Co.Market / ኮ-ገበያ
541 subscribers
5.06K photos
81 videos
3 files
2.47K links
  📲+251 9 11 81 16 72
https://ermitheethiopia.com

👉
Download Telegram
www.ermitheethiopia.com

For more info call
☎️📲251944365959
🚨 #ዉል_ማፍረስ#ዉል_መሠረዝ በምን ይለያል

👉 #ውል_ማፍረስ

የውል ማፍረስ ከውል አመሠራረት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ውሉ ከአመሰራረቱ በህጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱ ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል የውል መሰረዝ ጉዳይ ከውል አመሰራረት ችግር የሚነሳ ሳይሆን ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታውን ካለመወጣት የሚመነጭ ነው፡፡

👉 #ውል_መሰረዝ

ከተዋዋይ ወገኖች መካከል አንደኛው እንደ ውሉ ባለመፈጸሙና የውሉን ግዴታ በመጣሱ በተዋዋዩ ወይም በፍርድ ቤት ውሉን ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች ቀሪ ማድረግ ውል መሠረዝ ይባላል ፡፡

ይልቁንም የውል መሠረዝ ምክንያት ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታን ከመፈፀምና ካለመፈፀም ጋር ተያይዞ የሚከሠት ነው፡፡

የውል መሠረዝ ሥርዓትም የራሱ የሆነ አካሄድ አለው፡፡ ይኸውም ውሉን የመሠረዝ ፍላጐት ያለውን ወገን የውሉ ግዴታ ባለመፈፀሙ የተነሳ ከህግ ወይም ከውሉ ከራሱ ባገኘው መብት ተጠቅሞ ውሉን ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆንበት አጋጣሚም ግዴታው ባለመፈፀሙ የተነሳ የደረሰውን ጉዳት ከማረጋገጥ ጋር ተያይዞ የሚታይ እንጂ ጥያቄ አቅራቢው ሁል ጊዜ ተቀባይነት የሚያገኝበት አይደለም፡፡ በመሆኑም የውል ይሰረዝልኝና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች በህጉ አግባብ የሚስተናገዱ ስለመሆኑ የፍ/ህ/ቁ. 1784 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
የሚሸጥ የንግድ እና የአፓርትመንት አክሲዮን
- B+ G+6 ለአፓርታማ እና ለንግድ አገልግሎት(mixed use)
- ስፋት = 1,910 ካሬ( በሊዝ ለ ካሬ 2,500 ያሸነፈ)
* ቤዝመንት እና ሊፍት የተካተተለት
- ግንባታዉ 4ኛ ስላብ የተሞላና ግራወንዱን ለኪራይ ለማዘጋጀት የፊኒሽግ ስራ እየተሰራ ያለ
- 95 አባል ያለዉ
- ወርሃዊ መዋጮ = 6,600 ( ቀሪውን ግንባታ በአጭር ጊዜ ለመጨረስ የባንክ ብድር የተመቻቸ
- ለአንድ አባል 1 ባለ 2መኝታ(62 ካሬ)ለመኖሪያ እና ከግራውንድ 1 ባለ 8 ካሬ
ሱቅ ለእያንዳንዱ አባል የሚደርስ
1ኛ ፎቅ ለጋራ (ኮመን) አግልግሎት
- የቦታዉ መገኛ ባህርዳር ቀበሌ 11 ዲያስፖራ
* መሸጫ = 950,000 የመጨረሻ ዋጋ
0944365959
ጌሾ

ጌሾ በአፍሪካ ብቻ የሚበቅል በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ
የሚገኝ የተክል አይነት ነው።በኢትዮጵያ ለጠላ እና ለጠጅ አገልግሎት የሚውል
ሲሆን ።የሚበቅለውም ከባህር ወለል በላይ ከ1400-3200 ሜትር ላይ ነው

ጥቅሞቹ
ቆሮቆር እና ሌሎች የፈንገስ በሽታዎችን
በደቀቀ ፍሬው እና በቅጠሉ በመቀባት ማዳን ይቻላል

- ቂጥኝ በሽታን ለመከላከል
- ሆድ ድርቀትን ለማስወገድ
- ስሮቹ ደግሞ ደምን ለማጥራት ያገለግላል
የጌሾ ግንድ ጠንካራ ስለሆነ ለተለያዩ የእንጨት ውጤቶች ሊያገለግል ይችላል

የጌሾ ዛፍ በምንጮች አካባቢ ቢተከል
የመሬት መሸርሸርን ሊከላከል ይችላል
ከእርሻ ማሳ ዳርቻ ላይ በመትከልም የመሬትን ንጥረ ነገር ከንፋስና ከዝናብ መከላከል ይቻላል ። የጌሾ አበቦች በንቦች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ስላላቸው የጌሾ ተክል ለንብ እርባታና ለማር ምርት ሰፋ ያለ አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል።
Credit ፥ቁልፍ