Forwarded from አለ ሕግ
አንድ ሰው ከቤቱ ወይም ከመኖሪያው ቦታ ጋር ወደተያያዘ ቦታ ሰው ባይኖ አጥር ግቢ ሕጋዊ ነዋሪው ፈቅዶለት ከገባ በኋላ እንዲወጣ ሲጠይቀው ያልወጣ እንደሆነ፤ ከ 3 ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም በመቀጮ እንደሚቀጣ ያውቃሉ፡፡
የወንጀል ህግ አንቀጽ 604‼️
ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!
#አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig
Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
#አለ_ህግ #Ale_Hig
የወንጀል ህግ አንቀጽ 604‼️
ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!
#አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig
Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Telegram
የሕግ ቤት
የሕግቤት Access legal information from Law center, The House of Law.
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
https://www.facebook.com/lawsocieties
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
https://www.facebook.com/lawsocieties
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
Forwarded from አለ ሕግ
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ
የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ
አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው። ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችላቸው የኅብረት ስምምነት ድርድር በማድረግ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክሮች፣ የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በተጨማሪ አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ለመጠበቅ እንዲቻል የአሰሪና ሰራተኛ ህግ በኢትዮጵያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍም በግል በተቋቋሙ ድርጅቶችና መንግስታዊ በሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ባለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተደንግጎ የሚገኘውን የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱን እንመለከታለን።
የሰራተኞች ቅነሳ መቼ ይደረጋል?
የሰራተኞች ቅነሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሊደረግ የሚችለው የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚከተሉት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ ነው:-
• ሠራተኞች የተሰማሩባቸው ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት፤
• በአዋጁ አንቀጽ 18(5) እና (6) ላይ የተቀመጡት ከስራ ውል የሚመነጩ መብቶችና ግዴታዎች ለጊዜያዊ የሚታገዱበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ አሠሪው በሚያመርታቸው ምርቶች ወይም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የሥራ ውል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
• የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ ናቸው፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ነው ሊያስብል የሚችለው ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ቁጥራቸው ከድርጅቱ ሠራተኞች ቢያንስ ከመቶ አሥር የሚያህለውን ወይም የሠራተኞች ቁጥር (የአንድ አመት አማካኝ የሰራተኞች ቁጥር) ከሀያ እስከ ሀምሳ በሆነበት ድርጅት ቢያንስ አምስት ሠራተኞችን የሚመለከት ከአሥር ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የሚቆይ የሥራ ውል መቋረጥ ሲከሰት እንደሆነ በአስሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 29 ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ሂደት
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ አሰሪ በራሱ ጊዜ የፈለገውን ሰራተኛ መቀነስ የማይችል ሲሆን ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ በመጀመሪያ አሠሪው ከሠራተኞች ማኅበር ወይም ተወካይ ጋር በመመካከር የሥራ ችሎታ ያላቸውና ከፍተኛ የምርት ውጤት የሚያሳዩ ሠራተኞች በሥራቸው ላይ እንዲቆዩ ያደርጋል ወይም ከማይቀነሱ ሰራተኞች መካከል ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በድርጅቱ ውስጥ ተመሳሳይ የሥራ ችሎታ ያላቸውና ተመሳሳይ የምርት ውጤት የሚያመርቱ ሠራተኞች በሚኖሩ ጊዜ የሰራተኞች ቅነሳ የሚደረገው በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናል:-
1. በድርጅቱ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሠራተኞች፤
2. አነስተኛ ቁጥር የሆነ ጥገኞች ያሏቸው ሠራተኞች፤
3. ከተራ ቁጥረ (4) እስከ (7) ከተዘረዘሩት የሠራተኛ ክፍሎች ውጭ የሆኑ ሠራተኞች ቅነሳው በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከታቸው ይሆናል፤
4. አካል ጉዳተኛ የሆኑ ሠራተኞች፤
5. በድርጅቱ ሳሉ በሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች፤
6. የሠራተኞች ተጠሪዎች፤
7. ነፍሰጡር ሠራተኞች ወይም ከወለዱ እስከ 4 ወር ድረስ የሆናቸው ሴት ሠራተኞች ናቸው፡፡
በልዩ ሁኔታ የኮንስትራክሽን ስራ ማለትም ሕንጻ፣ መንገድ፣ የባቡር ሐዲድ፣ የባሕር ወደብ፣ የውሃ ግድብ፣ ድልድይ፣ የመሣሪያ ተከላና ሌላም ተመሳሳይ ሥራ የመሥራት የመለወጥ፣ የማስፋፋት፣ የማደስና የመጠገን ሥራ ተከታታይነት እያለቀ ሲሄድ የሥራው መጠን በመቀነሱ ምክንያት ተቀጥረው በሚሰሩ ሠራተኞች ላይ ቅነሳ ሲደረግ አሠሪው በዚህ ከላይ የተመለከቱትን የሠራተኞች ቅነሳ ሥነ ሥርዓት መከተል አይጠበቅበትም፡፡ ነገር ግን ሰራተኞች የተቀጠሩበት ሥራ ከማለቁ በፊት ከሆነ የሰራተኛ ቅነሳ ሲደረግ በአዋጁ ላይ የተገለጸውን ሥነ-ሥርአት መከተል የግድ ይለዋል። በተጨማሪም ቅነሳ ለማካሄድ አሰሪው የሁለት ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሚቀነሱት ሰራተኞች የመስጠት ግዴታ አለበት (አንቀፅ 35/1/መ)፡፡ እንዲሁም ድርጅቱ የሚወስደው እርምጃ፣ ከሰራተኞች ጋር የህብረት ስምምነት ካለው ይህንኑ እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በዚህ ረገድ የሚያወጣውን መመሪያ ያከበረ መሆን አለበት፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ያለው ውጤት
አንድ ሰራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 29 መሰረት በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ሲቋረጥ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው። የስራ ስንብት ክፍያ መጠንን በተመለከተ ለመጀመሪያው የአንድ ዓመት አገልግሎት የሠራተኛው ማለትም የተቀነሰው ሰራተኛ የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡ከአንድ ዓመት በታች አግልግሎ ለተቀነሰ ሰራተኛ ግን እንደአገልግሎት ጊዜው እየተተመነ ተመጣጣኝ ክፍያ ያገኛል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎ በሰራተኛ ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ የተቋረጠበት ሠራተኛ ከላይ በተጠቀሰው ክፍያ ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት ከላይ የተጠቀሰው ክፍያ አንድ ሦስተኛ እየታከለ የስራ ስንብት ክፍያው ይከፈለዋል፡፡ ነገር ግን ጠቅላላው ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡
በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ተቋርጦ ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ ከላይ ከተጠቀሰው የስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የሠራተኛው የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዝ በ60 ተባዝቶ እንደሚከፈለው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ አለመግባባት የሚፈጠር ከሆነ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ሰላም ለመፍጠር፣ ምርታማነትን ለማሻሻል ብሎም የሰራተኞች ህጋዊ መብቶች ለማስክበር በስራና ክህሎ ሚኒስቴር በሚመደብ አስማሚ ችግሩ እንዲፈታ መመልከት ወይም ይህን መሰል ጉዳይ የወል ስራ ክርክር በመሆኑ ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ዳኝነት መጠየቅ ይቻላል፡፡
Federal Justice and Law Institute
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
https://alehig.wordpress.com/blog-2/
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties

Forwarded from ይግባኝ ምክረ ሕግ ⚖️
#የሥራ ስንብት ክፍያ
የስራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ሠራተኛ በአዋጅ 1156/2011 ዓ.ም አንቀፅ 39 (1) (ለ) እና 40 (1) መሠረት እንደ ነገሩ ሁኔታ ለ1 ዓመት አገልግሎት የመጨረሻ ሳምንት አማካኝ ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ሲከፈለው ከ1 ዓመት በታች ያገለገለ በአገለገለው ልክ ይከፈለዋል፤ ከ1 ዓመት በላይ ያገለገለ እንደሆነ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ዓመት የዓመቱ 1/3ኛ እየተጨመረ ይከፈለዋል።
#የካሳ ክፍያ
የሥራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ከሥራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ በአዋጅ 1156/2011 ዓ.ም አንቀፅ 43 (4)(ለ) መሠረት የካሳ ክፍያ ያገኛል። ሆኖም ካሳው የሠራተኛውን ማዕከላዊ የቀን ደመወዝ በ180 ተባዝቶ ከሚያገኘው መጠን መብለጥ የለበትም።
#ያልተጠቀሙበት የዓመት ዕረፍት
የሥራ ውሉ አለአግባብ የተቋረጠበት ሠራተኛ ከሥራ ስንብት ክፍያ እና ከካሳ ክፍያ በተጨማሪ ያልተጠቀመበት የዓመት ዕረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ በአዋጅ 1156/2011 ዓ.ም አንቀፅ 77 (4) መሠረት ይከፈለዋል።
#ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ
ሠራተኛው የሚለግበትን የአሰሪ ንብረት መልሶ ክሊራንስ ከጨረሰ በኋላ ሊከፈሉት የሚገቡ ክፍያዎች በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ካልተከፈሉት በአዋጁ አንቀፅ 38 መሠረት እስከ 3 ወር ደመወዝ ሊከፈለው ይችላል።
#ያልተከፈለው የወር ደመወዝ ካለ ይከፈለዋል።
#ለተጨማሪ ሥራ ክፍያ
ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ በበዓል ቀናት የተሰራ ሥራ፣ በዕረፍት ቀናት የተሰራ ሥራ ካለ ለእነኚህ ሥራዎች በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀፅ 66 እና 68 መሠረት ሠራተኛው ክፍያ ያገኛል።
#የሥራ የምስክር ወረቀት (የሥራ ልምድ)
በአዋጅ ቁጥር 1156/2011ዓ.ም አንቀፅ 12 (8) መሠረት ሠራተኛው የሥራ ልምድ ማስረጃ ያገኛል።
ይግባኝ መብት ነው!!!

#የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ሠራተኛው ተከፋፍሎ እንዲሰጠው ሲጠይቅ እንዲሁም አሠሪው ሲስማማ ለሁለት ተከፍሎ ለሠራተኛው ሊሰጠው እንደሚችል ተቀምጧል። አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀጽ 79
#የዓመት ፈቃድ ሠራተኛው ሲጠይቅ አሠሪውም ሲስማማ ሊተላለፍ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 79 (2) ላይ ተደንግጓል። ነገር ግን ይህ ማራዘም ከ 2 ዓመት በላይ ሊበልጥ የማይችል ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 79 (3) ላይ ተመልክቷል።
👉የዓመት ፈቃድ ምን ያህል ጊዜ ነው ሚጠራቀመው🤔
#ብዙ ሠራተኞች የዓመት ፈቃዳቸውን በገንዘብ ሚጠይቁት ከአሠሪ ጋር አለመስማማት ተፈጥሮ ሥራቸውን ሲለቁ የ5 ወይም 10 ዓመት አልያም ከዛ በላይ የሆነውን ደምረው ይጠይቃሉ። ይህ ልክ ነው ወይ?
#የዓመት ፈቃድ መሠረታዊ ዓላማ ሠራተኛውን ዕረፍት እንዲያገኝ በማድረግ በአዕምሮና በአካል ብቁ እንዲሆን ማድረግ እንጂ ያለዕረፍት ሥራ እየሰራ ገንዘብ እንዲያገኝ ማድረግ አይደለም። ለዚህም ነው ልዩ ሁኔታ ከሌለ በስተቀር የዓማት ፈቃድ በገንዘብ የማይከፈለው።
በመሆኑም ማንኛውም ሠራተኛ የዓመት ፈቃዱን ከ 2 ዓመት በላይ ማራዘም የማይችል በመሆኑ ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው ፈቃዱ የሚቃጠልና በቀናት ፈቃድም በገንዘብም እንዲከፈለው ለመጠየቅ የማይችል ነው።
ይግባኝ መብት ነው!!!
የቴሌግራም ቻናል አድራሻችን
https://t.me/etonlinelegal
አዲስ የተከፈተውን ቴሌግራም ግሩፕ ለመቀላቀል ይህንን ይጫኑ
https://t.me/etonlinelegalchat
በግል መስመር በማንኛውም ጉዳይ የሕግ ምክር ለማግኘት ይህን የቴሌግራም አድራሻ ይጠቀሙ
@laws2016
በfacebook የሚለቀቁ መረጃዎችን ለማግኘት ገጹን ይቀላቀሉ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61551025119181

#በፍትሐ ብሔር ሕግ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ሟች ኑዛዜውን በሚያደርግበት ወቅት ለመውረስ የማይገቡትን ወራሾች በመለየት ከውርስ ሀብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ለማድረግ ሙሉ ሥልጣን አለው። የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 937 ነገር ግን ይህ ሥልጣን ገደብ የሌለው አይደለም።
1️⃣ያለምክንያት ከውርስ መንቀል
#ወራሽ የሆነን ሰው ከውርስ መንቀል የሚቻልባቸው ምክንያቶች በፍትሐ ብሔር ሕጋችን ቁጥር 838 ላይ ተዘርዝረዋል። ለምሳሌ በወራሹ ላይ ወይም በቤተሰቡ ወይም በትዳር አጋሩ ላይ የመግደል ሙከራ አድርጎ ወይም ከ10 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ በሚችል ወንጀል ላይ በሐሰት መስክሮ ከነበረው ወራሽ ቢሆንም ሟች ከውርስ ሀብቱ እንዳይጠቀም ሊናዘዝ ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ምክንያቶች ሳይኖሩ ከውርስ መንቀል በፍፁም አይቻልም።
2️⃣በዝምታ ከውርስ መንቀል
#በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 939 ላይ እንደተመለከተው አንድ ተናዛዥ ልጁን በማንኛውም መልኩ በዝምታ ከውርስ ሊነቅለው አይችልም በማለት ተመልክቷል። የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 10 መዝገብ ቁጥር 42546
3️⃣ትንሽ ድርሻ ሰጥቶ ከውርስ መንቀል
#ይህ ማለት ሟች ኑዛዜ በሚያደርግበት ወቅት ወራሽ ለሆነው ወገን ዋጋው እጅግ አነስተኛ የሆነን መጠን ብቻ በመናዘዝ ሌሎች ዋጋቸው ውድ የሆኑ ዋጋ ንብረቶችን ወራሽ ላልሆኑት በኑዛዜ ሰጥተው ሲገኙ የሚፈጠር ነው። እንዲህ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 11 በመዝገብ ቁጥር 54385 ላይ ወራሽ ለሆነ ሰው ከጠቅላላ የውርሱ ሀብት አንጻር ትንሽ ድርሻ ብቻን መስጠት በተዘዋዋሪ መልኩ ከውርስ መንቀል ነው፤ በመሆኑም ኑዛዜው አግባነት አይኖረውም የሚል አስገዳጅ የሆነ ውሳኔን ሰጥቷል።
⏭️እንደነዚህ ያሉ ከውርስ መንቀሎች ከተፈጠሩ በኋላ መፍትሔያቸውንና የሕግ ውጤታቸውን በቀጣይ ይጠብቁ!
ይግባኝ መብት ነው!

አያድርግብዎትና በአንድ ጉዳይ ላይ ቢከሰሱ እና የፍርድ ቤት መጥሪ ሲደርስዎት እነዚህን ነገሮች ያድርጉ!
1. የተሰጠዎት የፍርድ ቤት መጥሪያ በትክክል ከፍርድ ቤት የተሰጠ መሆኑን፣ ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆኑንና መዝገብ ቁጥሩ በመሸኛው በቀኝ በኩል አናት ላይ ከቀን መጻፊያው በላይ ወይም በታች መጻፉን ያረጋግጡ! ከፍርድ ቤት ስለመውጣቱ የራስጌ እና ክብ ማኅተሞችን በማየት ያረጋግጡ!
2. የቀጠሮው ቀን ለመቼ እንደሆነ ያረጋግጡ፤ አንድ ተከሳሽ ለተከሰሰበት ነገር መልሱን እንዲያቀርብ ሚታዘዘው በትንሹ የክስ አቤቱታው ከፍርድ ቤት ወጪ ከተደረገበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ነው፤ እጅጉን ቢያንስ ከ5 ቀና ያነሰ መሆን የለበትም፤ ረፍዶ የተሰጠዎትም ቢሆን ይቀበሉ!
3. የተቀበሉትን አቤቱታ የገጽ ብዛት ያረጋግጡ፤ በክስ አቤቱታው መሸኛ ላይ ከዚህን ያህል ገጽ ጋር ልከናል የሚል ከሆነ እና የደረሰዎት ጎዶሎ እንደሆነ ሲፈርሙ የተቀበሉትን ገጽ መጠን ጠቅሰው ይቀበሉ፤
4. መጥሪያውን ሲቀበሉ በቀን 18/01/2016 ዓ.ም ተቀብያለውኝ ብለው ቀሪው ላይ ይፈርሙና ለእርስዎ የተላከውን ይቀበሉ፤ እንዲህ በማለት መፈረምዎ መቼ እንደተቀበሉና ከሳሹ አዘግቶ ከሰጠዎ ማስረጃ ይሆኖታል!
በስተመጨረሻ ጊዜ ያለዎት ከሆነ መዝገብ ቁጥሩን በመያዝ በተጠቀሰው ፍርድ ቤት ከቀጠሮ በፊት ስለተጻፈው ቀጠሮ ትክክለኛነት ያረጋግጡ!
መብትና ግዴታዎን ለማወቅ በማንኛውም ጉዳይ ይግባኝ ማለት መብትዎ ነው!

Forwarded from የሕግ ዜና
አለአግባብ በሌላ ወራሽ ሆነ ሌላ መብት በሌለው ሰው የተያዘ ንብረት ስታስመልስ ከንብረቱ ያገኘውን ጥቅም (ለምሳሌ እያከራየው ከነበረ) መጠየቅ የሚቻለው ራሱን በቻለ ክስ አለአግባብ መበልፀግን በሚመለከቱ ድንጋጌዎች ነው።
ህጉ ነው የሚለው እኔ አይደለሁም።
"ለቀረው ጉዳይ ሁሉ.... አለአግባብ መበልፀግን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ይፈጸማሉ።"
ስለሆነም አለአግባብ የተያዘ የውርስ ሀብት ማስመለስ ክስ petitio haereditatis ዋናውን እንጂ ፍሬውን (ለምሳሌ የኪራይ ገንዘብ) መጠየቅ አትችልም።
እሱን በpetitio haereditatis ሳይሆን አለአግባብ መበልፀግን አስረድተህ ራሱን በቻለ ክስ እንጂ ከውርስ ክርክር ጋር ቀላቅለህ አይደለም እያለ ነው ህጉ
ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለው።
ያው ማስከፈል ነበረብኝ😎
አብርሃም ዮሀንስ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
https://t.me/NegereFej
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2)
Ignorance of the law is no excuse.
civil code article 2035(2)
ነገረ ፈጅ

ቼክን ሲቀበሉ እነዚህን ጥንቃቄዎች ያድርጉ!
#ቀኑ ከነወሩና ዓመት ምሕረቱ በትክክል መጻፉን ክፍያው ወዲያው ሚፈጸምሎት ከሆነ ጊዜው ተራዝሞ አለመጻፉን ያረጋግጡ።
#በቼኩ ላይ ስምዎት የሚጠቀስ ከሆነ በመታወቂያ ስምዎት አግባብ እንደተጻፈ ያመሳክሩ። የፊደል ስህተትንም ቢሆን አቅልለው አይዩ!
#የገንዘቡ መጠን በፊደልም በአሀዝም (በቁጥርም) መመሳሰሉን ያረጋግጡ። ካልተመሳሰሉ የፊደሉ ዋጋ መከፈል አለበት። የንግድ ሕግ ቁጥር 837 (1)
#ቼኩን የጻፈሎት ግለሰብን ፊርማ የሚያውቁት እንደሆነ ትክክለኛ የተለመደ ፊርማውን መጠቀሙን ያረጋግጡ።
ለምንዛሬ ባንክ ሲሄዱ
#ማንነትዎን የሚገልጽ ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ መያዝዎን አይርሱ!
#ቼኩን ግለሰቡ ለመጻፉ ለማረጋገጥ Confirmation ደውለውለት ስልኩ ባይሰራ የጻፈሎት ሰው ጋር ሄደው ስልክ እንዲያነሳ ያድርጉት ቢባሉ እና መጉላላት ቢገጥምዎ በሕግ ላምጪው እንዲከፍሉ ስለሚያስገድድ መብትዎን ይጠይቁ! ምክንያቱም ይህ የባንኮች የመጭበርበር ሥጋትን መቀነሻ መንገድ እንጂ በብሔራዊ ባንክ የወጣ መመሪያ አይደለም። ሁሉም ባንኮች መደወል ሳያስፈልጋቸው ወዲያው ቼኩ በትክክል መጻፉን እና ፊርማው የባለቼኩ መሆኑን አጣርተው ክፍያ ሚፈጽሙበት የገንዘብ መጠን ተመን አላቸው። ስለሆነም ቼክ ቆራጩ ጋር ሄደው እባክህ ስልክህን አንሳላቸው ብለው የመለመን ግዴታ የለብዎትም። ከፋዩ ባንክ ፊርማ ልክ መሆኑን አጣርቶ ሊከፍልዎ ግዴታ ነው።

#በቂ ስንቅ ባይኖረውስ? ብዙ ባንኮች ከፋዩ ጋር ሄደው ብር እንዲያስገባ ይንገሩት ብለው እንደመብት ባለጉዳዮችን ሲያጉላሉ ይስተዋላል። አንዳንዶች የቼክ ተከፋዩ 'ቼኩ ይመታልኝ!' ብለው ሲጠይቁ ለባለቼኩ በመደወል ቼክህ እንዳይመታብህ ብር አስገባለት ብለው የማስማማት ሥራን ይሰራሉ። ይህ ደንበኛቸውን የመጠበቅ እንጂ የሕግ መሠረት ያለው ሃሳብ 'ላምጪው እንዲከፈል ሕግ ያስገድዳል!' የሚለው ሆኖ በቂ ስንቅ የሌለውን ቼክ ወዲያውኑ መምታት እና ለተከፋዩ መመለስ ነው።
#በመጨረሻ የ1 ቼክ የክፍያ መጠየቂያ የጊዜ ገደብ ከተጻፈበት ቀን አንስቶ ለ6 ወራት እንደሆነ አይዘንጉ።
ይግባኝ መብት ነው!
#በመጨረሻ የ1 ቼክ የክፍያ መጠየቂያ የጊዜ ገደብ ከተጻፈበት ቀን አንስቶ ለ6 ወራት እንደሆነ አይዘንጉ።
ይግባኝ መብት ነው!
👍1
Forwarded from ይግባኝ ምክረ ሕግ ⚖️
#አንድ ወጣት በምሽት ሲዝናና ከአንዲት ወጣት ጋር ይግባቡና አብረው በማደር ግንኙነት ይፈጽማሉ። ወጣቶቹ ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው ጽንስ ይፈጠርና ለዚህ ሕጻን ወጣቱ አባትነቱ እንዲታወቅልኝ በማለት አቤቱታ ልታቀርብ ብትፈልግ ልጁ የተፈጠረበት መንገድ የሕግ ዕውቅና ያለው ነው ወይ?
📌ሃሳቡ በጥቂቱ ግርታ ሊፈጠር ቢችልም አሁንም ድረስ አከራካሪ ነውና በጥቂቱ ግልጽ ለማድረግ እንሞክር።
#በሀገራችን የቤተሰብ ሕግ መሠረት መወለድን በተመለከተ አንድ መሠረታዊ መርሕ አለ፤ እርሱም "አባትነት እምነት፤ እናትነት እውነት" የሚለው ነው።
#ለዚህ ማሳያው የተሻሻለው የቤተሰብ ሕጋችን በአንቀጽ 124 ላይ "እናት የተባለችው ሴት ልጁን የወለደችው በመሆኗ ብቻ እናትነቷ ይታወቃል።" በማለት በግልጽ መደንገጉ ስናይ በሀገራችን አንዲት ሴት ለወለደችው ልጅ እናት ናት። በሌላ አገላለጽ እናትነት አጠራጣሪም አከራካሪም አይደለም። ምክንያቱም በአንዳንድ ሀገራት እንዳሉት የማኅጸን ኪራይ ሕጋዊ ፈቃድ ስላልተሰጠው።
#አባትነትን በተመለከተ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 125 ላይ የሚታወቅባቸውን መንገዶች ሲዘረዝር 3 ነጥቦችን አስቀምጧል።
1. ልጁ በሚፀነስበት ወይም በሚወለድበት ጊዜ ከእናትየዋ ጋር በሕግ በታወቀ (ጋብቻ ወይም ሳይጋቡ እንደባልና ሚስት መኖር) ግንኙነትመኖሩ በመረጋገጡ አባትነት ይታወቃል።
2. አባትየው ልጁን ልጄ ነው በማለት ሲቀበል።
3. በፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔም አባትነት እንዲታወቅ ሊደረግ ይችላል። በዚህ ረገድ የሚወሰነው አባትነት መሠረቶቹ፦

ሀ. ልጁ በተፀነሰ ወይም በተወለደ ጊዜ የመደፈር ወይም የመጠለፍ ተግባር ከተፈጸመ፤
ለ. አገባሻለውኝ በሚል የተስፋ ቃል በመስጠት በእናቲቱ ላይ የማሳት ተግባር ከተፈጸመ፤
ሐ. አባት ነው የተባለው ሰው በማያሻማ መልኩ አባት መሆኑ የሚገልጽ ደብዳቤ ወይም ጽሑፍ ከተገኘ፤
መ. በሕግ የታወቀ ግንኙነት ሳይኖራቸው ከእናቲቱ ጋር ቀጣይነት ያለው ግብረ ሥጋ ግንኙነት ከተፈጸመ፤
ሠ. አባት ነው የተባለው ሰው ልጁን በማሳደግ ተግባር እንደአባት ከተሳተፈ ናቸው።
#እነዚህ ልብ ማለት የሚያስፈልገው አባትነትን የማረጋገጫ መንገዶች በቅደም ተከተል የሚተገበሩ ናቸው። ጋብቻ እያለ አባትነት መቀበል አይቀድምም ወይም በፍርድ ውሳኔ አባትነት ይታወቅልኝ አይባልም።
#ለምሳሌ አንዲት ሴት ጋብቻ እያላት አባትየው ልጁን ቢክድ ልትጠይቅ የምትችለው ዳኝነት በሕግ በታወቀ ጋብቻ እያለን ለተወለደ ልጅ አባቱ ነው በማለት የሕግ ግምት ውሳኔ ይሰጥልኝ እንጂ አባትነቱን ይቀበል ወይም በፍርድ ይታወቅልኝ የሚል አይሆንም።
👨🍼አባት የሌለው ልጅ🧒
#እዚህ ላይ የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 107ን መመልከቱ ለርዕሳችን ወሳኝነት አለው። ጋብቻ ሳይኖር ወይም ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ከሚኖሩ ሰዎች ውጪ የሚደረጉ ግንኙነቶች በሕግ ፊት ተቀባይነት የላቸውም። በሕግ ፊት ስለጉዲፈቻና አባትነትን ስለመቀበል የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ ፊት እውቅና በሌለው ግንኙነት የተወለደ ልጅ ከእናቲቱ በስተቀር ከአባቱ ጋር ምንም ዓይነት ሕጋዊ ግንኙነት አይኖረውም።
ጭማሪ ትንታኔዎችን ለመቀጠል የእርስዎን ሃሳብ ያጋሩን።

ሰ/መ/ቁ/211987
ለግዴታ አፈጻጸም ዋስ የሆነ ሰው ባለዕዳው ግዴታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት ዕዳውን ለባለገንዘቡ ሲከፍል ወለድ እና ወጪ ሊጠይቅ የሚችለው ከባለገንዘቡ ጋር ክርክር ተደርጎ ዋሱ ከዋናው ገንዘብ በተጨማሪ ወለድ እና ወጪ ጨምሮ መክፈሉ ሲረጋገጥ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ዋሱ የኪሳራ ጥያቄ ሊያቀርብ የሚችለው ለባለዕዳው ማስጠንቀቂያ መስጠቱ እንዲሁም በባለእዳዉ በኩል የተፈጸመ ጥፋት ወይም ቸልተኝነት መኖሩን ጭምር በማስረዳት ነው።
አብርሃም ዮሀንስ

የአስተዳደራዊ ዳኝነት ችሎት የዳኝነት ሂደት
በሁሉም ደረጃ ያሉ የአስተዳደራዊ የዳኝነት እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ዳኝነት ሲያዩ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እና ሰነዶችን ማንኛውም ሰው እንዲያቀርብላቸው የማዘዝ፣ ምስክሮች ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ የማዘዝ፣ ያስተላለፏቸውን ውሳኔዎችና ትዕዛዞች የማስፈፀም፣ ፖሊስን ወይም አግባብ ያለውን ሌላ አካል የማዘዝ እና የንግድ ዕቃዎች እንዲታገዱ እንዲያዙና እንደሸጡ የማድረግ ሥልጣን አላቸው፡፡
በተጫማሪም የአስተዳደራዊው የዳኝነት ችሎት የአስተዳደር ቅጣት ወይም አስተዳዳራዊ እርምጃ በሚወስንበት ጊዜ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡-
• የተፈፀመውን ጥፋት ባህሪ፣ የቆይታውን ጊዜ፣ የጥፋቱን ክብደትና መጠን
• በተፈፀመው ጥፋት ምክንያት የደረሰውን የጉዳት መጠን፣
• ጥፋቱ የተፈፀመበትን የገበያ ሁኔታ፣
• ከተፈፀመው ጥፋት አጥፊው ያገኘውን ጥቅም፣
• የአጥፊውን የኢኮኖሚ ደረጃ፣
• በምርመራው ወቅት አጥፊው ያደረገውን ትብብር እና የአጥፊውን የቀድሞ ባህሪና የጥፋት ሪከርዶች ከግምንት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት በህጉ ተደንግገጎ ይገኛል፡፡
ሌላው ይግብኝን በተመለከተ በአዋጁ አንቅጽ 39 ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ውህደትን ለመከልከል ወይም የውህደት ፈቃድን ለመሰረዝ ወይም የንግድ ማስታወቂያውን ለማገድ በሰጠው ውሳኔ ወይም በማንኛውም የየዳኝነት ችሎት ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ለይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይቻላል፡፡ በዚህ መሰረት በሚቀርብለት ይግባኝ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡ ሆኖም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 33(3) መሠረት ይግባኝ ሰሚው አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የበሰጠውን ውሳኔ በሚመለከት የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚል ወገን ውሳኔው በተሰጠ በ30 ቀናት ውስጥ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደ ሚችል በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
ማንኛውም መንግስታዊ አካል ያልሆነ ሰው ለአስተዳደራዊው የዳኝነት ችሎት ክስ ሲያቀርብ ወይም ለይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲያቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል እንዳለበት የተደነገገ በመሆኑ የዳኝነት ክፍያ መፈፀም አለበት፡፡ አስተደደራዊ የዳኝነት ችሎቶች ጉዳዮችን በሚያዩበት ወቅት እንደሁኔታው የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
ማጠቃለያ
የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ አስተዳደረዊ ዳኝነት ችሎት እና ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከላይ የተመለከቱ ስልጣንና ተግባራት ያላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ በአስተዳደራዊ ችሎቶቹ ስልጣን ሥር የሚታዩ ጉዳዮች ሲገጥሙ ጉዳዩን ለችሎቶቹ በማቅረብ ዳኝነት የመጠየቅ ልምዱን ሊያዳብር ይገባል፡፡
# በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

#አንዲት ወጣት ሴት በምሽት ከገበያ በምትመለስበት ወቅት የመኪና አደጋ ይደርስባታል። የመኪናው አደጋ ከደረሰባት በኋላ አደጋ አድራሹ ሕክምና ቦታ እሷን ከማድረስ ውጪ ምንም ያደረገው ነገር የለም። የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለፖሊስ በምታመለክትበት ወቅት ፖሊስም ዓቃቤ ሕግም ለምን አትታረቁም? ጉዳዩ እኮ ያን ያክል ወንጀል አይደለም። በማለት ጉዳዩን ያቃልሉባታል። እናም ለምክር ስትመጣ በቀጣይ ያለውን ሃሳብ አካፈልኳት ቢያንስ ለ1 ሰው ይጠቅማልና እነሆ#
🚘💥ዓቃቤ ሕግ አልከስም ቢል ምን ይደረጋል?🚘💥
📌ወንጀል ሁለት ዓይነት ነው።
#1. በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ እና
#2. በመንግሥት ከሳሽነት የሚያስቀጡ።
#በወንጀል ሕግ በአቤቱታ አቅራቢነት በሚያስቀጡ ወንጀሎች ላይ ክስ የማቅረብ ሥልጣንም ግዴታም የዓቃቤ ሕግ ነው። ይህን በማስመልከት የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 40 (1) "ዓቃቤ ሕጉ በተከሳሹ ላይ ክስ ለማቅረብ በቂ ምክንያት መኖሩን የተረዳው እንደሆነ በቁጥር 42 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ክፍል ድንጋጌ በተመለከተው መሠረት ክስ ማቅረብ አለበት።" በማለት ይደነግጋል።
#ዓቃቤ ሕግ ክስ ከማይሰረትባቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው በቂ ማስረጃ ስለሌለ ክስ ለማቅረብ አያስችለኝም የሚለው ነው። ሙሉ ክስ የማይቀርብበቸው ምክንያቶች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 42 ላይ በዝርዝር ተቀምጠዋል።
#ዓቃቤ ሕግ በአንድም በሌላም መልኩ በቂ ማስረጃ እያለው ክስ አላቀርብም ያለ እንደሆነ ምን ይደረጋል? የሚለውን በተመለከተ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በቁጥር 44 ላይ ተደንግጎ ይገኛል።

#ዓቃቤ ሕጉ ክስ ለማቅረብ አያስችለኝም ያለ እንደሆነ ክስ ለማቅረብ መብት ላለው ሰው በራሱ ክስ እንዲያቀርብ በጽሑፍ ይፈቅድለታል። ነገር ግን ይህ ፈቃድ ያልተሰጠው የግል ተበዳይ ዓቃቤ ሕጉ ክስ አይቀርብም በማለት ውሳኔ ከሰጠበት3️⃣0️⃣ቀናት አንስቶ በራሱ ክስ እንዲያቀርብ እንዲፈቀድለት ይጠይቃል።
#የግል ተበዳይ ክሱን የሚያቀርበው በራሱ ኃላፊነትና ወጪ ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 46
#የግል ክስ ለማቅረብ መብት ያላቸው ሰዎች
📌የተበደለው ሰው ወይም ተወካዩ ወይም
📌ባል ስለሚስቱ ወይም ሚስት ስለባሏ ወይም
📌ችሎታ ስለሌለው ሰው እንደራሴው ወይም
📌በሕግ የሰው መብት ስለተሰጠው ማኅበር ወኪሉ ናቸው።
#እንዲህ ከሆነ በኋላ ዓቃቤ ሕጉ የግል ተበዳዩ ወይም ተወካዩ በሚያቀርበው ክስ ላይ የበለጠ ከፍ ያለ ወንጀል ለመሠራቱ ለግል ኩ በቀረበው ማስረጃ የተገለጸ ሲሆን የግል አቤቱታው እንዲቋረጥ ለመጠየቅ ይችላል። ፍርድ ቤትም ክሱን ማስቆን አለበት። የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 48

Forwarded from የህግ ማዕበል/ጠበቃ ውብአለም መስፍን (Wubalem Mesfin)
አንድ ጓደኛ በሰጠኝ አስተያየት መሠረት ተገዶ የመያዝ ህጋዊነትን የማረጋገጥ ጉዳይ (habeas corpus) አስመልክቶ የዳኝነት ስልጣኑ ተለይቶ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያልተሰጠ በመሆኑ
የሚቀርብ አቤቱታን ተቀብሎ የማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5(1(ኘ)) እና
11(1)፣ (3) በማለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 230167 ውሳኔ መሰጠቱን አመላከተኝ።
ይህም ውሳኔ አግባብነት ያለው ነው የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ የሰበር ውሳኔዎች አስገዳጅ መሆናቸውን ተከትሎ አካሌ ነፃ ይውጣልኝ አቤቱታ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሚቀርብ መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 17 በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ማንኛውም ሰው ነፃነቱን እንደማያጣ ይደነግጋል።
በተጨማሪም ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ሊያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይንም ሳይፈረድበት ሊታሰር እንደማይችል በግልፅ ይደነግጋል።
ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀችው የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (ICCPR) አንቀፅ 9 ማንኛውም ሰው ነፃነቱ እና ደህንነቱ ተከብሮ የመኖር መብት እንዳለው እና በዘፈቀደ ከሚደረግ እስር ሊጠበቅ እንደሚገባ ይደነግጋል።
ሕግ አስከባሪዎች ማንኛውም ሰውን በቁጥጥር ስር ከማዋላቸው በፊት የዜጎች ነፃነትን ለመጠበቅ የወጡ ሕጎች የጣሉባቸውን ግዴታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
ምስል-በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተቀናበረ
#AHRE( Association for Human Rights in Ethiopia)
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣🔴ሕግ
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በመዝገቡ ተሳታፊ ለመሆን የሚቀርቡ አቤቱታዎች ስነ-ስርዓት
የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 78
በመዝገብ ላይ ተከሳሽ የነበረ ሰው(የተፈጥሮ/በህግ ሰውነት የተሰጠው) ለቀረበበት ክስ መልስ ሳይሰጥ ወይም ተገቢውን ክርክር ሳያደርግ ቀርቶ በሌለበት ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ የተሰጠበት እንደሆነ እነዚህ እንዲነሱለት ማመልከቻ ማቅረብ ወይም ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው:-
1. ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ እንደተሰጠ ባወቀ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ከሆነ
2. የፍርድ ቤት መጥሪያ በአግባቡ እንዳልደረሰው ካስረዳ
3. ወይም ቀርቦ መከራከር ያልቻለው በበቂ ምክንያት መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት ከቻለ ብቻ ነው።
ይህ አንቀፅ ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ሲነበብ ብቻ ላልተገኘ ሰው ተፈፃሚ አይሆንም።
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358
በመዝገብ ላይ ተከራካሪ መሆን የሚገባቸው ሰዎች በተለያየ ምክንያት ተሳታፊ ሳይሆኑ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል። ለዚህ መፍትሄ እንዲሆኑም የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ የተለያዩ የመፍትሄ አንቀጾች አስቀምጧል። ከነዚህ ውስጥ አንዱም አንቀፅ 358 ነው። የዚህ አንቀጽ ተጠቃሚ ለመሆንም :-
1. ጣልቃ ለመግባት አቤቱታ የሚያቀርበው ሰዉ በክርክሩ ተሳታፊ መሆን የሚገባው/የሚችል
2. የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካው ሰው መሆን ያለበት ሲሆን በዋነኝነት መቃወሚያው መቅረብ የሚችለው መብቴን ይነካዋል ያለው ፍርድ ከመፈጸሙ በፊት ነው።
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 418
አንድ ሰው የመዝገብ ተካፋይ/ተከራካሪ ባይሆንም ነገር ግን በክርክሩ ምክንያት የሱ የሆነ ንብረት እንደመያዣ/ ማስከበሪያ በተከራካሪ ወገኖች ቀርቦበት ሊሆን ይችላል። በዚህ ንብረት ላይ ያለውንም መብት ለማስጠበቅ በዚህ አንቀፅ መሠረት አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ሊያቀርብ ይችላል። አቤቱታውም:-
1. መዝገቡ አፈፃፀም እስኪደርስ የዘገየው በበቂ ምክንያት መሆኑን ማስረዳት
2. በፅሁፍ ሆኖ ፍርዱን ለሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት
3. በንብረቱ ላይ ያለውን የተቀዳሚነት መብት ወይም ባለይዞታነቱን የሚያረጋግጥ የፅሁፍ ማስረጃ አብሮ ማያያዝ አለበት።
አቤቱታውን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ቢያደርገው አቤት ባዩን በንብረቱ ላይ አዲስ ክስ ከመመስረት አያግደውም።