🫧 ɱყ ƚҽαɱ🦋🦋
40 subscribers
1 photo
Everyone can share he's idea,opinion.thought
Download Telegram
ጥገኛን ተውና ታታሪውን አሳድገው!

የሆነ ጊዜ የዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ መስራች ሼህ ረሺድን ኢንተርቪው አድርጌው ነበር። ስለነገዋ ዱባይ ስጠይቀው የሰጠኝ መልስ አስገርሞኝም አስደንቆኝም ነበር

ምን አለ?

"አያቴ ግመል ይጋልብ ነበር፣ አባቴም ግመል ይጋልብ ነበር፣ እኔ ደግሞ መርሰዲስ እየነዳሁ ነው። የኔ ልጅ ላንድሮቨር ይነዳል። የልጅ ልጄም እንደዚያው ላንድሮቨር ይነዳል። የልጅ ልጅ ልጄ ግን ግመል መጋለቡ አይቀሬ ነው!"

"ለምን ?"
ለምን ካልከኝማ!

"ክፉ ጊዜ ጠንካራ ሰዎችን ይፈጥራል። ጠንካራ ሰዎች ደግሞ ሁሉ ነገር ቀላል የሆነበትን ጊዜ ይፈጥራሉ።ቀላል ጊዜያት በተራቸው ደካማ ሰዎችን ይፈጥራሉ። ደካማ ሰዎች ደግሞ ክፉ ጊዜን መልሰው ያመጡታል።  ብዙዎች አይገነዘቡት ይሆናል ፣ ነገር ግን ይህ እንዳይመጣ  ታታሪዎችን ማሳደግ አለብን። ያ ሲሆን ጥገኞች አይፈጠሩም።"

By Melaku Berhanu
ባል:-እኔ ከሞትኩ ቦኃላ ታገቢያለሽ

ሚስት:-አረ አላገባም ከእህቴ ጋር ነው ምሆነው,አንተስ?

ባል:-ኧረ እኔም አላገባም ከእህትሽ ጋር ነው ምሆነው
😁2
እስራኤል የጋዛን ከበባ ለመስበር ሲጓዙ የነበሩ የግሎባል ሱሙድ መርከቦችን ጉዞ ማደናቀፏን ተጓዦቹ አስታወቁ

እስራኤል ግሎባል ሱሙድ በመባል የሚጠራውን የጋዛን ከበባ ለመስበር ሲጓዝ የነበሩ የመርከበኞች ቡድን ጉዞ ማደናቀፏን አልጀዚራ ዘግቧል። በዘገባው መሠረት፣ መርከቦቹ በእስራኤል ከበባ ውስጥ በምትገኘው ጋዛ 278 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አደገኛ የሚባለው ዞን ውስጥ ገብተዋል። ተጓዥ ቡድኑ የእስራኤል የማደናቀፍ ድርጊት የተፈፀመው በሦስት መርከቦች ላይ መሆኑን ገልጿል።

ባወጣው መግለጫ የቀጥታ ሥርጭትን ጨምሮ መገናኛ ዘዴዎች መቋረጣቸውን የገለፀው ቡድኑ፣ የተሳፋሪዎቹ እና የቡድኑ ሁኔታም አልታወቀም ብሏል። ድርጊቱንም ባልታጠቁ የሰብአዊ ርዳታ ሰጪዎች ላይ የተፈጸመ ሕገ ወጥ ጥቃት ነው ብሎታል።

የእስራኤል ማደናቀፍ ከተሰማ በኋላ ከተጓዦች መሃል ስዊድናዊቷ አክቲቪስት ግሬታ ተንበርግ በእስራኤል ወታደሮች ቁጥጥር ስር መውደቋ ተነግሯል። በተጨማሪም 25 የስፔን፣ 9 የቱርክ፣ 7 ብራዚላውያን፣ 4 የፈረንሣይ፣ 3 የጀርመን፣ 5 የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎች በወታደሮቹ እጅ መውደቃቸውን ሚድል ኢስት ዐይ ዘግቧል።

የመርከቦቹ ጉዞ በእስራኤል ጦር መደናቀፉን ተከትሎ በበርካታ የጣሊያን ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተጠርተዋል። በደቡባዊው የኔፕልስ ከተማ ሰልፈኞች ወደ ዋናው የባቡር ጣቢያ በመግባት የባቡር ትራፊክን አስቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጣሊያን የሠራተኛ ማኅበራት በመርከቦቹ ላይ የተፈፀመውን የማደናቀፍ ድርጊት በመቃወም የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

@H_Islamic_tube
@H_Islamic_tube
ከ አጥሩ ውጭ ሾልካ የወጣች አበባ  መጨረሻዋ
🗯 " በመንገደኞች🚶‍♂‍➡️"መቀንጠስ ነው!!

        የማወራው ሾለ አበባ አይደለም‼️🔉
👍1