قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
9.39K subscribers
523 photos
530 videos
12 files
1.28K links
قال رسول الله ﷺ: " إِذَا مَرَرْتُمْ بِرِيَاضِ الْجَنَّةِ ؛ فَارْتَعُوا ...

أسأل الله أن ينفع بالقناة ويتقبل منا
Download Telegram
✿ ድሮ ልጅ እያላችሁ «ይህን መሆን
እፈልጋለሁ!!»
ስትሉ የነበረውን ነገር
ሆናችሁ ወይስ ፍላጎታችሁን ቀየራችሁ?!

• ህይወት ከጊዜ ጋር ትለዋወጣለች!!

🌱 @TewhedandSuna
👍35
🌱 ጥብቅ የሳይበር ደህንነት ማስጠንቀቂያ‼
=========================
(ቴሌግራም ላይ የተሰማራው አደገኛው Botnet እና የብልግና ሊንኮች!)
||

✿ ሰሞኑን በቴሌግራም መድረክ ላይ እጅግ አደገኛ እና የተራቀቀ የአካውንት ጠለፋ (Account Takeover) ዘመቻ በስፋት እየተካሄደ ይገኛል። ይህ ጥቃት እንዴት እንደሚሰራ እና እያንዳንዳችንን እንዴት አደጋ ላይ እየጣለን እንደሆነ እውነታውን ላካፍላችሁ።


¹/ ጥቃቱ እንዴት ይሰራል?

•┈┈ አጥቂዎቹ (Hackers) የሚጠቀሙት "Phishing Attack" እና አውቶማቲክ የሆኑ የቴሌግራም Botnets በማጣመር ነው። ስልቱ እንዲህ ነው፦

  • ማጥመጃው (The Bait)፡ የሰውን ልጅ የስነ-ልቦና ድክመት (Social Engineering) ለመጠቀም ሲሉ፣ በጣም ፀያፍ የሆኑ (የብልግና) ምስሎችን ወይም ቪዲዮዎችን ይልካሉ። ከስሩም "ሙሉውን ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ" የሚል ማባበያ (Malicious Link) ያስቀምጣሉ።

• የታመነ ምንጭ (Trusted Sender)፡
ይህ ሊንክ የሚመጣው ከማታውቁት ሰው ብቻ አይደለም! አካውንቱ በጠላፊዎች (Hackers) ቁጥጥር ስር ከዋለ የቅርብ ጓደኛችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ፣ ወይም አብሮ አደጋችሁ ስም ሊመጣ ይችላል።


²/ ሊንኩን ስትነኩት ምን ይፈጠራል?

•┈┈ ሊንኩን ክሊክ ባደረጋችሁበት ቅጽበት In a fraction of a second ሁለት ነገሮች ይፈጠራሉ፦

1】  የቴሌግራም አካውንታችሁን የመቆጣጠር መብት (Access Token/Session Hijacking) ለአጥቂዎቹ አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ።

2】  በስተጀርባ የተጻፈው (Automated Script/Bot) ወዲያውኑ የእናንተን አካውንት በመጠቀም Contacts ላይ ለሚገኙ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች እና አባል ለሆናችሁባቸው ግሩፖች በሙሉ ያንኑ  የብልግና ምስል እና ቫይረስ በእናንተ ስም ያሰራጫል። አንዴ ከተጠለፈ አካውንታችሁን መልሶ ለማግኘት (Account Recovery) እጅግ ፈታኝ ይሆናል።

3】 ከሳይበር አደጋው ባሻገር፣ ይህ ነገር እጅግ ከባድ የሞራል እና የኃይማኖት ቀውስ እያስከተለ ነው። አንዳንዶች በስሜት (Curiosity) አሊያም በድንቁርና ሊንኩን ይከፍቱና፤ ለራሳቸውም ሐራም እያዩ፣ በራሳቸው አካውንት ምክንያት ደግሞ ያንኑ የብልግና ምስል ለብዙ መቶ ንጹሃን ሰዎች (ለቤተሰብ፣ ለኡስታዞች፣ ለወንድም እህቶች) ልከው በቅጽበት ሰውየውንም ሐራም እንዲያይ ያስገድዱታል።

▢ በዲናችን አስተምህሮ፡- "ወንጀልን (ፋሒሻን) ማሰራጨት እና ሰዎችን ወደ ሐራም መጋበዝ ከባድ ቅጣት አለው!" ዛሬ በእናንተ ድክመትና ስግብግብነት የላካችሁት ሊንክ የብዙ ወጣቶችን አዕምሮ ሊበክል፣ ስነ-ልቦና ሊጎዳ እና ትውልድ ሊያበላሽ ይችላል።

★ መፍትሄወ፦

•  አትንኩ! ከማንም ይምጣ ከማን (ከጓደኛም፣ ከዘመድም፣ ከባለቤታችሁም)፣ ፀያፍ ምስል ወይም የሚያጠራጥር ሊንክ (Link) ከተላከላችሁ በፍጹም አትንኩት ወዲያውኑ delete አድርጉት።

•  Two-Step Verification አብሩ: የቴሌግራም ሴኩሪቲያችሁን ለማጠናከር፣ Setting > Privacy and Security > Two-Step Verification ውስጥ በመግባት Password አድርጉበት! ይህ አካውንታችሁ በቀላሉ እንዳይጠለፍ ትልቅ ግድግዳ (Layer of security) ይፈጥራል።

• ያላወቃችሁትን Session አጥፉ: ወደ Setting > Devices ገብታችሁ እናንተ ከምትጠቀሙበት ስልክ ውጪ የሚታይ ሌላ የገባ (Active) አካውንት ካለ "Terminate all other sessions" በማለት ወዲያውኑ አጥፉት።


• የሳይበር ደህንነታችንን መጠበቅ ዲናችንንም፣ ክብራችንንም၊ ማህበራዊ ግንኙነታችንንም መጠበቅ ነው። የብዙዎች ህይወት፣ ትዳር እና ክብር በዚህ አደገኛ ጥቃት ምክንያት እየፈረሰ ነው።


እባካችሁ ንቁ! ለራሳችሁም ሆነ ለሌሎች ጥንቃቄ አድርጉ!


(ይህን ማስጠንቀቂያ Share በማድረግ ወዳጅ ዘመድዎን ከዚህ አደገኛ የሳይበር እና የሞራል ወጥመድ ይታደጉ!)
||

© STEM with Murad

🌱 @TewhedandSuna
👍11
✿ ዝናቡ ካለፈ በኋላ ዣንጥላ ለሁሉም ሰው ሸክም ይሆናል። ጥቅም ሲቆም ታማኝነት የሚያበቃው በዚህ መልኩ ነው። እያንዳንዱ ቅርበት እውነት አይደለም!

🌱 @TewhedandSuna
👍40
✿ አለም አንተን እንዲያይህ ሳይሆን
አለምን ለማየት ተራራውን ውጣ!!

🌱 @TewhedandSuna
👍38
✿ ነፍሴ ሆይ ..... ቀጥ በይ
ምናልባት መዳረሻሽ ተቃርቦ ይሆናል!!               

🌱 @TewhedandSuna
👍55
✿

• በዚህ ዘመን በጊዜ የሚተኛ የለም! አላህ
ያዘነለት ሲቀር ‥
ሁሉም የራሱ የሆነ ለትራሱ
የሚተርከው ታሪክ አለው ታሪኩ ወይ በፈገግታ
ወይ ደግሞ በለቅሶ የሚያልቅ ይሆናል ።                

🌱 @TewhedandSuna
👍57🎉1
▢ ባዶ ሆድ፣ ባዶ ኪስና የተሰበረ ልብ
በህይወትህ ውስጥ ምርጥ የሚባለውን
ትምህርት ያስተምሩሐል!!

🌱 @TewhedandSuna
👍41🏆8
✿ ሐሳቡ የመጣው ከዚህ ነው!

የምኑ ሐሳብ እንዳትሉኝ! ድረሱበት


🌱 @TewhedandSuna
👍41👌7
✿ ሰዎችን ለማሰረዳት ድምፅህን ሳይሆን
አነጋገርህን አሳምር ተክሎችን የሚያጠጣው
ዝናብ እንጂ መብረቅ አይደለም!!

🌱 @TewhedandSuna
👍30
✿ አንዳንድ ሰዎች ሲያስመስሉ የተካኑ ናቸው። ላንተ መጎዳት ምክኒያት ይሆኑና አንተ እንደጎዳሀቸው ያስመስላሉ!

🌱 @TewhedandSuna
👍38👌1
✿ ጌታችን ሆይ ....

• ስራችን ጀነት የሚያስገባ አይደለም። አቅማችንም የጀሐነምን እሳት የሚቋቋም አይደለም። አንተ ድክመታችንን ታውቃለህና በጥበብህ ሙላልን።

ያ ረብ ጀነትህን..

🌱 @TewhedandSuna
👍47👌1
✿ አንተ ከጦርነት ርቀህ
ስለጀግንነት ማውራት በጣም ቀላል ነው

🌱 @TewhedandSuna
👍38
✿ አንዳንዴ ሰዎች እንዲረዱህ እዲያውቁልህ የምትፈልጋቸው ስሜቶች አሉ። ነገር ግን ሚረዳህ ሰው ማታገኝላቸው።
.....ከኖርማል ማንነትህ የሚያስወጡህ ፣ከነበረህ  ባህሪ የሚቀይሩ ቀሽም የሆኑ ስሜቶች

ለሰው ብትነግረውም የማይረዱህ ብቻ አለ አ??
"ሰው ሰውን መረዳት አቆመ ዴ?!" ብለን እስከምናስብ ድረስ

ብቻ አብሽሩልኝ


🌱 @TewhedandSuna
👍30
¤ ለመናገር የማይመቹ
አንዳንድ ስሜቶች አሉ!!

🌱 @TewhedandSuna
🎉19👍6👌4
✿ ይሉኝታ


• ሰዎች አይደሉም ያንተን ማንነት የሚለኩት። ሁሉም በመሰለው መልኩ ይረዳህና ያለህበትን ሁኔታ ይወስናል። ግና እሱ አንተ ያለህበት ሁኔታ ሳይሆን ሰዎች ነህ ብለው የሚያስቡት ነው። መልእክቱ በሰዎች ይሉኝታ ታስረው የሚያስቡትን ነገር ከማድረግ ለተገቱትና ማድረግ የማይፈልጉት ለሚያደርጉ ነው። የሰው ልጅ ምንም ብትሆን ማውራቱ አይቀርም። ስለዚህ ህይወትህ ላይ ትክክለኛ ነገር እስከሆነ ድረስ ለሰዎች አሉባልታ ቦታ እንዳትሰጥ!


🌱 @TewhedandSuna
👍22🏆2
• ሳቅም ሲበዛ የሀዘንን ያህል እንባ ያስፈስሳል ፤ መቀመጥም ሲበዛ የመሥራትን ያህል ያደክማል ፤ ደግነት ሲበዛም እንዲሁ የክፋትን ያህል ይጎዳል ፤ ሁሉን ነገር በመጠን ከያዙት እንኳንስ መልካሙ ክፉውም ይጠቅማል።
-
🌱@TewhedandSuna
👍48👌7🎉3