قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
9.39K subscribers
523 photos
530 videos
12 files
1.28K links
قال رسول الله ﷺ: " إِذَا مَرَرْتُمْ بِرِيَاضِ الْجَنَّةِ ؛ فَارْتَعُوا ...

أسأل الله أن ينفع بالقناة ويتقبل منا
Download Telegram
🌱

✿ {عِـــــــــيْــــــــدٌكـــم مُــــــبَــــارك}

• عيدكم سعيد

▢ {تقبل الله منا ومنكم  }

✿ እንኳን ለ1447 የዒድ አል_አድሃ በዓል በሰላም አደረሳቹ።

🌱 @TewhedandSuna
👍10
✿ የዒድ በዓል ስነ-ስርዓቶች (آداب العيد)

▢ ​የዒድ ሰላት ስነ-ስርዓቶች (آداب صلاة العيد)

•​ገላን መታጠብና ሽቶ መቀባት፦ ለዒድ ሰላት ገላን መታጠብ፣ ሽቶ መቀባትና በጥሩ/በሚያምር ሁኔታ ተውቦ መውጣት የተወደደ (ሙስተሐብ) ነው።

•​መንገድ መቀየር፦ ሰጋጁ ወደ ዒድ ሰላት በአንድ መንገድ ከሄደ፣ ሲመለስ በሌላ መንገድ መመለሱ የነቢዩ ሱና ነው።

•​ማለዳ መውጣት፦ ከፈጅር ሰላት በኋላ ወደ ዒድ ሰላት ቀድሞ መውጣትና እየተራመዱ (በእግር) መሄድ ሱና ነው።

•​የሰላት ቦታ፦ የዒድ ሰላትን በሜዳ (ክፍት ቦታ) መስገድ ሱና ነው።

•​እጅን ማንሳት፦ ለእያንዳንዱ የዒድ ሰላት ተክቢራ እጅን ወደ ላይ ማንሳት ሱና ነው።

▢ ​የዒድ ቀን ስነ-ስርዓቶች (آداب يوم العيد)

•​እንኳን አደረሳችሁ መባባል፦ በዒድ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ የእንኳን አደረሰህ የደስታ መግለጫ መልእክቶችን መለዋወጥ የተፈቀደ (የተደነገገ) ነው።

•​ተክቢራ ማድረግ፦ ከዙልሒጃ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው የታሽሪቅ ቀን ጀምበር ግባት ድረስ ተክቢራ ማድረግ (አላህን ማክበር) የተደነገገ ነው።

•​ፈቀድ የተደረጉ ነገሮች፦ በዒድ ቀን በተፈቀዱ (ሀላል) በሆኑ የደስታ መግለጫዎች ላይ መሳተፍ ይፈቀዳል። ለምሳሌ፦ የልጆች ጨዋታ፣ የታናናሽ ሴት ልጆች መዝሙር/እንጉርጉሮ እና የመሳሰሉት።

@TewhedandSuna
👍9
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ
ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም – የ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሓ ኹጥባ በስልጥኛ
✿ የ1447 ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሓ ኹጥባ በስልጥኛ

  •  ረቡዕ ዙል-ሒጃህ 10/1447 ዓ.ሂ

🔊 በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

      
✿ ዱንያ ልክ እንደ ጥላ ናት፤
ልትይዛት ብትሮጥ ትሸሻለች፣
ትተሃት ብትሄድ ግን ትከተልሃለች።

🌱 @TewhedandSuna
👍42🏆2
✿ ፍፁም ሊዘለል የማይችል ጉድጓድ ......!

🌱 - @TewhedandSuna
👍52
✿ "እንግዳ እንደሚመጣ አይነት ቤትህን አፅዳ፤ ሞት እንደሚመጣም እያሰብክ ልብህን ንፁህ አድርግ!"

@TewhedandSuna
👍40🏆5👌1
የፈራነው ደረሰ‼
==========
(የጥላቻው ቅስቀሳ ፍሬ አፍርቶ ንጹሃንን መብላት ጀመረ!፣ በሰሚት የተፈጸመው ዘግናኝ የደረሶች ግድያ፣ ዳተኛው መንግስት እና ያንቀላፋው መጅሊስ!)
||
✍️ «የሐሰት ፕሮፓጋንዳና የጥላቻ ቅስቀሳ እሳቱ ሳይጫር ካልጠፋ፣ የየዋሁን አዕምሮ በክሎ ንጹሃንን ይበላል» ስንል የነበረው ጥርጣሬ፣ እነሆ ዛሬ በአዲስ አበባ እምብርት በተግባር ታይቷል!

▫️ ያ በትክክለኛና በፌክ አካውንት ጥላቻን ሲያረባ የነበረው የ"ሞዓ ተዋሕዶ" አክቲቪስት ስብስብ፣ «ቤተ-ክርስቲያን ስደት ላይ ነች» እያለ
በኤአይ (AI) በተቀነባበረና ተዛማጅ ባልሆነ ቪዲዮ ሃገር ሲያምስ የነበረው የሚዲያ ሠራዊት፣ ይህን እብደት ሲያሟሙቅ የነበረው አርቲስትና
የኃይማኖት አባት፣ አክቲቪስትና ሚዲያ... የዘራችሁት የጥላቻ መርዝ ዛሬ አብቦ ደም አፍስሷል።


▫️ ትናንትና ምሽት በአዲስ አበባ ሰሚት አካባቢ፣ ሁለት ሚስኪን ደረሶች/ጥበቃ ላይ የተፈጸመው ድርጊት የሰው ልጅ አዕምሮ ሊሸከመው የማይችል የጭካኔ ጥግ ነው። አረመኔዎቹ ገዳዮች አንደኛውን ደረሳ በገመድ አንቀው ሲገድሉት፣ ሁለተኛውን ደግሞ አንገቱ እስኪቆረጥ ድረስ አርደውታል፤ አልፎ ተርፎም ዓይኖቻቸውን አውጥተው ጥለዋቸዋል!

የክፋታቸውና የጭካኔያቸው ጥግ፣ ከነዚህ ሚስኪን ወንድሞቻችን መካከል የአንዱ ጀናዛ ለትጥበት እንኳ በማይመች ሁኔታ ተቆራርጦ፣ ዛሬ ከዙህር በኋላ በኮልፌ ሙስሊሞች መቃብር በታላቅ ሐዘን ተቀብረዋል። ኢንና ሊላሂ ወ ኢና ኢለይሂ ራጂዑን! አላህ ይዘንላቸው፣ ሐቃቸውን ያውጣላቸው።


➡️ በአርሲ አሰኮ በነበረው የፖለቲካ ግጭት 2 ክርስቲያኖች (1 ሙስሊም አብሮ ሞቶ ሳለ) መገደላቸውን ተከትሎ፣ የሟቾችን ቁጥር ወደ 53 አባዝተው፣ ሀገር ያናወጡ አካላት ዛሬ የት ገቡ⁉️ አርሲ ላይ የ"ዳግማዊ ግራኝ" ትርክት ፈብርከው ሲያላዝኑ የነበሩት፣ ዛሬ በዋና ከተማችን፣ በመንግስት አፍንጫ ስር ይህ ሁሉ ግፍ በሙስሊሙ ላይ ሲፈጸም ለምን ቋንቋቸው ተዘጋ⁉️ የሙስሊም ደም ሲፈስ ብቻ ዝምታ የሚመርጠው ሚዛናዊ መሳይ አስመሳይ ሁሉ ዛሬ ጥጉን ይዟል!


🔸 ይህ እብደት በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በአማራ ክልል፤ በጎንደር እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎችና ከተማው ላይ፣ እንዲሁም በደሴ "ሰላማዊ ሰልፍ" እና "የህሊና ጸሎት" በሚል ሽፋን የጥፋት ኃይሎችን በማደራጀት ሙስሊሙን ለመዝረፍና ለመግደል የታቀደ አደገኛ እንቅስቃሴ አለ፤ በተደጋጋሚ ለማክሸፍ እየተሞከረ ቢሆንም አጥጋቢና ተገቢ እርምጃ አልተወሰደም።


🪧 መንግስት እያየ ዝም ያለው ለምንድን ነው⁉️ አገርን ወደ እርስ በርስ የሃይማኖት ጦርነት ሊያስገቡ የተዘጋጁትን ግጭት ጠማቂዎች፣ ከነ ሰንሰለታቸው ለምን ለህግ አያቀርብም? የሰላማዊውን ዜጋ ደህንነት ማስጠበቅ የመንግስት ቁጥር አንድ ግዴታ አይደለም ወይ?


⬅️ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ በሰሚት የተፈጸመውን የሽብር ተግባር በአስቸኳይ አጣርቶ፣ እነዚህን አረመኔ ገዳዮች በካሜራ ፊት ለህዝብ ሊያቀርብና ፍትህ ሊሰጥ ይገባል!


➡️ ከሁሉ በላይ ልብ የሚያደማው ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ሞት መሰል ዝምታ ነው! ሙስሊሙ በአርሲ ሲገደል "አላህ ይማራቸው" ብሎ መግለጫ ማውጣት ያቃተው መጅሊስ፣ ዛሬ አዲስ አበባ እምብርት ላይ ደረሶች ታርደው አይናቸው ሲወጣ ምን እየጠበቀ ነው⁉️ አሁንም ኢሰመኮ እውነታውን እስኪነግረን እየጠበቅን ነው⁉️


🪶 ጀናዛው ዛሬ በኮልፌ ሲቀበር የመጅሊስ አመራሮች የት ነበሩ? የሙስሊሙ ህልውና አደጋ ላይ ወድቆ፣ ጽንፈኞች በየመንገዱ ደማችንን
እያፈሰሱ፣ መጅሊስ እስካሁን ያንቀላፋው ለምንድን ነው? የሙስሊም ተቋም የተቋቋመው ለወንበሩ ነው ወይስ ለኡማው?


🌐 ሙስሊሙ ለሌላው ሲያለቅስ፣ የራሱ ደም እንደ ርካሽ ውሃ የሚፈስበት፣ እንዲሁም የተረጨው የጥላቻ መርዝ ወደ ተግባር ተቀይሮ እኛኑ እየበላን በዝምታ የምናልፍበት ጊዜ አብቅቷል!

መንግስት የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ኃላፊነቱን በአፋጣኝ ሊወጣ፣ ገዳዮችን ለፍርድ ሊያቀርብ፣ እና ብጥብጥ ቀስቃሾችን በቁጥጥር ስር ሊያውል ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን፣ ነገሩ ጫፍ አልፏል፤ የሙስሊሙም ትዕግስት ተፈትኗል!

ፍትሕ በሰሚት ለታረዱት ደረሶች! የጥላቻና የደም ነጋዴዎች ለፍርድ ይቅረቡ!

#StopHateSpeech #Islamophobia #Ethiopia

(ይህን ዘግናኝ እውነታ እና የፍትህ ጥሪ ለሁሉም በማጋራት (Share በማድረግ) የሟች ወንድሞቻችን ድምጽ እንሁን!)

||
t.me/MuradTadesse
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍23
✿ ወዳጄ የሰው ልጅ ልክ እንደ ተራራ ነው …

ጥንካሬው በማይታየው ድብቅ ማንነቱ ውስጥ ነው ያለው። ጂኦሎጂስቶች እንደሚሉት “አንድ ተራራ ከሙሉ መጠኑ አንድ ሦስተኛ ክፍሉ ብቻ ነው ለኛ የሚታየን። ሁለት ሦስተኛው ክፍሉ ከመሬት ስር የተቀበረ ነው።

 እኛም እንዲሁ ነን!
የምንደብቀው ማንነታችን  ከምናሳየው በላይ ነው። በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ተቀበለውም ካደው፣ደበቀውም ይፋ አወጣው፤ የተዳፈነ ህመም አለው! ከላይ በምታየው ብቻ ተንተርሰህ ፍርድ ለመስጠት አትቸኩል፤ ነገሮች ለኛ መስለው እንደሚታዩን አይደሉም!

በሰላማዊ ሕይወቱ የምትቀናበት የተረጋጋ ሚመስልህ ሰው፤ በልቡ ውስጥ አላህ ብቻ የሚያውቀው ነበልባል እሳት ሊኖር ይችላል።
ጭስ ስላልወጣው፣እየተቃጠለ አይደለም ማለት አይቻልም !!!!


🌱 @TewhedandSuna
👍27
✿ «የአንዳንድ ሰዎች ጭንቅላት
ከፀጉር አስተካካይ ውጭ፤ ማንም አይጠቀምበትም‼»

🌱 @TewhedandSuna
👍19
✿ የቂያማ ቀን ቅሬታችንን ለአላህ እናቀርባለን!

እኛ ትዳርን ፈልገን ነበር! ነገር ግን ሴቶቹ መስፈርታቸው ገንዘብና መኖሪያ እንጂ ዲን እና ስነ-መግባር አልነበረም! ብለን ምንም ሳናስቀር ሁሉንም ለአላህ እንናገራለን።👐🏻

▢ ከላጤዎች መንደር

🌱 @TewhedandSuna
👍37