قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
9.39K subscribers
523 photos
530 videos
12 files
1.28K links
قال رسول الله ﷺ: " إِذَا مَرَرْتُمْ بِرِيَاضِ الْجَنَّةِ ؛ فَارْتَعُوا ...

أسأل الله أن ينفع بالقناة ويتقبل منا
Download Telegram
✿ ፍፁም ሊዘለል የማይችል ጉድጓድ ......!

🌱 - @TewhedandSuna
👍52
✿ "እንግዳ እንደሚመጣ አይነት ቤትህን አፅዳ፤ ሞት እንደሚመጣም እያሰብክ ልብህን ንፁህ አድርግ!"

@TewhedandSuna
👍40🏆5👌1
የፈራነው ደረሰ‼
==========
(የጥላቻው ቅስቀሳ ፍሬ አፍርቶ ንጹሃንን መብላት ጀመረ!፣ በሰሚት የተፈጸመው ዘግናኝ የደረሶች ግድያ፣ ዳተኛው መንግስት እና ያንቀላፋው መጅሊስ!)
||
✍️ «የሐሰት ፕሮፓጋንዳና የጥላቻ ቅስቀሳ እሳቱ ሳይጫር ካልጠፋ፣ የየዋሁን አዕምሮ በክሎ ንጹሃንን ይበላል» ስንል የነበረው ጥርጣሬ፣ እነሆ ዛሬ በአዲስ አበባ እምብርት በተግባር ታይቷል!

▫️ ያ በትክክለኛና በፌክ አካውንት ጥላቻን ሲያረባ የነበረው የ"ሞዓ ተዋሕዶ" አክቲቪስት ስብስብ፣ «ቤተ-ክርስቲያን ስደት ላይ ነች» እያለ
በኤአይ (AI) በተቀነባበረና ተዛማጅ ባልሆነ ቪዲዮ ሃገር ሲያምስ የነበረው የሚዲያ ሠራዊት፣ ይህን እብደት ሲያሟሙቅ የነበረው አርቲስትና
የኃይማኖት አባት፣ አክቲቪስትና ሚዲያ... የዘራችሁት የጥላቻ መርዝ ዛሬ አብቦ ደም አፍስሷል።


▫️ ትናንትና ምሽት በአዲስ አበባ ሰሚት አካባቢ፣ ሁለት ሚስኪን ደረሶች/ጥበቃ ላይ የተፈጸመው ድርጊት የሰው ልጅ አዕምሮ ሊሸከመው የማይችል የጭካኔ ጥግ ነው። አረመኔዎቹ ገዳዮች አንደኛውን ደረሳ በገመድ አንቀው ሲገድሉት፣ ሁለተኛውን ደግሞ አንገቱ እስኪቆረጥ ድረስ አርደውታል፤ አልፎ ተርፎም ዓይኖቻቸውን አውጥተው ጥለዋቸዋል!

የክፋታቸውና የጭካኔያቸው ጥግ፣ ከነዚህ ሚስኪን ወንድሞቻችን መካከል የአንዱ ጀናዛ ለትጥበት እንኳ በማይመች ሁኔታ ተቆራርጦ፣ ዛሬ ከዙህር በኋላ በኮልፌ ሙስሊሞች መቃብር በታላቅ ሐዘን ተቀብረዋል። ኢንና ሊላሂ ወ ኢና ኢለይሂ ራጂዑን! አላህ ይዘንላቸው፣ ሐቃቸውን ያውጣላቸው።


➡️ በአርሲ አሰኮ በነበረው የፖለቲካ ግጭት 2 ክርስቲያኖች (1 ሙስሊም አብሮ ሞቶ ሳለ) መገደላቸውን ተከትሎ፣ የሟቾችን ቁጥር ወደ 53 አባዝተው፣ ሀገር ያናወጡ አካላት ዛሬ የት ገቡ⁉️ አርሲ ላይ የ"ዳግማዊ ግራኝ" ትርክት ፈብርከው ሲያላዝኑ የነበሩት፣ ዛሬ በዋና ከተማችን፣ በመንግስት አፍንጫ ስር ይህ ሁሉ ግፍ በሙስሊሙ ላይ ሲፈጸም ለምን ቋንቋቸው ተዘጋ⁉️ የሙስሊም ደም ሲፈስ ብቻ ዝምታ የሚመርጠው ሚዛናዊ መሳይ አስመሳይ ሁሉ ዛሬ ጥጉን ይዟል!


🔸 ይህ እብደት በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በአማራ ክልል፤ በጎንደር እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎችና ከተማው ላይ፣ እንዲሁም በደሴ "ሰላማዊ ሰልፍ" እና "የህሊና ጸሎት" በሚል ሽፋን የጥፋት ኃይሎችን በማደራጀት ሙስሊሙን ለመዝረፍና ለመግደል የታቀደ አደገኛ እንቅስቃሴ አለ፤ በተደጋጋሚ ለማክሸፍ እየተሞከረ ቢሆንም አጥጋቢና ተገቢ እርምጃ አልተወሰደም።


🪧 መንግስት እያየ ዝም ያለው ለምንድን ነው⁉️ አገርን ወደ እርስ በርስ የሃይማኖት ጦርነት ሊያስገቡ የተዘጋጁትን ግጭት ጠማቂዎች፣ ከነ ሰንሰለታቸው ለምን ለህግ አያቀርብም? የሰላማዊውን ዜጋ ደህንነት ማስጠበቅ የመንግስት ቁጥር አንድ ግዴታ አይደለም ወይ?


⬅️ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ በሰሚት የተፈጸመውን የሽብር ተግባር በአስቸኳይ አጣርቶ፣ እነዚህን አረመኔ ገዳዮች በካሜራ ፊት ለህዝብ ሊያቀርብና ፍትህ ሊሰጥ ይገባል!


➡️ ከሁሉ በላይ ልብ የሚያደማው ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ሞት መሰል ዝምታ ነው! ሙስሊሙ በአርሲ ሲገደል "አላህ ይማራቸው" ብሎ መግለጫ ማውጣት ያቃተው መጅሊስ፣ ዛሬ አዲስ አበባ እምብርት ላይ ደረሶች ታርደው አይናቸው ሲወጣ ምን እየጠበቀ ነው⁉️ አሁንም ኢሰመኮ እውነታውን እስኪነግረን እየጠበቅን ነው⁉️


🪶 ጀናዛው ዛሬ በኮልፌ ሲቀበር የመጅሊስ አመራሮች የት ነበሩ? የሙስሊሙ ህልውና አደጋ ላይ ወድቆ፣ ጽንፈኞች በየመንገዱ ደማችንን
እያፈሰሱ፣ መጅሊስ እስካሁን ያንቀላፋው ለምንድን ነው? የሙስሊም ተቋም የተቋቋመው ለወንበሩ ነው ወይስ ለኡማው?


🌐 ሙስሊሙ ለሌላው ሲያለቅስ፣ የራሱ ደም እንደ ርካሽ ውሃ የሚፈስበት፣ እንዲሁም የተረጨው የጥላቻ መርዝ ወደ ተግባር ተቀይሮ እኛኑ እየበላን በዝምታ የምናልፍበት ጊዜ አብቅቷል!

መንግስት የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ኃላፊነቱን በአፋጣኝ ሊወጣ፣ ገዳዮችን ለፍርድ ሊያቀርብ፣ እና ብጥብጥ ቀስቃሾችን በቁጥጥር ስር ሊያውል ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን፣ ነገሩ ጫፍ አልፏል፤ የሙስሊሙም ትዕግስት ተፈትኗል!

ፍትሕ በሰሚት ለታረዱት ደረሶች! የጥላቻና የደም ነጋዴዎች ለፍርድ ይቅረቡ!

#StopHateSpeech #Islamophobia #Ethiopia

(ይህን ዘግናኝ እውነታ እና የፍትህ ጥሪ ለሁሉም በማጋራት (Share በማድረግ) የሟች ወንድሞቻችን ድምጽ እንሁን!)

||
t.me/MuradTadesse
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍23
✿ ወዳጄ የሰው ልጅ ልክ እንደ ተራራ ነው …

ጥንካሬው በማይታየው ድብቅ ማንነቱ ውስጥ ነው ያለው። ጂኦሎጂስቶች እንደሚሉት “አንድ ተራራ ከሙሉ መጠኑ አንድ ሦስተኛ ክፍሉ ብቻ ነው ለኛ የሚታየን። ሁለት ሦስተኛው ክፍሉ ከመሬት ስር የተቀበረ ነው።

 እኛም እንዲሁ ነን!
የምንደብቀው ማንነታችን  ከምናሳየው በላይ ነው። በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ተቀበለውም ካደው፣ደበቀውም ይፋ አወጣው፤ የተዳፈነ ህመም አለው! ከላይ በምታየው ብቻ ተንተርሰህ ፍርድ ለመስጠት አትቸኩል፤ ነገሮች ለኛ መስለው እንደሚታዩን አይደሉም!

በሰላማዊ ሕይወቱ የምትቀናበት የተረጋጋ ሚመስልህ ሰው፤ በልቡ ውስጥ አላህ ብቻ የሚያውቀው ነበልባል እሳት ሊኖር ይችላል።
ጭስ ስላልወጣው፣እየተቃጠለ አይደለም ማለት አይቻልም !!!!


🌱 @TewhedandSuna
👍27
✿ «የአንዳንድ ሰዎች ጭንቅላት
ከፀጉር አስተካካይ ውጭ፤ ማንም አይጠቀምበትም‼»

🌱 @TewhedandSuna
👍19
✿ የቂያማ ቀን ቅሬታችንን ለአላህ እናቀርባለን!

እኛ ትዳርን ፈልገን ነበር! ነገር ግን ሴቶቹ መስፈርታቸው ገንዘብና መኖሪያ እንጂ ዲን እና ስነ-መግባር አልነበረም! ብለን ምንም ሳናስቀር ሁሉንም ለአላህ እንናገራለን።👐🏻

▢ ከላጤዎች መንደር

🌱 @TewhedandSuna
👍37
#السؤال

|[ حكم مشاهدة المباريات الرياضية ]|

‎#الجواب من اللجنة الدائمة للبحوث العلمية والإفتاء :

مباريات كرة القدم التي على مال أو نحوه من جوائز حرام، لكون ذلك قمارا، لأنه لا يجوز أخذ السبق وهو العوض إلا فيما أذن فيه الشرع، وهو المسابقة على الخيل والإبل والرماية، وعلى هذا فحضور المباريات حرام، ومشاهدتها كذلك، لمن علم أنها على عوض، لأن في حضوره لها إقرارا لها .

أما إذا كانت المباراة على غير عوض ولم تشغل عما أوجب الله من الصلاة وغيرها، ولم تشتمل على محظور : ككشف العورات، أو اختلاط النساء بالرجال، أو وجود آلات لهو - فلا حرج فيها ولا في مشاهدتها.

وبالله التوفيق، وصلى الله على نبينا محمد وآله وصحبه وسلم »

📗 [ فتاوى اللجنة الدائمة (15/238) ]
👍3
قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
#السؤال |[ حكم مشاهدة المباريات الرياضية ]| ‎#الجواب من اللجنة الدائمة للبحوث العلمية والإفتاء : مباريات كرة القدم التي على مال أو نحوه من جوائز حرام، لكون ذلك قمارا، لأنه لا يجوز أخذ السبق وهو العوض إلا فيما أذن فيه الشرع، وهو المسابقة على الخيل والإبل…
✿ ጥያቄ

​|[ የስፖርት ውድድሮችን (ግጥሚያዎችን) የመመልከት ብይን ]|

▢ ​መልስ ፦ የፈትዋ ኮሚቴ (اللجنة الدائمة):

• ​በገንዘብ ወይም መሰል ሽልማቶች ላይ የተመሰረቱ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ቁማር በመሆናቸው ምክንያት የተከለከሉ (ሀራም) ናቸው። ምክንያቱም በሸሪዓው ከተፈቀዱት (እንደ ፈረስ ውድድር፣ የግመል ውድድር እና የውርወራ/ቀስት ውድድር) ውጪ በውድድር ላይ ክፍያ ወይም ዋጋ መውሰድ አይፈቀድም። በዚህም መሰረት፣ ውድድሩ በሽልማት (በገንዘብ) ላይ የተመሰረተ መሆኑን እያወቀ በቦታው መገኘትም ሆነ መመልከት የተከለከለ ነው፤ ምክንያቱም በቦታው መገኘቱ ድርጊቱን እንደማጽደቅ (እንደመቀበል) ይቆጠራል።

• ​ነገር ግን ጨዋታው ያለ ምንም ክፍያ (ሽልማት) ከሆነ፣ አላህ ግዴታ ካደረጋቸው ነገሮች (እንደ ሰላት እና መሰል ነገሮች) የማያዘናጋ ከሆነ፣ እና እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮችን ያላካተተ ከሆነ — ለምሳሌ፡ አውራትን መግለጥ፣ የሴቶችና የወንዶች መደባለቅ፣ ወይም የሙዚቃ መሣሪያዎች መገኘት — በጨዋታውም ሆነ እሱን በመመልከት ላይ ምንም ችግር (ሀጢአት) የለበትም።

​ስኬትም ከአላህ ነው፤ የአላህ ሰላትና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይውረድ። »

​📗 [ ፈታዋ አል-ለጅናህ አድ-ዳኢማህ (15/238) ]


🌱 @TewhedandSuna
👍13
✿

ወደፊት የምናደርገው እርምጃ አስቸጋሪ ከሆነ፤ ወደ ኋላ ለመመለስ የምናስበውም ጉዞ ስቃይ የበዛበት ከሆነና እንቅስቃሴያችንን ገታ አድርገን ባለንበት ቦታ ለመቆም አንዳች ችግር የሚፈጥርብን ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርብናል ትላላችሁ?

🌱 @TewhedandSuna
👍11
✿ የቂያማ ቀን የሚሰጥህ መፅሀፍ ደራሲው አንተ ነህ

🌱 @TewhedandSuna
👍34
✿ አንዳንዱ ......

¤ አንዳንዱ መሄድ ስለፈለገ ይሄዳል
አንዳንዱ ደግሞ " እፈልግሃለሁ  " የሚለውን
ለመስማት እሄዳለሁ ይላል።

🌱 @TewhedandSuna
👍33🏆1
✿ ዐቅላችን ትንሽ ነው! ከኛ ዐቅል ያነሰ ዐቅል ካለው ሰው ጋር ከተቀማመጥን፤ ያ ትንሹ ዐቅላችን ይሄዳል።"

-ሹዕባህ
📚روضة العقلاء

¤ @TewhedandSuna
1👍21🏆1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
​"በአላህ እምላለሁ! የውስጤን መጥፎነትና ድብቅ ማንነቴን ቢያውቁ ኖሮ፣ ያገኘኝ ሁሉ ሰላምታ ባልሰጠኝ ነበር።"


​"ከእኔም በራቁ፣ አብሮነቴንም በጠሉ ነበር፤ ከክብርም በኋላ በውርደት በተመለስኩ ነበር።"


​"ነገር ግን አንተ (ጌታዬ) ጉድለቶቼንና መጥፎ ምሳሌዎቼን ሸፈንክልኝ፤ ከስህተቶቼና ከማመፅዎቼም ይቅር አልክኝ።"


​"ስለሆነም ምስጋናና ውዳሴዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ ለአንተ ይሁን፤ በልቦናዬ፣ በአካላቶቼና በምላሴ ጭምር።"



🌱 @TewhedandSuna
👍20🏆2
✿ ውሀ ሻጭ?
   
¤ አንድ ሰው መንገድ ላይ እያዞረም ይሁን፣ ሱቅም ይክፈትለት፣ ሆቴልም ላይ ይደርድረው፣ ትምህርት ቤት፣ መስጂድ፣ ጤና ጣቢያ፣ ሌሎችም ቦታዎች ላይ ውሀን በማቅረብ ገቢ ካገኘ ውሀ ሻጭ ወይም ውሀ ይሸጣል መባሉ ትክክለኛ ስራውን ወይም ገቢውን ይገልፃል፡፡

መንደር ላይ ለዉዱእ በሃይላንድ የሚሸጠውም ሆቴል ላይ በውድ የሚሸጠውም “ውሀ ሸጡ” ነው የሚባለው፡፡ መያዣ እቃው ቢለያይ፣ ማርኬቲንጉ ከፍ እና ዝቅ ቢል፣ የቧንቧም ይሁን የሃይላንድ የተሸጠው ውሀ ነው፡፡ ውሀ!!
   
ወሬው ስለ ውሀ እንዳልሆነ አይጠፋችሁም!!!
   
አንድ ወንድ መስራት እየቻለ መስጂድ ላይ ቆሞም ቢጠይቅ፣ መንገድ ላይ ለማስመጥም ቢሞክር፣ ሚዲያ ላይ አካውንትም ቢለጥፍ፣ ሌላም ስም ይስጠው መስራት እየቻለ ክብሩን አውርዶ እየለመነ ነው፡፡ እየለመነ!!

ቦታው ስለተቀያየረ፣ አጠያየቁ ስላማረ ከልመናነት አይወገድም፡፡ ክብርን ሽጦ ልመና!
   
ሴቷም ብትሆን መንደር ላይም ይሁን፣ ሆቴልም ትሂድ፣ ሚዲያም ላይ በውበቷና ጭፈራ ትውጣ፣ ዋጋው ከፍም ይበል ዝቅ፣ ክብሯን(ሰውነቷን) በመጠቀም ገንዘብ ከሰራች ክብሯን ሽጣለች፡፡

የክብሩ ደረጃ የከፋም ይሁን ሻል ያለ ክብር እና ሐያእ ተሽጧል፡፡ ክብርን ሽጦ ሽቀላ!

©huneynn

🌱 @TewhedandSuna
👍19🏆3
▢ ሁሉም ያልፋል ........

¤ የአንዱ መንገድ ፍፃሜ ለሌላው መንገድ ጅማሮ ነው። በህይወት አበቃ የሚባልለትል ጉዞ የለም።
ገና እንደወጣት ብዙ ያላየናቸውና መኖር ያልጀመርናቸው ውብ የህይወት መልካም አጋጣሚዎች አሉና ታግሰን ንጋታችንን እንጠብቅ።


🌱 @TewhedandSuna
👍33🏆4
✿ ስናለቅስ ....


▢ ዘግተን ስናለቅስ እንዉልና እንባችንን ጠርገን የሚያለቅሱትን ለማጽናናት እንወጣለን።
"በጎ ማስመሰል" ይሏል ይህ ነው።
እንዲያ ካልሆንን ታዲያ ምን ኸይር አለን።



🌱 @TewhedandSuna
👍32
✿ ህይወት መሬት ላይ ተኝተን አልጋ
ላይ በምንነቃበት ጊዜ አስደሳች ነበረች!!

🌱 @TewhedandSuna
👍27
✿ ህይወት......

ነዳጇ ተግባር እንዲሁም
ንፋስ መቆጣጠሪያዋ ተስፋ የሆነች
መርከብ ናት

🌱 @TewhedandSuna
👍19
▢ "لن يصبح سارق المكان مالكاً له مهما فعل"

✿ "የቱንም ያህል ቢጥር ሌባ ባለቤት ሊሆን አይችልም"

#Palestine
👍24🏆5
قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ} pinned «✿ የቂያማ ቀን የሚሰጥህ መፅሀፍ ደራሲው አንተ ነህ 🌱 @TewhedandSuna»