Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (fasika aggena)
የቦሌ ክ/ከተማ የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ፣ ምርመራ፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና የተጠያቂነት ስርአትን ለመዘርጋት በወጣው ደንብ ቁጥር 143/2015 ዙሪያ በቀን 20/09/2016 ዐ.ም ስልጠና ሰጠ!!! በመድረኩም ከተለያዩ የሲቪክ ማህበራት፣ ማለትም፣ ከሴቶች፣ ከአካል ጉዳተኞች፣ ከወጣቶችና ከአረጋውያን አደረጃጀቶች፣ የተወጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የደንቡን አላማና አስፈላጊነት፣ የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ፣ ምርመራ፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና የተጠያቂነት ስርአትን እንዲሁም በደንቡ የተቋቋመውን የስራ ክፍል አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ተሳታፊዎችም ስልጠናው ጠቃሚ መሆኑ ገልጸው በቀጣይ መሰል ስልጠናዎች በስፋት እንዲሰጡ ሃሳብ ሰጥተዋል። እነሆ ከመድረኩ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎች!!!!
የቦሌ ክ/ከተማ የህግ ስርፀት እና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ከ ክፍለከተማው ምክር ቤት እና ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ስለ "የወንጀል ህግ ምንነት እና መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳቦች በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ" በሚል እርእስ ዙሪያ ከቀን 19/09/2016 - 20/09/2016 ዓ.ም ስልጠና ሰጠ። በመድረኩም ከክፍለከተማው የተወጣጡ ወጣቶችና ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን ስለ ወንጀል ህግ ምንነት፡ አላማ፡ የተሳታፊነት ደረጃ፡ የወንጀል ህግ መሰረታዊ መርሆዎች አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን አስተማሪ ውይይቶ እና ምላሾች ተሰጥተዋል። ስልጠናው ቀጣይነት ያለው ሲሆን ተሳታፊዎችም ስልጠናው ጠቃሚ እንደነበር እና መሰል ስልጠናዎችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሀሳብ ሰጥተዋል።
Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (fasika aggena)
የቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ግንቦት 23 ቀን 2016 ዐ.ም በፌደራሉ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ዙሪያ የንቃተህግ ስልጠና ሰጠ!!! በመድረኩ 300 ገደማ የሚሆኑ የሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአረጋውያንና የወጣቶች ተወካይ የሆኑ የክ/ከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ስለኪራይ ውል ምንነት፣ ዘመን፣ መታደስ፣ መቋረጥ እንዲሁም በአዋጁ ስለሚቋቋሙ ተቋማት ስልጣንና ሃላፊነት ግንዛቤ ተፈጥሯል። በተጨማሪም ተሳታፊዎች የነዋሪው ተወካይ እንደመሆናቸው መጠን ለአዋጁ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን ሚና ለመጫወት ከአሁኑ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተበረታትተዋል። እነሆ ከመድረኩ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎች!!!!!!
Forwarded from Tibebu S.
የቤት_ኪራይ_ቁጥጥር_አዋጅ_ማሰልጠኛ_ማንዋል13202016.pptx
1.6 MB
Forwarded from አለ ሕግ
የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ሰኔ አንድ ይጀምራል
የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ሰኔ አንድ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 ን ለመፈፀም የአከራይና ተከራይ ውል ከሰኔ አንድ ጀምሮ በየወረዳዎቹ ምዝገባ እንደሚጀመር ገልጿል።
የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ምዝገባውን ለማካሄድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገናል ብለዋል።
አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር በመሆን ከሰኔ አንድ ጀምሮ በየወረዳቸው በመገኘት መመዝገብ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ምዝገባውን ከስራ ሰአት ውጭ ለማከናወን እንደታቀደም ጠቁመዋል።
አዋጁና መመሪያው የአከራይ እና ተከራይን ሚዛናዊ ተጠቃሚነት የሚያስጠብቅ መሆኑንም ተናግረዋል።
ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ላይ እና የማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ ውይይት መካሄዱን አስረድተዋል።
አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

Telegram
የሕግ ቤት
የሕግቤት Access legal information from Law center, The House of Law.
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
https://www.facebook.com/lawsocieties
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
https://www.facebook.com/lawsocieties
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
👍1
Forwarded from ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️ (Daniel Fikadu √)
ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ በምዝገባ ወቅት ማሟላት ያለባቸው👇
👉በህግ አግባብ የተዘጋጀ የመኖሪያ ቤት
ውል ሰነድ
👉የአከራይና ተከራይ የነዋሪነት መታወቂያ ፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያ ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ ፓስፖርት ፣ የጠበቃ ፍቃድ ፣ የሰራተኞች ጡረታ መታወቂያ ፣ የዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ተማሪ የሙያ ስራ ፍቃድ ኦርጅናል ኮፒ ፤
👉የመኖሪያ ቤት ውሉ የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ ህጋዊ ውክልና የሁለት ምስክሮች የታደሰ መታወቂያ ኦርጅናል ኮፒ፤
👉አከራይ የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት የሚያስችል መብት እንዳለው የሚያሳይ ህጋዊ ሰነድ :-
- የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ
- ሰነድ አልባ ይዞታዎች መሆኑን
ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ወይም
- በፍርድ አፈፃፀም የተሸጠ ንብረት
ሰነድ ወይም
- የተከራየው ቤት በውርስ የተገኘ ሆኖ
ስም ዝውውር ካልተፈፀመ የወራሽነት
ማረጋገጫ
ኦርጅናል እና ኮፒ ይዘው መገኘት አለባቸው
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

Forwarded from M A
የመኖሪያ_ቤት_ኪራይ_ቁጥጥር_እና_አስተዳደር_መመሪያ_ቁጥር_7_2016.rtf
488 KB
Shared by One Read - an all-in-one file viewer: https://st.simplehealth.ltd/uAJjyu