قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
9.39K subscribers
523 photos
530 videos
12 files
1.28K links
قال رسول الله ﷺ: " إِذَا مَرَرْتُمْ بِرِيَاضِ الْجَنَّةِ ؛ فَارْتَعُوا ...

أسأل الله أن ينفع بالقناة ويتقبل منا
Download Telegram
🌱 ሰማይ ላይ ካሉ ፍጥረታት ለአላህ ቅርብ የሆነዉ ጅብሪል(ዐ.ሰ) ዱዐ ሲያደርግ ምድር ላይ ከሁሉ በላይ የሆኑት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አሚን አሉ.
...ረመዳንን አግኝቶ ይቅርታ ያላገኘ ይዋረድ አለ
አሚንም አሉ

ይህ ማለት በረመዳን ሳይማሩ መውጣት የለም
በረመዳን ካልተማርን ...
👍15
Audio
مناجاة خاشعة
للقارئ فيصل الهاجري
دعاء الليلة الخامسة
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💭 ኢማሙ በቁኑት ወቅት እንዲህ ሲል፦ አላሁመ-ህዲና ፊመን ሀደይት (አላህ ሆይ! ቀጥተኛውን መንገድ ከመራሃቸው ጋር ምራን) ሲል

• አንተ ምን ትላለህ? ... አሚን

• ​ኢማሙ፦ ወ ዓፊና ፊመን ዓፈይት (ጤናና ጥንካሬን ከሰጠሃቸው ጋር ስጠን) ሲል

• አንተ ምን ትላለህ ?  ... አሚን

• ​ እሺ እንዲህ ሲልስ፦ ኢነሁ ላ የዚሉ መን ዋለይት፣ ወላ የዒዙ መን ዓደይት፣ ተባረክተ ረበና ወ ተዓለይት (አንተ የወደድከውና ወዳጅ ያደረግከው ፈጽሞ አይዋረድም፣ አንተ ጠላት ያደረግከውም ፈጽሞ ክብር አያገኝም። ጌታችን ሆይ! አንተ ጥራት ይገባህ፣ ላቅክም ነህ) ሲል

• ​አንተ በዚህ ጊዜ ምን ትላለህ?

🪶 ከሱና ጋር በጣም የቀረበው ዝም ማለት ነው። ነገር ግን "ሱብሃን አላህ" ብትል ይፈቀዳል።

⛔ ​ ነገር ግን... "አሚን" ማለት አይፈቀድልህም። ምክንያቱም የአሚን ትርጉም "አላህ ሆይ! (ይህንን ዱዓ) ተቀበለን/መልስልን" ማለት ነው።

🪶​ ይህ ልክ አንድ ሰው ዱዓ እያደረገ "አላህ ሆይ! ደመናትን የምታንቀሳቅስ፣ የጠላትን ሰራዊት ድል የምታደርግ ሆይ!" ሲል እንደማለት ነው። አይሆንም፣ (እዚህ ላይ) አሚን አትልም። ምክንያቱም የአሚን ትርጉም "አላህ ሆይ! ጸሎቴን መልስልኝ፣ ይሁንልኝ" ማለት ስለሆነ ነው። (እነዚህ ደግሞ የጌታ መገለጫዎች እንጂ ልመናዎች አይደሉም)።

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍26🏆6
🥹 ​ረመዳን 🌙

​1️⃣. የቁርአን ወር (شهر القرآن)

•​አላህ እንዲህ ይላል፦ "የረመዳን ወር ያ ቁርአን በእርሱ ውስጥ የወረደበት ነው።" [በቀራህ፡ 185]

•​ጅብሪል (ዐ.ሰ) በየዓመቱ በረመዳን ሌሊቶች ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይመጣና ቁርአንን ያጠኑ ነበር። (ቡኻሪ ዘግበውታል)

​2️⃣. የጾም ወር (شهر الصيام)

•​አላህ እንዲህ ይላል፦ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደተደነገገው በናንተም ላይ ተደነገገ።" [በቀራህ፡ 183]

•​ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "የረመዳን ወርን በእምነትና ከአላህ ምንዳን በመፈለግ የጾመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

​3️⃣. የበጎ አድራጎት ወር (شهر الخير)

•​ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰው ሁሉ ይበልጥ ቸር ነበሩ፤ ይበልጥ ቸር የሚሆኑት ደግሞ በረመዳን ወር ነበር። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

•​ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "ጾመኛን ያስፈጠረ ሰው የጾመኛውን ያክል ምንዳ ያገኛል።" (አህመድ ዘግበውታል)

​4️⃣. የለይለቱል ቀድርና የሶላት ወር (شهر القيام)

•​ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "የረመዳን ወርን በእምነትና ከአላህ ምንዳን በመፈለግ (በሶላት) የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

•​ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "የለይለቱል ቀድርን ሌሊት በእምነትና ምንዳን በመፈለግ በሶላት የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

🔵 @TewhedandSuna ❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🥹 በማፍጠሪያ ወቅት የሚደረግ ዱዓ

• ​በማፍጠሪያ ወቅት ብዙ ሰዎች ገና በልጅነታቸው ጀምሮ የለመዱትንና በሰፊው የሚታወቀውን የሚከተለውን ዱዓ ሲያደርጉ እንሰማለን፦

​"አልላሁመ ለከ ሱምቱ ወዓላ ሪዝቂከ አፍጠርቱ"

(ጌታዬ ሆይ! ላንተ ብዬ ጾምኩኝ፣ በሰጠኸኝም ሲሳይ አፈጠርኩኝ)

😀​ነገር ግን ይህ ሐዲስ ትክክለኛነቱ (ሰሒሕነቱ) ያልተረጋገጠ ነው።

✅ ​ትክክለኛው መንገድ፦

• ​በመጀመሪያ "ቢስሚላህ" ብሎ መጀመር፣ ከዚያም እየበሉና እየጠጡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሩትን የሚከተለውን ትክክለኛ ዱዓ ማድረግ ይገባል፦

​"ዘሀበ-ዘመኡ ወብተለቲል ዑሩቁ ወሰበተል አጅሩ ኢንሻ አላህ"

(ጥሙ ተወገደ፣ ደም ስሮች ረጠቡ (ረኩ)፣ አላህ ከፈቀደም ምንዳው (አጅሩ) ተረጋገጠ)

🔵 @TewhedandSuna 🎴
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍13🏆3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💭አደራ ትርፋችን ረሃብና ጥም እንዳይሆንብን

🎙ustaz ahmed
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍27
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌙 ​"ረመዳን የዕድሜ ትምህርት ቤት ነው። አንድ ሰው ራሱን ለአላህ ታዛዥነት፣ አላህን በመገዛትና በመልካም ስራዎች ላይ የሚያንጽበት ትምህርት ቤት ነው። ስለዚህም አንድ ሰው ረመዳንን በአግባቡ ለመጠቀም ከታደለ፣ ከረመዳን ሲወጣ የአላህ ፍራቻን (ተቅዋን) ሰንቆ ይወጣል። ይህንንም የአላህ ፍራቻ እስከ ቀጣዩ ረመዳን ድረስ በህይወቱ ሙሉ አብሮት ይዘልቃል።"

🎙 الشيخ عبد الرزاق البدر

🔖ከሸይኽ አብድረዛቅ አል በድር ንግግር የምንወስደው ቁልፍ ነጥቦች፡

• ​ረመዳን እንደ ትምህርት ቤት ፡ ራስን መግራትና መልካም ስነ-ምግባርን መለማመጃ መሆኑን ይገልጻል።

• ​ተቅዋ (የአላህ ፍራቻ)፡ ከረመዳን የሚገኝ ትልቁ ስንቅ መሆኑን ያመለክታል።

• ​ቀጣይነት፡ በረመዳን የተገኘው መንፈሳዊ ጥንካሬ ከወሩ መጠናቀቅ በኋላም አብሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ያስገነዝባል።

🔵@TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌙 ​"የወራችሁ (የረመዳን) የመጀመሪያው አንድ ሶስተኛ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል። ብልህ እና አስተዋይ ሰው ማለት ይህንን ተረድቶ ግቡን ለማሳካት ቁርጠኛ የሆነ ነው።

• ​ወደ ጀነት ለመግባ መሽቀዳደም  ለሚፈልጉ እና ወደ አላህ ውዴታ ደረጃዎች ለመውጣት፣ እንዲሁም የራህማንን ይቅርታ ለማግኘት እና ከእሳት ነጻ ለመውጣት ለሚሹ ሁለት ሶስተኛው (የወሩ ክፍል) ቀርቷቸዋል።

• ​ስለዚህ ቀሪውን የወሩን ጊዜ በመልካም ስራዎች ተጠቀሙበት። ከሀጢያት ተቆጠቡ፤ ብቻውን የላቀ ለሆነው አምላክም (ስራችሁን) አጥሩ። በመልካም ስራዎች ላይ ተሽቀዳደሙ፤ በመንገዱም ላይ ተሯሯጡ።

• ​ቀኖቹን እና ሌሊቶቹን በመልካም ስራዎች የተጠቀመ ሰው ምንኛ የታደለ ነው! ራሱን  በጾም እና በሶላት (በቂያም) ታገለ፣ ሰውነቱን ያበረታ። በምጽዋትም እጆቹ የተዘረጉ፤ መልካምን ነገር እና ደስታን አገኘ።"

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍃🕯 ˓٭˛ ،🌸

🌹 ​እናንተ የጾመኞች ስብስብ  ሆይ! ዛሬ ፀሐይ ስትጠልቅ ወደ ጁምዓህ ቀን እና ሌሊት ትገባላችሁ።

• ​በዚህም ወቅት እኛም ሆንን እናንተ በውዱ ነቢይ ሙሐመድ (📿) ላይ ሰለዋት ማብዛት ይወደድልናል [ይኖርብናል] ።

•​ ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዲያወጣን አላህ በላከው ነቢይ ላይ ሰለዋትና ሰላምታ አብዙ።

•​ ከእሳት አውጥቶ ስፋቷ እንደ ሰማይና ምድር ወደሆነችው ጀነት መሪ በሆነን፣ ሱናው እዝነት በሆነልን፣ ልደቱ ለዘላለማዊው የኋለኛው ዓለም ሕይወት መዳኛና መሰላል በሆነልን ነቢይ ላይ ሰለዋት አውርዱ።

• ​አላህ ሆይ! ሙአዚኑን ስንሰማና ለጥሪው ምላሽ ስንሰጥ፣ ነቢዩ ሙሐመድ (📿) ከጌታቸው ብርሃን እንደወረደላቸው ስንመሰክር በነቢዩ ላይ ሰለዋት ይውረድ።

• ​ከጌታችሁ የአስር እጥፍ በረከትን በምትመኙት ልክ፣ በመመሪያው ብርሃንና በብሩህ መብራት በሆኑት ነቢይ ላይ ሰለዋትና ሰላምታ አውርዱ።

• ​ነቢዩ (📿) እንዳሉት "በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ፣ አላህ በእርሱ ላይ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል።"

• ​ጌታ ሆይ! በውዱ ነቢይ ሙሐመድ (📿) ላይ ሰለዋት የሚያወርዱት ሰዎች ባሉበት ልክ፣ ሰለዋትና ሰላምታ እንዲሁም በረከትን አውርድባቸው።

• ​ጌታ ሆይ! ስለ ሰለዋት በዘነጉት ሰዎች ልክም፣ በሳቸው ላይ ሰለዋት፣ ሰላምታና በረከትን አውርድባቸው።

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍15
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

ሰበር ዜና¡
~
• ዓለም ሁሌም የምታወራው አዲስ ነገር አላት። ፖለቲካው፣ ትንታኔው፣ ወሬው... መቼም አያልቅም። ስልካችንን እና ቴሌቪዥናችንን ባበራን ቁጥር፣ ዓለም አሁን ካልሰማናት የምትፈርስ ይመስል በየደቂቃው በዜና ታጣድፈናለች።

• ግን እዚህ ግርግር ውስጥ ምን ያህል ውድ ጊዜያችንን እያቃጠልን እንደሆነ አላስተዋልንም። የሌሎችን "ሰበር ዜና" ለመስማት ስክሪን ላይ ስናፈጥ፣ የራሳችን ዕድሜ በዝምታ እያለቀ የራሱን የሞት "ሰበር ዜና" እያቀረበልን ነው።

• ወዳጄ... አእምሮህን ከሚያደነቁረው ከዚህ ሁሉ ጫጫታ ራስህን አግልል። የልብህን እርጋታ ቀስ በቀስ ከሚሰርቀው የሚዲያ ሱስ ራቅና ስክሪንህን ዝጋው።

• ቁርኣንህን አንሳ። ጊዜው በፍጥነት እየሮጠ ነው። እነዚህ የተከበሩ የረመዷን ቀናት በቶሎ ያልፋሉ፤ ወይም ደግሞ ቀናቶቹ ሳያልቁ አንተ ታልፋለህ።ጊዜህን ተጠቀምበት፤ ቀናቶቹ የተቆጠሩ ናቸውና!

أياماً معدودات....

©abu sufyan

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍51🏆4
Audio
💥 [ الموقف من ضرب إسرائيل وأمريكا لإيران ]

💥አንድ ሙስሊም [ እስራኤል እና አሜሪካ ኢራንን በመምታታቸው ረገድ ሊኖረው የሚገባ አቋም ]

🔵 @TewhedandSuna 🎴
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍23🏆3
🌙 ረመዳን 🥹

​"የረመዳን ወር ሌሊቶች መሃል ላይ ደርሰዋል። ከፊታችን ያለው የቀረው ጊዜ ካለፈው ይልቅ ይበልጥ የተከበረ ነው። ስለዚህ መልካም ነገርን ከመፈለግ {ከመስራት} ወደ ኋላ አትበሉ፤ ጉዟችሁንም ለመቀጠል አትስነፉ። ከአጋማሹ በኋላ ያለው ጊዜ የመጨረሻው መቃረቢያ ነው፤ ከዚያም በውስጡ የሰራችሁትን ይዛችሁ ትጠቀልሉታላችሁ።"

​— ዶ/ር ሳሊህ አል-ኡሰይሚ

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍15
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌙 ​የረመዳን አጋማሽ 🥹

• ​የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እነሆ የረመዳን ወር አጋማሽ ላይ ደርሷል። ከእናንተ መካከል በዚህ ወር ውስጥ ራሱን የፈተሸና የቀና ማን አለ?

• ​በዚህ ወር የሚገባውን ክብር የሰጠውና መብቱን ያወቀ ማን አለ? እነሆ ወራችሁ መጉደል (ማለቅ) ጀምሯል፤ ስለዚህ በበጎ ስራዎች ላይ በርቱ።

• ​ወሩ ሊጠናቀቅ እንደሆነ ሁሉ፣ እያንዳንዱ ወር መጨረሻ አለው። ለሌሎች ወራት ምትክ ሊኖር ይችላል፤ ለረመዳን ግን ምትክ ከየት ይገኛል?

• ​ወሩ አጋማሽ ላይ ደርሷል ፣ መልካምን ስሩ ፤ በጀነቶችም ውስጥ ድልን የሚቀዳጁት በርትተው ያገለገሉ (የሰሩ) ናቸው።

• ​እንደ እኔ አይነቱ ዘንጊና ምስኪን ግን በሀዘን ተሰብሯል፤ ዋይ ለርሱ! ከዚህ ትልቅ እድል መታረሙ ምንኛ ከባድ ነው።

•​በመዝራት ወቅት ዘር ያመለጠው ሰው፣ ከመጸጸትና ከሀዘን ውጭ ምን ሊያጭድ ይችላል?

•​በዚህ ወር ውስጥ አላህን በመፍራት (ተቅዋ) የነገደና የአላህ ገመድ አጥብቆ የያዘ ሰው ምንኛ የታደለ ነው!

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍11
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌙 የረመዷን ቀናት እና የሰው ልጅ እድሜ 🥹

• ​"ረመዳን በብዙ መልኩ ከሰው ልጅ ሕይወት ጋር ይመሳሰላል፤ በመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት እንደ ልጅነት ሕይወት መጀመሪያ በደስታ፣ በንቃት፣ በተስፋና በጉጉት የተሞላ ነው። በሁለተኛዎቹ አስር ቀናት ደግሞ ልክ እንደ ወጣትነት ዕድሜ በጨዋታና በዝንጋቴ ይታለፋል። በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ግን እድሜው እንደገፋ ሽማግሌ ይሆናል፤ በዚህ ወቅት በርትቶ የሰራ ይረታል (ያተርፋል)፣ ቸል ያለ ደግሞ ይቆጫል።"

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍29
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⛓ነቢዩ {📿} እንዲህ ብለዋል፦

"በረመዳን ወር አራት ነገሮችን አብዙ፤ ሁለቱ ጌታችሁን የምታስደስቱባቸው ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ እናንተ በጭራሽ የማትበቃቁባቸው (የምትፈልጓቸው) ናቸው።"

​1️⃣. ጌታችሁን የምታስደስቱባቸው፦

🟠 ​ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ አምላክ የለም ብሎ መመስከር 〔ላ ኢላሀ ኢለላህ〕 ማለት

🟠ምሕረትን መለመን {አስቲግፋር}

​2️⃣. እናንተ የማትበቃቁባቸው (ሁልጊዜም የምትፈልጓቸው)፦

🟠አላህን ጀነትን መለመን

🟠ከእሳት (ከጀሀነም) በአላህ መጠበቅ

⬅️ @TewhedandSuna ➡️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍27🏆3