Co.Market / ኮ-ገበያ
537 subscribers
5.06K photos
81 videos
3 files
2.47K links
  📲+251 9 11 81 16 72
https://ermitheethiopia.com

👉
Download Telegram
ተኝቼ እንኳን አንተ ትጠብቀኛለህ። እራሴን መቆጣጠር በማልችልበት ሰዐት እንኳ አንተ ታስበኛለህ። ሁሌ ጥበቃህ ተጓድሎብኝ አያውቅም። ዛሬም የተጨፈኑትን ዐይኖቼን በምህረትህ ገለጽክልኝ። ያረፈውንም አእምሮዬን ቀኑን አንግተህ አነቃኸው። በመስኮቱ በኩል የፈነጠቀውንም ብርሀን ማየት ቻልኩኝ። የወፎቹንም ዝማሬ በጆሮዬ አንቆሮቆርክልኝ። በጠዋቱ ምንም ገንዘብ ሳልከፍል "ብርሀንን" ሰጠኸኝ። ምንም ሳልከፍልም የ"ወፎቹን ዝማሬ" አሰማኸኝ። ገና ከመነሳቴ ይህንን ሁሉ ድንቅ ስጦታ አሸከምከኝ። እንደገና የተፈጥሮን ውበት ማድነቅም ጀመርኩኝ። ገና ከመነሳቴ ይህንን ሁሉ ካገኘሁኝ በቀሪው የቀኑ ሰዐታት ደሞ ከአባቴ የሚበረከቱልኝ ስጦታዎች አጓጉኝ። አባቴ እንዴት መልካም ነው?! እንዴትስ ድንቅ ነው?!

ሁሌ ቸርነትህ ተጓድሎብኝ አያውቅም። አሁንም በቸርነትህ ይህቺን አዲስ ቀን እንዳይ አደረከኝ። በዚች ቀንም ከወዳጆቼም ጋ እንድገናኝ፣ስራዬን እንድሰራ፣እንድዝናናና አዲስ ነገር እንድፈጥር ፈቀድክልኝ። ከምንም በላይ በሰጠኸኝ ቀን ሌሎችን ማገዝና ማሰብ እንዳለብኝ ተረድቻለሁኝ። አንተ እንደጠበከኝኛ አንተ እንደረዳኸኝ እኔም ለሌሎች መትረፍ እንዳለብኝ አውቄአለሁ።

ዛሬ በሕይወት የነቃን ሁሉ ፤ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች ስለመትረፍ እናስብ። የአቅማችንን ውስንነት ሳይሆን የአቅማችንን ትልቅነት እንመልከት። በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን የፈጣሪን ክብር የሚያገዝፍ ስራ ለመስራት እንሞክር። ፈጣሪ እኛን እንደወደደን ሁሉ እኛም በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ እንውደድ። ይቺንም ቀን በሕይወታችን ላይ መጨመሯ ትክክል መሆኑን በስራችን ትልቅነት፣በሀሳባችን መልካምነት፣ከአፋችን በሚወጡት የከበሩ ውብ ቃላቶች እናሳይ! ይቺ ቀን ይገባችኋል ብሎ የሰጠንን ፈጣሪ የሚያስወድስ ግሩም ውሎን በፈቃዳችን እንዋል። በውሎአችንም እግዚአብሔር ጥበቃው አይለየንም! አሜን!
መልካም ቀን ይሁንልን!
ብሩክ የሺጥላ
🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️🖤❤️

አንድ አባት አንድ ትዕግስት የጎደለው ወጣት ልጅ ነበረው። ይህ ወጣት በትንሹም በትልቁም ቱግ እያለ፤ ሰዎችን ያስቀይም ነበር። ከአንደበቱ ክፉ ቃላቶችን ስለሚያወጣ ከሰው ጋር
መስማማት አልቻለም። ትዕግስት ፈፅሞ የለውም። ይህ ነገር እጅግ ያሳሰበው አባት፤ ልጁን የሚለውጥበት ዘዴ ሲያወጣ ሲያወርድ ቆይቶ አንድ መፍትሄ ላይ ደረሰ።

አንድ ቀንም በቀረጢት ሙሉ ሚስማር ያዘና ልጁን አስጠርቶ እንዲህ አለው

“ልጄ ሆይ …ይህን በቀረጢት ያለውን ሚስማር ተቀበለኝ፤ ሁሌም ትዕግስት በጎደለህ ጊዜ እና ሰው ባስቀየምክ ቁጥር አንድ ሚስማር የእንጨቱ አጥር ላይ ሰካ” አለው።

ልጁ ምንም ግራ ቢገባውም አባቱ እንዳዘዘው ማድረግ ጀመረ። በመጀመሪያ ሰሞን በጣም ብዙ ሚስማሮችን ሰካ….ቀስ እያለ ግን በቀን እንጨቱ ላይ የሚሰካቸው ሚስማሮች ቁጥር እየቀነሰ መጣ…. እያለ… እያለ…. በመጨረሻ ምንም ክፉ ያልተናገረ ቀን አንድም ሚስማር ሳይሰካ ዋለ። ልጁ በጣም ታጋሽ ሆኖ ባህሪው ተስተካከለ ማለት ነው። ይህንንም ለአባቱ አበሰረ። አባትየውም “ እሰይ ልጄ…… አሁን ደግሞ ምንም ያልተናደድክ ቀን እና ክፉ ያልወጣህ ቀን በፊት ከሰካሃቸው ሚስማሮች ውስጥ አንዱን ንቀል” አሉት።

ልጁ እንደተባለው አደረገ፤ ከቀናት
በኋላ ሁሉንም ሚስማሮች ነቅሎ ጨረሰ። ወደ አባቱም ሄዶ ሚስማሮችን አስረከበ። አባትየውም አንዲህ አለው “አየህ ልጄ……አሁን የሰካሃቸውን ሚስማሮች ነቅለህ ጨርሰሃል…..በጣም ታጋሽ ሆነሃል ማለት ነው፤ ነገር ግን እስቲ አጥሩን ተመለክት….ፈጽሞ እንደ ድሮው ሊሆን
አይችልም፤ ሚስማሩ ቢወጣም ተበሳስቷል። ክፉ ንግግርም ልክ
እንደ ሚስማር ነው፤ ሺህ ጊዜ ይቅር ብትልም፤ እንደሚስማሩ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል ፤ እናም ልጄ……..በህይወት ትዕግስት ይኑርህ…..አንደበትህን ቆጥብ” ብሎ አስተማረው።
@ermitheethiopia
🌙እንኳን አደረሳችሁ ለመላው
🕌
እስልምና ተከታዮች በሙሉ
መልካም በአል