው የሚከተሉትም ይጠቀሳሉ፦

1. ቾት ድልድይ (Choate Bridge)፦


በማሳቹሴትስ የሚገኝ ሲሆን የተገነባው በ1764 ነው። በአገሪቱ ውስጥ በሰነድ የተደገፈ አንጋፋው ባለ ሁለት ቅስት የድንጋይ ድልድይ ነው፤

2. ሃይድ ሆል የተሸፈነ ድልድይ (Hyde Hall Covered Bridge)፦


በኒው ዮርክ የሚገኝ ሲሆን የተገነባው በ1825 ነው። ከአገሪቱ አንጋፋ የእንጨት ጣራ የተሸፈነላቸው (Covered bridges) ድልድዮች ተርታ ይመደባል፤

3. ደንላፕስ ክሪክ ድልድይ (Dunlap's Creek Bridge)፦


በፔንሲልቬንያ የሚገኝ ሲሆን በ1839 የተገነባ ነው። በአሜሪካ የመጀመሪያው ከቀለጠ ብረት (Cast iron) የተሠራ ቅስት ድልድይ ነው፤

የብዙ ጥንታዊ ድልድዮች ዕድል በአሁኑ ወቅት ለእግረኛ መሄጃነት ወይም ለፓርክ መዝናኛነት መውለድ ነው፣ ለምሳሌ የሃይድ ሆል የእንጨት ድልድይ ዛሬ የሚገኘው በፓርክ ውስጥ እንጂ በዋናው አውራ ጎዳና ላይ አይደለም፤

ነገር ግን የፍራንክፎርድ አቨንዩ ድልድይ ታሪክ የተለየ ነው፣ ከተገነባ ከ320 ዓመታት በላይ ቢቆጠርም፣ ዛሬም ድረስ የ«US Route 13» ብሔራዊ መሥመር አካል ሆኖ መኪናዎችን እያስተናገደ ይገኛል፣ በአሁኑ ወቅት የ20 ቶን ክብደት ገደብ የተጣለበት ቢሆንም፣ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ አንጋፋው ድልድይ ዛሬም ድረስ በመኪናዎ ሊሻገሩት የሚችሉ ሕያው የታሪክ ምስክር ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

@etconp
❤10👍2
👉ሙሉ የ Quantity Surveying Full Course በቅናሽ ዋጋ በ ኦንላይን መማር ለምትፈልጉ 👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a5e233a9c5e0_etconp
❤2
👉​በኖህ ሪል ስቴት እና በቤት ገዢዎች መካከል የተነሳው የ50 ሚሊዮን ብር የክስ ሂደት ወደ ፍርድ ቤት አምርቷል

💫​በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት ዘርፍ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ ውዝግቦች ትኩረት ስበዋል። በካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 (ሴቶች አደባባይ አካባቢ) በሚገኘው "ኖህ ቪክትሪ ሳይት" ባለ 19 ወለል ህንፃ ላይ አፓርታማዎችን የገዙ ስድስት ግለሰቦች፣ አልሚውን "ኖህ ሪል ስቴት" በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰዋል።

🪧​የክሱ ዋና ነጥቦች፦

​የዘገየ ግንባታ፦ ከሳሾቹ እንደገለጹት፣ አፓርታማዎቹ በውል ስምምነታቸው መሠረት በ36 ወራት ውስጥ መጠናቀቅ ሲገባቸው፣ ግንባታው ስድስት ዓመታትን መውሰዱን ጠቅሰዋል።

​ክፍያ፦ ገዢዎቹ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ በሙሉ መፈጸማቸውን በመጥቀስ፣ ቤቶቹ ተጠናቀው ቁልፍ ለመረከብ ሲጠይቁ አልሚው ሊረክብ ፈቃደኛ እንዳልሆነ አስረድተዋል።

​የአልሚው (ኖህ ሪል ስቴት) ክርክር፦
ኩባንያው የግንባታውን መዘግየት እና ክፍያ መፈጸሙን አምኖ ተቀብሏል። ሆኖም ለውዝግቡ ምክንያት የሆነው የቦታ ስፋት መለዋወጥ መሆኑን ይገልጻል።

​በተናጠል ካርታ ዝግጅት ወቅት፣ ከውሉ ስምምነት በላይ ከ10 በመቶ በላይ (እስከ 57.13 ካሬ ሜትር) የቦታ ጭማሪ መታየቱን ጠቅሷል።

​በዚህም መሠረት ከ3 እስከ 4 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ መጠየቁን፣ ይህም በውሉ መሠረት ህጋዊ መብቱ መሆኑን ይከራከራል።

🏷​የቤት ገዢዎች ምላሽ፦

ገዢዎቹ በበኩላቸው በውሉ ላይ የተስማሙበት ዋጋ የመጨረሻ መሆኑንና ተጨማሪ ቦታ እንዳልተሰራላቸው በመጥቀስ፣ ተጨማሪ ክፍያ አንከፍልም በማለት ክርክራቸውን አቅርበዋል።

🧷​የፍርድ ቤቱ ውሳኔ፦

ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፣ ኖህ ሪል ስቴት ተጨማሪ ማስረጃዎችን አያይዞ እንዲያቀርብ በማዘዝ፣ ለጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

💫​የሪል ስቴት እና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የ YOUTUBE ቻናላችን ይከታተሉ 🏗️👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp
❤8👍1
👉JOB VACANCY

💫Office Engineer

📐Atta Trading Plc

📍Addis Ababa

💫Bachelor's Degree in Civil Engineering or with related field of study from a recognized university with relevant work experience

🪧Duties and Responsibilities

- Prepare quantity take-offs and measurement sheets.
- Verify executed work quantities.
- Prepare monthly work accomplishment reports.
- Monitor project progress against approved schedules.
- Track completed quantities and productivity.
- Review and certify subcontractor payment applications.
- Monitor variations and additional works.
- Maintain accurate quantity and payment records.
- Planning, Progress Monitoring & Cost Control
- Monitor project progress against approved schedules.
- Track completed quantities and productivity.

Quanitity Required: 2

Minimum Years Of Experience: #4_years
Maximum Years Of Experience: #5_years

Salary: 30000.00

Deadline: July 30, 2026

How To Apply: Submit your application and CV along with supporting documents via email: attatradingplc@gmail.com with a subject line "Office Engineer"

Note: Applicants must clearly indicate the projects they have worked on, their responsibilities, and major achievements in their CV and only candidates with Office Engineer experience on building construction projects and a minimum GPA of 3.2 will be considered.

@etconp
❤6👍2