قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
9.39K subscribers
523 photos
531 videos
12 files
1.28K links
قال رسول الله ﷺ: " إِذَا مَرَرْتُمْ بِرِيَاضِ الْجَنَّةِ ؛ فَارْتَعُوا ...

أسأل الله أن ينفع بالقناة ويتقبل منا
Download Telegram
✿ አንዳንድ ሰዎች ሲያስመስሉ የተካኑ ናቸው። ላንተ መጎዳት ምክኒያት ይሆኑና አንተ እንደጎዳሀቸው ያስመስላሉ!

🌱 @TewhedandSuna
👍38👌1
✿ ጌታችን ሆይ ....

• ስራችን ጀነት የሚያስገባ አይደለም። አቅማችንም የጀሐነምን እሳት የሚቋቋም አይደለም። አንተ ድክመታችንን ታውቃለህና በጥበብህ ሙላልን።

ያ ረብ ጀነትህን..

🌱 @TewhedandSuna
👍47👌1
✿ አንተ ከጦርነት ርቀህ
ስለጀግንነት ማውራት በጣም ቀላል ነው

🌱 @TewhedandSuna
👍38
✿ አንዳንዴ ሰዎች እንዲረዱህ እዲያውቁልህ የምትፈልጋቸው ስሜቶች አሉ። ነገር ግን ሚረዳህ ሰው ማታገኝላቸው።
.....ከኖርማል ማንነትህ የሚያስወጡህ ፣ከነበረህ  ባህሪ የሚቀይሩ ቀሽም የሆኑ ስሜቶች

ለሰው ብትነግረውም የማይረዱህ ብቻ አለ አ??
"ሰው ሰውን መረዳት አቆመ ዴ?!" ብለን እስከምናስብ ድረስ

ብቻ አብሽሩልኝ


🌱 @TewhedandSuna
👍30
¤ ለመናገር የማይመቹ
አንዳንድ ስሜቶች አሉ!!

🌱 @TewhedandSuna
🎉19👍6👌4
✿ ይሉኝታ


• ሰዎች አይደሉም ያንተን ማንነት የሚለኩት። ሁሉም በመሰለው መልኩ ይረዳህና ያለህበትን ሁኔታ ይወስናል። ግና እሱ አንተ ያለህበት ሁኔታ ሳይሆን ሰዎች ነህ ብለው የሚያስቡት ነው። መልእክቱ በሰዎች ይሉኝታ ታስረው የሚያስቡትን ነገር ከማድረግ ለተገቱትና ማድረግ የማይፈልጉት ለሚያደርጉ ነው። የሰው ልጅ ምንም ብትሆን ማውራቱ አይቀርም። ስለዚህ ህይወትህ ላይ ትክክለኛ ነገር እስከሆነ ድረስ ለሰዎች አሉባልታ ቦታ እንዳትሰጥ!


🌱 @TewhedandSuna
👍22🏆2
• ሳቅም ሲበዛ የሀዘንን ያህል እንባ ያስፈስሳል ፤ መቀመጥም ሲበዛ የመሥራትን ያህል ያደክማል ፤ ደግነት ሲበዛም እንዲሁ የክፋትን ያህል ይጎዳል ፤ ሁሉን ነገር በመጠን ከያዙት እንኳንስ መልካሙ ክፉውም ይጠቅማል።
-
🌱@TewhedandSuna
👍49👌7🎉3
✿ ጥበበኛው እንዲህ ይላል፦

• ልክህን በማያውቁ ሰዎች አትከፋ አይነ-ስውር አልማዝን ቢዳብስ ዋጋውን መተመን አይችልምና።

🌱 @TewhedandSuna
👍30👌2
• ግልፅ በሆነ ሀዲስ አንድ ሰው በዝናብ ምክኒያት ከጀመዐ ሰላት መቅረት ይችላል። ግን ለመቅረት ዑዝር ሚሆነው የዝናብ አይነት ልብስ ሚያረጥበውና ወደ መስጂድ ሲሄድ አስቸጋሪ ጭቃ ካለ ነው። ከዛ ውጪ ያለው ቀለል ያለ ዝናብ ከጀመዐ ሰላት ለመቅረት ዑዝር አይሆንም!

-ሸይኽ ዐብድሰላም አሽ'ወይዒር

🌱 @TewhedandSuna
👍44
✿ ከመጀመሪያ ውሸት በኋላ ..

ሁሉም እውነት ጥርጣሬ ይሆናል!

🌱 @TewhedandSuna
👍41🏆5👌1
🪟አባትነት ሚስጥር ነው።

"يقولون الأباء كلام غير مفهوم ثم تشرحه لنا الأيام"

አባቶች በሰዓቱ የማንረዳው የሆነን ቃል ይናግሩናል! ከዚያም ያንን ቃል ጊዜዎች ያብራሩልናል።

🌱 @TewhedandSuna
👍40👌3
🌱 ለወላጆች  መልካም መዋል ታሪክ ነዉ ይላሉ!
አንተ ትፅፈዋለህ ልጆችህ ይዘግቡታል።

✿ @TewhedandSuna
👍23
✿ አንበሳ ምንም ያህል ቢራብ እንኳ ሳር አይበላም... አንተም ልክ እንደ አንበሳው ሁን!
ለውስጣዊ ረሀብህና ስሜትህ ስትል ሰዋዊ ማንነትህን አንዳትለውጥ አደራ......

-------

🌱@TewhedandSuna
👍43
✿ ጀሊሉ

ውሰደን እንዳንል፣ ቅጣትህን ፈራን
አኑረን እንዳንል፣ ኖረንስ ምን ሰራን
                  

ዱዓ ጠፍቶብናል
በፈለከው ምራን

  ኢላሂ


🌱 @TewhedandSuna
👍65👌7
✿ ለሚገጥሙህ ችግሮች ሰበብ የሚሆኑ ግለሰቦች ይኖራሉ ቢሆንም ጉዳዩ በአንተ ላይ ቀድሞ የተፃፈ ነውና ታገስ ለዚህ ችግር ሰበብ ለሆኑብህም መልካም ዱዓእ አድርግ ሁሉም ነገር ባሰብከው ሳይሆን በተወሰነለት ጊዜና ሁኔታ ነው የሚከናወነው

🌱 @TewhedandSuna
👍35
~ተስፋ ካለ አሁንም ሕይወት አለ‼️

• ይህች ያለንባት ሀገረ ዱንያ የተፈጠረችበትን ባህሪዋን ብቻ ነው የምታሳየን፡፡ እኛው በክስተቶቿ እንደመማለን እንታመማለን እንጅ ዱኒያ ከባህሪዋ ውጭ የሆነን አዲስ ነገር ይዛ አልመጣችም፡፡ ዱኒያ ጀነት አይደለችምና አላህ ቀድሞውኑ ይህችን አገር ሲፈጥራት የፈተና፣ የመከራ፣ የበሽታ፣  የስደት፣ የልዩ ልዩና በርካታ መሰናክሎችና ውጣ ውረዶች ዓለም አድርጎ ነው ። ዱንያ የዕድሜ ጥፍጥናዋ በሞት የመረረ፣ ጤናዋ በበሽታ የተበረዘ፣ ደስታዋ በሀዘን ብዛት የደፈረሰ፣ ሰላሟ በጦርነት የተናጋ፣ ምቾቷ ከችግር ያልተላቀቀ፣ ስኬቷ ከውድቀት ጋር የተዳቀለ፣ ችግሯ እልፍ ቀዳዳዋ ሺህ የሆነች ሀገር ናት።
አኑራ የምትገድል፣ አስቃ የምታስለቅስ፣ ሰጥታ የምትነሳ፣  አክብራ የምታዋርድ፣  አገናኝታ የምታለያይ ናት። ዱንያ ትልቁን ስታሳንስ፣ ያመናትን ስትከዳ ግድየላትም፡፡ የሰራላትን ስትገፋ ይሉኝታ የሚባል ነገር አይዛትም፡፡

• ደረጃው ይበላለጥ እንጅ ወደ መሬቷ ውስጥ የገባም ሆነ በላይዋ ላይ የሚኖር ሁሉ ከችግሮቿ ዓይነቶች ቢያንስ በአንዱ ተገርፏል። ሁሉም በፈተናዋ ጉድ አይቷል፤ ከሙሲባዋ« ኡ ኡ ! ገላግሉኝ»ብሏል ። ዱኒያ አልነካህም ብላ ቃል የገባችለት ማንም ሰው የለም። አዎ የለም፡፡

• ታዲያ የዱኒያን ተለዋዋጭ ገፅታ በጥልቀት ያየና  በአትኩሮትም ያስተዋለ ሰው በደረሰበት የዱኒያ ላይ ሙሲባ ምክንያት አይደነግጥም፡፡ ለፈተና መከራዋም እጅ አይሰጥም፡፡ ፈጣሪዉንም አያማርርም።በሚሠራው ሁሉ አላማ ያለውና ምክኒያታዊ የሆነው ጌታችን አላህ ፍርዱም ሆነ ሥራው አድሎ የሌለበት ነዉና በሚሰራው አይጠየቅም፤በሚፈርደውም ቅሬታ አይቀርብበትም። ከሱ በላይ ፍርዱ ያማረ ለባሮቹ  አዛኝ የለምና፤ በደረሱብን ሙሲባዎች ሁሉ ነገራችንን ሁሉ ለሱ ትተን ክፍፍሉን መውደድና ምርጫውን መቀበል ይገባናል። የደረሰብን ሙሲባ የቱን ያህል ቢከፋና ህመሙ ዘልቆ ቢሰማንም እንኳ አላህን ከሚያስደሰት ቃል ውጭ መናገር የለብንም፤ ከሙእሚን ባህሪም መውጣት አይገባንም።

• ማን ያውቃል አዎን ማን ያውቃል! እኛ መጥፎ ሆኖ የታየን መልካም፤ መልካም ሆኖ የታሰበን ደግሞ መጥፎ ሊሆን ይችላል።
ማን ያውቃል ! አላህ የከለከለን እኮ ሊሰጠን፤ የጣለን ሊያነሳን፤ ያዘገየን በሰላም ሊያደርሰን፤ ያላመቻቸልን ቆይቶ ሊሸልመን፤ ያላሣካልንና ሊያሻሽለን ይሆን ይሆናል።አንድ የአላህ ባሪያ ፈጣሪውን ምንጊዜም በጥሩ ነገር ያስባል ይጠረጥራል፤ ፈጣሪውም መልካሙን ጥርጣሬውን ያፀናለታል። ሙእሚን ምንጊዜም ቢሆን ተስፋ አይቆርጥም፡፡አንድ ቀን ያሰብኩት ይሆንልኛል ብሎ ተስፋ ያደርጋል … ብደሀይ ያልፍልኛል፣ ብወድቅ ይሳካልኛል፣ ባጣ ይተካልኛል፣ ጌታዩ አላህ ሁሉንም ያደረገው ለኔው መልካምን ሽቶ የኔንም መሻሻል ፈልጎ ነው ሲል ያስባል፡፡

• ሙእሚን እንደ ስሙ ሁሉ በአላህ ከልቡ አማኝ ነዉና በደረሰበት ትንሽ የዱኒያ ላይ ጊዜያዊ ሙሲባ ተቆጥቶ ዛሬውኑ ቂያማ ትቁም አይልም፡፡ ተቆጥቶም እራሱንም ሆነ ሰውን አይረብሽም፡፡ ለንዴቱ ማብረጃም ገመድ ፍለጋ አይሮጥም፡፡ የህይወትን ባህሪ ያውቃል ስለሚያውቅም ይረጋጋል፡፡ አምላኩን ፈጣሪዉን አላህ ስለሚወድ ከሱ የሚመጣዉን ሁሉ ይወዳል፡፡ ለዚህም ችግርን እንደ ደስታ በሽታን እንደ ሀጢአት ማበሻ አድርጎ ይመለከታ። አብሽሩ ሕይዎት ይቀጥላል…!

©AbuSufiyan

🌱 @TewhedandSuna
👍17👌7🎉1
✿ ምናልባት ህመም ላይ ላለች ልብ
እረፍት ትሰጥ ይሆናል‥ 

 ﴿نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيم﴾      

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መሐሪ፣ አዛኝ እኔው ብቻ መሆኔን ለባሮቼ ንገራቸው፡፡

[አል-ሂጅር 49]

🌱 @TewhedandSuna
👍52🏆5
✿ ወንድ ልጅ በምትራቆት ሴት ሊፈተን ይችላል
ለትዳር የሚመኛት ግን ሂጃብ ለበሿን እና ሂጃብ ጠባቂዋን ነው ይሄ ነው እውነታው!

🌱 @TewhedandSuna
👍63👌3