Co.Market / ኮ-ገበያ
537 subscribers
5.06K photos
81 videos
3 files
2.47K links
  📲+251 9 11 81 16 72
https://ermitheethiopia.com

👉
Download Telegram
ጋዜጠኛ <<ከቅርብ ጊዜ ዘፋኞች የቱን ትወዳለህ!>>
ጋሽ ስብሀት <እንዲያው ይሄ ..ነይልኝ! የሚለው ልጅ ይመቸኛል!!>
ጋዜጠኛ <የማይመችህስ የቱ ዘፋኝ ነው?
ጋሽ ስብሀት <<ከሱ እየተቀበለ... ነይለት!>> የሚለው አቃጣሪ!!

💞 @ermitheEthiopia
ልብ በል ....

በህይወትህ አሸናፊ እንዳትሆን የሚያደርጉህን ነጥቦች ለያቸዉ በምንም መለኪያ ከአሸናፊነት የሚያግድህን ክስተት ሁሉ ቦታ አትስጠዉ አሸናፊ እስክትሆን አትድከም ወይም አትስነፍ፤ ደከመኝ በማለት ለራስህ ስንፍና አታስተምረዉ ።

በምድር ባለህ ቆይታ አሸናፊነትህ የሚወሰነዉ እስከዕለተ ሞትህ በምትከዉናቸዉ መልካም ስራዎችህ መሆኑን አስተዉል ።

ስኬት ስጋዊ ድሎት (የገንዘብ ክምር) ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ አቋምህም የላቀ በመሆኑ የሚገለጽ ጥምር ድል መሆኑን አስምረህ ተነስ ።

ስራህን ለመጀመር ነገ የሚለዉን ቃል ከአፍህም ከልብህም አስወግድ ዛሬ ላይ የምታደርገዉን ብቻ ወስንና ፈጽም ።

ሼር @ermitheethiopia
ተኝቼ እንኳን አንተ ትጠብቀኛለህ። እራሴን መቆጣጠር በማልችልበት ሰዐት እንኳ አንተ ታስበኛለህ። ሁሌ ጥበቃህ ተጓድሎብኝ አያውቅም። ዛሬም የተጨፈኑትን ዐይኖቼን በምህረትህ ገለጽክልኝ። ያረፈውንም አእምሮዬን ቀኑን አንግተህ አነቃኸው። በመስኮቱ በኩል የፈነጠቀውንም ብርሀን ማየት ቻልኩኝ። የወፎቹንም ዝማሬ በጆሮዬ አንቆሮቆርክልኝ። በጠዋቱ ምንም ገንዘብ ሳልከፍል "ብርሀንን" ሰጠኸኝ። ምንም ሳልከፍልም የ"ወፎቹን ዝማሬ" አሰማኸኝ። ገና ከመነሳቴ ይህንን ሁሉ ድንቅ ስጦታ አሸከምከኝ። እንደገና የተፈጥሮን ውበት ማድነቅም ጀመርኩኝ። ገና ከመነሳቴ ይህንን ሁሉ ካገኘሁኝ በቀሪው የቀኑ ሰዐታት ደሞ ከአባቴ የሚበረከቱልኝ ስጦታዎች አጓጉኝ። አባቴ እንዴት መልካም ነው?! እንዴትስ ድንቅ ነው?!

ሁሌ ቸርነትህ ተጓድሎብኝ አያውቅም። አሁንም በቸርነትህ ይህቺን አዲስ ቀን እንዳይ አደረከኝ። በዚች ቀንም ከወዳጆቼም ጋ እንድገናኝ፣ስራዬን እንድሰራ፣እንድዝናናና አዲስ ነገር እንድፈጥር ፈቀድክልኝ። ከምንም በላይ በሰጠኸኝ ቀን ሌሎችን ማገዝና ማሰብ እንዳለብኝ ተረድቻለሁኝ። አንተ እንደጠበከኝኛ አንተ እንደረዳኸኝ እኔም ለሌሎች መትረፍ እንዳለብኝ አውቄአለሁ።

ዛሬ በሕይወት የነቃን ሁሉ ፤ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች ስለመትረፍ እናስብ። የአቅማችንን ውስንነት ሳይሆን የአቅማችንን ትልቅነት እንመልከት። በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን የፈጣሪን ክብር የሚያገዝፍ ስራ ለመስራት እንሞክር። ፈጣሪ እኛን እንደወደደን ሁሉ እኛም በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ እንውደድ። ይቺንም ቀን በሕይወታችን ላይ መጨመሯ ትክክል መሆኑን በስራችን ትልቅነት፣በሀሳባችን መልካምነት፣ከአፋችን በሚወጡት የከበሩ ውብ ቃላቶች እናሳይ! ይቺ ቀን ይገባችኋል ብሎ የሰጠንን ፈጣሪ የሚያስወድስ ግሩም ውሎን በፈቃዳችን እንዋል። በውሎአችንም እግዚአብሔር ጥበቃው አይለየንም! አሜን!
መልካም ቀን ይሁንልን!
ብሩክ የሺጥላ