Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#ሰካራሙ-ክፍል ፲፫(13)


#አይኔ እንደገና እንደ ንጋት ፀሓይ አበራ
ትሺሺሺ ግን ምን አይነት ችኩል ነኝ
ደንባራ ነገር ነኝ ለካ እውነትም ህጻን ነገር ነኝ
ለነገሩ የወደደ ሰው ምን ቀልብ አለዉ በትንሽ በትልቁ መቅናት ማልቀስ ይወዳል
በደስታ ማዕበል ውስጥ ሆኜ ቡናው ወዲያውኑ አለቀ ከሱ ቤት ወጥተን እኛ ቤት
ገባን ቤቱን በጩሆት በአንድ እግሩ አቆምኩት ሮዛ አንቺ ቀስ በይ እንጅ ልጁ እኮ
እወድሻለሁ እንኩዋን አላለም ቆይ እወድሻለሁ ቢልሽ ምን ልትሆኝ ነው አለች
ቅድስት እስኪ አንቺ ዝም በይ ደስ እንዳላት ትሁን ሶስና አንቺ ደግሞ ቀስ በይ
ምንድነው ለሰካራም እንደዚህ መሆን አለችኝ
እንደውም ከዚህ በሓላ ሰካራም የሚል ሰው ከእኔ ጋር ይጣላል ከእሺ አልኳቸው
ጭራሽ ብለው ቤቱን በሳቀ አፈረሱት
እንደምንም ሆኖ የትምህርት ቤት ፈተና ጨረሰን
የህይወት ፈተና ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው ጥያቄው እስካሁንም አልተመለሰም
ዛሬ የሄለንን ወዛደር ለመፈለግ ወጥተን ነበረ እንደአጋጣሚ ሆኖ በቀላሉ
አግኝተነዋል አይኔ ያየው ነገር ግን በፍጹም ይሆናል ብዬ ያልጠበኩት ነገር ነው
ይሄ ወዛደር የተባለው ልጅ የሰፈሬ ልጅ ነው እንዲውም ትንሽ መግባባትም አለን
ልጁ ልጥጥ የሀብታም ልጅ ነው እንደውም በቅርቡ ካናዳ ሊሄድ ነው እየተባለ
ነበረ ታዲያ እንዴት ወዛደር ሊሆን ቻለ? በጣም እንቆቅልሽ ነው
ከወዛደሩ ጋር አንድ ላይ ሆነን አንድ ሆቴል ገባን ከዛም ምግብ መብላት ጀመረን
እኔ ልጁ አጠገብ ቁጭ አልኩኝ እኔ ሄለን ጭዋታ ይዘዋል እኔ ልጁ ጋር ጠጋ
አልኩና
አንተ ነህ ወዛደር ተብዬው አልኩት
አዎ እኔ ነኝ ምነው አለኝ
አይ ምንም ትንሽ ገርሞኝ ነው ታዲያ እንዴት ሊሆን ቻለ አልኩት
በቅርቡ ለትምህርት ወደ ካናዳ ሊሄድ ነው ስለዚህ በመልካምነት ላይ የተመሰረተ
አንድ ጥናት ጀምረያለሁ ለዚህ ይረዳኝ ዘንድ ብዬ ነኝ ወዛደር የሆንኩት
ሀብታም ድሃ አልልም ሁሉንም ሰው በነፃ እያገለገልኩ ነው ከዚህ ስራ ብዙ ነገር
እየተማርኩኝ ነው አለኝ
እኔ ደግሞ የጓደኛዬን ልብ ለመስረቅ ብለህ የሆንከው ነገረ መስሎኝ ነበረ አልኩት
ለሷ ብዬ ብሆን ኖሮ በጣም ደስ ይለኝ ነበረ እኔ ግን ቆንጆ ሴቶች ብዙም
አይመቹኝም አለ
ለምን አልኩት
ምክንያቱም ከቆንጆ ሴቶች በስተጀርባ ብዙ ውበታቻውን አምላኪ ወንዶች ይኖራሉ
እኔ ደግሞ እንደዚህ አይነት ነገር አልወድም አንዷን አንዳንቺ አይነት ፉንጋ አግብቼ
በደስታ መኖር ነው የምፈልገው ብሎ ሳቀ
አንተ እየተሳደብክ እኮ ነው አልኩት
እህህህህ ይሄ አሁን ስድብ ነው እውነትም አሷን እና አንቺን አንድ ላይ የያ ሰው
ከአንድ አፈር ነው የተሰራችሁት ብሎ አያምንም አለኝ
እንደውም ወዛደር እንደልሆንክ የሀብታም ልጅ እንደሆንክ አሁኑኑ እነግራታለሁ
አልኩት
እሺ ይቅርታ በእናትሽ ልቤን ሰትወስድ አትቀርም ስለዚህ ዝም በይ
አለኝና አንቺ ግን ልጅቷ ምን አይነት እንዝላል ናት ብዙ ብር መልሼላት እንኩዋን
አመሰግናለሁ አላለችም ምስጋና ፈልጌ ሳይሆን ነገሩ ገርሞኝ ነው አለኝ
ምናልባት ልቧን ወስደክ ይሆናል መጀመሪያ ሰው ልብ ሲኖረው ነው አይደል ማሰብ
የሚችለው አልኩት
በይ በይ አንቺ ዝም ካሉሽ ብዙ ታወሪለሽ ስለ እኔ ግን ምንም ነገር መናገር
የለብሽም አለኝ
እሺ ምስጢር ጠባቂ ነኝ አልኩት
ከዛም አብረን ተጫወተን ሶስና የልጁን ስልክ ቁጥር ተቀብላ መጣን።
የቅድስትን የልጇን አባትም አገኝተነዉ ነበረ እሱ ግን ነገሩን በቀላሉ አሜን ብሎ
መቀበል አልቻለም
ቅድስትም በግድ የኔ ባል ሁን አልልም ምክንያቱም በዚያን ጊዜ እኔም አንተም
ለስሜት ብለን እንጅ አንተ እኔን አስገድደህ ወይንም በሌላ ነገረ አታለህ ይሄን ነገር
አልፍጸምኩም
የዚያን ቀን እኔ ለስሜት ብቻ ብዬ ሳይሆን አንተን ገና ከመጀመሪያው ወድጄክ ነበረ
ስለዚህ እራሴን ለመቆጣጠር ምንም አቅም አልነበረኝም
አሁንም ምናልባት እኔን በልጅ ለማጥመድ ፈልገሽ ነው ምናምን ብለህ በፍጹም
አታስብ ልጁን እኔ ለብቻዬ ማሳደግ እችላለሁ እንድተውቀው የምፈልገው ነገር ግን
የእውነት ወድጀሀለሁ ልጄም ደግሞ ያለ አባቱ እንዲያድግ አልፈልግም አንተ
አይሆንም የምትል ከሆነ ግን ምርጫው የአንተ ነው ምናልባት አንድ ቀን እውነቱ
ገብቶክ መምጣት የሚትፈልግ ከሆነ ግን እኔ ሁለም የአንተ አፍቃሪ ነኝ ሁሌም
እጠብቃለሁ ከዚህ በፊት እኔ ወንዶችን ለስሜት እንጅ ለፍቅር ቀርቤ አላውቅም
ነበረ ለአንድም ወንድ እንደዚህ ብዬ አላውቅም ነበረ ብለ እያለቀሰች ልትሄድ
ስትል ቅድስት ብሎ ጠራት..
.
ይቀጥላል

http://t.me/USA2A