👍39
👍37
▢ ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል።
ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል።
ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል።
ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል።
"እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል።
© IbnuMunewor

🌱 @TewhedandSuna
👍35
ተስፋ (Expectation)
በሰዎች ላይ የምታደርገው ተስፋ በጨመረ መጠን፣ ሳያስቡት በሕይወትህ ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ ይጨምራል። ቃል ይገባሉ፣ እድሎችን ያቀርባሉ። አንተም ቃላቸውን አምነህ እቅድህን ትቀይራለህ፣ ሌሎች እድሎችን ትተዋለህ፣ የወደፊት ዕቅድህንም በቃላቸው ላይ ትገነባለህ።
ከዚያ ግን ሕይወት ይቀየራል። ይረሳሉ ወይም ሁኔታቸው በቅፅበት ይለወጣል። እነሱ ሕይወታቸውን ሲቀጥሉ፤ አንተ ግን ባልተፈጸሙ ተስፋዎች ላይ የተገነቡ ዕቅዶችህን ዋጋ ትከፍላለህ።
ይህ በሥራ ዓለም ብቻ የሚከሰት አይደለም። በወዳጅነት፣ በቤተሰብ፣ በአብዛኛው ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ ይከሰታል። "ይመጣል" ብለህ የጠበቅኸው ሰው ላይመጣ፤ "ከጎኔ ይቆማል" ብለህ ያሰብከው ሰው ሊሄድ፤ በጣም ያመንከው ሰውም ሊለወጥ ይችላል። እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች የሰው ተፈጥሮ አካል ናቸው።
እውነተኛው የሕመም ምንጭ ግን የእነሱ ድርጊት ብቻ አይደለም። ሰላምህ ሙሉ ለሙሉ ሰዎች ቃላቸውን በመጠበቃቸው ላይ ከተመሠረተ፣ እያንዳንዱ የተሰበረ ቃል ያናውጥሃል። ነገር ግን ልብህ በአላህ ላይ ብቻ ከተደገፈ፣ የሰዎች ቃል መሠረት ሳይሆን ተጨማሪ ፀጋ ይሆናል።
ቃላቸውን ከፈፀሙ አልሐምዱሊላህ፤ ካልፈፀሙም አቅጣጫህ፣ ሰላምህና ቁርጠኝነትህ አይለወጥም፤ ምክንያቱም ጉዞህን ከመጀመሪያው በሰዎች ላይ ሳይሆን በአላህ ላይ መሥርተሃልና።
"የሰዎች ቃል እንደ አንድ ሊፈፀም የሚችል እድል እንጂ እንደ መሠረት ሊቆጠር አይገባም። ብቸኛው የማይናወጥ ቃል የአላህ እና ለአላህ ተብሎ የተገባ ነው።"
© Huneynn

🎉10👍4👌1
¤ ደስታ ከድህነት ወይም ከሀብት ጋር የተቆራኘ ነገር አይደለም! ደስታ ማለት ባለችህ ጥቂት ነገርም ቢሆን ሰላምን ማገኘት ነው።
«ቀለል ያልክ ሰው ሁን ደስተኛ ትሆናለህ!»
────⊱◈◈◈⊰────
ትናንሽ ነገሮች ውስጥ ደስታን መፈለግ መልካም ነው፡፡ ጤነኛ መሆንን እያሰቡ ደስ መሰኘት...አምስት አውቃት ሶላት ቆመህ መስገድ በመቻልህ ደስ መሰኘት...ወዘተ....ህይወትን አጣጥመን ስንኖራት ነው መኖር ሚያምረው፤ ትንሿ ደስታ ወደ ትልቁ ደስታ ታደርሰናለች ለምስጋናም በር ትከፍታለችና ባለችን ነገር ፏ እንበል እንደሰት የጎደለውን አላህ ይሞላዋል።

👍30
قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
Video
🍃🍂🌱
✿ድምፅ የሌለው ጦርነት፣ ደም የሌለው ቁስል፣ እና መቃብርህ ውስጥ እስክትገባ ድረስ የማያቆም ውጊያ።
በአንተ እና በራስህ (በነፍስህ) መካከል ያለ ውጊያ ነው። በየቅጽበቱ ወደ ጀሀነም ልትገፋህ እና ከመዳን (ከጀነት) መንገድ ልታርቅህ ትሞክራለች። ሁሉንም መንገድ ትጠቀማለች፣ ሁሉንም በር ታንኳኳለች፤ አንድ ጊዜ በስሜት፣ አንድ ጊዜ በማዘግየት፣ አንድ ጊዜ ተስፋ በመቁረጥ፣ እና አንድ ጊዜ ደግሞ (ኃጢአትን) በማስዋብ።
{ነፍስህ} በአንድ ውጊያ ላይ ብትወድቅ፣ ከጀነት ሰዎች መስመር እንዳትሆን ሌላ ውጊያ እንደምትከፍትብህ እርግጠኛ ሁን። ስለዚህ ሰራዊት የሌላት፣ ድምፅ የማያሰማት ይህች ጦርነት የምታካሂደው በውስጥህ ብቻ ነው።
በነፍስህ ፍላጎት እና አላህ ከአንተ በሚፈልገው መካከል ያለ ጦርነት፤ ወደ ታች በሚስቡህ ፍላጎቶች እና ወደ ላይ በሚጠራህ ብርሃን መካከል ያለ ጦርነት። በህይወትህ ውስጥ የሚገጥሙህ በጣም ጠንካራ ጠላቶች ሰይጣኖች ወይም ሰዎች አይደሉም፤ ይልቁንም በውስጥህ ያለችው ነፍስህ ናት።
• አል-ሐሰን አል-በስሪ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡ «ወደ ጀነት ማንም ይቀድመኛል ብዬ አላሰብኩም ነበር፣ ወደ ራሴ (ነፍሴ) እስክመለከት ድረስ።»
አንዳንዴ ዓይንህ አላህ እርም ያደረገውን ነገር ትመኛለች፣ ስሜትህ ደግሞ፡ «አንዴ ብቻ ነው፤ አይጎዳህም» ብሎ በሹክሹክታ ይነግርሃል። ነገር ግን በልብህ ውስጥ ሌላ ድምፅ እንዲህ ይላል፡ «ይልቁንስ ይህች ጊዜ በብርሃን ሚዛን ወይም በኃጢአት ጨለማ ውስጥ ትጻፋለች።»
ስለዚህ አስተውል፡ የምትቃወማት እያንዳንዱ ፍላጎት፣ የምታዞራት እያንዳንዱ እይታ፣ እና የምትቆጣጠራት እያንዳንዱ ቃል በሰማይ የሚመዘገብልህ አሸናፊ ውጊያ ነው።
• ሱፍያን አል-ሰውሪ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡ «ከነፍሴ ይልቅ የከበደኝን ምንም ነገር አልታገልኩም፤ አንድ ጊዜ ከእኔ ጋር ትሆናለች፣ አንድ ጊዜ ደግሞ በእኔ ላይ ትሆናለች።»
የአላህን ውዴታ የምትፈልግ ሆይ! ያለ ትግል ያን ቀን አትጠብቅ፤ ይልቁንስ የምታሸንፍበትን ቀን ጠብቅ። በጥሩ ሁኔታ አስታውስ፡ በምስጢር ነፍሱን ያሸነፈን ሰው አላህ በግልጽ ከፍ ያደርገዋል።

👍21🎉2
ከሰዎች ዘለፋና ትችት እድናለሁ ያለ እሱ የአእምሮ በሽተኛ ነው ይላሉ
ኢማሙ ሻፊዒይ
══━━━።◈።━━━━══
የሰዎች አድናቆትም ሆነ ትችት የእነሱ ምልከታ እንጂ የአንተን ትክክለኛ ቦታ አያሳይም!
ስለዚህ ሀቢቢ ሰዎች ለምን ይተቹኛል አትበል! በእዚህች ዱንያ ላይ ምንም የስራ ልምድና እውቀት የማይጠይቅ ነገር ቢኖር ትችት ነውና።

👍25
🔘ካርታ የሌላት መሬት
▪️ወንድሜ ሆይ ዱኒያ የኮንትራት ምድር ናት፤ እሷ ላይ የመኖር ኮንትራታችን መቼ እንደሚያበቃ ማናችንም አናውቅም።
ዱኒያ ልክ ካርታ እንደሌለው መሬትም ናት፤ መች እንደምትፈርስ አይታወቅም።
የሷን መፍረስ ባታይም እድሜና ጉልበትህ ቀስ በቀስ እየፈረሰ አንተ ቀደመህ ትፈርሳለህ/ሽ።
▪️ስለዚህም በጤና፣ በወጣትነትና በከንቱ ምኞት ወዘተ. አንታለል!
▪️ሞት መችና በምን አቅጣጫ እንደሚመጣ አይታወቅም።
የመልካም ሥራ ሻንጣችንን ይዘን ሁሌም ዝግጁ ሆነን መጠበቅ ብቻና ብቻ ነው የሚያዋጣን።
ወደ ዋናው ሀገራችን (ኣኺራህ) ምን ይዘን እንደምንመለስ ዘወትር እናስብ።
▪️ትልቁ ድህነት ማለት የኣኺራህ ድህነት ነው።
ትልቁ ውርደትና መከራም የጀሀነም እስረኛ መሆን ነው።
▪️ትልቁ እድልና ስኬት ደግሞ በዱኑያ ቆይታ የተስተካከለ እምነት ላይ ሆኖ ብዙ መልካም ሥራዎችን ሰርቶ በመሄድ ኣኺራህ ላይ ጀነትን መሸለም ነው!
{ كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤئقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوۡنَ أُجُورَكُمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۖ فَمَن زُحۡزِحَ عَنِ ٱلنَّارِ وَأُدۡخِلَ ٱلۡجَنَّةَ فَقَدۡ فَازَۗ وَمَا ٱلۡحَیَوٰةُ ٱلدُّنۡیَاۤ إِلَّا مَتَـٰعُ ٱلۡغُرُورِ }
[سُورَةُ آلِ عِمۡرَانَ: ١٨٥]
"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ የስራችሁን ዋጋ የምታገኙት የቂያማ ቀን ነው።
ከእሳት ርቆ/ድኖ ጀነት የገባ ሰው በእርግጥም የምኞቱን በማግኘት ታድሏል።
ይህች የዱኒያ ህይወት መታለያ መገልገያ እንጂ ሌላ አይደለችም!" ኣል ዒምራን: 185
▪️አላህ የሁለት ዓለም ሕይወታቸውን ካሳመረላቸው ባሮቹ ያድርገን🤲
✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም 6/3/1448 ዓ.ሂ

👍16
📌 مقال
" الاحتفال بالمولد النبوي - شُبُهات ورُدود "
✍️ بقلم علوي بن عبدالقادر السَّقَّاف
المشرف العام على مؤسسة الدرر السنية
http://dorar.net/article/1944

👍3
¤ እንስሳ vs ሰው
~ ሊታረድ ቢላዋ እየተሳለለት፣ ሊቀቀል ድስት ተጥዶለት፣ ከሰከንዶች በኋላ ወደ ሞት ጉዞ መሳፈሩ ላይቀር እሱ ዘና ብሎ ሣሩን ይግጣል።
የኛ ና የዱንያ ነገር እንዲህ ነው።