Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_14

#ቀናት ቀናትን እየወለዱ ሄዱ እኔም ከቀናቱ ጋር እየተሻለኝ ሄዶ መራመድ ጀመርኩ ታዲ እና ሊና ከጎኔ ተለይተው አያውቁም ከስራ እንደተመለሱ ውሎዋቸው አዳራቸው ከእኔ ጋር ነው ሁሌም ያበረታቱኛል። ጓደኛዬ ሃናንም ከስራ ወጥታ ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ እየመጣች ትጠይቀኛለች ምን እንደሚሰማኝ እምታውቀው እሷ ብቻ ናት የውስጤን አውጥቼ እምነግረው ለሷ ብቻ ነው። በመጨረሻም ከአንድ ወር በላይ በፈጀ ተከታታትይ ህክምና ሙሉ ለሙሉ አገግሜ ከሆስፒታል ወጣው አካሌ ቢድንም ግን ታላቅ የመንፈስ ስብራት ነበረብኝ አልጠግነው ነገር በምወዳት እህቴ በኩል ነው የግድ ከሁለት አንዳችን መጎዳት ነበረብን ሊኑ መቼም እንድትጎዳ አልፈልግም የሷን ጉዳት ለኔ ያድርልኝ!። ወደቤት ስመለስ ቤቱ እንደነበረው ሆኖ አልጠበቀኝም ሌላ ደሳሳ ቤት መስሎ ታየኝ አዎ ቤት ቀይራ ነበር እህቴ ለኔ ብላ ያላትን ብር ጨርሳ የቤቱን እቃ ሸጣ ከታድኤል ጋር አንድ ላይ እየኖሩ ነበር በኔ ምክንያት በኔ ምክንያት! ከዛ ከመሰለ ቤት ውስጥ ወጥታ አ..አ..ሁ..ን....
ፅናት ታሪኳን ከዚ በላይ ልትቀጥልልኝ አልቻለችም አይኖቿ በእንባ ተሞሉ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች በጣም አሳዘነችኝ በፍጥነት ኪሴ ውስጥ የነበረውን ሶፍት አውጥቼ ሰጠኃትና አይዞሽ ብዬ ለማፅናናት ሞከርኩ ብዙ ግዜ እንደዚ አይነት ሁኔታዎች ላይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ትንሽ ከተረጋጋች በኃላ ቀለል እንዲላት ተነስተን ወክ እንድናረግ ጠየቅኳት ምንም ሳታቅማ ተነሳች የፓርኩን ባለድንጋይ ንጣፍ መንገዶች እየተከተልን ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ጀመርን ሰአቱ መሽቷል ፓርኩ ውስጥ ምንም የሰው ዘር የለም ያስፈራል ታሪኳን እንድትጨርስልኝ ፈልጊያለው ግን ደግሞ እኔ ብዙ ማምሸት አልችልም ታሪኳን ዛሬ ካልጨረሰችልኝ ነገ እንደማገኛት ምንም ማረጋገጫ የለኝ ምን እንደማደርግ እያሰላሰልኩ እያለ ዝም አልክ አለችኝ ከሄድኩበት ሃሳብ እንደመንቃት እያልኩ እእእ አይ ምንም አይደለም እየመሸ ስለሆነ ከዚ ወጥተን ሌላ ቦታ እንቀመጥ እራት በልተሻል አልኳት ሳላስበው ከት ብላ ሳቀች ምነው ብዬ ጠየቅኳትና ትዝ ሲለኝ ለካ ከከሰአቱን ሙሉ ከኔ ጋር እንደነበረች ትዝ አለኝ እኔም ፈገግ እያልኩ ኦው ይቅርታ በቃ ነይ አብረን እንብላ አልኳት እሺ ብላኝ ከፓርኩ መውጣት ጀመርን።
ወደ ቦሌ ወደሚያስወጣው አስፓልት እየሄድን ለፅናት ምን ማለት እንዳለብኝ። ቅድም ወደዚ ስመጣ ታክሲ ውስጥ ምን አነበብኩ መሰለሽ " እንደ ዳዊት ሊያነግስህ ሲፈልግ ጎልያድን የሚያክል መከራ ይልክብሃል" ምናልባት ይህንን ፅሁፍ ያነበብኩት ላንቺ እንድነግርሽ ታስቦ ይሆናል ይኀውልሽ ፅናት እኔ ስላንቺ ብዙም አላውቅም ግን እስካሁን በነገርሽኝ ታሪክ ውስጥ ፅናት እምትባል ሴት ጠንካራ እንደሆነች አይቻለው አውቃለው ህይወት ቀላል አይደለችም ሁሌም ፈተና እና መከራ የሞላባት ናት ግን እነኛ ፈተና እና መከራዎች ናቸው የህይወትን ጣእም እንድናውቅ እሚያደርጉን የሰላም ጥቅም የሚገባሽ ረብሻና ሁካታ ውስጥ ስትሆኝ ነው እንደዚሁም የህይወት ታላቅ ምስጢር የሚገባሽ ፈተና ውስጥ ስትሆኝ ነው እና እነኚን ፈተናዎችሽም አትጥያቸው በህይወትሽ ገና ብዙ እሚገጥሙሽ ነገሮች አሉ ራስሽን ለዛ ማዘጋጀት ነው ያለብሽ በእሳት ያልተነጠረ ወርቅ ለጌጥነት አይወልም በእሳት ያልተፈተነ ሸክላ ለስራ አይወልም ምክንያቱም እሳቱ ስለሚፈትናቸውና ትክክለኛ ማንነታቸውን እንዲያወጡ ስለሚያደርጋቸው ነው በፈተና ብዛት የሚመጣ ማንነት ትክክለኛ ማንነታችን ነው ብዬ አምናለው ምናልባት አጋጥሞሽ ከሆነ አላውቅም በደግ ግዜ ከጎንሽ አለው አለው የሚሉሽ ሰዎች በችግርሽ እና በፈተናሽ ግዜ ጥለውሽ ይጠፋሉ ያኔ የነሱን ትክክለኛ ማንነት ታዩበታለች እናም ፈተናዎችሽን አትጥያቸው ትክክለኛ ማንነትሽን እንድታወጪ እና ምን ያክል ጠንካራ እንደሆንሽ እንድታውቂ ይረዳሻል አልኳት። ፅናት በመገረም እያየችኝ ነበር ትንሽ ፈገግ አለችና እሺ አለችኝና ወደቦርሳዋ መለስ ብላ ዚፑን ከፍታ መጎርጎር ጀመረች ትንሽ ቆይታ አንድ ቢጫ ሃይላንድ መሰል ነገር አወጣች ጨልሞ ስለነበር ምንነቱን በደምብ መለየት አልቻልኩም ቢጫውን እቃ ወደኔ እያስጠጋችው ታውቃለህ ረምሃይ ዛሬ እዚ ፓርክ የመጣሁት አንድ የመጨረሻ ሲጋራ አጭሼ ይሄንን በረኪና ጭልጥጥጥ... አድርጌ ጠጥቼ ራሴን ላጠፋ ነበር አለችኝ በጣም ደነገጥኩ ፈፅሞ ያልጠበቅኩት ነገር ነበር ይበልጥ እየደነገጥኩ ምንንንን! ብዬ ጮህኩባት ወዲያው.አማተብኩና በረኪናውን ከእጇ ነጠቅኳትና ያዝኩት። ፅናት ግን ማውራቷን አላቁመችም አሁንም ፈገግ እንዳለች ነው። ታውቃለህ ዛሬ ራሴን ላጠፋ እዚ ፓርክ መጣው ይህንን ፓርክ ያሳየኝ ታዲ ነበር እሱን እያስታወስኩ ሲጋራዬን ምጌ ስጨርስ በረኪናውን ለመጠጣት እያሰብኩ እያለ አንተ መጣህ እና ሲጋራውን ስጪኝ አልኩኝ ለሲጋራው ደንታ ባይኖረኝም አጋጣሚው በጣም ገረመኝ ምን አይነት ልጅ ነው እያልኩ ነበር ምናልባትም እንድታድነኝ ይሆናል አምላክ አንተን የላከህ አላውቅም!። ፅናት ይህንን ስትለኝ ከፓርኩ ወጥተን ወንዙን የሚያሻግረው ድልድይ ላይ ነበርን ወዲያው አስቆምኳትና ከድልድዩ በስተግራ በኩል ያሉ የጎመን አትክልቶች መብራት በርቱባቸው ይታያሉ ወንዙ በመሃላቸው አቋርጦ ያልፋል ወደዛ ወሰድኳትና በረኪናውን ድልድዩ ስር አስቀመጥኩት። የውልሽ ፅናት ታሪክሽን ሙሉ ለሙሉ ስላልነገርሽኝ እኔም ለመምከር አልተመቸኝም እስካሁን የነገርሽኝ ታሪክ ራስን ለማጥፋት እንደማያደርስ በደምብ አውቃለው ከዚ የባሰ ሌላ ታሪክ እንዳለሽ ይሰማኛል ነገ ተገናኝተን ሁሉንም ከነገርሽኝ እኔ መርዳት የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ ሌላው ቢቀር እመክርሻለው ያንን ማድረግ ካልቻልኩ እኔ ይህንን በረኪና ጠጣለው ባንቺ ፈንታ አልኳት ፅናት እየሳቀች እሺ ነገ እንገናኝና ጨርስልሃለው አለችኝ። ቃል ግቢልኝ ነገ እዚ እንደምትመጪ እና ዛሬ ራስሽን ለማጥፋት ምንም እንደማታደርጊ ቃል ግቢልኝ እመኚኝ ነገ በዚ ሰአት የሚኖርሽ ስሜት ርሌላ ይሆናል ብቻ አንቺ ቃል ግቢልኝ አልኳ እሺ አለችኝና የማርያም ጣቷን ዘረጋችልኝ እኔም ጣቴን ዘረጋሁላትና ቃል ተገባባን በረኪናውን ገፋ አድርጌ ወደ ወንዙ ጣልኩት አንተተ... ለራስህ እንዳትጠጣው ነዋ አለችኝ እየሳቅኩ ችግር የለም ነገ አዲስ እንገዛለን አልኳት ከት ብላ ሳቀች።

ከፅናት ጋር እራት አብረን በላን የተለያዩ አዝናኝ ነገሮችን እየነገርኳት አመሸን ድጋሚ ታሪኳን ጀምራልኝ እማይሆን ስሜት ውስጥ ገብታ መጥፎ ውሳኔ እንዳትወስን ብዬ በተቻለኝ መጠን ለማስረሳት ጣርኩ። እራት በልተን ከጨረስን በኃላ ነገ እሁድ ጠዋት አራት ሰአት ላይ እዚው ፓርክ እንድንገናኝ ተቀጣጥረን ተለያየን። በታክሲ ወደቦሌ እየተመለስኩ ቅድም ፓርክ ውስጥ እየገባው ፅናትን አክቻት ዝም ብያት አልፌ ተመልሼ ሄጄ ባላወራት ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቤ በጣም ተገረምኩ ፈፅሞ ሌላ ታሪክ ሊፈጠር እንደሚችል አሰብኩት ፈፅሞ ሌላ ታሪክ ይሆን ነበር ለካ ለዚ ነው ቀን ላይ እያክለፈለፈ ወደዚ ያመጣኝ አልኩ ለራሴ። ብርቅርቅታን እያነበብኩ ሲጋራ እምታጨሰውን ልጅ እንዳወራት ህሊናዬ ያስገደደኝ ለዚህ ነበር! ነገ ሳገኛት ምን እንደምትነግረኝ እያሰብኩ ለሷ እምላትን እያሰላሰልኩ ወደቤቴ ገባው....
#ይቀጥላል.......

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_15_ቶሎ_እንዲለቀቅ
http://t.me/usa2a