قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
9.39K subscribers
523 photos
530 videos
12 files
1.28K links
قال رسول الله ﷺ: " إِذَا مَرَرْتُمْ بِرِيَاضِ الْجَنَّةِ ؛ فَارْتَعُوا ...

أسأل الله أن ينفع بالقناة ويتقبل منا
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌙 ​የረመዳን አጋማሽ 🥹

• ​የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እነሆ የረመዳን ወር አጋማሽ ላይ ደርሷል። ከእናንተ መካከል በዚህ ወር ውስጥ ራሱን የፈተሸና የቀና ማን አለ?

• ​በዚህ ወር የሚገባውን ክብር የሰጠውና መብቱን ያወቀ ማን አለ? እነሆ ወራችሁ መጉደል (ማለቅ) ጀምሯል፤ ስለዚህ በበጎ ስራዎች ላይ በርቱ።

• ​ወሩ ሊጠናቀቅ እንደሆነ ሁሉ፣ እያንዳንዱ ወር መጨረሻ አለው። ለሌሎች ወራት ምትክ ሊኖር ይችላል፤ ለረመዳን ግን ምትክ ከየት ይገኛል?

• ​ወሩ አጋማሽ ላይ ደርሷል ፣ መልካምን ስሩ ፤ በጀነቶችም ውስጥ ድልን የሚቀዳጁት በርትተው ያገለገሉ (የሰሩ) ናቸው።

• ​እንደ እኔ አይነቱ ዘንጊና ምስኪን ግን በሀዘን ተሰብሯል፤ ዋይ ለርሱ! ከዚህ ትልቅ እድል መታረሙ ምንኛ ከባድ ነው።

•​በመዝራት ወቅት ዘር ያመለጠው ሰው፣ ከመጸጸትና ከሀዘን ውጭ ምን ሊያጭድ ይችላል?

•​በዚህ ወር ውስጥ አላህን በመፍራት (ተቅዋ) የነገደና የአላህ ገመድ አጥብቆ የያዘ ሰው ምንኛ የታደለ ነው!

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍11
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌙 የረመዷን ቀናት እና የሰው ልጅ እድሜ 🥹

• ​"ረመዳን በብዙ መልኩ ከሰው ልጅ ሕይወት ጋር ይመሳሰላል፤ በመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት እንደ ልጅነት ሕይወት መጀመሪያ በደስታ፣ በንቃት፣ በተስፋና በጉጉት የተሞላ ነው። በሁለተኛዎቹ አስር ቀናት ደግሞ ልክ እንደ ወጣትነት ዕድሜ በጨዋታና በዝንጋቴ ይታለፋል። በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ግን እድሜው እንደገፋ ሽማግሌ ይሆናል፤ በዚህ ወቅት በርትቶ የሰራ ይረታል (ያተርፋል)፣ ቸል ያለ ደግሞ ይቆጫል።"

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍29
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⛓ነቢዩ {📿} እንዲህ ብለዋል፦

"በረመዳን ወር አራት ነገሮችን አብዙ፤ ሁለቱ ጌታችሁን የምታስደስቱባቸው ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ እናንተ በጭራሽ የማትበቃቁባቸው (የምትፈልጓቸው) ናቸው።"

​1️⃣. ጌታችሁን የምታስደስቱባቸው፦

🟠 ​ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ አምላክ የለም ብሎ መመስከር 〔ላ ኢላሀ ኢለላህ〕 ማለት

🟠ምሕረትን መለመን {አስቲግፋር}

​2️⃣. እናንተ የማትበቃቁባቸው (ሁልጊዜም የምትፈልጓቸው)፦

🟠አላህን ጀነትን መለመን

🟠ከእሳት (ከጀሀነም) በአላህ መጠበቅ

⬅️ @TewhedandSuna ➡️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍27🏆3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌙በለይለቱል ቀድር ሌሊት ምን መደረግ አለበት❕

⏰️ ​በዚህ ታላቅ ሌሊት ሊከናወኑ የሚገቡ አራት ዋና ዋና ተግባራት፦

•​መስገድ (ቂያሙለይል)፦ "ለይለቱል ቀድርን አምኖና ከአላህ ምንዳን ፈልጎ የሰገደ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"

•​በመስጂድ መቆየት (ኢዕቲካፍ)፦ በዚህች ሌሊት በመስጂዶች ውስጥ ተገልሎ አምልኮን ማብዛት የተወደደ ተግባር ነው።

•​ዱዓ ማድረግ፦ አይሻ (ረ.ዐ) "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ለይለቱል ቀድር ካገኘው ምን ልበል?" ብለው ሲጠይቁ፤ እሳቸውም፦ "አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሒቡል ዓፍወ ፈዕፉ ዓኒ" (ጌታዬ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፣ ይቅርታንም ትወዳለህና ይቅር በለኝ) በይ አሏቸው።

•​ቁርዓን መቅራት፦ በተለይ በዚህች ሌሊት ቁርዓንን በብዛት መቅራት እጅግ አስፈላጊ ነው።

​እነዚህን አራት ተግባራት በመፈጸም ቢዚ መሆን ፤ ከሌሎች ስራዎች ሁሉ በላጭና የተመረጡ ናቸውና።

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍16
🌙 የረመዷን ቀናቶች ላይ ምግብና መጠጥ መሸጥ ይቻላልን?
حكم بيع الطعام والشراب في نهار رمضان لغير معذور


الحمد لله، والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه أجمعين، أما بعد:
يحرم بيع الطعام والشراب وكذا منحه بلا مقابل في نهار رمضان لغير معذور في ترك صومه، لما في ذلك من تسبب في المعصية، وانتهاك لحرمة الشهر، وقد نص على ذلك فقهاء الشافعية وغيرهم.

ረመዷንን መጾም የኢስላም አንዱ መሰረት ነው፡፡ የመጾም አቅም ያለው፣ ለአካለ መጠን የደረሰ፣ ጉዞ ላይ ያልሆነ፣ አካልና አዕምሮው ጤነኛ የሆነና ጾምን የሚከለክሉ ሁኔታዎች ላይ ያልሆነ ሰው ላይ በሙሉ ረመዷንን መጾም ግዴታ ነው፡፡
የረመዷንን ወር መጾም ግዴታነት የነቢዩ ሙሐመድ  ﷺ ተከታዮች ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ይልቅ ከዚህ ቀደም ያለፉ የነቢያት ተከታዮች ላይም ጭምር ግዴታ ነበር፡፡

(يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ كُتِبَ عَلَيۡكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ 183 ) [البقرة: 183]

“እናንተ አማኞች ሆይ እናንተ ላይ ጾም ግዴታ ተደረገ፤ ልክ እነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ ግዴታ እንደተደረገው ሁሉ...” አልበቀረህ፡183፡፡

የተፍሲር ሊቃውንት እንደገለጹት የነቢዩ ዒሳ (ዐለይሂስ_ሰላም) ተከታዮችም ጭምር ይጾሙ የነበረው ረመዷንን ወር ላይ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ነው በተለያዩ ምክንያቶች ወሩ ላይ ቀናትን እየጨመሩ ጾማቸው ይዘቱን ለቆ አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ የደረሰው፡፡

ይህን ከጥንት ጀምሮ የተከበረን የጾም ወር በቂና ተቀባይነት ያለው ምክንያት (ኡዝር) ሳይኖር መጾሙን ትቶ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ መብላትና መጠጣት ዝሙት ከመስራት፣ አስካሪ መጠጥ ከመጠጣትና ከቁማር የከፋ ወንጀል መሆኑን አል ኢማም አዝዘሀቢ (አልከባኢር) ላይ ገልጸዋል፡፡

ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ምግብ/ሻይ ቤት፣ ካፍቴሪያ ወዘተ ከፍተው መደበኛ ሥራቸውን የሚሰሩ፣ የመንገዶች ዳርና ዳር ላይ የጀበና ቡና/ ሻይና ዳቦ ወዘተ ቀለል ያሉ ምግቦችን የሚሸጡ ሙስሊሞችን እናያለን!!  ተመጋቢው ማንም ይሁን ማን ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ይህን ማድረጉ በኢስላም የማይፈቀድ ተግባር መሆኑንና ከዚህ የሚገኘው ገቢም ሐላል እንደማይሆን ማወቅ ይገባል!

አል ኢማም ሸምሱዲን አርረምሊ “ሚንሃጅ አጥጣሊቢን” የተሰኘውን የኢማም አንነወዊይ ታዋቂ የሻፊዒየህ መዝሀብ የፊቅህ ኪታብ ሲተነትኑ “ኒሃየቱል ሙሕታጅ” ላይ የሚከተለውን ብለዋል፥  
‌قال العلامة شمس الدين الرملي: "...وَمِثْلُ ‌ذَلِكَ ‌إطْعَامُ ‌مُسْلِمٍ مُكَلَّفٍ كَافِرًا مُكَلَّفًا فِي نَهَارِ رَمَضَانَ، وَكَذَا بَيْعُهُ طَعَامًا عَلِمَ أَوْ ظَنَّ أَنَّهُ يَأْكُلُهُ نَهَارًا كَمَا أَفْتَى بِهِ الْوَالِدُ - رَحِمَهُ اللَّهُ تَعَالَى -؛ لِأَنَّ كُلًّا مِنْ ذَلِكَ تَسَبُّبٌ فِي الْمَعْصِيَةِ وَإِعَانَةٌ عَلَيْهَا..." نهاية المحتاج: (3/182)

“የሙዚቃ መሳሪያን ለዘፋኝ፣ የሐር ጨርቅን ወንድ ልጅ ሊለብሰው፣ የጦር መሳሪያን ለሽፍታ ወዘተ መሸጥ እንደማይቻለው ሁሉ ሙስሊም የሆነ ሰው አንድን በአላህ የማያምን ሰው (ካፊርን) ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ምግብ ሊያበላና እንዲሁም ቀን ላይ ሊበላው እንደሚችል እያወቀ ወይም እየገመተ ሊሸጥለት አይገባም (መሸጥ አይቻልም!) ... ምክንያቱም ይህን ማድረግ አላህ እንዲታመፅ መንስኤ መሆንና ይህም ላይ ማገዝን ስለሚያስከትል ነው” ኒሃየቱል ሙሕታጅ፡ 3/182፡፡

ያለበቂ ምክንያት የተከበረውን ረመዷን የማይጾምን ማንኛውንም ሰው (ሙስሊምም የሚባል ይሁን ካፊር) የጾም ቀን ላይ በመጋበዝም ይሁን ምግብ በመሸጥ ማብላትና ማጠጣት አላህን ማስቆጣትና እርሱን የሚያምጹ ሰዎችን መተባበር ስለሚሆን ወንጀልና ከሙስሊም የማይጠበቅ ተግባር ነው፡፡
ስለዚህም ቀን ላይ የሆነ ሥራ የሚያሰሩት ያለበቂ ምክንያት የማይጾም ሰራተኛም ይሁን፣ የምግብ እርዳታ ሽቶ ቤት እያንኳኳ የሚጠይቅ አቅመ ደካማም ይሁን ረመዷን ቀን ላይ እንዲበላ መተባበርና ምግብ ማቀበል ወንጀል ነው፡፡
ይበልጥ ወንጀሉ ድርብርብ የሚሆነው ደግሞ የተከበረው ረመዷን ወር ላይ ሥራዬ ብሎ ምግብ/ሻይ ቤት ከፍቶ እንዴትኛውም ወርና ጊዜ ቀን ላይ ምግብ እየሸጡና የመጣውን ሁሉ እየመገቡ መዋል ነውና ሙስሊም ሆይ ከዚህ ነውርና ፍጹም ከሙስሊም ከማይጠበቅ ተግባር ተጠንቀቅ/ቂ!!

ካፊር አልጾምም ካለ ራሱን ችሎ ጌታውን ያምጽ እንጂ ሙስሊም የሆነና የጾምን ግዴታነት የሚያምን ሰው የረመዷንን ክብር የማይጠብቁ ሰዎችን ሊተባበርና ምግብ ሊያቀርብላቸው አይገባም፡፡
ለዚህም ነው በዘመናችን የሚገኙ በርካታ ሊቃውንትና የፈትዋ ተቋማትም ጭምር “ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍል ጊዜ ውስጥ ምግብ ቤቶችን መዝጋት ግዴታ ነው” የሚሉ ፈትዋዎችን የሰጡት፡፡

የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች፣ ሱፐር ማርኬትና ዳቦ ቤቶችም ቢሆን እየሸጡለት ያለው ግለሰብ ጾምን ለመተው በቂ ምክንያት የሌለው ከመሆኑ ጋር ቀን ላይ ሊበላው እንደሆነ ከሁኔታው ካወቁ ወይም በአመዛኙ ከገመቱ ለርሱ መሸጥ አይፈቀድላቸውም፡፡

ያ ዐብደላህ፥ ሪዝቅ የሚሰጠው አላህ ነው፤ እሱን እያመጹ የሚገኝ ገቢ በረካም አይኖረውም፡፡
የሥራ ዘርፍ መቀየር ወይም ደግሞ ረመዷን ላይ ማምሻውን ብቻ በመስራት በትንሹ መብቃቃትና ወንጀለኛ የማያደርጉ የግብይት ዓይነቶችን ብቻ እየለዩ መጠቀም (ቀን ላይ ለማይመገቡት፣ ለሕፃናትና በበቂ ምክንያት መጾም ግዴታ ለማይሆንባቸው ብቻ መሸጥ) መሰል መፍትሄዎችን መጠቀም ይገባል፡፡

ምን ችግር አለው!? ሀገራችን ላይ የተለመደ ተግባር ነው! ታድያ ድሃ ምን ሰርቶ ይብላ/ እንዴት ይኑር? እኛ ሃገር ላይ ይህን ማድረግ ይከብዳል... ወዘተ ማለት አላህ ዘንድ ከመጠየቅ አያድኑም፡፡

“እኔን ምን አገባኝ? ሁሉም በስራው እራሱ ነው የሚጠየቀው” የሚል የአላዋቂ ንግግር የሚናገሩ ሰዎችም አሉ! ከላይ እንደተገለጸው ረመዷን ቀን ላይ ያለበቂ ምክንያት መብላት ከዝሙትና መሰል ወንጀሎች የከፋ ተግባር ነው፤ ታድያ ዝሙት ለሚሰራ ሰው ሁኔታዎችን ማመቻቸት ምንም ችግር የለውም ማለት ነው?! ሱብሓነላህ!  አላህ በተከበረው ቃሉ የሚከተለውን ብሏል፥

(وَتَعَاوَنُواْ عَلَى ٱلۡبِرِّ وَٱلتَّقۡوَىٰۖ وَلَا تَعَاوَنُواْ عَلَى ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ 2 ) [المائدة: 2]

“በመልካም ስራና ወንጀልን በማስወገድ (አላህን በመፍራት) ተባበሩ፤ በወንጀልና ወሰን በማለፍ አትተባበሩ፤ አላህ ቅጣቱ ብርቱ ነውና” አል ማኢዳህ፡ 2፡፡

ይህን መልእክት ለሚመለከታቸው ሁሉ በማድረስም በመልካም የማዘዝና መጥፎን የማውገዝ ግዴታ እንወጣ፡፡

✍️ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ረመዷን 20/1447 ዓ.ሂ

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍13
🌱When forgiveness is abundant in
Ramadan, the one who misses it
is truly deprived.

«በረመዳን ወር የምህረት ሰበቦች
(ምክንያቶች) በበዙበት ሁኔታ፣ ምህረቱ
ያመለጠው ሰው
በእርግጥም
የመጨረሻው እድለቢስ (የተከለከለ) ነው!»

📱 @TewhedandSuna 🔵
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍10
Audio
مناجاة خاشعة
للقارئ: #فيصل_الهاجري
دعاء ليلة ٢٧
من #ليالي_رمضان ١٤٤٧هـ 🌙

قناة رياض الجنة
👍8
🌱 ነፃ ዑምራ ለመሸለም ኦፊሲያል ኑሱክ አፕ ላይ ተወዳደሩ።

Your chance to win one of 30 free Umrah trips in the Nusuk Challenge 🕋! Use the code to support me, sign up via the link, and start the challenge — your next journey to Umrah could be yours. #NusukApp
https://services.nusuk.sa/app?p=27&id=NG-fPTOnvlR
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የያዝነውን ይዘን ከዱንያ እንወጣለን።


📱 @TewhedandSuna 🔵
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍26
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

• የ1447ኛው ዓ.ሂ የዒድ አል-ፊጥር በዓል መቼ እንደሚከበር ዛሬ ምሽት ይታወቃል!

በዚህም መሰረት፦ 

✅ጨረቃዋ ዛሬ ከታየች፦ ነገ ሐሙስ ደማቁ የዒድ አል-ፊጥር በዓል ይከበራል።

❌ጨረቃዋ ዛሬ ካልታየች፦ የረመዳን ወር 30 ቀናትን ፁመን ዒድ የፊታችን ጁሙዓ ይሆናል።
~
ዛሬ ትኩስና ወቅታዊ የሆኑ የዒድ መረጃዎችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን። እስከዚያው ተከታተሉን!

➡️@TewhedandSuna
➡️@TewhedandSuna
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍10
🌱 ኢድ መቼ ነው ❔

• ዛሬ አመሻሽ ላይ የሸዋል ጨረቃ ከታየች ነገ ሐሙስ ኢድ ይሆናል

• ካልታየች ደግሞ ነገ ፁመን ጁሙዓህ ኢድ እናከብራለን ።

• ኢድ መች እደሆነ ለማወቅ ከናንተ የሚጠበቁው " የጀነት ጨፌ " ቻናልን ተቀላቅሎ መከታተል ብቻ ነው ።

👈 قناة رياض الجنة.
👉〖የጀነት ጨፌ〗                      

╭┈──── ••↯↯↯
╰┈➢🌐@tewhedandsuna ✰••👈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍29
🌱Shawwal 1447 Crescent Search Today

The Shawwal 1447 crescent will be searched for today in Saudi Arabia to determine the day of Eid Al-Fitr 1447.

The result of the moon sighting is expected to be announced around 6:10 PM (Makkah time).

🌱ለሸዋል 1447 የጨረቃ ፍለጋ ዛሬ ይካሄዳል።
​የዒድ አል-ፊጥርን ቀን ለመወሰን በሳዑዲ አረቢያ የሸዋል 1447 የጨረቃ ፍለጋ ዛሬ ይከናወናል። የጨረቃ እይታው ውጤት በመካ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12:10 (6:10 PM) አካባቢ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

👈 قناة رياض الجنة. 
👉〖የጀነት ጨፌ〗                      

╭┈──── ••↯↯↯
╰┈➢🌐@tewhedandsuna ✰••👈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍42
🌱Right now..

• Special coverage to investigate the sight of Hilal Shawal.

#العيد #السعودية

• የሸዋልን ጨረቃ (ሂላል) እይታ ለመከታተል የሚደረግ ልዩ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን።

👈 قناة رياض الجنة. 
👉〖የጀነት ጨፌ〗                      

╭┈──── ••↯↯↯
╰┈➢🌐@tewhedandsuna ✰••👈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
‏مواعيد غروب الشمس اليوم في مراصد المملكة:

‏•مرصد الدمام: 5:50 مساءً
‏•مرصد العيينة: 6:05 مساءً
‏•مرصد تمير: 6:07 مساءً
‏•مرصد حوطة سدير: 6:08 مساءً
‏•مرصد الحريق: 6:05 مساءً
‏•مرصد شقراء: 6:10 مساءً
‏•مرصد بريدة: 6:15 مساءً
‏•مرصد حائل: 6:24 مساءً
‏•مرصد المدينة المنورة: 6:32 مساءً
‏•مرصد مكة المكرمة: 6:32 مساءً
‏•مرصد تبوك: 6:44 مساءً

🌱 በዛሬው ዕለት በሳውዲ አረቢያ ታዋቂ የምልከታ ጣቢያዎች (Observatories) የፀሐይ መግቢያ ሰዓታት የሚከተሉት ናቸው፡

​በሳውዲ አረቢያ የፀሐይ መግቢያ ሰዓታት

• የምልከታ ጣቢያ (Observatory) የፀሐይ መግቢያ ሰዓት (ምሽት)

ደምማም (Dammam) 5:50
አል-ኡየይና (Al-Uyaynah) 6:05
ተሚር (Tumair) 6:07
ሐውጣት ሰዲር (Houtat Sudair) 6:08
አል-ሐሪቅ (Al-Hariq) 6:05
ሸቅራ (Shaqra) 6:10
ቡረይዳህ (Buraidah) 6:15
ሀኢል (Hail) 6:24
መዲና (Madinah) 6:32
መካ (Makkah) 6:32
ታቡክ (Tabuk) 6:44

🚫 ማሳሰቢያ: እነዚህ ሰዓታት እንደየቦታው ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ መጠነኛ ልዩነት አላቸው።


👈 قناة رياض الجنة. 
👉〖የጀነት ጨፌ〗                      

╭┈──── ••↯↯↯
╰┈➢🌐@tewhedandsuna ✰••👈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
‏الآن:

‏خروج جميع لجان الترائي في مناطق المملكة لتحري رؤية هلال عيد الفطر.

• አሁን፡

​የዒድ አል-ፈጥርን ጨረቃ ለመመልከት በሁሉም የሳውዲ አረቢያ ግዛቶች የሚገኙ የጨረቃ ታዛቢ ኮሚቴዎች በሙሉ ወደየመመልከቻ ቦታዎቻቸው ወጥተዋል።

‏
👈 قناة رياض الجنة. 
👉〖የጀነት ጨፌ〗                      

╭┈──── ••↯↯↯
╰┈➢🌐@tewhedandsuna ✰••👈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍46