Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
#Update

🚨የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 5.1 ተለክቷል !!

ባለፉት ሳምንታት ትንሽ ጋብ ብሎ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ጠንክሮ ተሰምቷል።

የአዋሽ አካባቢ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ በርካታ አከባቢዎች እጅግ የጠነከረ ንዝረትም ለሰከንዶች ነበር።

" ከወትሮው ፍጹም የተለየ ነበር " ያለው አንድ የቤተሰባችን አባል " ያለሁበት ህንጻ ላይ ከፍተኛ መነቃነቅ ተሰምቶናል ፤ እጅግ ያስፈራም ያስደግጥም ነበር " ሲል ገልጿል።

በርካቶችም በተመሳሳይ ህንጻ ላይ የነበረው ስሜት ከፍተኛ እንደነበር ጠቁመዋል።

ከአዲስ አበባ ውጭም በርካታ ከተሞች ላይ ንዝረቱ በደምብ ተሰምቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ጠቁሟል።

በሬክተር ስኬልም 5.1 መለካቱን አመላክቷል።

@etconp
😢8👍7🔥2