👍84🏆4
👍80
👍66
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌱 ጀነትም ይሁን ጀሀነም የጊዜ አጠቃቀም ውጤቶች ናቸው ።
👍37
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌱 ስም ማቆላመጥ ?
•ጥያቄ፡- ‘ዐብዱላህ’ የሚለውን ስም ‘ዐቡድ’፣ ወይም ‘ዐብዱራሕማን’ የሚለውን ‘ደሑም’ ብሎ ማቆላመጥ (ማሳነስ) እንዴት ይታያል? ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም?
•መልስ፡- ይህ ይፈቀዳል። ይህ የብዙ ሰዎች ልማድ ነው፤ እንዲያውም የኡለማዎች (ሊቃውንት) ጭምር። ስለዚህ ‘ዐብዱልዐዚዝን’ - ‘ዐዙዝ’፣ ‘ዐብዱልመጂድን’ - ‘መጁድ’ እያሉ ማቆላመጥ ይፈቀዳል።
ምክንያቱም እያቆላመጥክ (እያሳነስክ) ያለኸው የሰውየውን ስም ነው። ክልክል የሆነው የአላህን ስሞች ማሳነስ ነው፤ ይህ በሊቃውንት ስምምነት (ኢጅማዕ) የተከለከለ ነው። ለምሳሌ ከአላህ ስሞች አንዱ የሆነውን ‘አል-ዐዚዝ’ የሚለውን ‘ዐዘይዝ’ (ለአላህ ተብሎ) ቢባል — አላህ ይጠብቀንና — ይህ በፍጹም አይፈቀድም። ነገር ግን የአላህ ባሪያዎችን ስም ማቆላመጥ (ማሳነስ) ይቻላል።
🌱 @TewhedandSuna

👍35🏆3
👍75
👍41
🌱 ፆታ ሲሆን smart ዘር ሲሆን ዘረኛ
• የዘረኝነት ትልቁ ችግር ሰዎች በራሳቸው ባላመጡት ማንነት ላይ ለመመፃደቅ መሞከራቸው አልፎም ሌሎችን አንቋሾ መመልከታቸው ነው፡፡
ብዙዎቻችን ዘር ሲሆን ይህን የዘቀጠ አስተሳሰብ እናስተውላለን፡፡
ነገር ግን አላህ ወደ ሰጠን ፆታ ስንመጣ በራሳችን ያገኘነው ይመስል፤ "ወንድኮ" "ሴትኮ" እያልን እንበሻሸቃለን፡፡
የተሰጠንን ሐላፊነት ከመወጣት ይልቅ በእንቶ ፈንቶ ክርክሮች፣ አላማ ቢስ በሆኑ ፉከራዎች እና መበሻሸቆች ጊዜያችንን እናጠፋለን፡፡
አንድ ሰው እኔ ከሌሎች የተሻለ “የሆነ ነገር” አለኝ ካለ፤ በዛ ነገሩ ሌሎችን ምን ጠቀመ፣ ለራሱስ ምን ተጠቀመ የሚለው እንጂ “አለኝ” እና “ነኝ” ማለቱ ብቻ ጥቅም የለውም፡፡
የተሻለ ነገር ኖሮት ምንም ካልሰራበት ደግሞ ሳይኖረው ከተቀመጠ ሰው የበለጠ ውርደት ላይ ነው፡፡
አላህ በሰጠን ማንነት ከመመፃደቅ ወጥተን ከኛ ምን ይጠበቃል ላይ እንበርታ!!!
© huneynn
• @TewhedandSuna

👍17🏆1
🌱 በ20ዎቹ እድሜ ሁነህ የ50 አመት ሰውዬ
የያዘውን መኪና እና ኑሮ አይተህ ራስህን
የምትጠላ ከሆነ ችግርህ የገንዘብ ሳይሆን
የአእምሮ መቀንጨር ነው!!
ዝም ብለህ ያገኘኸውን ወጥረህ ስራ!
በአሏህ ፍቃድ በቅርቡ ከሱ የተሻለ ትሆናለህ!!
• @TewhedandSuna
የያዘውን መኪና እና ኑሮ አይተህ ራስህን
የምትጠላ ከሆነ ችግርህ የገንዘብ ሳይሆን
የአእምሮ መቀንጨር ነው!!
ዝም ብለህ ያገኘኸውን ወጥረህ ስራ!
በአሏህ ፍቃድ በቅርቡ ከሱ የተሻለ ትሆናለህ!!
• @TewhedandSuna
👍76🏆7
👍32
قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
🌱 በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በኩል ፈትዋ መውሰድ ይቻላል? 🌱 @TewhedandSuna
🌱 በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በኩል ፈትዋ መውሰድ ይቻላል?
መልሱ፦ በሸሪዓዊ ፈትዋዎች ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መመካት የተከለከለ (ሀራም) ነው።
ይህ የሆነው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦
• አንደኛ፦ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ወደ እውቀት ባለቤቶች እንድንመለስ አዞናል። እንዲህም ብሏል፦ “የማታውቁ ከሆናችሁም የእውቀትን ባለቤቶች (አህለ-ዚክር) ጠይቁ።” ትእዛዙ እውቀት ያላቸው ሰዎች ላይ እንድንመለስ እንጂ ወደ ድረ-ገጾች እንድንመለስ አይደለም።
•ሁለተኛ፦ የምንጩ አለመታወቅ (ጅሃለቱል መስደር)። አሁን መረጃ ይሰጥሃል፤ ግን ይህን መረጃ ከየት ነው ያመጣው? የዚህ መረጃ ምንጭ ምንድነው? ከመናፍቃን (ሙብተዲዓ) ድረ-ገጽ ነው? ወይስ ከመናፍቅ ሼህ? ወይስ ከአህለ-ሱና ወል-ጀመዓ ሼህ? የመረጃው ምንጭ አይታወቅም፤ ታዲያ እንዴት ሸሪዓዊ ፈትዋ ከእሱ ትወስዳለህ?
•ሶስተኛ፦ የፈትዋ ብቃት (አህሊያ)፣ ነባራዊ ሁኔታን የመረዳት እና የጠያቂውን ሁኔታ የማወቅ ጉድለት ነው። አንድ አሊም (ሊቅ) የጠያቂውን ሁኔታ ማወቅ አለበት፣ ነባራዊ ሁኔታውንም ማወቅ አለበት። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ይህንን እንዴት ሊያውቅ ይችላል?
•አራተኛ፦ በሙከራዎች እንደተረጋገጠው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አንዳንዴ፣ ይልቁንም ብዙ ጊዜ የተሳሳቱ መረጃዎችን ይሰጣል።
ሼሁ ያጋጠማቸውን ገጠመኝ ሲያወሱ፦
"ነገሩን ለማንሳት ያህል፣ በአንድ ወቅት አውሮፕላን ውስጥ ነበርኩ። አጠገቤ የነበረ ሰው የሶላት ወቅት ገና እንደገባ በአውሮፕላን ውስጥ መስገድ ጀመረ። እኛ ግን የምንጓዝበት ሀገር የሶላቱ ወቅት ሳይወጣ እንደርሳለን።
ለእሱ ግዴታ የነበረበት ሶላቱን እስከ ወቅቱ መጨረሻ ማቆየት ነበር፤ በዚያም ሀገር ሲደርስ ሙሉ ሶላቱን ቂብላን ተቀጣጭቶና ቆሞ መስገድ ይችል ነበር። አሁን ግን (አውሮፕላን ውስጥ በመስገዱ) ቂብላን የመቀጣጨት መስፈርትን እና የመቆም (ቂያም) ግዴታን አጓድሏል።
ጠየቅኩት፦ 'ለምን አሁን ትሰግዳለህ? ገና በወቅቱ መጀመሪያ ላይ ነን፣ ጅዳ አየር ማረፊያ ኢንሻአላህ ወቅቱ ሳይወጣ ደርሰን እንሰግዳለን' አልኩት።
እሱም፦ 'አይ፣ እኔ ፈትዋ ጠይቄ እንዲህ ብለው ነው የመለሱልኝ' አለኝ።
'ፈትዋ የሰጠህ ሰው ማነው?' አልኩት።
እሱም፦ስልኩን አወጣ ከዛ 'ሼህ ጎግል (Google)!' ብሎ መለሰልኝ። እንደምታውቁት ማለት ነው።"

👍21🏆2👌1