قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
9.39K subscribers
523 photos
530 videos
12 files
1.28K links
قال رسول الله ﷺ: " إِذَا مَرَرْتُمْ بِرِيَاضِ الْجَنَّةِ ؛ فَارْتَعُوا ...

أسأل الله أن ينفع بالقناة ويتقبل منا
Download Telegram
قناة رياض الجنة 🌱 {የጀነት ጨፌ}
Video
🍃🍂🌱

✿ድምፅ የሌለው ጦርነት፣ ደም የሌለው ቁስል፣ እና መቃብርህ ውስጥ እስክትገባ ድረስ የማያቆም ውጊያ።

​በአንተ እና በራስህ (በነፍስህ) መካከል ያለ ውጊያ ነው። በየቅጽበቱ ወደ ጀሀነም ልትገፋህ እና ከመዳን (ከጀነት) መንገድ ልታርቅህ ትሞክራለች። ሁሉንም መንገድ ትጠቀማለች፣ ሁሉንም በር ታንኳኳለች፤ አንድ ጊዜ በስሜት፣ አንድ ጊዜ በማዘግየት፣ አንድ ጊዜ ተስፋ በመቁረጥ፣ እና አንድ ጊዜ ደግሞ (ኃጢአትን) በማስዋብ።

{ነፍስህ}​ በአንድ ውጊያ ላይ ብትወድቅ፣ ከጀነት ሰዎች መስመር እንዳትሆን ሌላ ውጊያ እንደምትከፍትብህ እርግጠኛ ሁን። ስለዚህ ሰራዊት የሌላት፣ ድምፅ የማያሰማት ይህች ጦርነት የምታካሂደው በውስጥህ ብቻ ነው።

​በነፍስህ ፍላጎት እና አላህ ከአንተ በሚፈልገው መካከል ያለ ጦርነት፤ ወደ ታች በሚስቡህ ፍላጎቶች እና ወደ ላይ በሚጠራህ ብርሃን መካከል ያለ ጦርነት። በህይወትህ ውስጥ የሚገጥሙህ በጣም ጠንካራ ጠላቶች ሰይጣኖች ወይም ሰዎች አይደሉም፤ ይልቁንም በውስጥህ ያለችው ነፍስህ ናት።

• ​አል-ሐሰን አል-በስሪ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡ «ወደ ጀነት ማንም ይቀድመኛል ብዬ አላሰብኩም ነበር፣ ወደ ራሴ (ነፍሴ) እስክመለከት ድረስ።»

​አንዳንዴ ዓይንህ አላህ እርም ያደረገውን ነገር ትመኛለች፣ ስሜትህ ደግሞ፡ «አንዴ ብቻ ነው፤ አይጎዳህም» ብሎ በሹክሹክታ ይነግርሃል። ነገር ግን በልብህ ውስጥ ሌላ ድምፅ እንዲህ ይላል፡ «ይልቁንስ ይህች ጊዜ በብርሃን ሚዛን ወይም በኃጢአት ጨለማ ውስጥ ትጻፋለች።»

​ስለዚህ አስተውል፡ የምትቃወማት እያንዳንዱ ፍላጎት፣ የምታዞራት እያንዳንዱ እይታ፣ እና የምትቆጣጠራት እያንዳንዱ ቃል በሰማይ የሚመዘገብልህ አሸናፊ ውጊያ ነው።

• ​ሱፍያን አል-ሰውሪ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡ «ከነፍሴ ይልቅ የከበደኝን ምንም ነገር አልታገልኩም፤ አንድ ጊዜ ከእኔ ጋር ትሆናለች፣ አንድ ጊዜ ደግሞ በእኔ ላይ ትሆናለች።»

​የአላህን ውዴታ የምትፈልግ ሆይ! ያለ ትግል ያን ቀን አትጠብቅ፤ ይልቁንስ የምታሸንፍበትን ቀን ጠብቅ። በጥሩ ሁኔታ አስታውስ፡ በምስጢር ነፍሱን ያሸነፈን ሰው አላህ በግልጽ ከፍ ያደርገዋል።

🌱 @TewhedandSuna
👍21🎉2
ከሰዎች ዘለፋና ትችት እድናለሁ ያለ እሱ የአእምሮ በሽተኛ ነው ይላሉ

ኢማሙ ሻፊዒይ
══━━━።◈።━━━━══

የሰዎች አድናቆትም ሆነ ትችት የእነሱ ምልከታ እንጂ የአንተን ትክክለኛ ቦታ አያሳይም!

ስለዚህ ሀቢቢ ሰዎች ለምን ይተቹኛል አትበል! በእዚህች ዱንያ ላይ ምንም የስራ ልምድና እውቀት የማይጠይቅ ነገር ቢኖር ትችት ነውና።

🌱 @TewhedandSuna
👍25
🔘ካርታ የሌላት መሬት

▪️ወንድሜ ሆይ ዱኒያ የኮንትራት ምድር ናት፤ እሷ ላይ የመኖር ኮንትራታችን መቼ እንደሚያበቃ ማናችንም አናውቅም።
ዱኒያ ልክ ካርታ እንደሌለው መሬትም ናት፤ መች እንደምትፈርስ አይታወቅም።
የሷን መፍረስ ባታይም እድሜና ጉልበትህ ቀስ በቀስ እየፈረሰ አንተ ቀደመህ ትፈርሳለህ/ሽ።

▪️ስለዚህም በጤና፣ በወጣትነትና በከንቱ ምኞት ወዘተ. አንታለል!

▪️ሞት መችና በምን አቅጣጫ እንደሚመጣ አይታወቅም።
የመልካም ሥራ ሻንጣችንን ይዘን ሁሌም ዝግጁ ሆነን መጠበቅ ብቻና ብቻ ነው የሚያዋጣን።
ወደ ዋናው ሀገራችን (ኣኺራህ) ምን ይዘን እንደምንመለስ ዘወትር እናስብ።
▪️ትልቁ ድህነት ማለት የኣኺራህ ድህነት ነው።
ትልቁ ውርደትና መከራም የጀሀነም እስረኛ መሆን ነው።

▪️ትልቁ እድልና ስኬት ደግሞ በዱኑያ ቆይታ የተስተካከለ እምነት ላይ ሆኖ ብዙ መልካም ሥራዎችን ሰርቶ በመሄድ ኣኺራህ ላይ ጀነትን መሸለም ነው!
{ كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤئقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوۡنَ أُجُورَكُمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۖ فَمَن زُحۡزِحَ عَنِ ٱلنَّارِ وَأُدۡخِلَ ٱلۡجَنَّةَ فَقَدۡ فَازَۗ وَمَا ٱلۡحَیَوٰةُ ٱلدُّنۡیَاۤ إِلَّا مَتَـٰعُ ٱلۡغُرُورِ }
[سُورَةُ آلِ عِمۡرَانَ: ١٨٥]

"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ የስራችሁን ዋጋ የምታገኙት የቂያማ ቀን ነው።
ከእሳት ርቆ/ድኖ ጀነት የገባ ሰው በእርግጥም የምኞቱን በማግኘት ታድሏል።
ይህች የዱኒያ ህይወት መታለያ መገልገያ እንጂ ሌላ አይደለችም!" ኣል ዒምራን: 185

▪️አላህ የሁለት ዓለም ሕይወታቸውን ካሳመረላቸው ባሮቹ ያድርገን🤲

​✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም  6/3/1448 ዓ.ሂ


🌱 @TewhedandSuna
👍16
📌 مقال
" الاحتفال بالمولد النبوي - شُبُهات ورُدود "

✍️ بقلم علوي بن عبدالقادر السَّقَّاف
المشرف العام على مؤسسة الدرر السنية

http://dorar.net/article/1944
👍3
🍃🍂🌱

¤ ወዳጅ የወዳጁን ሞት በማክበር ሊደሰትበት እንዴት ይቻለዋል ¿

©copy

🌱 @TewhedandSuna
👍18
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
¤
እነዚህ ሰሃቦች ነብዩን አይወዱም ነበር ?!


🌱 @TewhedandSuna
👍13🏆1
¤ እንስሳ vs ሰው

~ ሊታረድ ቢላዋ እየተሳለለት፣ ሊቀቀል ድስት ተጥዶለት፣ ከሰከንዶች በኋላ ወደ ሞት ጉዞ መሳፈሩ ላይቀር  እሱ ዘና ብሎ ሣሩን ይግጣል።
የኛ ና የዱንያ ነገር እንዲህ ነው።

🌱 @TewhedandSuna
👍25
¤ በግ ህይወቱን ሙሉ ተኩላውን በመፍራት ይኖርና ግን በእረኛው ይበላል።

🌱 @TewhedandSuna
👍25
¤ አንዳንዴ ህልማችን ምነው እውን በሆነ ብለን
እንመኛለን አንድ አንዳንዴ እውናችን ምነው
ህልም በሆነ ብለን እንመኛለን ።                       

🌱 @tewhedandsuna
👍30
¤ የቅርብ ወንድሞቹ "أقتلوا يوسف" አሉ።
ዝምድና የሌለው የሩቅ ሰው ደግሞ "أكرمي مثواه " አለ።

ውዴታ ሪዝቅ ነው! ከየትኛው ልብ እንደምትረዘቅ አታውቀውም!!

🌱 @TewhedandSuna
👍47
🌱 መተንፈስ እስከቻልክ ድረስ መቀየር ትችላለህ !

¤ @TewhedandSuna
👍30
✿ አንድ ነገር በጣም ከተወደደብ በመተዉ አርክሰዉ ‼

🌱 @TewhedandSuna
👍39👌2
✿ ተመልከቱ ይህች ዛፍ የባቡሩን መቅረት ወይም መዘግየት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅማ መንገዱን ሙሉ በሙሉ ወረሰችው፣ ነገር ግን አንድ ቀን ባቡሩ ተመልሶ የመጣ እለት ከነስሯ ነቅሎ እንደሚጥላት ፈጽሞ አላስተዋለችም ነበር።

አንዳንድ ክፉና በዳይ ሰዎችም ልክ እንደዚሁ ናቸው። የእውነትና የፍትህ ባቡር የዘገየ በመሰላቸው ጊዜ መንገዱን ተቆጣጥረው በበደልና በባጢል ነገሡበት፣ በረቱበትም...

ነገር ግን ያ የማይቀረው የሐቅና የፍትሕ ባቡር ዳግም ተመልሶ የመጣ ቀን የበደልን ሥሮች በሙሉ ነቅሎ ይጥላቸዋል!!

እውነትና ፍትህም ነግሰው፤ በዳዮችም የእጃቸውን አግኝተውና ውርደትን ተከናንበው፤ መኖራቸው ፈፅሞ የማይቀር የዚህች አለም ህግ ነው!!
------

አላህ በደለኞችን ይያዝልን ፤ተንኮላቸውንም ከንቱ ያደርግልን።🤲

©

🌱 @tewhedandsuna
👍39👌3🏆3