Co.Market / ኮ-ገበያ
539 subscribers
5.06K photos
81 videos
3 files
2.47K links
  📲+251 9 11 81 16 72
https://ermitheethiopia.com

👉
Download Telegram
ለራስ ምታት ፍቱን የሆኑ 9 የምግብ አይነቶች
(ሼር ሼር ሼር....)

1. ሃብሃብ

ሃብሃብ - በውስጡ እጅግ ብዙ ፈሳሽ እና ማዕድናትን የያዘ ከፍራፍሬዎችም በትልቅነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬትና ሐዋሳ መስመር ሲሄዱ በመንገድ ዳር ተሸክመው ሲሸጡት እንመለከታለን፡፡ ሞክረውት እንደሆነ ባላውቅም በጉዞው ወቅት ለሚኖረው ሙቀት እና የውሃ ጥም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጥቅሙም ባሻገር ለራስ ምታት ፍቱን መድሃኒት መሆኑ በባለሙያዎች ተጠንቶ ተቀምጧል፡፡

2. ዝንጅብል

ዝንጅብል ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ቅመሞች ራስ መታቱን እንደሚያስታግስ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት ይገልጣል፡፡ ራስ ምታቱን ሙሉ በሙሉ ባያቆመው እንኳ ከራስ ምታት ጋር የሚመጡ ደስ የማይሉ እንደ ማቅለሽለሽ አይነት ስሜቶችን በቶሎ ይቀንሳል፡፡

3. ቡና

ለአንዳንዶች ቡና ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት ሲሆን ማይግሬይን ላለባቸው አንዳንድ ሰዎች ላይ በብዛት ሲወሰድ ማይግሬይኑን የሚቀሰቅስበት አጋጣሚ አለ፡፡ እስካሁን ባሉት ጥናቶች መሰረት ግን ቡናን ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ መጠኑን በልክ ማድረግ አብሮ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ እጅግም ወፍራም ያልሆነ አንድ ወይም ሁለት ስኒ ቡና ከሁለት ክኒን የተሻለ ተፈጥሯዊ መድሃኒት ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በተጨማሪም

4. ስፒናች

5. ሙዝ፣

6. እርጎ፣

7. ጉበት፣

8. ድንች እና

9. ቃሪያም ራስ ምታትን በመቀነስ በኩል ፍቱን እንደሆኑ በጥናት ተረጋግጥዋል፡፡

ምርጥ እቃዎችን ለመግዛትና ለማዘዝ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።