Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_15

#በማግስቱ ከፅናት ጋር የተቀጣጠርንበት ሰአት ሲደርስ እንደምትመጣ ተስፋ እያደረግኩ ወደፓርኩ ሄድኩ። እንደሁልጊዜዬ ፓርኩ ውስጥ ገብቼ ትናንት ፅናት ወደተቀመጠችበት ቦታ አመራው ግን አልነበረችም አይ እየመጣች ነው በቃ ብዬ ወደራሴ ቦታ ሄድኩ ፅናት የኔ ቦታ ላይ ቆጭ ብላ ማዶ ከሚታየውን የእርሻ መሬት እያየሽ ስትመሰጥ አገኘኃት ስታየኝ ፈገግ አለችና ሰላም አለችኝ እኔም ፈገግታዋን በፈገግታ መልሼ ሰላም አልኳት። አንዳድን ነገሮችን ስናወራ ካረፋፈድን በኃላ እሺሺሺ... ትናንት ምን ላይ ነበር ያቆምኩልህ አለችኝ ትንሽ እንደማስታወስ አልኩና እእእ ከሆስፒታል ወጥተሽ ወደቤት ስትመለሽ ነበር ያቆምሽልኝ አልኳት አ...ው! አለችና እእእእ ከዛ ቤት ስንመለስ ቤት ተቀይሮ ነበር ያገኘሁት ልክ ወደቤት እንደገባን ሊና እንዳልደነግጥ ብላ በተረጋጋ መንፈስ ልታስረዳኝ ሞከረች እእእ እየውልሽ ፅኑዬ አንቺ የመኪና አደጋ ሲደርስብሽ ግዜ አንቺን የማሳክምበት በቂ ገንዘብ አልነበረኝም ደሞ ታውቂዋለሽ የወር ደሞዜን ብቻ ከየትም ከየትም ተበዳድሬ አሳከምኩሽ ነገር ግን አንቺ ስላልነቃሽ ሆስፒታል ውስጥ መቆየት ነበረብሽ እኔም ከመስሪያ ቤት ተበድሬ ቤት ውስጥ ያለውን እቃ ሸጬ አንቺን ማሳከም ቀጠልኩ ታዲም እሱ ከቤተሰቦቹ እና ከጓደኞቹ እየተበደረ የሚችለውን ያግዘኝ ነበር እሱም የቤቱን እቃ ሸጦ በተገኘው ገንዘብ በቻልነው መጠን አንቺን በህይወት ለማቆየት ጣርን ሊና እንዲ እያለች እያወራችልኝ እያለ የታዲ ስልክ ጠራ እና ሊያወራ ወጣ። ሊና ታዲ እስኪወጣ ከጠበቀች በኃላ ቀጠለችልኝ እና በዛን በጣም በጨነቀኝ ሰአት ከጎኔ ሳይለየኝ የነበረው ታዲ ብቻ ነበር ሁሉም ከግዜ በኃላ ተስፋ እየቆረጡ ሲሄዱ ታዲ ግን አንድም ቀን ከጎኔ አልተለየኝም እኔም የታዲ መልካምነት እንድወደው አደረገኝ ይህንን ላንቺ ምንገር የነበረብኝ አሁን እንዳልሆነ አውቃለው ግን... አሁን እኔና ታድኤል አንድ ላይ ነው እምንኖረው አለችኝ በጣም እየከበዳት። ታዲ የኔ እንዲሆን ብፈልግም ግን ለእህቴ የሚሰጣት ሰላምና ደስታ ከኔ እንደማይበልጥ አሰብኩ ምናልባትም በነዚያ ለሷ ከባድ በነበሩት ወራት ላይ ታዲ ከጎኗ ባይኖር ኖሮ በጣም ሊከብዳት እንደሚችል አሰብኩ። አው ገምቼ ነበር አልኳት ፈገግ ብዬ ሊና ደነገጠች እእእ እንዴት አለችኝ አይ ሁኔታችው ያስታውቃል ማለት ሁሌ እኔ ጋር ስትመጪ ምግብ ይዘሽለት ትመጫለሽ እሱም አንቺ ከኔ ጋር ስታድሪ ቁርስ ይዞልሽ ይመጣል ከኔ የሚተርፍሽን ግዜ ከሱ ጋር ማሳለፍ ነው ምትፈልጊው እሱም ስላንቺ አውርቶልኝ አይጠግብም ብቻ ገምቼ ነበር አልኳት ፈገግ እያልኩ ማሽላ እያረረ ይስቃል አይደል እሚባለው እኔም እየተቃጠልኩ ለእህቴ ስል ልሳቅ። እሺ እንደዛ ከሆነ ጥሩ ታዲያ ግን አይደብርሽን አይደል ማለት ከታዲ ጋር ስለምንኖር ያው ጥሩ ጓደኛሽ እንደሆነ ነግሮኛል አለችኝ አረ... በፍፁም ሊናዬ ምንም እንዳታስቢ ምንም የሚደብረኝ ነገር የለም እንደውም ደስ ብሎኛል ታዲን የመሰለ ጥሩ ሰው ስላገኘሽ። ምን ያክል ትወጂዋለሽ አልኳት ፈገግ እያልኩ እሷም ፈገግ እያለች ፅኑዬ ካንቺ ቀጥሎ በዚ አለም ላይ የምወደው ሰው ቢኖር ታዲ ነው አለችኝና እንደመሽኮርመም እያለች ጎኔን ጎሸም እያደረገችኝ እድሜ ላንቺ... አለችኝ ሳቋን እየለቀቀችው እኔም የግዴን ሳቅኩ። ታዲ ስልክ አውርቶ ሲጨርስ ወደ ውስጥ ገባና ምን ተገኝቶ ነው ሳቅ በሳቅ የሆናቹት አለን ሊና እንደማፈር እያለች አረረ... ምንም አለችው።
ምሳ ከበላን በኃላ ሊና ለታዲ ስለነሱ ለኔ እንደነገረችኝ ነገረችው ታዲም ትንሽ እንደመደንገጥ አለና እህትሽ ጠንካራ ሴት ናት ያንን በጣም አደንቅላታለው ያ ነበር ከሊና የማረከኝ ነገር አለኝ። ሊና ከከሰአት ስራ የግድ መግባት ስለነበረባት ሄደች ቤት ውስጥ እኔና ታዲ ብቻ ቀረን ከታድኤል ጋር አንድ ቤት ውስጥ መቀመጥ በጣም ከበደኝ በየደቂቃው ምን ያህል እንደማፈቅረው ልነግረው እፈልግ አስባለው ሊኑዬ ትታወሰኝና አፌን ይዤ እቀመጣለው ከዚህ በኃላ ታዲን ለመርሳት ወሰንኩ ግን እንዴት ተደርጎ አንድ ቤት ውስጥ እየተኖረ እንዴት!።
ፀሃይዋ በረድ ማለት ስትጀምር ታዲ ወደውጪ እንድንወጣ ጠየቀኝ ከተማውን ካየሁት ዘመን አልፎኛል ነይ እንናፈስ አለኝና ወጣን ቦሌ ከዛኔ ልንገናኝ የነበረበት ይሄ ፓርክ ማለት ነው ይዞኝ ሄደ ቦሌ ማተሚያ አከባቢ ስደርስ ልቤ በፍጥነት እየመታ ነበር መኪና የገጨኝን አስፓልት የታዲን እጅ ጭብጥ አድርጌ በጥንቃቄ ተሻገርኩ። እሱ እየመራኝ ወደ ፓርኩ ሄድን ለመጀመሪያ ግዜ እዚህ ፓርክ የመጣሁት ከታዲ ጋር ነበር ይህንን ፓርክ ታዲ ስላሳየኝ ይሁን ፀጥታው ደስ ስለሚል አላውቅም ብቻ በጣም ወደዋለው ሰላም ይሰማኛል። ወደውስጥ ገብተን ትናንተ ተቀምጬ ያገኘኀኝ ቦታ ላይ ሄደን ተቀምጠን አንዳድን ነገሮችን ማወራት ጀመርን ስለቤት ስለሊና በመሃል አንድ ነገር ታወሰኝ ሊና ለኔ ጤንነት መመለስ ብዙ ስትለፋ ነበር ነገር ግን ታዲም ከሷ እኩል በቻለው መጠን ለኔ ጤንነት ብዙ ሲለፋ እንደነበር እሱም ተጎሳቁሎ እንደነበር ብዙም ልብ አላልኩም። ውስጤ ጥያቄ ተፈጠረ ለምን ይህንን ሁሉ መስዋእት መክፈል ፈለገ ለኔ ሲል ወይስ ለሊና ሲል? የግድ መጠየቅ ነበረብኝ። ታዲ ግን ለምን ይህንን ሁሉ ውለታ ለኔ ማድረግ ፈለግክ አልኩት ትንሽ ካሰበ በኃላ እውነት ለመናገር ላንቺ ብዬ አልነበረም ያደረግኩት ለራሴ ስል ነበር ያደረግኩት ለምን እንደሆነ ባላውቅም ገና ካወቅኩሽ ቀን ጀምሮ እንደ ታናሽ እህቴ ነበር እማይሽ ችኩል ብትሆኚም በልብሽ መልካምነት እንዳለ አውቃለው እና የሆነ ነገር ማድረግ እየቻልኩ ህይወትሽ ሲያልፍ ዝም ብዬ ማየት አልችልም ሲቀጥል ደሞ ይህ ሁሉ የሆነው እኔን ልታገኚ ስለነበር ነው እና ለማንም ብዬ ሳይሆን ለራሴው ብዬ ነው አለኝ የታዲ አስተሳሰብ በጣም ይገርመኛል ውስጤ ይላወስ ጀመር ንገሪው ንገሪው ንገሪው የሚል ስሜት መጣብኝ ምንም አፍኜ ላቆየው አልቻልኩም ለሊና ባልነግራት እንኳን ታዲ የሚሰማኝን ይወቅልኝ አልቻልኩም በቃ!። ታዲ አልኩት ወዬ ፅኑ አለኝ።
#ይቀጥላል.......

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_16_ቶሎ_እንዲለቀቅ
http://t.me/usa2a