Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
The-Active-City-2017-10-10-lowres.pdf
11.6 MB
👉በነጻ የቀረበ መጽሀፍ

🚧The Active City Urban Design Strategy

💫ለእግርጉዞ፣ ብስክሌት እና ለአካልብቃት የተመቹ ከተሞች ንድፍ ላይ የአምስተርዳምን ተሞክሮ ይዞ በስፋት የሚያስተምር መጽሀፍ ነው።

Via ethiopian architecture and urbanism

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
🙏6❤3
👉 የሁለተኛው ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውና ዛሬ የተመረቀዉ ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ ኮሪደር ያለዉ ፕሮጀክቶች - በምስል

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤9
👉በደሴ ከተማ በ357 ሚሊየን ብር የተገነባው ባለሰባት ወለል ስማርት ሲቲ የጋራ መኖሪያ አፖርታማ ሕንፃ ተመረቀ

💫በደሴ ከተማ በመናፈሻ ክፍለ ከተማ በቀድሞው ፔፕሴ ፋብሪካ አካባቢ በ 357 ሚሊየን ብር የተገነባው ባለሰባት ወለል ስማርት ሲቲ የጋራ መኖሪያ አፖርታማ ሕንፃ ተመርቋል።

በ500 መቶ ካሬ ቦታ ላይ ያረፈው ስማርት ሲቲ የጋራ መኖሪያ አፖርታማ ሕንፃ ግንባታው የተጀመረው በ2011 ዓ.ም ነበር።


የስማርት ሲቲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት አቶ ከድር አሊ፦ የደሴ ከተማን በዕድገት ሌሎች ከተሞች የደረሱበት ደረጃ ለማድረስ እና በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለማሳደግ የተሠራ ሕንፃ ነው ብለዋል።

ስማርት ሲቲ የጋራ መኖሪያ አፖርታማው ባለአንድ መኝታ 13 ክፍሎች እና ባለሁለት መኝታ 28 ክፍሎች ያለው ሲሆን፣ ሁለት የድርጅት አገልግሎት የሚሠጡ ክፍሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 43 አባወራዎችን የሚይዝ ነው።


ስማርት ሲቲ የጋራ መኖሪያ አፖርታማ የራሱ የከርሰ ምድር ውሃ፣ የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ፣ አስተማማኝ እና ዘመናዊ አሳንሰር፣ ዋይፋይ፣ ኪችን ካቤኔት የተገጠመለት ሲሆን፣ በተጨማሪም የእርድ ቦታ እና ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶች መሟላታቸውን ገልጸዋል።

የአፖርታማ ግንባታው ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ 400 ለሚደርሱ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተማው እያደገ ሲመጣ የማህበረሰብ ቁጥር እና የመኖሪያ ቤት ፈላጊው ይጨምራል ያሉት የደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለባቸው ሠይድ በአቶ ከድር አሊ የተገነባው ስማርት ሲቲ የጋራ መኖሪያ አፖርታማ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግርን ይቀርፋል ብለዋል።

Via Dessie Communication

@etconp
❤15
👉አንድ ሚሊየን ተመልካቾች የሚይዝ ስታዲየም ይመጣል ወይንስ ሃሳብ ብቻ ሆኖ ይቀራል❓

በአለማችን ብዙ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ግዙፍ ስታዲየም የሚገኘው በሰሜን ኮሪያ ነው።

በሰሜን ኮሪያ ዋና ከተማ ፒዮንግያንግ ውስጥ የሚገኘውና 114 ሺህ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም  ያለው " Rungrado 1st of May Stadium" ከእግር ኳስ እና አትሌቲክስ ስፖርታዊ ውድድሮች በተጨማሪ ትላልቅ የመዝናኛ መርሃ ግብሮችን በማካሄድም ይታወቃል።

ከዚያ ውጪ በአለማችን የሚገኙ ብዙዎቹ ስታዲየሞች ተመልካች የመያዝ አቅማቸው ከ100 ሺህ በታች ነው።


ይሁን እንጂ፣ አሜሪካዊው Paul Pfeiffer ወደፊት በአለማችን አንድ ሚሊዮን መቀመጫ ያለው ስታዲየም መገንባቱ አይቀሬ መሆኑን ይናገራል።

ፖል ይህን ሃሳቡን ለማሳካት አንድ ሚሊዮን ተመልካቾችን የሚይዝ የስታዲየም ንድፍን ሠርቶ ለዕይታ አቅርቧል።


በዘመናዊ የስነጥበብ ሙዚየም ውስጥ ለእይታ የበቃው የፖል ሃሳባዊ ንድፍ አንድ ሚሊዮን ተመልካቾችን ለማስተናገድ የተነደፈ የስታዲየም ሞዴል ነው።

ይህ ምስል አሁን ካለው የአለም ትልቁ ስታዲየም ተመልካቾችን በመያዝ አቅም በአስር እጥፍ የሚበልጥ ነው። ምንም እንኳን ሞዴሉ 10 ጫማ ርዝመት ያለው ቢሆንም፣ የስታዲየሙ ግንባታ እውን ቢሆን ግን የሚኖረው ርዝመት የ14 ፎቅ ቁመት ያህል ነው።

የፖልን ንድፍ የተመለከቱና አንድ ሚሊዮን ተመልካቾች የሚይዝ ስታዲየም ከምናብ ወጥቶ አንድ ቀን ዕውን የሚሆንበት ቀን መቼ ነው በሚል እየሞገቱ ቢሆንም፣ ጥያቄውን በቅርብ አመታት ውስጥ ለመመለስ ያስቸግራል በሚል ሃሳባቸውን የሚያጋሩ ባለሙያዎች ግን ብዙ ናቸው።


@etconp
❤10
👉የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

⭐️የቧንቧ ሰራተኛ

📍አዲስአበባ

🚧በቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4/3 በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ች አግባብ ከሆነ የስራ ልምድ ጋር

📜ዋና ኃላፊነቶች፡

- በጣም ጥሩው እጩ የውሃ አቅርቦት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ እና የንፅህና አጠባበቅ ስርዓቶች፣ ንድፎችን የማንበብ እና የደህንነት ደንቦችን የመከተል ችሎታ ሊኖረው ይገባል።
- የውሃ አቅርቦት መስመሮችን, የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶችን እና የጋዝ መስመሮችን መትከል, መጠገን እና ማቆየት
- የቧንቧ ጉዳዮችን መመርመር እና ፍሳሾችን መዝጋት እና ሌሎች ጉድለቶችን መጠገን
- ንድፎችን, ቴክኒካዊ ንድፎችን እና የግንባታ ኮዶችን ማንበብ እና መተርጎም
- እንደ ማጠቢያዎች, መጸዳጃ ቤቶች, ቧንቧዎች, የውሃ ማሞቂያዎች እና እቃዎች የመሳሰሉ መገልገያዎችን መጠገን
- ለፍሳሽ የቧንቧ መስመሮችን መፈተሽ እና ትክክለኛ ተግባራትን ማረጋገጥ
- ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የኤሌክትሪክ ባለሙያዎችን እና የግንባታ ሰራተኞችን ጨምሮ ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር መስራት
- የደህንነት ደረጃዎችን እና የግንባታ ደንቦችን መከታተል

⏺Quanitity Required: 15

⏺Minimum Years Of Experience: #1_years

⚡️Deadline: August 13, 2025

📩How To Apply: ይህንን የቴሌግራም ሊንክ በመጠቀም ያመልክቱ @Heranye

@etconp
❤8
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

♧ ሁሉን በአንድ ቦታ ለሁሉም ቅርብ

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

♧ ይደውሉልን ያማክሩን

0904040477
0994941708
❤3
👉የጨረታ ማስታወቂያ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍5❤2👏1