Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.59K photos
56 videos
536 files
3.81K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
Income_Tax_Regulation_Amendment_Draft_የገቢ_ግብር_ደንብ_ማሻሻያ_ረቂቅ@Taxation.pdf
9.4 MB
👉የገቢ ግብር ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ

🚧Income Tax Regulation Amendment Draft

🏷የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ቢሮዎችን እና የክልል ፋይናንስ ቢሮዎች ባለሞያዎችን በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ለማስፈጸም የተዘጋጀው ረቂቅ የገቢ ግብር ደንብ ላይ ውይይት ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ገንዘብ ሚኒስቴር አዳራሸ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

📩ሌሎቻችን ደግሞ፡ ረቂቁን ተመልከቱ ሃሳባችሁ ስጡበት።

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤4
ጨረታ

አዲስ ዘመን የካቲት 19 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1👏1
ጨረታ

አዲስ ዘመን የካቲት 19 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1🥰1
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1👏1
ጨረታ

አዲስ ዘመን የካቲት 25 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2
ጨረታ

አዲስ ዘመን የካቲት 25 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2👍1
አሊኮ ዳንጎቴ በቀጣይ ወደ ብረት፣ ኃይል ማመንጨት እና ወደብ ግንባታ ላይ እንደሚሰማሩ ገለጹ

የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አሊኮ ዳንጎቴ ወደ ብረት ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እና የወደብ ልማት ዘርፎች ለመግባት ማቀዳቸውን ይፋ አድርገዋል።

ቢሊየነሩ ይህንን እቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት ከነዳጅ ማጣሪያ ባለፈ አፍሪካ ለኢንዱስትሪ የሚያስፈልጓትን ግብዓቶች በራሷ እንድታመርትና የውጭ ጥገኝነትን እንድትቀንስ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

በናይጄሪያ የሚገኘውና በቀን 650,000 በርሜል ነዳጅ እያጣራ የሚገኘው ግዙፉ የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የማምረት አቅሙን ወደ 1.4 ሚሊዮን በርሜል እንደሚያሳድግም ይጠበቃል።

አዲሶቹን የማስፋፊያ ዕቅዶች ጨምሮ የዳንጎቴ ግሩፕ ለ65,000 የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በኢትዮጵያም በሲሚንቶ ምርት ዘርፍም በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

@etconp
❤9👍4
👉እስኪ እንወያይበት

💫አንድ ስራ ተቋራጭ አንድን ህንጻ per contract requirement (design and specification) ስራውን ያለጉድለት ሰራቶ ቢያጠናቅቅ ነገር ግን በህንጻ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 ዓንቀጽ 16(2) የተደነገገው የመገልገያ ሕንጻው ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ያልሆነና  እንደሆነ  ርክክብ መፈጸም ይቻላል?

በህግ  ወይም በህንጻ ስታንዳርድ የተቀመጡ መስፈርቶች አለማሟለት እንደ defect ተቆጥሮ በremark  on legal requirement ተይዞ በሕጉ አግባብ መታረም አለበት ወይስ  በውሉ መሰረት ስለሰራ በቀጥታ (technical and contractual remark) በመያዝ ብቻ ርክክብ መፈጸም ይቻላል?

@etconp
❤6👍1
የባቱ - አርሲ ነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናቀቁ

የአዲስ አበባ - ሞያሌ - ናይሮቢ - ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ - ሐዋሳ ክፍል 3፡ ባቱ - አርሲ ነገሌ 57 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናቀቁ።

የፍጥነት መንገዱ በ90 ሜትር የመንገድ ወሰን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ የጎን ስፋቱ የመንገድ አካፍይን ጨምሮ 31 ነጥብ 6 ሜትር ነው።

መንገዱ ሙሉ በሙሉ ከከተማ ውጪ የሚያልፍና ከከተማዎች ጋር የሚያስተሳስሩ አገናኝ መንገዶች ያሉት ሲሆን አገናኝ መንገዶቹ በገጠር 10 ሜትር፣ በከተማ ደግሞ 22 ነጥብ 5 ሜትር የጎን ስፋት አላቸው።

ግንባታውን ለማከናወን የዋለው 5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተሸፈነ ነው።

የግንባታ ሥራውን ዓለም አቀፉ የሥራ ተቋራጭ ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሲያከናውነው፤ ኩንሃ ኢንጂነሪንግ እና ኮንሰልቲንግ ከኮሪያ ኤክስፕረስዌይ ኮርፖሬሽን ጋር በትብብር፣ እንዲሁም ሀገር በቀሉ ንዑስ አማካሪ ኢትዮ ኢንፍራ ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ የማማከሩንና የቁጥጥሩን ሥራ በጋራ ሰርተውታል።

መንገዱ የአዲስ አበባ - ሞጆ - ሞያሌ - ላሙ - ሞምባሳ ትራንስ ኢንተርናሽናል ሐይዌይ እንዲሁም 10,000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የታላቁ የምስራቅ አፍሪካ ኮሪደር (ኬፕታውን ትራንስ አፍሪካን ሐይዌይ) አካል በመሆኑ፣ የጎረቤት ሀገራትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር በማጠናከር ረገድ የላቀ ሚና ይጫወታል።

የፕሮጀክቱ የ ITS intelligent Transport system ተከላ ተጠናቅቆ መንገዱ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ እና የቱሪዝም ፍሰት ለማቀላጠፍ የሚያስችል ይሆናል።

የመንገድ ኮሪደሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች የሚገኙትን የባቱ ከተማን፣ የአዳሚ ቱሉ እና አርሲ ነገሌ ወረዳዎችን ጨምሮ ከ17 በላይ ቀበሌዎችን ያስተሳስራል።

በተጨማሪም የእርሻና ኢንዱስትሪ ማዕከላትን እንዲሁም የቱሪስት መስህቦችን ለማገናኘት የሚያስችል ሲሆን፤ በተለይም የሀሮ ደምበል፣ ላንጋኖ፣ አብያታ እና ሻላ ሐይቆችን እንዲሁም ሐዋሳን ለመጎብኘት ለሚሄዱ የሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

ፕሮጀክቱ ከሞጆ - ሐዋሳ የነበረውን የ4 ሰዓት የጉዞ ጊዜ ወደ 2 ሰዓት ዝቅ በማድረግ፣ ለመንገዱ ተጠቃሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችላል።

ከዚህም ባሻገር እንደ ስንዴ፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ፓፓያ እና ድንች ያሉ የግብርና ውጤቶች ሳይዘገዩ በፍጥነት ለገበያ እንዲቀርቡ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

Via ERA

@etconp
❤13
👉JOB VACANCY

💫JS House Construction and Rent SC

⭐️1. OFFICE ENGINEERS

🚧Job Requirement

📜የትምህርት ደረጃ፡ በ Civil Engineer፤ በ Construction Technology and Management ወይም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ

⏺ተጨማሪ ትምህርት፡ Engineering software በቂ ልምድ

⏺የስራ ልምድ፡ 5 አመት እና ከዚያ በላይ ሆነው office engineer ስራዎች በቂ ልምድ ያላቸው


⭐️2. SITE ENGINEERS 

🚧Job Requirement

📜የትምህርት ደረጃ፡ በ Civil Engineer፤ በ Construction Technology and Management ወይም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ

⏺ተጨማሪ ትምህርት፡ Engineering software በቂ ልምድ

⏺የስራ ልምድ፡ 5 አመት እና ከዚያ በላይ እና በስትራክቸር ግንባታ /structural/ ስራ ላይ በቂ ልምድ ያላቸው

⏺ፆታ: አይለይም
⏺የቅጥር አይነቱ: በኮንትራት
⏺ደሞዝ: በስምምነት

📩How to Apply

⏺ከላይ በዝርዝር በተጠቀሱት መሰረት አመልካቾች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ የትምህርት ማስረጃቸውን እና የስራ ልምዳችሁን በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከዚህ በታች በሚጠቀሰው የማህበሩ አድራሻ መጥተው ማመልከት ወይም በኢ-ሜል መላክ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

📍የማህበሩ አድራሻ፡ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ አባ መላ የገበያ መዕከል 3ኛ ፎቅ በአካል ወይም e-mail: jshousecon2006@gmail.com

📞ለበለጠ መረጃ፡ 0911438371/0927357195/0911627293 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

⚡️Dead Line March 12/2026

@etconp
❤7👏1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

0904040477
0911016833
❤4👏1
👉አሁን ይዤላቹ የመጣሁት ስለ የውሃ ማጣሪያ ምህንድስና (Water Treatment Engineering)

1. ትርጉም
የውሃ ማጣሪያ ምህንድስና የአካባቢ ምህንድስና ክፍል ሲሆን ከወንዞች፣ ከሀይቆች፣ ከረዘርቮዋሮች እና ከመሬት በታች የሚገኝ ውሃ ውስጥ ያሉ አካላዊ፣ ኬሚካላዊ እና ባዮሎጂካዊ ቆሻሻዎችን ለማስወገድ የሚያገለግል መርሀ ግብር ነው።

ውሃ ከሰዎች ጤና ጋር በጣም የተያያዘ ስለሆነ ወደ ህዝብ ከመቅረቡ በፊት በውሃ ማጣሪያ ፋብሪካ (Water Treatment Plant) ውስጥ በተከታታይ ሂደቶች ይታከማል።

2. የውሃ ማጣሪያ ዓላማ
የውሃ ማጣሪያ ዋና ዓላማዎች እነዚህ ናቸው፦
• የተንጠለጠሉ ንጥረ ነገሮችን (suspended solids) ማስወገድ
• ጭጋግነት (turbidity) መቀነስ
• አደገኛ ባክቴሪያና ቫይረሶችን ማጥፋት
• ሽታ፣ ቀለም እና ጣዕም ማስወገድ
• አደገኛ ኬሚካሎችን መቀነስ
• የመጠጥ ውሃ ደረጃን የሚያሟላ ውሃ ማቅረብ

3. የRaw Water ባህሪያት
Raw water በአብዛኛው 3 ዓይነት ቆሻሻ ይይዛል።

1. አካላዊ ቆሻሻ (Physical Impurities)
• ተንጠለጠሉ ነገሮች
• ጭጋግ (Turbidity)
• ቀለም
• የሙቀት ልዩነት

2. ኬሚካላዊ ቆሻሻ (Chemical Impurities)
• የተፈጥሯዊ ጨዎች
• አይረን (Iron)
• ማንጋኒዝ (Manganese)
• ከባድ ኬሚካሎች

3. ባዮሎጂካል ቆሻሻ (Biological Impurities)
• ባክቴሪያ
• ቫይረስ
• አልጌ (Algae)
• ፕሮቶዞዋ

4. የውሃ ማጣሪያ ሂደቶች
የተለመደ የውሃ ማጣሪያ ሂደት ይህንን ቅደም ተከተል ይከተላል።

Raw Water → Screening → Aeration → Coagulation → Flocculation → Sedimentation → Filtration → Disinfection → Storage → Distribution

5. Screening (መመርመር)
Screening የውሃ ማጣሪያ መጀመሪያ ደረጃ ሲሆን ትልቅ እቃዎችን ከውሃ ለማስወገድ ይጠቅማል።

ዓላማ
• ትልቅ ቆሻሻ ማስወገድ
• ፓምፖችን መጠበቅ
• ፓይፕ መዘጋትን መከላከል

የሚወገዱ ነገሮች
• ቅጠሎች
• ቅርንጫፎች
• ፕላስቲኮች
• ድንጋዮች
• ተንሳፋፊ ቆሻሻ

የScreens አይነቶች
Coarse Screen
Fine Screen

6. Aeration (አየር ማስገባት)
Aeration ውሃን ከአየር ጋር በመገናኘት የውሃ ጥራትን ማሻሻል ነው።

ዓላማ
• የተቀላቀሉ ጋዞችን ማስወገድ
CO₂ , H₂S
• ሽታን መቀነስ
• አይረን እና ማንጋኒዝ ኦክሲዴሽን ማድረግ

የAeration ዘዴዎች
• Cascade aerator
• Spray aerator
• Diffused aerator

ኬሚካል ምላሽ
4Fe²⁺ + O₂ + 10H₂O → 4Fe(OH)₃ + 8H⁺

7. Coagulation (ኮአጉሌሽን)
Coagulation በውሃ ውስጥ ያሉ ትንሽ ነገሮችን እንዲጣበቁ ኬሚካል መጨመር ነው።
ብዙ ጊዜ እነዚህ ነገሮች ኔጌቲቭ ኤሌክትሪክ ቻርጅ ይይዛሉ እና አይጣበቁም።

የሚጠቀሙ ኬሚካሎች
• Alum (Al₂(SO₄)₃)
• Ferric Chloride
• Ferric Sulfate

የAlum Reaction
Al₂(SO₄)₃ + 6H₂O → 2Al(OH)₃ ↓ + 3H₂SO₄
Al(OH)₃ የሚባለው gel-like precipitate ቆሻሻን ይይዛል።

8. Flocculation (ፍሎኩሌሽን)
Flocculation በዝቅተኛ ፍጥነት በማቀላጠፍ ትንሽ ነገሮች እንዲቀላቀሉ እና ትልቅ flocs እንዲፈጠሩ ይረዳል።

ባህሪ
• ቀስ በቀስ መቀላቀል
• ትልቅ ነገሮች መፍጠር
• በsedimentation ውስጥ መቀመጥን ያሻሽላል
ጊዜ
20 – 40 ደቂቃ

9. Sedimentation (ሰዲመንቴሽን)
Sedimentation በግራቪቲ ተጽእኖ ነገሮች ከውሃ በታች እንዲቀመጡ የሚያደርግ ሂደት ነው።
ይህ በ Sedimentation Tank ወይም Clarifier ውስጥ ይከናወናል።

ጥቅም
• 60–70% ቆሻሻ ማስወገድ
• Turbidity መቀነስ

የStokes Law
Vs = g(ρp − ρ)d² / 18μ
Vs = settling velocity
g = gravity
ρp = particle density
ρ = water density
d = particle diameter
μ = dynamic viscosity
10. Filtration (ማጣሪያ)
Filtration በ filter media በመጠቀም የቀሩ ነገሮችን ከውሃ ማስወገድ ነው።

Filter Materials
• Sand
• Gravel
• Anthracite

1. Slow Sand Filter
• ዝቅተኛ filtration rate
• ባዮሎጂካል layer (Schmutzdecke) ይጠቀማል
Filtration rate
0.1 – 0.2 m³/m²/hr

2. Rapid Sand Filter
• ከፍተኛ filtration rate
• በትልቅ water treatment plant ይጠቀማል
Filtration rate
4 – 10 m³/m²/hr
Filtration Formula
Rate of filtration = Q / A
Q = discharge (m³/hr)
A = filter area (m²)

11. Disinfection (ማጥፊያ)
Disinfection የመጨረሻ ደረጃ ሲሆን ባክቴሪያና ቫይረሶችን ለማጥፋት ይጠቅማል።

ዘዴዎች
• Chlorination
• Ozonation
• Ultraviolet

Chlorination
Reaction
Cl₂ + H₂O → HOCl + HCl
HOCl ዋና disinfecting agent ነው።
Chlorine Demand
Chlorine Demand = Chlorine Added − Residual Chlorine
Residual Chlorine
0.2 – 0.5 mg/L

12. Water Storage (የውሃ ማከማቻ)
ከማጣሪያ በኋላ ውሃ በሚከተሉት ይቀመጣል።

• Clear Water Reservoir
• Service Reservoir
• Elevated Tank

ዓላማ
• በPeak demand ጊዜ ውሃ ማቅረብ
• በdistribution system ግፊት መጠበቅ

13. የWater Treatment Engineering አስፈላጊነት
• የህዝብ ጤናን ይጠብቃል
• የውሃ በሽታዎችን ይከላከላል
• የውሃ ጥራትን ያሻሽላል
• ለመጠጥ እና ለቤት አገልግሎት ደህና ያደርገዋል።

Via Mekamu Mohammed

@etconp
❤10
👉የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

🚧ሳኒተሪ ፎርማን - Ayat Real Estate S.C

🔰Deadline Date March 12, 2026

📍አዲስ አበባ

📜Job Requirement

⏺ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ: ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ በሲቪል ኢንጂነሪንግ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሮት በሙያዉ 4 ዓመት እና ከዚያ በላይ አግባብነት ያለዉ የሥራ ልምድ ያለዉ/ላት  ወይም በቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ ዲፕሎማ /ደረጃ 4 ኖሮት በሙያዉ 6 ዓመት እና ከዚያ በላይ አግባብነት ያለዉ የሥራ ልምድ ያለዉ/ላት

❇️ደረጃ: 7
⏺ተፈላጊ ብዛት: 2
⏺ደመወዝ: አዲስ በተሻሻለው የድርጅቱ ደመወዝ ስኬልመሰረት

📍የሥራ ቦታ፡  አዲስ አበባ እና በአካባቢው

📩How to Apply

🎲የምዝገባ ቀን፡ ይህ ማስታውቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት፣በአካል በመቅረብ

⏺የምዝገባ አድራሻ፡ አያት አክስዮን ማህበር ዋና መ/ቤት (ከመገናኛ ወደ ወሰን ግሮሰሪ በሚወስደው መንገድ ሚካኤል የትራፊክ መብራቱ አጠገብ)

⚡️ማሳሰቢያ፡ አመልካቾች ለምዝገባ ሲቀርቡ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃቸውን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡

💫አመልካቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 09-72-57-86-37 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

@etconp
👍3❤1🎉1
👉URGENT VACANCEY ANNOUNEMNET

🏷M AND B ENGINEERING PLC

🚧M and B Engineering Plc would like to hire for our Project on Positions

1. Junior Site Engineer
2. Site Engineer 
3. Store and Time Keeper

💫REQUIRED NO:- 2 in Junior Site Engineer and 3 in Site Engineer position

❇️JOB TYPE: Contract

🔰Job Requirement: Junior Site Engineer

⏺Education: BSc Degree in Civil Engineering or Construction Technology of Management (Apparent ship Experience Paper Should be Attached)
⏺CGPA- 3.00 and above
⏺Work Experience: 0

🔰Job Requirement : Site Engineer
⏺QUALIFICATION:  PE licensed and BSc Degree   in Civil Engineering
⏺WORK EXPERIENCE: 3 Years in BSC Degree work experience in building projects.

🔰የስራ መደብ ፡ ስቶር ኪፐር እና ሰአት ተቆጣጣሪ
⏺የትምህርት ደረጃ፡ 8ኛ ክፍል ከዛ በላይ
⏺የሰው ብዛት፡ 3
⏺የቅጥር ሁኔታ: በፕሮጀክት
⏺የስራ ልምድ፡ ከ1 አመት ያላነሠ በስቶር ኪፐር እና ሰአት ተቆጣጣሪ የስራ

🎲SALARY: As per the organization scale

📍PLACE OF WORK: Addis Ababa
⚡️APPLICATION DATE:  March 06, 2026 – March 16, 2026

📩HOW TO APPLY

⏺Submit your non-returnable CV in person to M and B Engineering Plc Head office located 22, Gollagul Tower 5th floor HR & Administration Department, office. No 510/509.

📞Phone. No: +251 116 90 01 10

@etconp
❤4🎉1
👉መጪው የአዋሽ ባንክ አዲሱ ግዙፍ ሕንፃ

💫የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ ለሚገነባው የአዋሽ ባንክ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት ወሳኝ የሆነ የጂኦሎጂካልና ጂኦቴክኒካል ጥናት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

🏷የኮርፖሬሽኑ ባለሙያ የሆኑት ጂኦሎጂስት ጌትነት መሸሻ እንደገለጹት፣ ጥናቱ በዋናነት የመሬቱን የመሸከም አቅም (bearing capacity) ለማወቅና ለግዙፉ ህንጻ አስተማማኝ መሰረት ለመጣል ያለመ ነው።

በአጠቃላይ 11 ስልታዊ ጉድጓዶች የተቆፈሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል አምስቱ እያንዳንዳቸው 115 ሜትር ጥልቀት አላቸው። ቀሪዎቹ ስድስት ጉድጓዶች ደግሞ እስከ 60 ሜትር ጥልቀት ደርሰዋል።


ከቁፋሮው የተገኙ ሙሉ የአለትና የአፈር ናሙናዎች (Samples) በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የላቦራቶሪ ምርመራ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ምንም እንኳን የህንጻው ትክክለኛ ከፍታ በቀጣይ በሚደረጉ ጥልቅ ጥናቶች የሚወሰን ቢሆንም፣ አሁን ባለው ግምት ግን በኢትዮጵያ እስካሁን ከተገነቡት ታላላቅ ህንጻዎች ሁሉ የላቀ ከፍታ ሊኖረው እንደሚችል ይጠበቃል።

የጂኦቴክኒካል ኢንቨስትጌሽኑ ዋና ግብ፦

ህንጻው ወደ ውስጥ የሚኖረውን ተፅዕኖ (depth of influence) መለየት።

የህንጻው ግዙፍ ክብደትና ጫና በመሬቱ ንጣፎች ላይ እንዴት እንደሚከፋፈል (distribute) ማረጋገጥ።

አዲሱን ስትራክቸር በአስተማማኝ ሁኔታ መሸከም የሚችል የከርሰ-ምድር ንጣፍ መለየት ነው።

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ የንብ፣ የህብረት፣ የፀደይ፣ የዓባይ እና የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንኮችን ግዙፍ ህንጻዎች ግንባታ መሰረት የሆኑ ተመሳሳይ ጥናቶችን ማከናወኑ ይታወቃል።

@etconp
❤16👍3