This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• በማፍጠሪያ ወቅት ብዙ ሰዎች ገና በልጅነታቸው ጀምሮ የለመዱትንና በሰፊው የሚታወቀውን የሚከተለውን ዱዓ ሲያደርጉ እንሰማለን፦
"አልላሁመ ለከ ሱምቱ ወዓላ ሪዝቂከ አፍጠርቱ"
(ጌታዬ ሆይ! ላንተ ብዬ ጾምኩኝ፣ በሰጠኸኝም ሲሳይ አፈጠርኩኝ)
• በመጀመሪያ "ቢስሚላህ" ብሎ መጀመር፣ ከዚያም እየበሉና እየጠጡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሩትን የሚከተለውን ትክክለኛ ዱዓ ማድረግ ይገባል፦
"ዘሀበ-ዘመኡ ወብተለቲል ዑሩቁ ወሰበተል አጅሩ ኢንሻ አላህ"
(ጥሙ ተወገደ፣ ደም ስሮች ረጠቡ (ረኩ)፣ አላህ ከፈቀደም ምንዳው (አጅሩ) ተረጋገጠ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍13🏆3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍27
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• ረመዳን እንደ ትምህርት ቤት ፡ ራስን መግራትና መልካም ስነ-ምግባርን መለማመጃ መሆኑን ይገልጻል።
• ተቅዋ (የአላህ ፍራቻ)፡ ከረመዳን የሚገኝ ትልቁ ስንቅ መሆኑን ያመለክታል።
• ቀጣይነት፡ በረመዳን የተገኘው መንፈሳዊ ጥንካሬ ከወሩ መጠናቀቅ በኋላም አብሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ያስገነዝባል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• ወደ ጀነት ለመግባ መሽቀዳደም ለሚፈልጉ እና ወደ አላህ ውዴታ ደረጃዎች ለመውጣት፣ እንዲሁም የራህማንን ይቅርታ ለማግኘት እና ከእሳት ነጻ ለመውጣት ለሚሹ ሁለት ሶስተኛው (የወሩ ክፍል) ቀርቷቸዋል።
• ስለዚህ ቀሪውን የወሩን ጊዜ በመልካም ስራዎች ተጠቀሙበት። ከሀጢያት ተቆጠቡ፤ ብቻውን የላቀ ለሆነው አምላክም (ስራችሁን) አጥሩ። በመልካም ስራዎች ላይ ተሽቀዳደሙ፤ በመንገዱም ላይ ተሯሯጡ።
• ቀኖቹን እና ሌሊቶቹን በመልካም ስራዎች የተጠቀመ ሰው ምንኛ የታደለ ነው! ራሱን በጾም እና በሶላት (በቂያም) ታገለ፣ ሰውነቱን ያበረታ። በምጽዋትም እጆቹ የተዘረጉ፤ መልካምን ነገር እና ደስታን አገኘ።"
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• በዚህም ወቅት እኛም ሆንን እናንተ በውዱ ነቢይ ሙሐመድ (
• ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዲያወጣን አላህ በላከው ነቢይ ላይ ሰለዋትና ሰላምታ አብዙ።
• ከእሳት አውጥቶ ስፋቷ እንደ ሰማይና ምድር ወደሆነችው ጀነት መሪ በሆነን፣ ሱናው እዝነት በሆነልን፣ ልደቱ ለዘላለማዊው የኋለኛው ዓለም ሕይወት መዳኛና መሰላል በሆነልን ነቢይ ላይ ሰለዋት አውርዱ።
• አላህ ሆይ! ሙአዚኑን ስንሰማና ለጥሪው ምላሽ ስንሰጥ፣ ነቢዩ ሙሐመድ (
• ከጌታችሁ የአስር እጥፍ በረከትን በምትመኙት ልክ፣ በመመሪያው ብርሃንና በብሩህ መብራት በሆኑት ነቢይ ላይ ሰለዋትና ሰላምታ አውርዱ።
• ነቢዩ (
• ጌታ ሆይ! በውዱ ነቢይ ሙሐመድ (
• ጌታ ሆይ! ስለ ሰለዋት በዘነጉት ሰዎች ልክም፣ በሳቸው ላይ ሰለዋት፣ ሰላምታና በረከትን አውርድባቸው።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍15
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍34🏆1
ሰበር ዜና¡
~
• ዓለም ሁሌም የምታወራው አዲስ ነገር አላት። ፖለቲካው፣ ትንታኔው፣ ወሬው... መቼም አያልቅም። ስልካችንን እና ቴሌቪዥናችንን ባበራን ቁጥር፣ ዓለም አሁን ካልሰማናት የምትፈርስ ይመስል በየደቂቃው በዜና ታጣድፈናለች።
• ግን እዚህ ግርግር ውስጥ ምን ያህል ውድ ጊዜያችንን እያቃጠልን እንደሆነ አላስተዋልንም። የሌሎችን "ሰበር ዜና" ለመስማት ስክሪን ላይ ስናፈጥ፣ የራሳችን ዕድሜ በዝምታ እያለቀ የራሱን የሞት "ሰበር ዜና" እያቀረበልን ነው።
• ወዳጄ... አእምሮህን ከሚያደነቁረው ከዚህ ሁሉ ጫጫታ ራስህን አግልል። የልብህን እርጋታ ቀስ በቀስ ከሚሰርቀው የሚዲያ ሱስ ራቅና ስክሪንህን ዝጋው።
• ቁርኣንህን አንሳ። ጊዜው በፍጥነት እየሮጠ ነው። እነዚህ የተከበሩ የረመዷን ቀናት በቶሎ ያልፋሉ፤ ወይም ደግሞ ቀናቶቹ ሳያልቁ አንተ ታልፋለህ።ጊዜህን ተጠቀምበት፤ ቀናቶቹ የተቆጠሩ ናቸውና!
أياماً معدودات....
©abu sufyan
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍51🏆4
Audio
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍23🏆3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍12
"የረመዳን ወር ሌሊቶች መሃል ላይ ደርሰዋል። ከፊታችን ያለው የቀረው ጊዜ ካለፈው ይልቅ ይበልጥ የተከበረ ነው። ስለዚህ መልካም ነገርን ከመፈለግ {ከመስራት} ወደ ኋላ አትበሉ፤ ጉዟችሁንም ለመቀጠል አትስነፉ። ከአጋማሹ በኋላ ያለው ጊዜ የመጨረሻው መቃረቢያ ነው፤ ከዚያም በውስጡ የሰራችሁትን ይዛችሁ ትጠቀልሉታላችሁ።"
— ዶ/ር ሳሊህ አል-ኡሰይሚ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍15
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እነሆ የረመዳን ወር አጋማሽ ላይ ደርሷል። ከእናንተ መካከል በዚህ ወር ውስጥ ራሱን የፈተሸና የቀና ማን አለ?
• በዚህ ወር የሚገባውን ክብር የሰጠውና መብቱን ያወቀ ማን አለ? እነሆ ወራችሁ መጉደል (ማለቅ) ጀምሯል፤ ስለዚህ በበጎ ስራዎች ላይ በርቱ።
• ወሩ ሊጠናቀቅ እንደሆነ ሁሉ፣ እያንዳንዱ ወር መጨረሻ አለው። ለሌሎች ወራት ምትክ ሊኖር ይችላል፤ ለረመዳን ግን ምትክ ከየት ይገኛል?
• ወሩ አጋማሽ ላይ ደርሷል ፣ መልካምን ስሩ ፤ በጀነቶችም ውስጥ ድልን የሚቀዳጁት በርትተው ያገለገሉ (የሰሩ) ናቸው።
• እንደ እኔ አይነቱ ዘንጊና ምስኪን ግን በሀዘን ተሰብሯል፤ ዋይ ለርሱ! ከዚህ ትልቅ እድል መታረሙ ምንኛ ከባድ ነው።
•በመዝራት ወቅት ዘር ያመለጠው ሰው፣ ከመጸጸትና ከሀዘን ውጭ ምን ሊያጭድ ይችላል?
•በዚህ ወር ውስጥ አላህን በመፍራት (ተቅዋ) የነገደና የአላህ ገመድ አጥብቆ የያዘ ሰው ምንኛ የታደለ ነው!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍11
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• "ረመዳን በብዙ መልኩ ከሰው ልጅ ሕይወት ጋር ይመሳሰላል፤ በመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት እንደ ልጅነት ሕይወት መጀመሪያ በደስታ፣ በንቃት፣ በተስፋና በጉጉት የተሞላ ነው። በሁለተኛዎቹ አስር ቀናት ደግሞ ልክ እንደ ወጣትነት ዕድሜ በጨዋታና በዝንጋቴ ይታለፋል። በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ግን እድሜው እንደገፋ ሽማግሌ ይሆናል፤ በዚህ ወቅት በርትቶ የሰራ ይረታል (ያተርፋል)፣ ቸል ያለ ደግሞ ይቆጫል።"
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍29
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"በረመዳን ወር አራት ነገሮችን አብዙ፤ ሁለቱ ጌታችሁን የምታስደስቱባቸው ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ እናንተ በጭራሽ የማትበቃቁባቸው (የምትፈልጓቸው) ናቸው።"
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍27🏆3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍18🏆1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍28🏆2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
•መስገድ (ቂያሙለይል)፦ "ለይለቱል ቀድርን አምኖና ከአላህ ምንዳን ፈልጎ የሰገደ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"
•በመስጂድ መቆየት (ኢዕቲካፍ)፦ በዚህች ሌሊት በመስጂዶች ውስጥ ተገልሎ አምልኮን ማብዛት የተወደደ ተግባር ነው።
•ዱዓ ማድረግ፦ አይሻ (ረ.ዐ) "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ለይለቱል ቀድር ካገኘው ምን ልበል?" ብለው ሲጠይቁ፤ እሳቸውም፦ "አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሒቡል ዓፍወ ፈዕፉ ዓኒ" (ጌታዬ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፣ ይቅርታንም ትወዳለህና ይቅር በለኝ) በይ አሏቸው።
•ቁርዓን መቅራት፦ በተለይ በዚህች ሌሊት ቁርዓንን በብዛት መቅራት እጅግ አስፈላጊ ነው።
እነዚህን አራት ተግባራት በመፈጸም ቢዚ መሆን ፤ ከሌሎች ስራዎች ሁሉ በላጭና የተመረጡ ናቸውና።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16
حكم بيع الطعام والشراب في نهار رمضان لغير معذور
الحمد لله، والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه أجمعين، أما بعد:
يحرم بيع الطعام والشراب وكذا منحه بلا مقابل في نهار رمضان لغير معذور في ترك صومه، لما في ذلك من تسبب في المعصية، وانتهاك لحرمة الشهر، وقد نص على ذلك فقهاء الشافعية وغيرهم.
ረመዷንን መጾም የኢስላም አንዱ መሰረት ነው፡፡ የመጾም አቅም ያለው፣ ለአካለ መጠን የደረሰ፣ ጉዞ ላይ ያልሆነ፣ አካልና አዕምሮው ጤነኛ የሆነና ጾምን የሚከለክሉ ሁኔታዎች ላይ ያልሆነ ሰው ላይ በሙሉ ረመዷንን መጾም ግዴታ ነው፡፡
የረመዷንን ወር መጾም ግዴታነት የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ተከታዮች ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ይልቅ ከዚህ ቀደም ያለፉ የነቢያት ተከታዮች ላይም ጭምር ግዴታ ነበር፡፡
(يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ كُتِبَ عَلَيۡكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ 183 ) [البقرة: 183]
“እናንተ አማኞች ሆይ እናንተ ላይ ጾም ግዴታ ተደረገ፤ ልክ እነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ ግዴታ እንደተደረገው ሁሉ...” አልበቀረህ፡183፡፡
የተፍሲር ሊቃውንት እንደገለጹት የነቢዩ ዒሳ (ዐለይሂስ_ሰላም) ተከታዮችም ጭምር ይጾሙ የነበረው ረመዷንን ወር ላይ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ነው በተለያዩ ምክንያቶች ወሩ ላይ ቀናትን እየጨመሩ ጾማቸው ይዘቱን ለቆ አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ የደረሰው፡፡
ይህን ከጥንት ጀምሮ የተከበረን የጾም ወር በቂና ተቀባይነት ያለው ምክንያት (ኡዝር) ሳይኖር መጾሙን ትቶ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ መብላትና መጠጣት ዝሙት ከመስራት፣ አስካሪ መጠጥ ከመጠጣትና ከቁማር የከፋ ወንጀል መሆኑን አል ኢማም አዝዘሀቢ (አልከባኢር) ላይ ገልጸዋል፡፡
ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ምግብ/ሻይ ቤት፣ ካፍቴሪያ ወዘተ ከፍተው መደበኛ ሥራቸውን የሚሰሩ፣ የመንገዶች ዳርና ዳር ላይ የጀበና ቡና/ ሻይና ዳቦ ወዘተ ቀለል ያሉ ምግቦችን የሚሸጡ ሙስሊሞችን እናያለን!! ተመጋቢው ማንም ይሁን ማን ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ይህን ማድረጉ በኢስላም የማይፈቀድ ተግባር መሆኑንና ከዚህ የሚገኘው ገቢም ሐላል እንደማይሆን ማወቅ ይገባል!
አል ኢማም ሸምሱዲን አርረምሊ “ሚንሃጅ አጥጣሊቢን” የተሰኘውን የኢማም አንነወዊይ ታዋቂ የሻፊዒየህ መዝሀብ የፊቅህ ኪታብ ሲተነትኑ “ኒሃየቱል ሙሕታጅ” ላይ የሚከተለውን ብለዋል፥
قال العلامة شمس الدين الرملي: "...وَمِثْلُ ذَلِكَ إطْعَامُ مُسْلِمٍ مُكَلَّفٍ كَافِرًا مُكَلَّفًا فِي نَهَارِ رَمَضَانَ، وَكَذَا بَيْعُهُ طَعَامًا عَلِمَ أَوْ ظَنَّ أَنَّهُ يَأْكُلُهُ نَهَارًا كَمَا أَفْتَى بِهِ الْوَالِدُ - رَحِمَهُ اللَّهُ تَعَالَى -؛ لِأَنَّ كُلًّا مِنْ ذَلِكَ تَسَبُّبٌ فِي الْمَعْصِيَةِ وَإِعَانَةٌ عَلَيْهَا..." نهاية المحتاج: (3/182)
“የሙዚቃ መሳሪያን ለዘፋኝ፣ የሐር ጨርቅን ወንድ ልጅ ሊለብሰው፣ የጦር መሳሪያን ለሽፍታ ወዘተ መሸጥ እንደማይቻለው ሁሉ ሙስሊም የሆነ ሰው አንድን በአላህ የማያምን ሰው (ካፊርን) ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ምግብ ሊያበላና እንዲሁም ቀን ላይ ሊበላው እንደሚችል እያወቀ ወይም እየገመተ ሊሸጥለት አይገባም (መሸጥ አይቻልም!) ... ምክንያቱም ይህን ማድረግ አላህ እንዲታመፅ መንስኤ መሆንና ይህም ላይ ማገዝን ስለሚያስከትል ነው” ኒሃየቱል ሙሕታጅ፡ 3/182፡፡
ያለበቂ ምክንያት የተከበረውን ረመዷን የማይጾምን ማንኛውንም ሰው (ሙስሊምም የሚባል ይሁን ካፊር) የጾም ቀን ላይ በመጋበዝም ይሁን ምግብ በመሸጥ ማብላትና ማጠጣት አላህን ማስቆጣትና እርሱን የሚያምጹ ሰዎችን መተባበር ስለሚሆን ወንጀልና ከሙስሊም የማይጠበቅ ተግባር ነው፡፡
ስለዚህም ቀን ላይ የሆነ ሥራ የሚያሰሩት ያለበቂ ምክንያት የማይጾም ሰራተኛም ይሁን፣ የምግብ እርዳታ ሽቶ ቤት እያንኳኳ የሚጠይቅ አቅመ ደካማም ይሁን ረመዷን ቀን ላይ እንዲበላ መተባበርና ምግብ ማቀበል ወንጀል ነው፡፡
ይበልጥ ወንጀሉ ድርብርብ የሚሆነው ደግሞ የተከበረው ረመዷን ወር ላይ ሥራዬ ብሎ ምግብ/ሻይ ቤት ከፍቶ እንዴትኛውም ወርና ጊዜ ቀን ላይ ምግብ እየሸጡና የመጣውን ሁሉ እየመገቡ መዋል ነውና ሙስሊም ሆይ ከዚህ ነውርና ፍጹም ከሙስሊም ከማይጠበቅ ተግባር ተጠንቀቅ/ቂ!!
ካፊር አልጾምም ካለ ራሱን ችሎ ጌታውን ያምጽ እንጂ ሙስሊም የሆነና የጾምን ግዴታነት የሚያምን ሰው የረመዷንን ክብር የማይጠብቁ ሰዎችን ሊተባበርና ምግብ ሊያቀርብላቸው አይገባም፡፡
ለዚህም ነው በዘመናችን የሚገኙ በርካታ ሊቃውንትና የፈትዋ ተቋማትም ጭምር “ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍል ጊዜ ውስጥ ምግብ ቤቶችን መዝጋት ግዴታ ነው” የሚሉ ፈትዋዎችን የሰጡት፡፡
የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች፣ ሱፐር ማርኬትና ዳቦ ቤቶችም ቢሆን እየሸጡለት ያለው ግለሰብ ጾምን ለመተው በቂ ምክንያት የሌለው ከመሆኑ ጋር ቀን ላይ ሊበላው እንደሆነ ከሁኔታው ካወቁ ወይም በአመዛኙ ከገመቱ ለርሱ መሸጥ አይፈቀድላቸውም፡፡
ያ ዐብደላህ፥ ሪዝቅ የሚሰጠው አላህ ነው፤ እሱን እያመጹ የሚገኝ ገቢ በረካም አይኖረውም፡፡
የሥራ ዘርፍ መቀየር ወይም ደግሞ ረመዷን ላይ ማምሻውን ብቻ በመስራት በትንሹ መብቃቃትና ወንጀለኛ የማያደርጉ የግብይት ዓይነቶችን ብቻ እየለዩ መጠቀም (ቀን ላይ ለማይመገቡት፣ ለሕፃናትና በበቂ ምክንያት መጾም ግዴታ ለማይሆንባቸው ብቻ መሸጥ) መሰል መፍትሄዎችን መጠቀም ይገባል፡፡
ምን ችግር አለው!? ሀገራችን ላይ የተለመደ ተግባር ነው! ታድያ ድሃ ምን ሰርቶ ይብላ/ እንዴት ይኑር? እኛ ሃገር ላይ ይህን ማድረግ ይከብዳል... ወዘተ ማለት አላህ ዘንድ ከመጠየቅ አያድኑም፡፡
“እኔን ምን አገባኝ? ሁሉም በስራው እራሱ ነው የሚጠየቀው” የሚል የአላዋቂ ንግግር የሚናገሩ ሰዎችም አሉ! ከላይ እንደተገለጸው ረመዷን ቀን ላይ ያለበቂ ምክንያት መብላት ከዝሙትና መሰል ወንጀሎች የከፋ ተግባር ነው፤ ታድያ ዝሙት ለሚሰራ ሰው ሁኔታዎችን ማመቻቸት ምንም ችግር የለውም ማለት ነው?! ሱብሓነላህ! አላህ በተከበረው ቃሉ የሚከተለውን ብሏል፥
(وَتَعَاوَنُواْ عَلَى ٱلۡبِرِّ وَٱلتَّقۡوَىٰۖ وَلَا تَعَاوَنُواْ عَلَى ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ 2 ) [المائدة: 2]
“በመልካም ስራና ወንጀልን በማስወገድ (አላህን በመፍራት) ተባበሩ፤ በወንጀልና ወሰን በማለፍ አትተባበሩ፤ አላህ ቅጣቱ ብርቱ ነውና” አል ማኢዳህ፡ 2፡፡
ይህን መልእክት ለሚመለከታቸው ሁሉ በማድረስም በመልካም የማዘዝና መጥፎን የማውገዝ ግዴታ እንወጣ፡፡
ረመዷን 20/1447 ዓ.ሂ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍13
قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5