قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
9.39K subscribers
523 photos
531 videos
12 files
1.28K links
قال رسول الله ﷺ: " إِذَا مَرَرْتُمْ بِرِيَاضِ الْجَنَّةِ ؛ فَارْتَعُوا ...

أسأل الله أن ينفع بالقناة ويتقبل منا
Download Telegram
🌧#የዝናብ እና የንፋስ ወቅት የሚባሉ (ዱዓዎች)

​1. ዝናብ ሲዘንብ

​ اللَّهُمَّ صَيِّبًا نَافِعًا

ትርጉም፦ "አላህ ሆይ! ጠቃሚ ዝናብ አድርገው።"

​2. ዝናቡ ሲበረታ

​ اللَّهُمَّ حَوَالَيْنَا وَلَا عَلَيْنَا

ትርጉም፦ "አላህ ሆይ! በዙሪያችን (በሜዳውና በተራራው) አድርገው እንጂ በእኛ ላይ (ጉዳት በሚያደርስ መልኩ) አታድርገው።"

​3. ዝናብ ዘንቦ ሲያበቃ

​ مُطرْنَا بِفَضْلِ اللَّهِ وَرَحْمَتِهِ

ትርጉም፦ "በአላህ ችሮታና እዝነት ዝናብ ዘነበልን።"

​4. ነጎድጓድ ሲሰማ

​ سُبْحانَ الَّذي يُسَبِّحُ الرَّعْدُ بِحَمْدِهِ وَالمَلائِكَةُ مِنْ خيفَتِهِ

ትርጉም፦ "ያ ነጎድጓድ እሱን እያመሰገነ የሚያጠራው፣ መላእክትም ከእርሱ ፍራቻ የተነሳ የሚያጠሩት (ጌታ) ጥራት ይገባው።"

​5. ንፋስ ሲበረታ

​ اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ خَيْرَهَا، وَخَيْرَ مَا فِيهَا، وَخَيْرَ مَا أُرْسِلَتْ بِهِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّهَا، وَشَرِّ مَا فِيهَا፣ وَشَرِّ مَا أُرْسِلَتْ بِهِ

ትርጉም፦ "አላህ ሆይ! የዚህን ንፋስ መልካም ነገር፣ በውስጡ ያለውን መልካም ነገር እና የተላከበትንም መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ። ከክፉው፣ በውስጡ ካለው ክፉ ነገር እና ለክፉ ከተላከበት ነገር ባንተ እጠበቃለሁ።"

🔵 @TewhedandSuna 🌐
👍38
💧 يقول ابن القيم عن ‎#المطر:

يرسله قطرات منفصلة لا تختلط قطرة منها بأخرى ولا يتقدم متأخرها ولا يتأخر متقدمها
ولا تدرك القطرة صاحبتَها فتمتزج بها،
ولو نزلت دفعة واحدة لتضرر الناس ولأفسدت الزروع والثمار

" فإن كان هذا حسن تدبيره في قطرات المطر فكيف بحسن تدبيره في أمورنا سبحانه؟

• ኢብኑ አል-ቀዪም (አላህ ይዘንላቸውና) ስለ ዝናብ እንዲህ ይላሉ፦

​"አላህ ዝናብን አንዷ ጠብታ ከሌላዋ ጋር ሳትቀላቀል፣ የኋላው ሳይቀድም የፊተኛውም ሳይዘገይ በተናጠል ያወርደዋል። አንዷ ጠብታ ሌላዋን አትደርስባትም (አይጋጩም)፣ አይዋሃዱምም። በአንድ ጊዜ ተከምሮ ቢወርድ ኖሮ ሰዎች ይጎዱ፣ አዝመራና ፍራፍሬዎችም ይወድሙ ነበር።"

​"በዝናብ ጠብታዎች ላይ ያለው የአላህ ጥበብና አመራር (ተድቢር) እንዲህ ካማረ፣ በሕይወታችንና በጉዳዮቻችን ላይ ያለው ጥበቡማ እንዴት ይሆን? ሱብሃነላህ!

•┈┈•┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈┈••┈┈•┈•⊰✿◇✿⊱•┈•┈┈•

• ይህ ንግግር የሚያስተምረን አላህ ለፍጥረታቱ ያለውን ረቂቅ ጥበብ ነው። ዝናብን ጠብታ በጠብታ እንዲወርድ ያደረገው ለጥቅማችን እንደሆነ ሁሉ፣ በሕይወታችን ውስጥ የሚገጥሙን ነገሮችም በጊዜያቸውና በልክ የሚከሰቱት ለእኛ ባለው መልካም ዕቅድ ነው።


🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍42
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አላህ አንድን ሰው ለራህመቱ ስያጨው ... ❕


🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍60
🏪 🏪

⏰️ ጊዜን ለፈጠረ አምላክ እንዴት ጊዜ አይኖርህም ❔

سبحان الله .... ❕
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍93
🌱
የከፋው ሰው ሲሞት የደላው መች ቀረ
ሁሉም ይሞታታል አስጠላም አማረ
ሁሉም ይጓዛታል ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ

ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁላህ

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍66🏆3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌱ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፦

​"አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው፦ 'ሱብሃነላህ' (አላህ ጥራት ይገባው)፣ 'ወልሐምዱሊላህ' (ምስጋና ለአላህ ይሁን)፣ 'ወላ ኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) እና 'ወላሁ አክበር' (አላህ ከሁሉም በላይ ታላቅ ነው)።"

​"እነዚህ ቃላቶች በአላህ ዙፋን (ዐርሽ) ዙሪያ እንደ ንብ ጩኸት ድምፅ አላቸው፤ ባለቤታቸውን (እነዚህን ቃላት የሚለውን ሰው) በአላህ ዘንድ ያስታውሳሉ። ታዲያ ከእናንተ መካከል አላህ ዘንድ የሚያስታውሰው (ስሙን የሚያነሳለት) ነገር እንዲኖረው የማይፈልግ አለን?"

🔵 @TewhedandSuna 🌐
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍55
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍23🏆3
🌱 « ልብ የሰውነት (የአካል) ንጉስ ነው።
ንጉሱ ( መሪው ) ከተስተካከለ ተገዢዎቹ ( ህዝቡ ) ይስተካከላሉ ።»

• ኢብኑ አል-ጀውዚ

🔵 @TewhedandSuna
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍51🏆2
• قَال ابنُ القَيم رَحِمَهُ اللَّه : -

«اللسان يُطلِعُ ما في القلب، شاء صاحبه أم أبى».

- الدَّاءُ وَالدَّوَاء صـ ٣٦٤.📚


• ኢብን አል-ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦

​«ምላስ ባለቤቱ ቢፈልግም ባይፈልግም በልብ ውስጥ ያለውን ነገር አውጥቶ ያሳያል።»

​ምንጭ፦ አዳኡ ወደዋእ፣ ገጽ 364። 📚

🌱 @TewhedandSuna
👍29🏆5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌱 የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

​“ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እናንተ ባትበድሉ (ኃጢአት ባትሰሩ) ኖሮ አላህ እናንተን ያስወግዳችሁ ነበር፤ ከዚያም ኃጢአት የሚሠሩና አላህን ምሕረት የሚለምኑ ሰዎችን ያመጣ ነበር፤ እርሱም ምሕረት ያደርግላቸው ነበር።”

• @TewhedandSuna
👍49🏆6
🌱 አጀል ከደረሰ ሁሉም ነገር ለመግደል ሰበብ ነው።

• @TewhedandSuna
👍45🏆2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌱 በአዳም ሀጢአት ለምን እየሱስ ይሰቀላል ?

• @TewhedandSuna
👍31
🌱 ዱዓእ የችግር ጠላቱ ነው ።
👍52