Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (Wubalem Mesfin)
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
በፍትሐብሄር ጉዳይ በሚነሱ ክርክሮች ይርጋ የማያግዳቸው የህግ መከራከሪያዋች ምንድናቸው?
♨️♨️♨️
የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ በተወሰነው ወይም በተገደበው ጊዜ ውስጥ ስልጣን ላለው አካል እንዲቀርቡ ግዴታን በማስቀመጥ መብቴ ተጣሰብኝ የሚል ወገን ዳተኛ ሳይሆን በትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል መሆኑ ይታወቃል።
ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዬች ከንብረቶቹ ልዩ ባህሪና የመንግስት ፖሊሲ አንፃር ህግ አውጪው በይርጋ እንዳይታገዱ አድርጎ ያስቀመጣቸው የፍትሀብሄር ጉዳዬች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦
#የመፋለም ክስ ( petitory action)
♨️♨️♨️🛑🛑🛑🛑♨️
ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡
ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡
ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....) ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን።
በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600)
N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል።
#ህገ ወጥ ውል (unlawful contrat)
♨️🛑🛑🛑🛑♨️♨️♨️🛑
እንድ ውል የፀና ውል ለመሆን መሟላት ከሚገባው አንዱ ነጥብ ውሉ ህጋዊ በሆነ ጉዳይ ላይ የተመሰረተ መሆን የሚገባው እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ 1678 ይደነግጋል። አንድ ውል ህገ ወጥ ውል ነው የሚባለው ደግሞ ተዋዋዬቹ የተዋዋሉበት መሰረታዊ ጉዳይ ዓላማ በመሰረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዴታ እንዲፈጥሩበት በህግ ያልተፈቀደ ወይም በህግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው።
አንድ ውል የተመሰረተበት መሰረታዊ ጉዳይ (object of contract) በህግ ክልከላ የተደረረበት በሆነ ጊዜ ውሉ በህግ ፊት እንደሌለና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል (null and void contrat) እንዲሁም ችግሩን በማስተካከል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የማይቻል ነው። ለምሳሌ፦ የመሬት ሽያጭ ውል፣ በሰው ለመነገድ የተደረግ ውል፣ ወንጀል ለመፈፀም የተደረገ ውል......
ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ ደግሞ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በይርጋ የሚታገዱ አይደሉም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 43226)
N.B= ይህ ሲባል ግን የህጉን መስፈርት ያላሟሉ ውሎች (illegal contract) ከህገ ወጥ ውል በተለየ ሁኔታ ታይተው የይርጋ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆንባቸው መሆኑን መረዳት ይገባል።
#የመንግስትን መሬት የማስመለስ ክስ
♨️♨️🛑🛑🛑♨️♨️🛑
ግለሰቦች በፌደራሉ እና በክልሉ መንግስት በወጡ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር አዋጅ በሚደነግጉት መሰረት በህጋዊ መንገድ ሳይሰጣቸው ከህግ ውጪ የወል ወይም የመንግስትን መሬት ይዘው መቆየታቸው እና የመሬቱ ባለይዞታ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማግኘታቸው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ ሊያደርጋቸው አይችልም። በወረራ የተያዘ የመንግስት መሬትም ይርጋ የሌለው መሆኑን የአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 በግልፅ ያስቀምጣል።
በመሆኑም ከህግ ውጭ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን መኖራቸውን ሲረዳ መሬት አስተዳደርም ሆነ የመንግስት ወኪል የሆነ አካል መሬቶቹን ለማስመለስ የሚያቀርበው ክስ በይርጋ የሚታገድ አይደለም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 93013 እና 96203 ያልታተሙ)
#በህገ ወጥ መንገድ የተያዘ የግለሰብ ይዞ መሬት
🛑🛑🛑🛑🛑🛑♨️♨️
ከላይ እንደተመለከትነው ህገ ወጥ ውልን መሰረት አድርጎ የግለሰብን መሬት በያዘ ሰው ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የሌለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 መሰረት ህጉ በማይፈቅድበት መንገድ በሀይልም ሆነ በህገ ወጥ አግባብ የገጠር መሬትን ይዞ የተገኘ ግለሰብ ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የለውም።
N.B= በህገ ወጥ መንገድ የሚለው ሀሳብ በህግ ተቀባይነት በሌለው አኳኋን የያዘን በሚመለከት እንጂ የህጉን መስፈርት ባላሟላ ውል ወይም ተግባር (illegal contrat) አማካኝነት የተያዘን መሬት የሚመለከት አይደለም። ምክንያቱም መሬቱን የያዘው በህጉ በተፈቀደ የውል ተግባር ሆኖ የሚፈለገውን ፎርማሊቲ ወይም መስፈርት አለማለቱ ብቻ አያያዙ ህገ ወጥ ነው የሚያስብል ስላልሆነ ነው።
#የአደራ ውል
🛑🛑🛑🛑♨️♨️
አደራ ተቀባይ በአደራ የሚጠብቀውን ዕቃ የሚመልስበት የጊዜ ገደብ በውል ተመልክቶ ከሆነ ይህ ጊዜ ሲያበቃ ዕቃውን መመለስ ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2781(1) የተመለከተ ሲሆን በውል ላይ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ከሌለ ግን አደራ ሰጪው እንደጠየቀ ወዲያውኑ እንደሚመለስ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2989(1) ስር ተመላክቷል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው አደራ ተቀባይ ዕቃውን የሚመልስበት የጊዜ ገደብ ከሌለ በቀር አደራ ሰጪው በአደራ እንዲቀመጥ የሰጠው ዕቃ ያለምንም የጊዜ ገደብ በማንኛውም ጊዜ እንዲመለስለት መጠየቅ የሚችል መሆኑን ነው።
#የውርስ ሀብት ክፍፍል
🛑♨️♨️♨️♨️🛑
ወራሾች ተለይተው እና የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ነገር ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየን የውርስ ሀብት በማናቸውም ጊዜ መጠየቅ እንደሚችልና በይርጋ የሚታገድ እንዳልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1060 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል።
እንዲሁም ከውርስ ሀብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሀብቱን በእጁ አድርጎ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የውርስ ንብረት በጋራ ይዞ ከቆየ ሰው ላይ የውርስ ድርሻዬን ልወቅ ወይም ይለይልኝ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት አግባብ የለም። Join @henoktayelawoffice
https://t.me/ethiolawtips
🛑👆👆👆👆👆👆👆👆

Forwarded from Click Ethiopian Laws⚖
ሰ/መ/ቁጥር---228231 የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
የተራ ዋስትና እና የአንድነት ዋስትና ልዩነት
በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብት ለመጠቀም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1935(1) ዋሱ እንደ ተከሰሰ ወዲያውኑ ባለገንዘቡን ከባለዕዳው ጋር ተከራከር ካላለ በቀር ባለገንዘቡ ከዋናው ባለዕዳ ጋር ለመከራከር ግዴታ የለበትም በማለት ሲደነግግ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1936 ደግሞ በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የሚለውን መብት ለመጠቀም እንደቅድመ ሁኔታ መሟላት ያለባቸው ነገሮች ያስቀመጠ ሲሆን ይኸውም ክርክሩን የሚጠይቀው ዋስ ለባለገንዘቡ የዋናውን ባለዕዳ ንብረቶች መምራትና ለዚሁም ክርክር የሚያስፈልገውን በቂ ወጪ አስቀድሞ ለባለገንዘቡ መስጠት አለበት በማለት አስቀምጧል።
#Click Ethiopian Laws
ይህም የሚያስገነዝበን ዋሱ በቅድሚያ ከባለዕዳው ጋር ተከራከር የሚለውን መብት ለመጠቀም፥
አንደኛ ክሱ እንደቀረበበት ወዲያውኑ በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር በማለት ማንሳት አለበት፤
ሁለተኛ በደፈናው ባለዕዳው ንብረቶች ማለት ብቻ ሳይሆን ከክርክር ነጻ የሆኑ የባለዕዳው ንብረቶችን ቆጥሮ ወይም መርቶ ማሳየት አለበት፤
ሦስተኛ ለክርክር የሚያስፈልገውን በቂ ወጪ መዴቦ ለባለገንዘቡ መስጠት ይኖርበታል፡፡
ከእነዚህ ሦስት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ እንኳ ካልተሟላ ባለገንዘቡን በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብቱን እንደሚያጣ በግልጽ ያሳያል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የክፍያው ጊዜ ደርሶ ገንዘቡ ያልተከፈለው ባለገንዘብ ቢፈልግ ባለዕዳውንና ዋሱን በአንድ ሊይ መክሰስ ወይም ባለዕዳውን ትቶ ዋሱን ብቻ መክሰስ የሚችል ሲሆን ተራ የሆነ ዋስትና ግዴታ የገባው ዋስ የአንድነት ዋስትና ከገባው ዋስ የሚለየው ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብቱን ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ በአግባቡ መጠቀም ሲችል ብቻ መሆኑን ነው፡፡
ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ከባለዕዳው ጋር በቅድሚያ ተከራከር የማለት መብቱን ያልተጠቀመ ተራ ዋስ በተናጠልም ሆነ ከባለዕዳው ጋር በጋራ የዋስትና ግዴታ የገባውን ዕዳ አልከፍሌም ማለት የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም፡፡
#Click Ethiopian Laws
👇👇👇⚖⚖⚖👇👇👇

👍1
Forwarded from ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️ (Daniel Fikadu)
10 መሰረታዊ የውል አተረጓጎም ደንቦች
***
በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)
***
ውል ቅኔ መሆን የለበትም። በተቻለ መጠን ለሁሉም ተዋዋይ ወገን እንዲሁም ለሶስተኛ ወገኖች ጭምር ግልፅ በሆነ መንገድ መደረግ አለበት ። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በተለያየ መንገድ የሚደረጉ ውሎች ግልፅነት የጎደላቸው ይሆኑና የግጭት ና ያለሙግባባት መንስኤ ሆነው ለትርጉም አስማሚ ወይም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ይህ ሲሆን ፍርድ ቤቶች ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ መሰረታዊ የሆኑ የውል አተረጓጎም ደንቦች አሉ። እነሱን እጠር አርገን ከተያያዥ የሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉሞች ጋር እንመልከት:
የውል አተረጓጎም መሰረታዊ ደንቦች
1. ውሉ ግልፅ ከሆነ ምንም አይነት ትርጉም አያስፈልግም። ( If the contract is clear no need of interpretation ) /፩/
2. የውሉ ትርጉም ውጤት መገኘት ያለበት ከራሱ ከውሉ እንጂ ፣ ውሉ ወይም ግዴታው ከትርጉሙ ሂደት መመንጨት የለበትም። / The interpretation of the contract must come from the contract not the contract from the interpretation./ በሌላ አማርኛ ፍርድ ቤት ውልን በመተርጎም ስም ያልነበረ ውል ወይም ግዴታ ሊፈጥርና ሊሰራ አይችልም።
3. የቅን ልቦና አተረጓጎን ደንብ (1732) :- ማንም ሰው የራሱን መብት በአግባቡ ከመጠቀም አልፎ በሌላው ተዋዋይ ላይ አላስፈላጊ ጉዳት የማድረስ ፍላጎት የለውም የሚል አወንታዊ መነሻ ሃሳብ ( positive premise) አለ። ከዚህ ተቃራኒ የሄነ ሃስብ ይዞ ከቅን ልቦና በተቃራኒ ጉዳት ለማድረስ ያለው ተዋዋይ ወገን ካለ ህግ በመርህ ደረጃ ጥበቃ ያደርግለታል። /፪/
4. በተገቢው መንገድ ያልተብራሩ ሃሳቦችን አተረጓጎም በተመለከተ ለልማዳዊ አሰራሮች እና አፈፃፀሞች በቂ ትኩረት ሊቸረው ይገባል። ውል ከአካባቢው አሰራርና ተቀባይነት ካላቸው ልምዶች አንፃር እየተገናዘበ መተርጎም ይኖርበታል።
5. አሻሚ የሆኑ ቃላት እና ሃረጎችአተረጓጎም፣
" A plain contract means what it says "
ግልፅ የሆነ ውል የውሉ ቃላት በቀጥታ የሚያስተላልፈው ትርጉም ብቻ ነው
በተቃራኒው የውሉ ሃሳብ ግልፅ ካልሆነና አሻሚ ከሆነ ግን የተዋዋዮች ሃሳብ ምን እንደሆነ ለማወቅ ተገቢውን ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። ይህም ማለት ትርጉም በመስጠት ሂደት ውሉን እንዲተረጉም የቀረበለት አካል ትርጉሙን የሚፈልገው በውሉ ውስጥ ከሚገኙ ቃላት ላይ ብቻ አይደለም ። ውሉ ለድርድር ( ለስምምነት ) በቀረበበት ጊዜ ( Offer and Acceptance ) ፣ እንዲሁም የውሉ ድርድር በሚካሄድበት ጊዜ ፣ ድርድሩ በቀረበበት እና ተቀባይነት ባገኘበት ጊዜ ፣ ከዚያም በፊት የተከናወኑ ቀዳሚ ግንኙነቶች በተደረጉበት ጊዜ የተደረጉ እና የተከናወኑ ጉዳዮች ሁሉ ተገናዝበው ትርጉም ሊሰጣቸው ይገባል።
አሻሚ የሆነው ቃል አጠቃላይ አነጋገር ከሆነ በትርጉም የሚወሰደው የቃሉ የተለመደ ትርጉም ነው።
በቅጡ ተለይቶ ያልታወቀ የውል ፍሬ ነገር ( Object ) ካለ ሁሉንም የውሉን ቃላት አረፍተ ነገሮች አንዱን ከአንዱ በማገናዘብ የመጨረሻ ትርጉም ላይ መድረስ ይቻላል።/፫/
6. ከውሉ ባህርይ ጋር የሚቀራረበው ትርጉም ከማይቀራረበው ይመረጣል።
7. ውሉን ዋጋ ከሚያሳጣው ትርጉም ይልቅ ውጤታማ የሚያደርገው ይመረጣል።/፭/
8. የውሉን ባለመብት ከሚጠቅመው ባለዕዳውን የሚደግፈው ይመረጣል።/፬/
9. ውሉን ካዘጋጀው ወገን ይልቅ ውሉን ላላዘጋጀው የሚጠቅመው ትርጉም ይመረጣል።
10. ያለዋጋ በተደረገ ውል ( Gratuitous contract) በውሉ መብት ካገኘው ሰው ይልቅ ውሉ ግዴታ ለሚጥልበት ሰው የሚጠቅመው ትርጉም ይመረጣል።/፮/ /፯/
ተዛማጅ የሰበር ውሳኔዎች
/፩/ ሠ/መ/ቁ 15662 ( ቅፅ 4) - ውሉ ግልፅ በሆነ ጊዜ ግልፅ ሆኖ ካለው ሃሳብ በመራቅ የተዋዋዮቹ ፍቃድ ምን እንደነበር ዳኞች ለመተርጎም አይችሉም።
/፪/ ሠ/መ/ቁ 25165 (ቅ.7) የቅን ልቦና መከራከሪያን ወደጎን በመተው ውልን ተርጉሞ አንድን ውል ማፍረስ ትክክል አይደለም።
/፫/ ሠ/መ/ቁ 38544 (ቅፅ 10) - ተዋዋዮች ውላቸውን ከመዋዋላቸው አስቀድመው ወይም ከተዋዋሉ በኋላ የነበሩትን ሁኔታዎች ፣ የፈፀሙትን ተግባራት በማመዛዘንና ሃሳባቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ መሞከር ፣ የውሎችን ቃላቶች አንዱን ከአንዱ ጋር እያዛመዱ መመልከት ለውሉ ጉዳይ አግባብ ያለው ትርጉም ለመስጠት ተገቢ ነውና
/፬/ ሠ/መ/ቁ 41893 (ቅፅ 10) - የስጦታ ውል ሊተረጎም የሚገባው በውሉ ውስጥ የሚገኘውን አንድ ሃረግ ነጥሎ በማውጣት ሳይሆን የውሉን አጠቃላይ ይዘት በመመልከት ነው።
/፭/ ሠ/መ/ቁ 27869 (ቅፅ 5 ) - የቤቱ መለያዎች እና ቦታ ሳይጠቀስ አንድ ቤት ለማክበር በአይነት መዋጮ ቢሄንና ሰውየው ያለው አንድ ቤት ብቻ እንጂ ሌላ ቤት የሌለው ከሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 መሰረት ሲተረጎም በውሉ ላይ የተገለፀው እያዋጣው ያለውን አንድ ቤት እንደሆነ መተርጎም አለበት። ስመ ንብረቱ በማህበሩ ባይመዘገብም በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2878 መሰረት ለ3ተኛ ወገን መቃወሚያ እንዳይሆን ይከለክላል እንጂ መዋጮውን ውጤት አያሳጣውም።
/፮/ ሠ/መ/ቁ 103910 ( ቅፅ 10 ) - በውሉ ውስጥ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም የውሉ ድንጋጌ መተርጎም ያለበት በውሉ አስገዳጅ ( ባለመብት ) የሆለው ወገን በሚጠቅም ሁኔታ ሳይሆን በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1738 መርህ መሰረት በውል ተገዳጅ ለሆነው ሰው ምቹ በሚሆንበት አኳኋን ነውና
/፯/ ሠ/መ/ቁ 107990 (ቅ.17) - በግልፅ የሰፈረ የውል ቃል ባይኖርም ስጦታ ሰጪው በድህነት ላይ ወድቆ እያለ ስጦታ ተቀባይ የምክር ግዴታ ያለበት ሲሆን ስጦታ ተቀባይ ከስጦታ ሰጪ የተቀበለውን የእርሻ መሬት እየተጠቀመ በውለታ ቢስነት ስጦታ ሰጪውን የሚጎዳ ተግባር ፈፅሞ ከተገኘ ስጦታ ሰጪው ውሉ እንዲፈርስለት የመጠየቅ መብት አለው።

👍2
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ባልና ሚስት በጋብቻ መካከል የሚያደርጉት የስጦታ ውል ተቀባይነት አለው?
በጋብቻ መካከል በየትኛውም ንብረት ላይ ባልና ሚስት እርስ በራስ የሚያደርጉት የስጦታ ውል ፍ/ቤት ቀርቦ ካልፀደቀ በቀር በህግ ፊት ተቀባይነት የለውም።ሲል የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ.መ.ቁ. 158292 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
Telegram 🔥👇
https://t.me/ethiolawtips
በጋብቻ መካከል በየትኛውም ንብረት ላይ ባልና ሚስት እርስ በራስ የሚያደርጉት የስጦታ ውል ፍ/ቤት ቀርቦ ካልፀደቀ በቀር በህግ ፊት ተቀባይነት የለውም።ሲል የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ.መ.ቁ. 158292 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
Telegram 🔥👇
https://t.me/ethiolawtips
መኪናን ከባለቤቱ ተከራይቶ ሲጠቀም የነበረው ግለሰብ ጉዳት ቢያደርስ የጉዳት ካሳ መክፈል የሚገባው የመኪናው ባለቤት ወይንስ መኪናውን ከባለቤቱ ተከራይቶ ሲገለገልበት የነበረ ተጠቃሚ?
የመኪና ባለቤት መኪናውን አከራይቶ: መኪናው በተከራዩ እጅ እያለ ጉዳት ቢያደርስ ተጠያቂው እና የጉዳት ካሳውን መክፈል የሚገባው የመኪናው ተከራይ ብቻ ነው:: የመኪናው ባለቤት በአንድነትና በነጠላ ከተከራዩ ጋር ተጠያቂ አይሆንም::
የሰ/መ/ቁ 230493 ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም የተሰጠ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ነው።

Telegram
Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
@lawyerhenoktaye (LL.B LL.M) 0953758395 ☎️
Youtube👇
https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg
Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@lawyer_henok.t?_t=8iQ7AEnkz4v&_r=1
Facebook 👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100071372553654&mibextid=ZbWKwL

Forwarded from ETHIOPIAN TAX AND CUSTOMS LAW CORNER የኢትዮጵያ ታክስ እና ጉምሩክ ሕግ
ከተሽከርካሪ ጫረታ ጋር በተያያዘ ለጥንቃቄዎ!
◘ የጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ሕግን ከመተላለፍ ጋር ተያይዞ የተወረሱ ዕቃዎችን እና በአስመጪዉ የተተዉ ዕቃዎችን በጫረታ መሸጥ እንዳለበት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 63 ላይ ተደንግጓል፡፡ ይህን የጫረታ ሽያጭና ሌሎች የማሶገጃ ዘዴዎችን ዝርዝር አፈጻጻም አስመልክቶ የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 167/2012 ወጥቶ ሥራ ላይ ዉሏል፡፡
◘ በመሰረቱ ጫረታ/Auction/ የዕቃ ሽያጭ የሚካሄድበት የስርዓት ዓይነት እንደመሆኑ መጠን የንብረት መብት የሚተላለፍበት ልዩ የዉል ዓይነት ነዉ፡፡ የንብረት መተላለፍ ካለ ንብረቱን የሚያስተላልፍ ሻጭ እና ገንዘብ ከፍሎ ንብረቱን የሚረከብ ገዢ የሚባሉ ሁለት ተዋዋዮች እንደመኖራቸዉ መጠን የዉል ግንኙነቱ የሚገዛዉ በዋናነት በፍትሐብሔር ሕጉ ከቁጥር 2266-2402 ጀምሮ ባሉት ጠቅላላ የሽያጭ ድንጋጌዎች ሲሆን እንዲሁም በንዑስ ክፍል 7 ከአንቀጽ 2403-2407 ጫረታን በሚመለከቱ ልዩ የሽያጭ ድንጋጌዎች ነዉ፡፡ እንግዲህ ከላይ የተገለጸዉ የጉምሩክ ዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 ከነዚህ ሽያጭን ከሚመለከቱ ጠቅላላ ድንጋጌዎች በተጨማሪነት ጉምሩክ የሚያካሂደዉን የዕቃዎች ሽያጭ አፈጻጸም ሂደት እና በጉምሩክ ኮሚሽን እና በገዢዎች መካከል የሚመሰረተዉን/የሚቋቋመዉን/ የሽያጭ ዉል ስርዓት በከፊል የሚገዛ ልዩ ሕግ ነዉ ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ መመሪያ ድንጋጌዎች በሚፈጠረዉ የግዢ ዉል ላይ ያላቸዉ ተፈጻሚነት አድማስ ምን ያህል ነዉ? የሚለዉ ሲታይ ዉስንነት ያለዉ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የዚህም ምክኒያቱ በዋናነት መመሪያ ቁጥር 167/2012 ሁነኛ ዓላማ የሚፈጠረዉን የዉል ግንኙነት መግዛት ሳይሆን በዋናነት የጫረታ ሽያጭ ዓይነትን ጨምሮ አጠቃላይ የንብረት መስወገጃ ስርዓትን መዘርጋት በመሆኑ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ የሽያጭ ዉል መቼ ተፈጽሟል ማለት እንደሚቻል( የመመሪያዉን አንቀጽ 10(5) ይመልከቱ)፣የሽያጭ ክፍያ እና የዕቃ እርክክብ መቼ እንደሚደረግ እና ተዋዋዮች ምን ምን ግዴታ እንዳለባቸዉ የተወሰኑ ድንጋጌዎች ተቀምጠዋል (አንቀጽ 13 ይመልከቱ)፡፡በመሆኑም የሽያጩን ዉል የሚገዙ አንዳንድ ድንጋጌዎችን ይዟል ማለት ይቻላል፡፡
◘ ይሁን እንጂ የጉምሩክ ኮሚሽን የሽያጩን ዉል አስመልክቶ ምን አይነት ግዴታዎች ይጠበቁበታል? ግዴታዉን ባይወጣስ ምን መፍትሄ አለ? የሚሉትን ከዉል አፈጻጸም ጋር ተያይዘዉ ያሉ ጥያቄዎችን አስመልክቶ መመሪያዉ የሚለዉ ነገር የለም፡፡ በመሆኑም ወደ ፍትሃብሔሩ የሽያጭ ሕግ ድንጋጌዎች መፍትሄ መፈለግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ክርክር የሚያስነሱ ከተሽከርካሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሁለት የጉምሩክ ኮሚሽን ግዴታዎችን እና ግዴታዉን ባይወጣ የሽያጭ ዉልን አስመልክቶ መፍትሄዎች ለማየት እንሞክራለን፡፡
◘ አንዱ ግዴታ ከላይ በተገለጸዉ አዋጅ አንቀጽ 63(2) መሰረት ጉምሩክ ሽያጭ ከፈጸመ በኋላ በተሸጠዉ ዕቃ(ተሽከርካሪ ላይ) የባለቤትነት መብት ለገዢዉ መተላለፍ ይችል ዘንድ አስፈላጊ ማስረጃ መስጠት እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ ይህም መረጃ በዋናነት ዕቃዎች በጨረታ ከጉምሩክ ለመገዛታቸዉ የሚያሳይ ማስረጃ ሲሆን ዜሮ ዴክራሲዮን መስጠትንም ይጨምራል( የመመሪያዉን አንቀጽ 14(8) ይመልከቱ)
◘ ሁለተኛዉ ግዴታ በፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 2281ና 2282 ላይ የተደነገገዉ ሲሆን ይህም ሻጭ( የጉምሩክ ኮሚሽን) በተሸጠዉ ነገር ላይ የማያስነካ መብት ለገዢዉ ለማስተላለፍ (Obligation of transferring unassailable rights ) አስፈላጊ ተግባር የመፈጸም ሲሆን በተሸጠዉ ተሽከርካሪ ላይ መብት አለኝ የሚል ሰዉ ቢኖር ለገዢዉ መድህን የመሆን ግዴታ ነዉ፡፡ ነገሩን በምሳሌ ለማስረዳት፡- የጉምሩክ ኮሚሽን ከጉምሩክ ሕግ መተላለፍ ጋር ተያይዞ አንድ ተሸከርካሪ ይዞ ሊወርስ ይችላል፡፡ የተያዘዉ ተሽከርካሪ ባንክ ወይም ግለሰብ ላበደረዉ ብድር ወይም ጉምሩክም ሆነ የገቢዎች ሚኒስቴር ለሚፈልጉት የታክስ ወይም የታክስና ቀረጥ ዕዳ የተያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህን ጊዜ ሻጭ ጉምሩክ እግዱን በማስነሳት የባለቤትነት መብት እንዲተላለፍ እርምጃ ሊወስድ የሚገባ ሲሆን ይሄን ማድረግ ካልቻለ እንደነገሩ ሁኔታ ገዢዉ ዉሉ በግድ እንዲፈጸም፣እንዲፈርስ የመጠየቅ፣በገዢ ላይ ለሚደርስ ኪሳራ ካሳ የመካስ ግዴታ ጨምሮ ገዢ የከፈለዉን ዋጋ የመመለስ ግዴታዎች አሉበት (የፍ.ሕ.ቁ. 2329፣2284፣2341 እና 2360 ይመለከቷል)
◘ ምንም እንኳ የጉምሩክ ኮሚሽን ተገቢዉን ጥንቃቄ ያደርጋል ተብሎ ቢታመንም ይሄ ሳይሆን ቀርቶ የጉምሩክ ኮሚሽን የታገደ ተሽከርካሪ በጫረታ ቢሸጥ በጫረታ የገዛዉ ገዢ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ በፍትህ መንበር ሊያገኝ የሚችላቸዉ መፍትሄዎች ሲሆን ፍርድ ቤት ሄዶ መብትን ማስጠበቅ ያለዉ ዉጣ ዉረድ እና ወጪን ከማስቀረት አንጻር ገዢዎች የሚገዙትን ተሽከርካሪ አስመልክቶ ከሚመለከተዉ አካል ቀርበዉ ዕግድ የሌለበት መሆኑን አጣርተዉ ቢጫረቱ ካላስፈላጊ ዉጣ ዉረድ እና እንግልት ራሳቸዉን ያድናሉ የሚል ምክር ነዉ፡፡

Forwarded from እንደ ❤️ (kidane M)
ክፉ ምላስ በሕግ ዐይን - በመሳደብዎ ሕግ እንደሚቀጣዎ ያውቃሉ?
******
ለዛሬው የሕጉ ምን ይላል ጽሑፍ መነሻ የሆነው በዚሁ ኢቢሲ ሳይበር ላይ "ክፉ ምላስ - የስድብና የመጥፎ ቃላት ወረርሺኝ በዘመናችን" በሚል እርዕስ የወጣው ጽሑፍ ላይ የእስልምና፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የፕሮቴስታንት እምነቶች ሊቃውንት እንደየ ሃይማኖታቸው አስተምህሮዎች የስድብ እና ማዋረድ ድርጊቶች በመንፈሳዊም በዓለማዊም እሳቤ የተጠሉ በመሆናቸው ከክፉ ምላስ እንድንታቀብ ያስትላለፉት መልክት ነው።
ለመሆኑ ስድብ እና ማዋረድ በሕግ ዐይን ምን ዓይነት ኃላፊነት ያስከትላሉ?
“የምላስ ወለምታ በቅቤ አይታሽም!!” ይባላል - ባለማስተዋል ሳት ብሎን የሰውን ክብር መንካት እንኳን በቀላሉ እንደማይመለስ ለመግለጽ።
አሁን አሁን ግን ከማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መስፋፋት ጋር የስድቡም፣ የመሳደቢያ ዘዴ እና ዓይነቱም የበዛ ይመስላል። ስድብ ጥግብ ማለት ከፈለጋችሁ የትም አትሂዱ፤ እዚሁ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የሆነች አነጋጋሪ ነገር ጻፉ ወይም አንዱ ጽሑፍ ላይ የሆነ አስተያየት ስጡ። ለመጻፍ ቀርቶ ለማሰብ የሚከብዱ ፀያፍ ቃላት እንደ ጉድ ይዘንቡባችኋል።
“ይህ ሰው ለምን ሰደበኝ? በሐሳቤ ካልተስማማ መተቸት ያለበት ሐሳቤን አይደለም እንዴ?” ብላችሁ ብትጠይቁም መልስ የለም።
ይሄን ጽሑፍ አንብባችሁ ወደ አስተያየት መስጫው ወረድ ስትሉ ጉድለትን የሚጠቁሙ፣ የሚያነጋግሩ፣ የሚያበረታቱ፣ የሚያርሙ፣ የሚያዝናኑ መልካም አስተያየቶች እና ጥያቄዎችን እንደምታዩት ሁሉ ከተነሣው ጉዳይ ጋር የማይገናኙ ፍረጃዎችን እና ስድቦችም ቀላል እንዳይደሉ መታዘብ ትችላላችሁ።
አንዳንዶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በስድብ አንደኛ ሲሆኑባችሁም “ይህ ነገር በባህልም፣ በሃይማኖትም፣ በሕግም ክልክልነቱ ቀረ እንዴ?!” ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ። ስድብ ግን የተፈቀደ እስኪመስለን ቢጧጧፍም ወንጀል ነው።
በወንጀል ሕጋችን በአንቀፅ 615 ሥር ስድብ እና ማዋረድ በክብር ላይ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መሐል አንዱ ሆኖ ተደንግጓል።
ማንም ሰው ተበዳዩን በቀጥታ በመናገር፣ በአሽሙር ስድብ ክብሩን ከነካ፣ በምልክት ወይም በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ካዋረደ እና ተበዳዩ ክስ ካቀረበበት በወንጀል ይቀጣል። ቅጣቱም ከሦስት ወር የማይበልጥ እስራት ወይም እስከ ሦስት መቶ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ነው።
ተሳዳቢዎችን በሦስት ከፍለን ማየት እንችላለን
የመጀመሪያው ‘ተራ ተሳዳቢ’ ነው። እንዲያው ልማድ ሆኖበት አፉን የሚበላው፣ ያገኘውን ሁሉ የሚሳደብ፣ ሚሰድበው ቢያጣ ራሱን ወይም እንሰሳትን፣ ግዑዝ ነገሮችን ሁሉ የሚዘልፍ የስድብ ሱሰኛ ነው።
ሁለተኛው ‘ሰድቦ ለሰዳቢ የሚሰጥ’ ነው። በአደባባይ ሰው እስኪሰማ ጠብቆ ተሳድቦ እንድትሰደቡ ለቢጤዎቹ የሚያቀብላችሁ ወይም “ልክ ልኩን ነገርኩት፣ ሙልጭ አደረኩት፣ እስኪበቃው አስታጠኩት!” እያለ የተሳደባቸውን ስድቦች በየአጋጣሚው እያወራ የሚነዛ ነው።
ሦስተኛው ‘ሰድቦ አሳዳቢ’ ነው። የፈለገ ጨዋ ብትሆኑም ደኅና አድርጎ ሲዘረጥጣችሁ ወይም የሆነ አስፀያፊ ነገር ሲያደርግባችሁ ያለመሳደብ ትህትናችሁ ተንዶ እንድትሞልጩት የሚያስገድዳችሁ እና የስድብ ሙያ ምዘና ቢኖር ተሸላሚ ተሳዳቢ የሚሆን ዓይነት ሰው ነው።
በሦስተኛ ደረጃ ያስቀመጥናቸው ሰድቦ አሳዳቢዎችን ሕጉም ያውቃቸዋል። እነዚህ ተሳዳቢዎች አይደለንም በናንተ ላይ ሌላ ሰው ላይ ሲሆን የሚቀፍ እጅግ አሳፋሪ፣ አስፀያፊ ወይም አስቀያሚ ትችት ሊሆን በሚችል ተግባር ቀስቅሰዋችሁ ወይም ገፋፍተዋችሁ ብትሳደቡ እና ብትከሰሱ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 616 መሠረት ፍርድ ቤቱ ላይቀጣችሁ ይችላል።
በተለይ ምላሻችሁ ወዲያውኑ እና ከተሰደባችሁት ስድብ ጋር ተመጣጣኝ ከሆነ ሁለታችሁንም ወይም አንደኛችሁን ከቅጣት ነፃ ሊያደርጋችሁ ይችላል። ምክንያቱም እነዚህ ዓይነትን ተሳዳቢዎች ችሎ ማለፍ እንደሚከብድ ሕጉም ራሱ ተረድቶታል።
በስድብ ተከሳችሁ ጉዳዩ እየታየ እያለ ያለአግባብ ነው የተሳደብኩት “ምነው ያን ቀን ምላሴን በቆረጠው!” በሚል ስሜት መጸጸታችሁን ከገለጻችሁም ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ሊያቀልላችሁ ይችላል። ተሳዳቢው ከሳሹን በሽማግሌ ይቅርታ ጠይቆ “አፉ ብዬሀለሁ!” ካለውም በእርቅ ክሱ እንዲቋረጥ ማድረግ ይቻላል።
ስድቡ ቀላል ነው የሚባል ስድብ ወይም ማዋረድ ከሆነ፣ ነገሩ ለተሰዳቢው ለራሱም ካልገባው፣ ስድቡ ካልተሰራጨ ወይም ከሰዳቢ እና ከተሰዳቢ ውጭ ሌላ ሰው ካልተረዳው ቅጣቱም እንደ ስድቡ እና እንደ አሰዳደቡ ቀላል ነው።
ይህ ዓይነቱ ስድብ በወንጀል ሕጋችን አንቀፅ 844 ስር የደንብ መተላለፍ ጥፋት በመሆኑ እስከ መቶ ብር የገንዘብ ቅጣት ወይም በስምንት ቀን የማረፊያ ቤት እስር ሊያስቀጣ ይችላል።
ተሳዳቢው የተሳደበው ግዴታውን በማከናወን ላይ ያለን የመንግሥት ሠራተኛን ከሆነ ወይም ከመንግሥት ሥራው ወይንም ተግባሩ ጋር በተያያዘ መንገድ አስቦበት ከሆነ በአንፃራዊነት ቅጣቱ ከባድ ነው። ቅጣቱ ከስድስት ወር ማይበልጥ እስር እና ከአንድ ሺህ ብር ማይበልጥ መቀጮ ነው።
የሀገራችንን መንግሥት በአደባባይ መስደብ፣ ማዋረድ፣ የፌዴራሉን ወይም የክልል ሰንደቅ ዓላማዎችን በተንኮል ወይም በንቀት ወይም በመሰል ማንኛውም ሐሳቦች ተነሥቶ የመስደብ፣ የመድፈር ወይም የማዋረድ ድርጊቶችም በወንጀል ሕጋችን አንቀፅ 244 እንደተደነገገው ከሦስት ወር በማያንስ እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ያስቀጣሉ።
የውጭ ሀገር መንግሥትን ወይም መሪን፣ በሀገራችን የሚገኘውን የውጭ ሀገር የዲፕሎማቲክ አባልን ወይም ተጠሪን መስደብ ወይም ማዋረድ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላማዊ ወዳጅነት ያለውን መንግሥት የሉዓላዊነት ምልክቶችን በተለይም የዚሁ ሀገር ተጠሪ የሚያውለበልበውን አርማ ወይም ሰንደቅ ዓላማ፣ በመንግሥታት መካከል የተቋቋሙ እና ሀገራችን አባል የሆነችባቸውን ድርጅቶች ወኪልን ወይም የታወቀ ምልክቱን ባደባባይ ማዋረድም በቀላል እስር ወይም በገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል።
ይህ ዓይነቱ ክስ የሚቀርበው ግን የተሰደበው ሀገርም ተመሳሳይ ጥበቃ የሚሰጥ ሲሆን እና የሀገሪቱ መንግሥት ተሳዳቢው እንዲከሰስለት ጠይቆ የፍትሕ ሚኒስትሩ ሲፈቅዱ ብቻ ነው።
“ቢቆስልም ይድናል የተደበደበ
ስድብ ግን ይኖራል እንዳንገበገበ!!”
ብለዋል ባለቅኔው ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል። ስድብ አነሰም በዛ ማስከፋቱ አይቀርም። ስለዚህ ሐሳብ የመግለጽ ነፃነታችንን ስንጠቀም ስሜታዊ ባንሆን እና ሳንሳደብ ሐሳብን በሐሳብ በመሞገት ወይም መልካም ቃላትን ብቻ በመጠቀም ብንተች ወይም ብንቃወም ይመረጣል። የስድብ እና የማዋረድ ተግባር ላይ በተለያየ መልኩ ምንሳተፍ ሰዎችም የሕጉን ኃላፊነት ፈርተን ብቻ ሳይሆን ይህን የተወገዘ ተግባር ማስወገድ ይኖርብናል።
ስናጠቃልለውም "ክፉ ምላስ" በሚል ርዕስ የተጻፈውን እና በመግቢያችን ላይ የጠቀስነውን የሃይማኖት አባቶችን መልዕክት ተግባራዊ በማድረግ እና የራሳችንንም ኅሊና አክብረን ባለመሳደብ፣ ለሌሎችም አርአያ በመሆን፣ ጨዋነትን ማሳየት በየእምነታችን የሚጠበቅብን ግዴታ ከመሆኑም ባሻገር ከጠቀስናቸው በስድብ ምክንያት ሊመጡ ከሚችሉ የወንጀል ቅጣቶችም ያድነናልና ልብ ልንለው እና ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል። ቸር እንስንብት!( EBC online ላይ የወጣ ፅሁፌ ነው)

መጥሪያ አደራረስ ሥነ -ሥርዓት እና ውጤቱ
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑♨️👇
በፍትሐብሕር ጉዳይ ተከሣሽ ለሆነ ወገን ከፍ/ቤት የሚላከውን መጥሪያ ለተከሳሹ ሊደርስ የሚችልበትን የተሻለ አማራጭ መንገድ በመለየት ሊላክ ይገባል፡፡ የመኖሪያ አድራሻው በግልፅ ለሚታወቅ ተከሳሽ ፍ/ቤቱ የሚልከውን መጥሪያ በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ብቻ እንዲለጠፍ በማድረግ ተከሳሹ አልቀረበም በሚል በሌለበት ጉዳዩ እዲታይ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢነት የለውም፡፡ በዚህ መንገድ በአግባቡ መጥሪያ እንዲደርሰው ያልተደረገ ተከሳሽ በሌለበት ታይቶ የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሣለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተገቢነት ያለው ነው፡፡ ተከሳሽን በአግባቡ መጥራት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ከተቀመጡት የመስማት መብት ከሚረጋገጥባቸው መርሆዎች አንደ ነው፡፡ ይህን መርህ ባለመጠበቅ የሚሰጠው ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ በሕጉ አግባብ እንደተሰጠ አይቆጠርም፡፡ በመሆኑም ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ወደጉዳዩ ሥረ-ነገር ገብቶ ተከሣሹን ባለዕዳ የሚያደርግ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ተከሳሹን በአግባቡ ስለመጠራቱ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 105(1), 78. በሌላ በኩል ደግሞ ለተከሳሽ የተላከው መጥሪያ በጋዜጣ ጥሪ ሊደረግ የሚገባው ሌሎች አግባብነት ያላቸው የመጥሪያ አላላክ መንገዶች ቅደም ተከተላቸውን በጠበቀ መልኩ ከተከናወኑ በኋላ ነው፡፡ መጥሪያ በአግባቡ ደርሷል ለማለት የሚላክለት ሰው ስም በተሟላ ሁኔታ ተገልጾ መላክ ያለበት በአድራሻው መላክ አለበት፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 94-110, 78, 70/ሀ/
ለአንድ የመንግስት ተቋም የተላከ መጥሪያ መጥሪያው በአግባቡ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ካልደረሰ በስተቀር መጥሪያው ለተቋሙ መዝገብ ቤት ገቢ በመሆኑ ብቻ መጥሪያው እንደደረሠ ተቆጥሮ ክርክሩ ተቋሙ በሌለበት ሊታይ አይገበም፡፡ የመጥሪያ አሰጣጥ ዘዴና ቅደም ተከተል እንዲሁም መጥሪያው ለማን እንደሚሰጥ የሚመለከተው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ክፍል ዓይነተኛ ዓላማ ከሆኑት መካከል አንዱ ተከራካሪ ወገኖችን እኩል የመከራከር መብት እንዲኖራቸው በማድረግ ጉዳዩን ፍትሓዊ በሆነ አኳኋን ለመወሰን ማስቻል መሆኑን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ መጥሪያ የሚደርስበትን ተገቢ መንገድና ለማን መድረስ እንዳለበት ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ መጥሪያ በተገቢው መንገድ ደርሶት ተከራካሪ ወገን ካልቀረበ ወይም መጥሪያን አልቀበልም ካለ ፍርድ ቤቱ ሊከተለው የሚገባው ስርዓትም በሕጉ በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ከእነዚህም ድንጋጌዎች መካከል አንደ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 70(ሀ)፣ 103፣ 104፣ 105፣ 106 እና 107 ስር የተመለከተው ሲሆን በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት ተከሳሽ በላለበት ክርክሩ ታይቶ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችለው መጥሪያው በአግባቡ የደረሰው መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ ወይም ሊገኝ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መጥሪያውን ለመቀበሌ ፈቃደኛ አለመሆኑ ወይም ሊገኝ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ ድንጋጌዎቹ መጥሪያው በትክክል ያልደረሰው መሆኑ ከተረጋገጠ ጉዳዩ ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይ የማይታዘዝ ስለመሆኑ ያስገነዝባል፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 70(ሀ) ድንጋጌ ስር ላይ ‛መጥሪያው በትክክል መድረሱ“ የሚለው ሐረግ መኖሩም የሚያሳየው ስለመጥሪያ አሰጣጥና አደራረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 94 እስከ 110 ድረስ የተመለከቱት ሁኔታዎች በአግባቡ መሟላታቸውን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ አንድ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ ከተሰጠውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78 መሰረት መፍትሔ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት መፍትሔ ሊጠየቅ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው በሚያቀርበው አቤቱታ ላይ የጥሪው ትዕዛዝ ‛በሚገባ ያልደረሰው“ መሆኑን በመጥቀስ ይህንኑ ማረጋገጥ ሲችል ነው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው አንድ ሰው የመከራከር መብቱን እንደተወው የሚቆጠረው መጥሪያው በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓትና ቅደም ተከተል መሰረት ደርሶት ክርክር ያለው መሆኑን እያወቀ ሳይቀርብ ሲቀር ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት ተከትሎ አማራጭ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት ከፈጸመ መጥሪያው ለተከሳሹ እንደደረሰ እንደሚቆጠርና በቂና ሕጋዊ ምክንያት ካለው ብቻ ወደ ክርክሩ እንድገባ የሚፈቀድ መሆኑን ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያስገነዝባል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ውሳኔ መሰጠት ያለበትም በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት መጥሪያው መድረሱ በሚገባ የተረጋገጠና የተከሳሽ የመከራከር መብት የተጠበቀ መሆኑ ሲታወቅ ሊሆን ይገባል፡፡ የፍ/ሥ/ህ/ቁ 70/ሀ/፣78/2/፣96፣102
ከላይ በተመለከተው መሠረት ለተከሳሽ የተላከው መጥሪያ በአግባቡ መድረስ አለመድረሱ ሳይረጋገጥ ክርክሩ በሌለበት ይቀጥል በሚል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ክርክሩ የቀጠለ እንደሆነ ክርክሩን ወደ ኋለ የሚመልስና ለአላስፈላጊ እንግልት የሚዳርግ ነው፡፡ ስለዚህ በሌለበት ክርክሩ ይቀጥል ለማለት መጥሪያው ለሚመለከታቸው ተከሳሾች መድረስ አለመድረሱን በአግባቡ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ መጥሪያ በአግባቡ ያልደረሰው ሰው ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠው ውሳኔ እንድነሳለት የሚጠይቀው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 መሠረት ሲሆን አንድ አንድ ጊዜ በስህተት ወይም ባለማወቅ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሚቀርብበት ጊዜም አለ፤ ይህ ደግሞ ተገቢነት ያለው አይደለም፡፡ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሚቀርበው ከጅምሩ በክርክሩ መግባት የነበረበት ግን በክርክሩ ውስጥ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ያልተጠቀሰ፤ በተሰጠው ውሳኔም መብቱ/ጥቅሙ የተነከ ሰው ነው፡፡ በክርክር ወቅት መጥሪያ አልደረሰኝም ብሎ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሥነ-ሥርዓት ህጉን የተከተለ አይደለም፡፡ የሰበር ውሳኔዎች ቅጽ 9 የመ/ቁ. 50022, ቅጽ 9 የመ/ቁ. 50376
Join👇🔥

የፍርድ ቤት እግድ የተሰጠበትን ቤት በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ የሽያጭ ውሌ ህጋዊ ውጤት የሌለው እና ሊፈርስ የሚገባ ነው፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.154 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች፣ የፍትሃ ብሄር ህግ ቁጥር 1808.
ሰ.መ.ቁ. 177862 ቅፅ - 25
https://t.me/ethiolawtips
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.154 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች፣ የፍትሃ ብሄር ህግ ቁጥር 1808.
ሰ.መ.ቁ. 177862 ቅፅ - 25
https://t.me/ethiolawtips
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች
የስጦታ ምንነት
በአጭሩ ለማስቀመጥ ስጦታ ማለት ሰጪው ተቀባይ ለተባለ ሌላ ሰው ከንብረቶቹ አንዱን ያለ ዋጋ የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ነው።
በመሆኑም ስጦታ በራሱ ውል ነው ማለት ነው።
የስጦታ ልዩ ባህሪያት
በመርህ ደረጃ ስጦት ግላዊ ተግባር ነው ይህም ማለት ስጪው እራሱ የሚያድረገው ተግባር ነው ማለት ነው። ስጦታ የሚደረገው በወኪሉ ሲሆን ደግሞ የሚሰጠው ንብረት አይነት እና ለማን እንደሚሰጥ በግልጽ ሊመለከት ይገባል። ስጦታ የሚደረገው የሰጪው ንብረት በሆነው ለይ ብቻ ነው።ስጦታ አድርጋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል መስጠት በህጉ መሠረት ግዴታን አያስከትልም ከዚህም በተጨማሪ ስጦታ ተቀባዩ ስጦታውን እቀበላለሁ በሚል ሀሳቡን
መግለፅ ይኖርበታል።ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት አመት ለዳኞች ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም።
የስጦታ ሥርዓት ፎርም*
ስጦታ በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ ወይም በሚይንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ ሊደረግ ይችላል።
*1)በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ *
በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በፍትሐብሔር ህግ አንቀጽ 881 ላይ በተደነገገው መሠረት በግልጽ ኑዛዜ ሥርዓት ፎርም መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ህጉ ያስረዳል።በሌላ በኩል በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ለይ የሚደረገው ስጦታ በፍ/ህግ አንቀጽ 1723 መሠረት በጽሁፍ ሆኖ በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሆን አለበት።
*2) በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ለይ የሚደረግ ስጦታ*
በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በሁለት አይነት መልኩ ሊደረግ ይችላል ይህም እጅ በእጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ወይም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረገው ፎርም ሊሰጥ ይችላሉ።
ስጦታ እንደማድረግ የማይቆጠርባቸው ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን እነኚህም ሁኔታዎች።
1)ያለ ዋጋ የሚደረግ የአገልግሎት ሥራ ወይም የራሱን እቃ ያለ ዋጋ ዝግጁ ማድረግ ስጦታ አይባልም የፍ/ህግ አንቀጽ 2430።
2)መንፈሳዊ ተግባርን ለመፈጸም የሚደረገው የገንዘብ መክፈል ስራ ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2432።
3) አንድ ሰው ለሰጪው ወይም ለቤተሰቡ አገልግሎት በልማድ መሠረት ያደረገው የሥራ ዋጋ መክፈል ስጦታ አይባልም የፍ/ህ አንቀጽ 2433።
4)ወራሽነትን አልፈልግም ብሎ መተው ወይም ኑዛዜ የተደረገለትን ስጦታ አልቀበልም ማለት ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም የፍ/ህግ 2431።
ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች*
በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ለይ የተደረገው ስጦታ በህጉ በተጠቀሱት በተለያየ ምክንያቶ ፈራሽ ሊሆን የሚችሉባቸው ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነኚህም:-
1ኛ የሰጪው አዕምሮ ትክክል አለመሆን
ሰጪው ስጦታውን በሚያድርግበት ወቅት በአዕምሮ መታወክ(ህመም ምክንያት) በፍርድ የተከለከለ ሲሆን ያደረገው ስጦታ ፈራሽ ሊሆን ይችላል ።የፍ/ህ አንቀጽ 2437
2ኛ ግብረ ገብነት የሌለው ወይም ህገ ወጥ ምክንያት ያለበት ስጦታ ፈራሽ ነው። የፍ/ህ አንቀጽ 2438
3)በመንፈስ መጫን ምክንያት የተደረገውን ስጦታ ዳኞች ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ።የፍ/ህ አንቀጽ 2439
4ኛ በ ፍ/ህ አንቀጽ 2442 ሥር በሚፈቅደው መሠረት ስጦታው የተደረገው በስህተት ወይም በተንኮል የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ይሆናል።
5 ስጦታ የተደረገው ክርክር ያለበት ሀብት ላይ ሲሆን ስጦታው ፈራሽ ይሆናል።የፍ/
@lawyerhenoktaye👇👇👇
🛑 ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ👇
https://t.me/EthioLawtips
business law👇
@henoktayelawoffice

Forwarded from አለ ሕግ
👉👉አደራ እና የወንጀል ኃላፊነት
በወንጀል ሕጋችን 675 መሠረት እምነት ማጉደል ማለት ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ የሌላ ሰውን ለተወሰነ አገልግሎት (በውሰት) ወይም በአደራ የተቀበለውን ዋጋ ያለው ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ለራሱ ያደረገ፣ የወሰደ፣ ያስወሰደ፣ የሰወረ፣ ለራሱ ወይም ለሌላ አገልግሎት ያዋለ ወይም መሰል ድርጊቶችን የፈፀመ እንደ ነገሩ ሁኔታ በቀላል እስራት ወይም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ እስራት ይቀጣል።
https://wp.me/pfoz3m-1L

AleHig🔴አለሕግ
አደራ’ በሕጎቻችን – ከጥንት እስከ ዛሬ
በኪዳኔ መካሻ ተፃፈ “የአምባሰል ማር ቆራጭ ይወጣል በገመድ፣አደራ ቢሰጡት ይበላል ወይ ዘመድ?” – ድምፃዊ ካሣ ተሰማዐፄ ዘርዐያቆብ ከ1414-1468 ዓ.ም ከዓረብኛ ወደ ግዕዝ ያስተረጎሙት እና በሥራ ላይ ያዋሉት ሕግ ፍትሐ ነገሥት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ፍትሕን የሚመለከት በሀገራችን ታሪክ ቀዳሚ የሕግ…
👍1
Forwarded from አለ ሕግ
አንድ ሰው ከቤቱ ወይም ከመኖሪያው ቦታ ጋር ወደተያያዘ ቦታ ሰው ባይኖ አጥር ግቢ ሕጋዊ ነዋሪው ፈቅዶለት ከገባ በኋላ እንዲወጣ ሲጠይቀው ያልወጣ እንደሆነ፤ ከ 3 ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም በመቀጮ እንደሚቀጣ ያውቃሉ፡፡
የወንጀል ህግ አንቀጽ 604‼️
ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!
#አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig
Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
#አለ_ህግ #Ale_Hig
የወንጀል ህግ አንቀጽ 604‼️
ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!
#አለ_ህግ #Ale_Hig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏
@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig
Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Telegram
የሕግ ቤት
የሕግቤት Access legal information from Law center, The House of Law.
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
https://www.facebook.com/lawsocieties
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
https://www.facebook.com/lawsocieties
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
Forwarded from አለ ሕግ
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ
የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ
አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው። ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችላቸው የኅብረት ስምምነት ድርድር በማድረግ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክሮች፣ የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በተጨማሪ አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ለመጠበቅ እንዲቻል የአሰሪና ሰራተኛ ህግ በኢትዮጵያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍም በግል በተቋቋሙ ድርጅቶችና መንግስታዊ በሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ባለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተደንግጎ የሚገኘውን የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱን እንመለከታለን።
የሰራተኞች ቅነሳ መቼ ይደረጋል?
የሰራተኞች ቅነሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሊደረግ የሚችለው የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚከተሉት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ ነው:-
• ሠራተኞች የተሰማሩባቸው ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት፤
• በአዋጁ አንቀጽ 18(5) እና (6) ላይ የተቀመጡት ከስራ ውል የሚመነጩ መብቶችና ግዴታዎች ለጊዜያዊ የሚታገዱበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ አሠሪው በሚያመርታቸው ምርቶች ወይም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የሥራ ውል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
• የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ ናቸው፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ነው ሊያስብል የሚችለው ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ቁጥራቸው ከድርጅቱ ሠራተኞች ቢያንስ ከመቶ አሥር የሚያህለውን ወይም የሠራተኞች ቁጥር (የአንድ አመት አማካኝ የሰራተኞች ቁጥር) ከሀያ እስከ ሀምሳ በሆነበት ድርጅት ቢያንስ አምስት ሠራተኞችን የሚመለከት ከአሥር ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የሚቆይ የሥራ ውል መቋረጥ ሲከሰት እንደሆነ በአስሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 29 ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ሂደት
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ አሰሪ በራሱ ጊዜ የፈለገውን ሰራተኛ መቀነስ የማይችል ሲሆን ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ በመጀመሪያ አሠሪው ከሠራተኞች ማኅበር ወይም ተወካይ ጋር በመመካከር የሥራ ችሎታ ያላቸውና ከፍተኛ የምርት ውጤት የሚያሳዩ ሠራተኞች በሥራቸው ላይ እንዲቆዩ ያደርጋል ወይም ከማይቀነሱ ሰራተኞች መካከል ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በድርጅቱ ውስጥ ተመሳሳይ የሥራ ችሎታ ያላቸውና ተመሳሳይ የምርት ውጤት የሚያመርቱ ሠራተኞች በሚኖሩ ጊዜ የሰራተኞች ቅነሳ የሚደረገው በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናል:-
1. በድርጅቱ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሠራተኞች፤
2. አነስተኛ ቁጥር የሆነ ጥገኞች ያሏቸው ሠራተኞች፤
3. ከተራ ቁጥረ (4) እስከ (7) ከተዘረዘሩት የሠራተኛ ክፍሎች ውጭ የሆኑ ሠራተኞች ቅነሳው በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከታቸው ይሆናል፤
4. አካል ጉዳተኛ የሆኑ ሠራተኞች፤
5. በድርጅቱ ሳሉ በሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች፤
6. የሠራተኞች ተጠሪዎች፤
7. ነፍሰጡር ሠራተኞች ወይም ከወለዱ እስከ 4 ወር ድረስ የሆናቸው ሴት ሠራተኞች ናቸው፡፡
በልዩ ሁኔታ የኮንስትራክሽን ስራ ማለትም ሕንጻ፣ መንገድ፣ የባቡር ሐዲድ፣ የባሕር ወደብ፣ የውሃ ግድብ፣ ድልድይ፣ የመሣሪያ ተከላና ሌላም ተመሳሳይ ሥራ የመሥራት የመለወጥ፣ የማስፋፋት፣ የማደስና የመጠገን ሥራ ተከታታይነት እያለቀ ሲሄድ የሥራው መጠን በመቀነሱ ምክንያት ተቀጥረው በሚሰሩ ሠራተኞች ላይ ቅነሳ ሲደረግ አሠሪው በዚህ ከላይ የተመለከቱትን የሠራተኞች ቅነሳ ሥነ ሥርዓት መከተል አይጠበቅበትም፡፡ ነገር ግን ሰራተኞች የተቀጠሩበት ሥራ ከማለቁ በፊት ከሆነ የሰራተኛ ቅነሳ ሲደረግ በአዋጁ ላይ የተገለጸውን ሥነ-ሥርአት መከተል የግድ ይለዋል። በተጨማሪም ቅነሳ ለማካሄድ አሰሪው የሁለት ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሚቀነሱት ሰራተኞች የመስጠት ግዴታ አለበት (አንቀፅ 35/1/መ)፡፡ እንዲሁም ድርጅቱ የሚወስደው እርምጃ፣ ከሰራተኞች ጋር የህብረት ስምምነት ካለው ይህንኑ እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በዚህ ረገድ የሚያወጣውን መመሪያ ያከበረ መሆን አለበት፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ያለው ውጤት
አንድ ሰራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 29 መሰረት በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ሲቋረጥ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው። የስራ ስንብት ክፍያ መጠንን በተመለከተ ለመጀመሪያው የአንድ ዓመት አገልግሎት የሠራተኛው ማለትም የተቀነሰው ሰራተኛ የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡ከአንድ ዓመት በታች አግልግሎ ለተቀነሰ ሰራተኛ ግን እንደአገልግሎት ጊዜው እየተተመነ ተመጣጣኝ ክፍያ ያገኛል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎ በሰራተኛ ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ የተቋረጠበት ሠራተኛ ከላይ በተጠቀሰው ክፍያ ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት ከላይ የተጠቀሰው ክፍያ አንድ ሦስተኛ እየታከለ የስራ ስንብት ክፍያው ይከፈለዋል፡፡ ነገር ግን ጠቅላላው ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡
በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ተቋርጦ ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ ከላይ ከተጠቀሰው የስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የሠራተኛው የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዝ በ60 ተባዝቶ እንደሚከፈለው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ አለመግባባት የሚፈጠር ከሆነ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ሰላም ለመፍጠር፣ ምርታማነትን ለማሻሻል ብሎም የሰራተኞች ህጋዊ መብቶች ለማስክበር በስራና ክህሎ ሚኒስቴር በሚመደብ አስማሚ ችግሩ እንዲፈታ መመልከት ወይም ይህን መሰል ጉዳይ የወል ስራ ክርክር በመሆኑ ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ዳኝነት መጠየቅ ይቻላል፡፡
Federal Justice and Law Institute
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
https://alehig.wordpress.com/blog-2/
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties

Forwarded from ይግባኝ ምክረ ሕግ ⚖️
#የሥራ ስንብት ክፍያ
የስራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ሠራተኛ በአዋጅ 1156/2011 ዓ.ም አንቀፅ 39 (1) (ለ) እና 40 (1) መሠረት እንደ ነገሩ ሁኔታ ለ1 ዓመት አገልግሎት የመጨረሻ ሳምንት አማካኝ ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ሲከፈለው ከ1 ዓመት በታች ያገለገለ በአገለገለው ልክ ይከፈለዋል፤ ከ1 ዓመት በላይ ያገለገለ እንደሆነ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ዓመት የዓመቱ 1/3ኛ እየተጨመረ ይከፈለዋል።
#የካሳ ክፍያ
የሥራ ውሉ አላግባብ የተቋረጠበት ከሥራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ በአዋጅ 1156/2011 ዓ.ም አንቀፅ 43 (4)(ለ) መሠረት የካሳ ክፍያ ያገኛል። ሆኖም ካሳው የሠራተኛውን ማዕከላዊ የቀን ደመወዝ በ180 ተባዝቶ ከሚያገኘው መጠን መብለጥ የለበትም።
#ያልተጠቀሙበት የዓመት ዕረፍት
የሥራ ውሉ አለአግባብ የተቋረጠበት ሠራተኛ ከሥራ ስንብት ክፍያ እና ከካሳ ክፍያ በተጨማሪ ያልተጠቀመበት የዓመት ዕረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ በአዋጅ 1156/2011 ዓ.ም አንቀፅ 77 (4) መሠረት ይከፈለዋል።
#ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ
ሠራተኛው የሚለግበትን የአሰሪ ንብረት መልሶ ክሊራንስ ከጨረሰ በኋላ ሊከፈሉት የሚገቡ ክፍያዎች በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ካልተከፈሉት በአዋጁ አንቀፅ 38 መሠረት እስከ 3 ወር ደመወዝ ሊከፈለው ይችላል።
#ያልተከፈለው የወር ደመወዝ ካለ ይከፈለዋል።
#ለተጨማሪ ሥራ ክፍያ
ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ በበዓል ቀናት የተሰራ ሥራ፣ በዕረፍት ቀናት የተሰራ ሥራ ካለ ለእነኚህ ሥራዎች በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀፅ 66 እና 68 መሠረት ሠራተኛው ክፍያ ያገኛል።
#የሥራ የምስክር ወረቀት (የሥራ ልምድ)
በአዋጅ ቁጥር 1156/2011ዓ.ም አንቀፅ 12 (8) መሠረት ሠራተኛው የሥራ ልምድ ማስረጃ ያገኛል።
ይግባኝ መብት ነው!!!

#የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ሠራተኛው ተከፋፍሎ እንዲሰጠው ሲጠይቅ እንዲሁም አሠሪው ሲስማማ ለሁለት ተከፍሎ ለሠራተኛው ሊሰጠው እንደሚችል ተቀምጧል። አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም አንቀጽ 79
#የዓመት ፈቃድ ሠራተኛው ሲጠይቅ አሠሪውም ሲስማማ ሊተላለፍ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 79 (2) ላይ ተደንግጓል። ነገር ግን ይህ ማራዘም ከ 2 ዓመት በላይ ሊበልጥ የማይችል ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 79 (3) ላይ ተመልክቷል።
👉የዓመት ፈቃድ ምን ያህል ጊዜ ነው ሚጠራቀመው🤔
#ብዙ ሠራተኞች የዓመት ፈቃዳቸውን በገንዘብ ሚጠይቁት ከአሠሪ ጋር አለመስማማት ተፈጥሮ ሥራቸውን ሲለቁ የ5 ወይም 10 ዓመት አልያም ከዛ በላይ የሆነውን ደምረው ይጠይቃሉ። ይህ ልክ ነው ወይ?
#የዓመት ፈቃድ መሠረታዊ ዓላማ ሠራተኛውን ዕረፍት እንዲያገኝ በማድረግ በአዕምሮና በአካል ብቁ እንዲሆን ማድረግ እንጂ ያለዕረፍት ሥራ እየሰራ ገንዘብ እንዲያገኝ ማድረግ አይደለም። ለዚህም ነው ልዩ ሁኔታ ከሌለ በስተቀር የዓማት ፈቃድ በገንዘብ የማይከፈለው።
በመሆኑም ማንኛውም ሠራተኛ የዓመት ፈቃዱን ከ 2 ዓመት በላይ ማራዘም የማይችል በመሆኑ ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው ፈቃዱ የሚቃጠልና በቀናት ፈቃድም በገንዘብም እንዲከፈለው ለመጠየቅ የማይችል ነው።
ይግባኝ መብት ነው!!!
የቴሌግራም ቻናል አድራሻችን
https://t.me/etonlinelegal
አዲስ የተከፈተውን ቴሌግራም ግሩፕ ለመቀላቀል ይህንን ይጫኑ
https://t.me/etonlinelegalchat
በግል መስመር በማንኛውም ጉዳይ የሕግ ምክር ለማግኘት ይህን የቴሌግራም አድራሻ ይጠቀሙ
@laws2016
በfacebook የሚለቀቁ መረጃዎችን ለማግኘት ገጹን ይቀላቀሉ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61551025119181